The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ይሄ_ሰው_ማነው?
#ነብይ_ዘነበ

ተወልዶ ያደገው እንዲሁም ትምህርቱን የተከታተለው ሀረር ከተማ ነው። የ2 ልጆች አባትም ጭምር ነው። የ2 ልጆቹ እናት የሆነችው ባለቤቱ አብሮ አደጉ እና ጎረቤቱ ነች።

ይህ አገልጋይ ወደ ዛሬው መንፈሳዊ አገልግሎቱ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ በ1980ዎቹ አከባቢ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተነስቶ እና በመላው ኢትዮጵያ ተቀስቅሶ በነበረው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ ህይወታቸው ከተቀየሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው።

በወቅቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ወንጌል በስፋት ይሰሩ ነበር። 1987ዓ.ም ድሬደዋ ከተማ ላይ ትልቅ ኮንፈራንስ ነበር በወቅቱ ይሄን ወጣት ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ድብደባ ደርሶባቸዋል።

ይህ ወጣትም በወቅቱ ተደብድቦ ሞቷል ተብሎ መንገድ ላይ ጥለውት ሄደውም ጭምር ነበር። ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ተርፎ ዛሬም ድረስ ለምስጋና ቆሟል።

የቀድሞ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ የዛሬው የአማኑኤል ቤተክርስቲያን ህብረት (ሓልዎት) አጥብያ መሪ እና አገልጋይ ነው ነብይ ዘነበ (ዘኔ)።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።