The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አዲስ #ዜና

ዩጋንዳ እና ጋናን በመከተል ደቡብ አፍሪካዊቷ ናሚብያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ህገ ወጥ ልታደርግ ነው።

#አዲሱ #ህግ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትን ህገወጥ የሚያደርግና ጋብቻንም በህግ የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በላይኛው ፓርላማ ያለምንም ተቃውሞ ተቀባይነት ያገኘው ህጉ ከታችኛው #ፓርላማ ተቀባይነት ካገኘና የሃገሬው #ፕሬዝደንት #ወደ ተግባር ካሳለፉት ሰሞኑን ህግ ሆኖ ሲጸድቅ ከአፍሪካ ሃገራት #ብቻ ሶስተኛው ነው።

ህጉ በተጨማሪ #ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንድ #ሴት መካከል ብቻ የሚኖር ህብረት ነው ብሎ ይደነግጋል። በውጪ ሃገራት እንኳን ተመሳሳይ ጾታ ትዳርን ይዞ ወደ ሃገር #ውስጥ መግባት ድርጊቱን በሃገረ ናሚቢያ ህገወጥ ያደርገዋል።

ምንም እንኳን ከቅርብ #ጊዜ ወዲህ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተደጋጋሚ አክቲቪስቶች ወደ ፍርድ #ቤት ቢሄዱም #ምንም ለውጥ ሳይመጣ ቀርቷል።
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።
የቀድሞው የ #አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ #ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።

ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

#ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

ትራምፕ ዝርዝር #ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።

“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ God Bless The USA Bible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

#አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።