The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
152 #ሰዎች ተጠመቁ!!!

#በመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን 152 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደው #ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ ።

ቦሰት አካባቢ 62 ሰዎች እና በመካከለኛው ሥምጥ ሸለቆ ዝዋይ አጥቢያ አማካኝነት ደግሞ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 152 ወገኖች በዛሬው ዕለት የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቅለዋል ።

በተጨማሪም #ነገ ዕለት በደቡብ አዳማ ክልል ሌሎች 40 ሰዎች የውሃ ጥምቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን "#አጀንዳ28 19" ወይም "#አጀንዳችን_ወንጌል" የሚለውን እንደ መራህ በመከተል በዓመት እያንዳንዱ አጥቢያ በቁጥር 10% እድገት እንዲያሳዩ በተቀመጠው አቅጣጫ አካል መሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

#ወንጌል ካልሰራን #ምንም አልሰራንም።