The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ዛሬ
#እሁድ_ስለሆነ_በደንብ_ይነበብ!!!

በልጅነት ጊዜ እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን እንድሄድ ከሚያጓጉኝ ነገሮች አንዱ የህፃናት ፕሮግራም ነዉ።

አገልጋዮች ለልጆች እንፀልያለን ልጆች ወደፊት ኑ ብለዉ ሲጣሩ ከቤተሰብ ጋር የተቀመጡ ልጆች በሙሉ ተሯሩጠን ወደ መድረክ እኔሄዳለን።

ይህ የልጅነት ጊዜ ትዉስታ ሁሌም ቢሆን ይናፍቀኛል። ግን አሁን ይሄ ተግባር በበርካታ አብያተክርስቲያናት እንዳለ ተስፋ አደርጋለሁ።

ይሄንን የምለዉ ሁሌም ቢሆን በተለይ የቴሌቪዥን መስኮት ያላቸዉ አብያተክርስቲያናት ስለ ፈዉስ እና ትንቢት ፕሮግራም እንጂ ስለ ልጆች ፕሮግራም ሲያስተዋዉቁ ስላላየሁ ነዉ።

ለማንኛውም ለዛሬ ለዉይይት የማቀርበው ረዕሰ ጉዳይ "የልጆች አገልግሎትን" የተመለከተ ነዉ።

#በቤተክርስቲያን_የልጆች_አገልግሎት_ምን_መምሰል_አለበት?

ሁላችሁም ያላችሁን ሀሳብ እና እናንተ ባላችሁበት ቤተክርስቲያን ያለዉን ልምድ አካፍሉን።

መልካም እለተ ሰንበት!!!🙏🙏🙏
የሙሉ ወንጌል ታዳጊ ህፃናት
ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#ዛሬ #እሁድ ነዉ።

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ... 🏠 🚶‍♀️🚶‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️
#የሐዘን_መግለጫ
#እሁድ #ስረዓተ_ቀብር #ይፈፀማል

ዘማሪት ሒሩት በቀለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም ሞት እንደሚያድን አምነው በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሕይወት አጥቢያ ስገለገሉና ስያገለግሉ ቆይተሙ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ወደ ጌታቸው እቅፍ ተሰብስበዋል።

እሁድ ግንቦት 6/2015 ዓም በምስራቅ አዲስ አበባ አጥቢያ የአስክሬን ሽኝት ከተደረገ በኃላ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ሥርዓተ ቀብር ይፈጸማል።

በዚሁ አጋጣሚ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወደጅ ዘመዶቻቸው መጽናናት እንዲሆን ሁላችንም በጸሎት አብረናቸው እንዲንሆን ቤተክርስቲያን ታሳስባለች።
🌄 #ክርስቲያን ትሪፕ #ወደ ወንጭ

🌄 #Christian Trip to wenchi
👉 #እሁድ ፡ ሀምሌ 16 (Jun 23)
ጉዞ ወደ ተወዳጁ እና የአለም ምርጡ የቱሪዝም መንደር ፤ ወንጪ
💚Hiking Trip to Wenchi Crater Lake💚

A beautiful crater lake, which is the highest volcano in #Ethiopia.

🗺 መገናኛ #ቦታ ፦ Hyatt Regency Hotel ፊትለፊት
🕰መገናኛ ሰዓት ፡ ጠዋት 12:00-12:05
መነሻ ሰዓት፡ ጠዋት 12:15

💰 የጉዞ ሂሳብ👇
ቀድመው ለሚከፍሉ 8 ሰዎች ብቻ 1800 ብር
ዘግይተው ለሚከፍሉ ፡1900 ብር
Foreigner: $60

የጉዞ ሂሳብ የሚያካትተው፦
🚌 ትራንስፖርት
🧾 የመግቢያ ክፍያ
🚶‍♂አስጎብኚ
🍕 ስናክ
🥘 ምሳ
💧 ውሃ
📸 ፎቶ

Activities
🧗‍♂🧗🧗‍♀ Hiking
🏊🏊‍♂🏊‍♀ Swimming
⚽️🏐⚽️ Game
🏇🏇🏇 Horse Riding
🚣🚣‍♀🚣‍♂ Boat Cruise

ያለን ጥቂት ቦታ ስለሆነ👇
አሁኑኑ ይመዝገቡ
BOOK NOW
📞0948888498
📞0943880861
ማሳሰቢያ
👉የመመዝገቢያ #ቀን ከአሁን ጀምሮ ያለን ቦታ እስከሚሞላ ብቻ ይሆናል
#ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጨመ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ።

በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገደሉ።

ቡርኪና ፋሶ #ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ #ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

#እሁድ #ቀን በቡርኪና ፋሶ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ምዕመናን ተገድለዋል።

ኢሳካኔ በተባለው ስፍራ ለእሁድ ጸሎት ሥነ ሥርዓት በተሰባሰቡት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ አንድ የቤተ ክርስቲያኗ ባለሥልጣን ከሰዋል።

በመስጂድ እና በቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው በይፋ የታወቀ ነገር ባይኖርም አንድ የቡርኪና ፋሶ የግል ጋዜጣ ጥቃቶቹ የተቀነባበሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እምብዛም ያልተለመደ አይደለም ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ከሰሜናዊቷ ጂቦ ከተማ ከአምስት #ዓመት በፊት ተጠልፈው የተወሰዱ #አንድ ቄስ አስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከሦስት ዓመት በፊት ደግሞ ከዚያው ከተማ በታጣቂዎች የተጠለፉ አንድ ኢማም ከቀናት በኋላ ሞተው ተገኝተዋል። ዘገባው የBBC ነው።
በመቱ የሙሉ #ወንጌል አማኞች #ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረቱ ጠየቀ።

#እሁድ ግንቦት 25 በመቱ ከተማ ለወንጌል ስርጭት በወጡ ክርስቲያኖች ላይ በፖሊስ እና ሚሊሻዎች ድብደባ ተፈጽሟል። ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ወገኖች መካከል አስተያቷን ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የሰጠችው ኤደን ግርማ እንዲህ ብላለች።

ኤደን ግርማ፣ ጥቃት የደረሰባት “የእሁድ አምልኮ ጨርሰን ለወንጌል ስርጭት ሶሪ ዳቦ የሚባልበት አካባቢ ስንደርስ ፖሊሶችና ሚልሻዎች በመኪና መጡ። መሬት ላይ ተቀመጡ ካሉ በኋላ፣ የተወሰኑ ወጣቶች ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱን።

አመሻሽ ላይ ከአንዱ አመራር ጋር ፖሊስ ጣብያው አካባቢ መሬት ተቀመጡ ብሎ እያወራን፣ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ድብደባ ጀመሩ። እኔ ጭንቅላቴን ተመቼ ስደማ፣ ሌሎችም በጣም ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ለህክምና ተወስደናል።” ስትል ተናግራለች።

#ቄስ ደበላ ያደታ፣ የኢሉባቦር ዞን ወንጌላዊያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ሰብሳቢ በበኩላቸው “እኛ ህገ መንግስቱ በሚሰጠን መብት መሰረት እምነታችንን የማካሄድ መብት አለን። ከመንግስት ጋርም በሚያስፈልጉ ነገሮች ዙርያ በትብብር ስንሰራ ቆይተናል። መንግስት እንደዚህ ያደርጋል የሚል እምነት ባይኖረንም፣ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ይሄንን እንዳደረሱ በትክክል እናውቃለን። ስለዚህ ሁኔታው በትክክል እንዲታራ እንጠይቃለን።” ብለዋል።

አቶ ተሻለ ኤጄርሶ፣ የመቱ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው “ከሳምንት በፊት ለነበረው ስብከተ ወንጌል ፍቃድ የተሰጠ ቢሆንም፣ እሁድ ግንቦት 18 ሲደረግ ለነበረው የወንጌል ስርጭት የተሰጠ ፍቃድ የለም። አላስፈላጊ ድብደባና ግጭት ከፖሊስ ዘንድ መድረሱን ተመልክተናል። ከጸጥታ አካላት ጋርም ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ ነው።”

VOA Amharic