The Christian News
5.37K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አዲስ #ዜና
#ህብረቱ ጠቅላላ ጉባኤ እያደረገ ነዉ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት 38ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአሁን ሰዓት በግዮን ሆቴል እየተከናወነ ይገኛል።

በጉባኤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ፣ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮች እና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተገኝተዋል።

ህብረቱ በዚህ ጉባኤ እንደ ሀገር አቀፍ ለወንጌላዉያን ከፍተኛ የሚባሉ በብዙ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

ፎቶ 📸 Christian ዜማ Tube
#አዲስ #ዜና

ዩጋንዳ እና ጋናን በመከተል ደቡብ አፍሪካዊቷ ናሚብያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ህገ ወጥ ልታደርግ ነው።

#አዲሱ #ህግ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትን ህገወጥ የሚያደርግና ጋብቻንም በህግ የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በላይኛው ፓርላማ ያለምንም ተቃውሞ ተቀባይነት ያገኘው ህጉ ከታችኛው #ፓርላማ ተቀባይነት ካገኘና የሃገሬው #ፕሬዝደንት #ወደ ተግባር ካሳለፉት ሰሞኑን ህግ ሆኖ ሲጸድቅ ከአፍሪካ ሃገራት #ብቻ ሶስተኛው ነው።

ህጉ በተጨማሪ #ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንድ #ሴት መካከል ብቻ የሚኖር ህብረት ነው ብሎ ይደነግጋል። በውጪ ሃገራት እንኳን ተመሳሳይ ጾታ ትዳርን ይዞ ወደ ሃገር #ውስጥ መግባት ድርጊቱን በሃገረ ናሚቢያ ህገወጥ ያደርገዋል።

ምንም እንኳን ከቅርብ #ጊዜ ወዲህ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተደጋጋሚ አክቲቪስቶች ወደ ፍርድ #ቤት ቢሄዱም #ምንም ለውጥ ሳይመጣ ቀርቷል።
#አዲስ #ዜና

የካናዳ ፍርድ #ቤት አብያተ ክርስቲያናት ላይ የኮቪድ ወቅት እግድን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።

#ፍርድ ቤቱ የካናዳ #ሁለት ግዛቶች #ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በበረታበት ወቅት በአካል መሰብሰብን አግዶ በነበረበት ወቅት በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው ጉዳዩን አልመለከተውም ያለው።

በወቅቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በካናዳ #መንግስት የተወሰነውን በአካል ተገናኝቶ የማምለክ እገዳን ተላልፈው ሲሰበሰቡ ነበር ተብሏል።

ዘ ቸርች ኦፍ ጋድስ የተሰኘችው ቤተ ክርስቲያኗ ይሄንንም በመተላልፏ 240ሺህ ዶላር ቅጣት በግዛቷ ፍርድ ቤት ተጥሎባታል።

በኦንታሪዮ የምትገኘው የቸርች ኦፍ ጋድ መሪዎች በበኩላቸው ይሄ የፍርድ ቤት ውሳኔ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብለውታል።
በሃገሪቱ የፍትህና ነጻነት ታሪክም አሳዛኝ #ቀን ነው ብለውታል።

ሬስቶራንቶችና ስፖርት ቤቶች፣ መክፈት በተፈቀደበት #ጊዜ #ቤተክርስቲያን እንዲዘጋና አቤቱታን አላስተናግድም ማለታቸው የእምነትን ነጻነት የሚጋፋ ነው ብለውታል።

እኛ ሰውን ሰምተን ሳይሆን #እግዚአብሔርን ነው የምንታዘዘው በማለት በወቅቱ በሮቻቸውን ሳይዘጉ የአምልኮ መርሃ ግብሮቻቸውን ሲያካሂዱ እንደነበረ ገልጸዋል።
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።
የአዲስ አመትን አስመልክቶ #ልዩ ፕሮግራም በአዲስ አበባ እስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" እየተካሄደ በሚገኘው ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ላይ ክብርት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ የእንኳን አደረሳሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን...

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#በድል #ተጠናቋል
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ሲካሄድ የቆየው #ልዩ የበዓል #ፕሮግራም በድል ተጠናቋል።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ

#መልካም #አዲስ#አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production #እናመሰግናለን
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።
#የወንጌል ዘመቻ ሊካሄድ ነዉ።

ጋፕስ አለም አቀፍ አገልግሎት
አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ

ጋፕስ ያለፉትን 14 ዓመታት የአገልጋዮችን የኑሮ ክፍተት መሙላት፡ የመንፈሳዊ ክፍተት መሙላት (ማጎልበት፡ ማስተማር) ላይ ሲሰራ ቆይቷል።

አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ የ10 ቀናት የወንጌል ዘመቻ በነገው እለት ጀምሮ ከሚያዝያ 9-19 ድረስ ይካሄዳል።

ዘመቻው፡ የቡና #ሻይ ሰዓትን ለወንጌል፡ ሙስሊም ኢቫንጀሊዝም፡ የደም ልገሳ፡ የጎዳና ወንጌል፡ #አንድ #ሰው ለኢየሱስ፡ ማህበራዊ ሚድያን ከወንጌል፡ አርትን ለወንጌል፡ በመርዳት ወንጌል መስበክ፡ ሙዚቃን ለወንጌል፡ የርህራሄ አገልግሎት በዘመቻው በየእለቱ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው።

የጋፕስ ሚኒስትሪ መስራችና መሪ መጋቢ ዳንኤል ዋለልኝ ሁሉም ሰው የተልዕኮ ሰራተኛ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡ በእነዚህ 10 ቀናት ሁሉም #ክርስቲያን አንጾኪያ በሚያደርገው የወንጌል ዘመቻ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የክርስቲያን መገናኛ ብዙሃንም በዚህ የወንጌል ዘመቻ በትልቅ ተሳትፎ እንዲሰራ፡ የክርስቲያን ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ግርማ ጥሪ አቅርበዋል።

አንጾኪያ ሙቭመንት #አዲስ የወንጌል ተኮር አገልግሎት ነው። አላማው በሐዋ ስራ 11 እንደተገለጸው፡ የአንጾኪያ ቤ/ክ የወንጌል አካሄድ መድገም ነው።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫውን በስፍራዉ በመገኘት አሰናዳንላችሁ።
#አዲስ መጽሐፍ #በቅርብ #ቀን...

ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተ #ድንቅ የአማርኛ መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በዘላለም መንግስቱ ተዘጋጅቶ በቅርብ ቀን ወደ አንባቢያን ይደርሳል።

23 ዓመታት የፈጀው #ይህ #ድንቅ መጽሀፍ በቅርብ ቀን በአዲስ አበባ ሰኔ 15 2016 በኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ (ETC) የምስጋና ጊዜ ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት በድምቀት ይመረቃል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አዲስ #ጫማ - 1000 ብር
#አዲስ #ደብተር- 720 ብር
#አዲስ #ቦርሳ- 500 ብር
የፅፈት መሣሪያዎች 204 ብር
አካውንት ቁጥሮች
የብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን
#ንግድ_ባንክ 1000414483228
#ብርሃን ባንክ 1600550004325
የዊን ሶልስ ፎር ጓድ ኢቫንጀሊካል ሚኒስትሪስ
ንግድ ባንክ 1000000391526
ብርሃን ባንክ 1000835472170
ለበለጠ መረጃ
+251929917573
+251912156166 ይደውሉ
#የትግራይ የሀይማኖት አባቶች ፖለቲከኞች ልዩነቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

አባቶቹ አክለዉ አለመግባባቶችን ለመፍታት #ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የትግራይ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባቶች የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (#ህወሓት) አመራሮች #እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዩነታቸውን ሊያባብሱ ከሚችሉ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

በትላንትናዉ #እለት በሰጡት መግለጫ፣ በተለይም በክልሉ ወቅታዊ ፈተናዎች #ውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል ሲል #አዲስ እስታንዳርድ አስነብበዋል።

"አባቶቹ ጥሪውን ያቀረቡት የአሜሪካው አምባሳደር ሁለቱንም ቡድኖች በመቀሌ ካነጋገሩ በኋላ ነው"

#Ethiopia #addisababa #news #NewsUpdate #BREAKING #BreakingNews
የሀልዎት አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን #አዲስ ለምታስገነባው የማምለኪያ አዳራሽ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ- ስርዓት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አከናወነች።

የቤተክርስቶያኒቱ መሪ ነብይ ዘኔ ለ The Christian News - የክርስቲያን ዜና እንደገለጹልን ቤተክርስቲያኒቱ ከተመሰረተች በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት ገደማ ማህበረሰቡን በሁለንተና መልክ ስታገለግል መቆየቷን ገልጸውልን አሁንም አገልግሎቷን ለማስፋት አዲስ በተሰጣት ቦታ የመሰረት ድንጋይ ማኖራቸውን ተናግረዋል።

አዲስ የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠው ቦታ ከ7ሺህ በላይ ምዕመናን በአንድ ጊዜ ማገልገል እንዲቻል ተደርጎ እንደሚገነባ የተናገሩ ሲሆን ሕጻናትን ጨምሮ ማህበረሰቡን በሁለንተናዊ መልኩ ለማገልገል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘው አዲሱ የቤተክርስቲያኒቱ ቦታ በቤተክርስቲያኒቱ መሪ ነብይ ዘነበ ግርማ ፤ በኢትዮጵያ የአማኑኤል ሕብረት ቤ/ክ ፕሬዝደንት መጋቢ ጌታሁን ታደሰ እና በቂርቆስ ክ/ከተማ ተወካይ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ-ስረዓት ተከናውኗል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው በመገኘት በመከታተል መረጃውን ለእናንተ ያደረሰን ሲሆን ለቤተክርስቲያኒቱም ደስታችንን እንገልጻለን።
በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ፓስተር ጻዲቁ አብዶ

የ2017 #አዲስ አመት አስመልክቶ #የኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አንዶ ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ወቅት የራሱን በረከት ይዞ ይመጣል። ወቅቶች የሚፈራረቁት ለሰዎች የሚሰጡት ካለው በረከት አንጻር ነው ብለዋል።

በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ያሉት ፓስተር ጻዲቁ ተገቢ ባልሆነ ድርጊቶቻችን ያመጣናቸው ነገሮች በማራቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሃገራችን ሰላም ለሕዝባችን መቀባበል እና ይቅር መባባል እንድንሰራ አሳስበዋል።
#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የቦሌ #አማኑኤል ህብረት #ቤተክርስቲያን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ #ብርሃን የምገባ ማዕከል ማዕድ የማጋራት መርኃግብር አካሂዷል።

ከአስርት አመታት በላይ በዚህ የበጎ ፍቃድ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን የተናገሩት የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ፓስተር አመሉ ጌታ ዘንድሮም ይህንን አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

በበጎ ፍቃደኞች የሚከናወኑ መሰል ተግባራት አቅም ያነሳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ዓመትን ብቸኝነት እንዳይሰማቸውና ከጎናቸው ሰው እንዳለ እንዲሰማቸው ያደርጋልም ብለዋል።

#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ1ሺ 200 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ማዕድ ማጋራታቸውን የተናገሩት ፓስተር አመሉ፣ መሰል በጎ ተግባር ከሚሰጠው የህሊና እርካታ በተጨማሪ ከፈጣሪ የሚሰጠው በረከት ሀገርን የሚያሻግር መሆኑን ገልፀዋል።

መርዳትን ሳይሆን ማካፈልን ባህል አድርገን ልንሰራ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
#አዲስ አመት ፡ አዲስ ስጦታ #እንዳያመልጣችሁ ...
🌻🌻🌻
ከገሊላ #ኢንተርናሽናል ሴሚናሪየም
👇
⛳️ #christiancounseling & #psychology
⛳️ #christianleadership & #management
⛳️ #bible & #Theology
⛳️ #christianbusiness #administration
⛳️ Christian #socialwork
⛳️ #doctor of #ministry

በአዲሱ አመት በ5ቱ ካምፓሶቻችን ከትላንት ይልቅ ወደርሶ ቀርበናል

#9720 ይደውሉ፡ አሁኑኑ ይመዝገቡ
#Online ትምህርት ፈላጊዎች
👇👇👇
www.elearning.gelilaseminary.com
መመዝገብና መማር ትችላላችሁ!

ማህበራዊ ሚድያችንን ይጎብኙ፡ ይቀላቀሉ
👇👇👇
#website :
https://gelilaseminary.com/

#Telegram :
https://t.me/gelilaintenationalseminary

#FacebookPage :
gelilaseminary

#Youtube :
https://youtube.com/@gelilainternationalseminary?feature=shared

#tiktok ፡ gelilaseminary