The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ቦሌ #አማኑኤል
#አዲስ #መረጃ

የቦሌ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርስቲያን የበሬ ቅርጫ በማዘጋጀት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ፤ አካል ጉዳተኞች 500 ወገኖች ድጋፍ አደረገች።

ዛሬ ማለዳ በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተደረገው ድጋፍ ኑሮዓቸው በካናዳ እና የተለያዩ አለም የሚገኙ ቅዱሳን ባደረጉት ድጋፍ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ቤተክርስቲያኒቱ ኑሮዓቸው በጎዳና ላደረጉ እና በቀን ስራ ተሰማርተው አነስተኛ ገቢ ያላቸው 1000 ወገኖችን በመሰብሰብ "የትንሳኤ በዓልን" ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ አድርጋለች።

የቦሌ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 12 ዓመታት አቅመ ደካሞችን የመደገፍ እና ኑሮአቸውን የሚያሻሽሉበት ሁኔታ ለመፍጠር ስትሰራ ቆይታለች።

የቦሌ አማኑኤል ሕብረት ቤተክርስቲያን በዓላት ሲመጡ ለማህበረሰቡ በዚህ መልክ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በቋሚነት 180 በላይ ወልጅ አልባ ሕጻናትን እና 72 አረጋውያንን እየደገፈ ይገኛሉ።

እንዲህ አይነት መልካም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥል መልዕክታችን ነው። በድጋሜ #መልካም #በዓል
#አንድ #አመት #ሆነዉ
#ቤተክርስቲያን እንስራ

#በኢትዮጵያ #አማኑኤል ህብረት በሐመር #ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ምሽት ላይ የዛሬ አመት በዚህ ወር በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ የቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ወደቀች።

ይህ ከተፈጠር አንድ አመት ሆነዉ። በአከባቢው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት 75% አርብቶ አደር የሆኑ ሲሆን በወቅቱ የተጀመረዉ ድጋፍ በመቋረጡ እስካሁን አልተገነባችም።

አከባቢው ገና በወንጌል ያልተደረሰበት ከመሆኑም ባሻገር በአከባቢው ላሉ የወንጌል ጣቢያዎች እናት ቤተክርስቲያን በመሆኗ ፈተናውን አብዝቶብናል።

የዛሬ አመት ጥሪዉ እንደቀረበ የተወሰነ እርብርብ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም ድጋፉ ተጠናክር ስላልቀጠለ ዛሬም አከባቢው የነበረችዉ እናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሽ የላትም።

አሁን ደግሞ ክረምት እየደረሰ በመሆኑ ምዕመናን እና መሪዎች ስጋታችዉ ጨምሯል።

ሁላችንም ተረባርበን ቤተክርስቲያንን እንስራ!!!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ
#Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)

Phone Number:-
☎️ +2519111575204
📱+251 912169165
#ድንቅ #ተግባር

#ደም በመስጠት ፍቅራችንን እንግለጽ" በሚል መሪ ቃል የሃልዎት #አማኑኤል #ቤተክርስቲያን #የደም ልገሳ እያከናወነች ነው።

የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ደም ከመለገስ ባሻገር በአከባቢያቸው ያሉ አቅመ ደካሞን ሲረዱ የቆየ ሲሆን ከወረዳው ጋር በመነጋገር በቋሚነት አረጋውያንን የማገዝ ስራ እየሰራች ትገኛለች።

ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ እየተከናወነ በሚገኘው የደም ልገሳ የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላትን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው #ሰዎች ደም በመለገስ ፍቅራቸውን እየገለጹ ይገኛል።

ቤተክርስቲያን #ይህን መልካም ተግባር ሲታከናውን ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉ አመታት በተመሳሳይ በተከናወነው መሰናዶ በርካታ ሰዎች ደም መለገሳቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መዘገባችን ይታወሳል።

የዛሬው መረሃ ግብር እስከ 10:00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን ምዕመናን በስፍራው ተገኝተው ደም እንዲለግሱ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አቅርባለች።
#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የቦሌ #አማኑኤል ህብረት #ቤተክርስቲያን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ #ብርሃን የምገባ ማዕከል ማዕድ የማጋራት መርኃግብር አካሂዷል።

ከአስርት አመታት በላይ በዚህ የበጎ ፍቃድ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን የተናገሩት የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ፓስተር አመሉ ጌታ ዘንድሮም ይህንን አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

በበጎ ፍቃደኞች የሚከናወኑ መሰል ተግባራት አቅም ያነሳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ዓመትን ብቸኝነት እንዳይሰማቸውና ከጎናቸው ሰው እንዳለ እንዲሰማቸው ያደርጋልም ብለዋል።

#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ1ሺ 200 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ማዕድ ማጋራታቸውን የተናገሩት ፓስተር አመሉ፣ መሰል በጎ ተግባር ከሚሰጠው የህሊና እርካታ በተጨማሪ ከፈጣሪ የሚሰጠው በረከት ሀገርን የሚያሻግር መሆኑን ገልፀዋል።

መርዳትን ሳይሆን ማካፈልን ባህል አድርገን ልንሰራ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።