The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ይህን_ምስኪን_ደሃ_ማህበረሰብ_አትጫውቱበት
የሃሰተኞች ትርክት "ሚራክል መኒ" ወደ ሀገራችን ከገባ ከ50ዓመት በላይ ይሆነዋል።

"ይህ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ሶስት አስር ዓመታት (30ዓመት) አልፎታል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሃገራችን በሰረገ ጊዜ አንዳንድ አስገራሚ ነገሮችም ተደርገው ነበር። ለምሳሌ ፤ አስር ባለ አንድ ብር ኖቶችን እመሬት ላይ ደርድረው ባለ መቶ ብር ኖቶች እንዲሆኑ ሁለት ወንድሞች ለረጅም ጊዜ ተንበርክከው ጸልየው ነበር።

እግዚያብሄር የሃገር ምጣኔ ሀብትን የሚያቃውስ ያልተመዘገበ ገንዘብ እየሰራ የሚያድል ሸፍጠኛ ያለመሆኑን በየዋሃነት አልተረዱትም እና። ይህን ማድረግ የጌታ ባህሪ አይደለምና።

"መንፈስ ቅዱስ እና ካሪዝማቲክ ቀውሶች" ከሚለው መጽሐድ ገጽ 229 ተቀንጭቦ የተወሰደ።

በወንድም ዘላለም መንግስቱ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ታትሞ ከወጣ 25ዓመት ይሆነዋል። ይህ ማለት ዛሬ እየተነሱ በተዓምር ገንዘብ ታገኛላችሁ የሚሉት የሃሰተኞች ትርክት መነሻው ቆየት ያለ እና ብዙዎችም እየተታለሉበት እየተበሉበት የነበረ እንደሆነ ማሳያ ነው።

ይህ ከመካከለኛው እና ከምዕራብ አፍሪካው የመጣው የጥንቆላ ስራ ነው። ምናለ በሉ ደግሞ በቅርብ ቀን ተዓምራዊ ገንዘብ ታገኛለህ/ሽ ተብዬ ብሬ ተበላው የሚሉ አልቃሽ ወገኖችን በቅርብ ቀን በየሚዲያው መስማታችን አይቀርም።

ያኔ በየሚዲያው ከማልቀሳችሁ በፊት ዛሬ አርፋችሁ እቤታችሁ ተቀመጡ እና እግዚያብሄር የሰጣችሁን ገንዘብ ሰርታችሁ አትርፉበት።

ወይ ደግሞ በርግጥም ሚራክል መኔ ሆኖላችሁ ከሆነ ወጥታችሁ መድረክ ላይ ከመመስከር ይልቅ ከአካውንታችሁ የገባላችሁን ሚራክል መኔ በድጋሜ እንዲበዛላችሁ አውጡና ለሚራክል አድራጊው በጥሬ ገንዘብ ስጡት። Done.

ሚራክል አድራጊዎች ደግሞ ምንጣፍ አንስታችሁ መቶ ብር ከምታቀምጡ ምንጣፉን ማንሳታችሁ ካልቀረ ደና ብር አስቀምጡ። ይህን ምስኪን ህዝብ በ10 ብር እና በ100 ብር ሙድ አትያዙበት። 100 ብር ምንጣፍ ስር አስቀምጣችሁ 100ሺህ ብር ድጋፍ አድርግልኝ አትበሉት።

ለማንኛውም ሚራክል አድራጊዎች እባካችሁ ከታች ባስቀምጥኩላችሁ Acc. ቁጥር ሚራክል መኔውን ወደ እኔ አስገቡልኝ። 😂😂😂
#ይህን ወጣት ካወኩት 2 ዓመት አከባቢ ሊሆነኝ ነዉ። በዚህ እድሜዉ የሚያነሳቸዉን እና የሚፅፋቸዉን ረዕሰ ጉዳዬች ሳነብ እገረምበታለሁ።

አሁን ደግሞ ለሁላችንም መልካም ዜናዎችን ይዞልን መጥቷል።

Christian ዜማ Tube በሚል በማህበራዊ ድረ-ገጽ (በፌስ ቡክ) ላይ በተለያዩ ጽሑፎቹ የምናውቀው ወንድማችን ዘሪሁን ግርማ፣ "የዘር ሐሳቦች" የተሰኘ ከዚህ ቀደም የጻፋቸው እና አዳዲስ ጽሑፎችን የያዘ የመጣጥፎች ስብስብ መጽሐፍ በመጋቢት 26 ሰኞ ዕለት በመማጸኛ ከተማ ቤተ ክርስቲያን (ዩጎ) ከ 10:00 ጀምሮ ያስመርቃል።

እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#3ቀን #ቀረዉ

በቀሩት #ጥቂት ቦታዎች እየደወላችሁ ተመዝገቡ

የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ሲሆን

#ይህን #ስልጠና ከተካፈሉ በኋላ

፩. ስለጋብቻ ያላቸውን አይታ ያድሳሉ ፣ ያጎለብታሉ አናሞ ያስተካክላሉ፤

፪. ጋብቻቸውን የሚያፀነባቸውን አና የሚያጠነክሩባቸውን ጥበቦች ይታጠቃሉ፤ - አጠቃላይ የጋብቻን መሰረታዊ ተግዳሮቶች በማወቅ የጋብቻቸውን ተግዳሮት በመለየት የሚቀርፉበትን መንገዶች ይማራሉ፤

፫. ሥራቸውን አና ጋብቻቸውን አመጣጥነው ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የሚመሩባቸውን ጥበቦች ይካፈላሉ፤

፬. ጋብቻን በማስተዋልና በጥበብ ለመስራት የሚረዱ ጤናማ ልምምዶችን ምንነት እና አነዚያንም ልምምዶች የሚያዳብሩባቸውን መንገዶች ይማራሉ፤

፭. የተግባቦት፣ የገንዘብ አና የወሲብ ህይወታቸውን
የሚያጎለብቱባቸውን/ የሚያሻሽሉባቸውን ዘዴዎች ይቀስማሉ፤

፮. በአዎንታዊ አስተሳሰብ ጋብቻን የመምራት ምንነት አና ጥቅሞቹን ያውቃሉ፤

፯. ጋብቻን በጽናት ፣ በስኬታማነት እንደዚሁሞ በፍሬያማነት ለመምራት የሚያስፈልጉትን ወሳኝ አስተሳሰቦች ይመለከታሉ፤

#ይታደሙ ትዳርዎትን ይስሩ!
#ሌሎች ጥንዶችን ስፖንሰር ያድርጉ

ከስልጠናው የሚገኘው ትርፍ የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በስልጠናና #እና በማቋቋም ለሚያግዛቸው ችግረኛ ጥንዶች የሚውል ይሆናል።

ለበለጠ #መረጃ

0911136520
0911642595

ይደውሉልን።

ጎጆዬ የጋብቻ ሪፎርሜሽን ሴንተር ከሲቢኤምሲ #ኢትዮጵያ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጋብቻ ሴሚናር።

📍 ስልጠናው በሳፋየር #አዲስ ሆቴል ከሐምሌ 24 -28 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡30-2፡00 አና ሐምሌ 29 ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 (ሙሉ ቀን)

9 ክፍለ-ጊዜያትን ከሞሳ ጋር በሰው በ6ዐዐዐ ብር ብቻ (ለጥንዶች 12000 ብር)!
#ድንቅ #ተግባር

#ደም በመስጠት ፍቅራችንን እንግለጽ" በሚል መሪ ቃል የሃልዎት #አማኑኤል #ቤተክርስቲያን #የደም ልገሳ እያከናወነች ነው።

የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ደም ከመለገስ ባሻገር በአከባቢያቸው ያሉ አቅመ ደካሞን ሲረዱ የቆየ ሲሆን ከወረዳው ጋር በመነጋገር በቋሚነት አረጋውያንን የማገዝ ስራ እየሰራች ትገኛለች።

ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ እየተከናወነ በሚገኘው የደም ልገሳ የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላትን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው #ሰዎች ደም በመለገስ ፍቅራቸውን እየገለጹ ይገኛል።

ቤተክርስቲያን #ይህን መልካም ተግባር ሲታከናውን ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉ አመታት በተመሳሳይ በተከናወነው መሰናዶ በርካታ ሰዎች ደም መለገሳቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መዘገባችን ይታወሳል።

የዛሬው መረሃ ግብር እስከ 10:00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን ምዕመናን በስፍራው ተገኝተው ደም እንዲለግሱ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አቅርባለች።