#ሱዳን #ጦርነት
#ቤተክርስቲያን ማቃጠል
#የክርስቲያኖች #ስደት
በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረሱን ቀጥሏል ተባለ።
ባለፈው ሳምንት #ብቻ #ሁለት የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በጦርነቱ ምክኒያት ጋይተዋል። በሱዳን ሁለተኛ ጥንታዊ እና ትልቁ #ቤተክርስቲያን በኦምዱርማን ከተማ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
ጥቃቱ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የሚገኝን የክርስቲያኖች ትምህርት ቤት ኢላማ ያደረገ ቢሆንም፣ የፕሪባይቴሪያን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ህንጻም ፈራርሷል። ውስጥ የሚገኙ መጽሃፍ ቅዱስ፣ የመዝሙር ደብተር እና ዶክመንቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያም ወላጅ አልባ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ የጥቃቱ ሰለባ ነው። ምንም እንኳን ህንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም፣ ሰው ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም።
በጦርነቱ ከጥቅም ውጪ ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ፣ 81 አመታትን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረ ነው። ባለፈው አርብ በደቡባዊ ካርቱም፣ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ተፈጽሞበት፣ 5 መነኩሴዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በጦርነቱ ዋነኛ የጥቃት ሰለባ የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት መሆናቸውም እየተዘገበ ይገኛል። ኦምዱርማንና ካርቱም ብቻ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ የተባለው ጦር፣ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ተቆጣጥሮ የጦር ማዘዣ አድርጓል። በካርቱም የምትገኝን አንዲት ቤ/ክ ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ለጦርነት አላማ እያዋለ ይገናል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ጌሪፍ የተባለን የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ቤት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተማሪዎችን ዶርም፣ መማሪያ ክፍሎችና የአምልኮ ስፍራም ጥቃት ተፈጽሞበት ከጥቅም ውጪ ሆኗል ነው የተባለው።
በሱዳን ጦርና ፈጣን ሃይል ሰጪ በሚባለው ጦር መካከል እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛ አመቱን በያዘው ጦርነት፣ እስካሁን 10ሺህ የሚሆኑ ንጹሃን #ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ወደ 5.6 ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል ሲል ተ.መ.ድ አስታውቋል።
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃንና የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሉ መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ደጋሎ በጋራ የሲቪሉን የሽግግር መንግስት ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፣ በመካከላቸው የተፈጠረ ልዩነት ሱዳንን ዛሬ ላይ አድርሷታል።
#ምንም #እንኳን ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ኦማር አልበሽር የስልጣን ዘመን የነበረው የክርስቲያኖች ስደት ይቀንሳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ በጦርነቱ ምክኒያት ግን እየተባባሰ ይገኛል ነው የተባለው።
ኦፕን ዶርስ በ2023ቱ ሪፖርት መሰረት፣ ሱዳን በ2021 ከነበረችበት የ13ኛ ደረጃ የክርስቲያኖች ስደት ተባብሶ ወደ 10ኛ ደረጃ ከፍ አድርጓታል።
ክርስቲያኒቲ ቱደይ እንዳስነበበው በሱዳን ከአጠቃላይ 43 ሚሊዮን ህዝቧ መካከል፣ 4.3 በመቶው ወይም ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆነው #ሕዝብ #ክርስቲያን ነው።

#መንግሥት በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚያደርገውን ግፍ ቀጥሏል።
የአልጄሪያ መንግስት በአብያተ ክርስቲያናት #ላይ እየወሰደ ያለውን ስልታዊ እርምጃ ቀጥሏል።
አልጄሪያ 42 ሚሊዮን #ህዝብ እንዳላት የሚነገር ሲሆን 1% ህዝብ በካቶሊኮች እና ፕሮቴስታንቶች የተወከለው የክርስቲያን ማህበረሰብን ናቸዉ።
#እንደ #ክርስቲያን ኮንሰርን ዘገባ ከሆነ በእስራኤል እና በሃማስ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሰሜን አፍሪቃዊቷ ሀገር ላሉ ክርስቲያኖች ህይወትን አስቸጋሪ አድርጎታል።
"የአልጄሪያ መንግስት በግጭቱ #ውስጥ እስራኤልን እንደሚደግፉ እና የውጭ እና የምዕራባውያን ተፅዕኖዎች የአገሪቱን ብሄራዊ አንድነት እንደሚያበላሹ ይገነዘባሉ" ሲል ICC በሪፖርቱ ገልጿል።
ባለፈው #አመት በአጠቃላይ 16 አብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸውን ተከትሎ የአልጄሪያ መንግስት የክርስቲያን አገልግሎቶች እስከ 10 #ሰዎች #ብቻ እንዲስተናገዱ መወሰኑን ዘገባዉ አክሏል።
በተጨማሪም፣ ICC እንዳለው፣ ባለፉት ሳምንታት በርካታ የአልጄሪያ ፓስተሮች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል።
ICC (አይሲሲ) በሪፖርቱ "አብዛኞቹ የአልጄሪያ ክርስቲያኖች ከካቢሌ ጎሳ የመጡ በመሆናቸው የክርስቲያኖች ሁኔታ በአልጄሪያ ያለው ሁኔታ የበለጠ የተወሳሰበ ነው" ሲል ገልጿል።
"በአልጄሪያ ውስጥ ያለው ክርስትና ረጅም #ታሪክ ያለው ነው እና በአልጄሪያ መንግስት በአልጄሪያ ክርስቲያኖች እምነት እና በአካባቢው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መካከል ያለውን ልዩነት በአልጄሪያ መንግስት መለየት አለበት" ሲል አይሲሲ ተናግሯል.
አልጄሪያ በኦፕን ዶርስ የአለም ለክርስትና አስቸጋሪ ከሆኑ ሀገራት የ2023 ዝርዝር መሰረት ክርስትያኖች ከሚሰደዱባቸው 50 ሀገራት 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

#እስካሁን ከመንግስት ምንም #ፍትህ አላገኘንም
ይህንን ያለችዉ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በዛሬዉ እለት #ጊዳሚ መካነ #ኢየሱስ ምዕመናን ላይ የደረሰዉን ግፍ አስመልክታ በሰጠችዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ።
ቤተክርስቲያኒቱ በሰጠችዉ መግለጫ በወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን ተወስደው ከተገደሉ 9 #ሰዎች መካከል #5ቱ_ከአንድ_ቤተሰብ መሆናቸው ተገልፆል።
ቤተሰቦቻቸውን #እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ወገኖች ቤተ ክርስቲያኗ መጽናናትን የተመኘች ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ ፍትህን ከመንግስት ለማግኘት ስትጠባበቅ የቆየች ቢሆንም፣ ለአሁኑን ጥቃትም ይሁን ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ ጥቃቶች ከመንግስት ዘንድ ምንም አይነት የፍትህ ምላሽ ሳታገኝ ቀርታለች ብሏል።
በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ስም ዝርዝር
1. ተሊላ ለሜሳ ታሲሳ
2. ቶሊና ለሜሳ ታሲሳ
3. ታምራት ለሜሳ ታሲሳ
4. ቀበና ቡልቻ ጉተማ
5. ጌታቸው ቤከታ ታይሳ
6. ሂካ አያና ያደሳ
7. ጅረኛ ድንገታ ቴሶ
8. ሰለሞን ድንገታ ቴሶ
9. ሲራጅ ደኑ
መግለጫዉ አክሎ አሁንም መንግስት ዘላቂ #ሰላም እንዲያስከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍንና ዜጎች በነጻነት ወጥተው መግባት፣ የአምልኮ ነጻነታቸውን እንዲያስጠብቅ እንደ ከዚህ ቀደሙ ጥሪዋን ታቀርባለች ብሏል መግለጫው።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ ከዚህ በታች ተያይዟል።

የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...
መነሻ ቃል 1ሳሙ 17
👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::
👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::
✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።
✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::
👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም
👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::
✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::
✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::
✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️
#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::
እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።
👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️
✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::
✝️ ካፈጠጠብኝ በአለም ካለው
እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️
#መጋቢ ጻድቁ አብዶ

#ድንቅ #ተግባር
#ደም በመስጠት ፍቅራችንን እንግለጽ" በሚል መሪ ቃል የሃልዎት #አማኑኤል #ቤተክርስቲያን #የደም ልገሳ እያከናወነች ነው።
የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ደም ከመለገስ ባሻገር በአከባቢያቸው ያሉ አቅመ ደካሞን ሲረዱ የቆየ ሲሆን ከወረዳው ጋር በመነጋገር በቋሚነት አረጋውያንን የማገዝ ስራ እየሰራች ትገኛለች።
ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ እየተከናወነ በሚገኘው የደም ልገሳ የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላትን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው #ሰዎች ደም በመለገስ ፍቅራቸውን እየገለጹ ይገኛል።
ቤተክርስቲያን #ይህን መልካም ተግባር ሲታከናውን ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉ አመታት በተመሳሳይ በተከናወነው መሰናዶ በርካታ ሰዎች ደም መለገሳቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መዘገባችን ይታወሳል።
የዛሬው መረሃ ግብር እስከ 10:00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን ምዕመናን በስፍራው ተገኝተው ደም እንዲለግሱ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አቅርባለች።

በ #ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጨመ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ።
በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገደሉ።
ቡርኪና ፋሶ #ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ #ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
#እሁድ #ቀን በቡርኪና ፋሶ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ምዕመናን ተገድለዋል።
ኢሳካኔ በተባለው ስፍራ ለእሁድ ጸሎት ሥነ ሥርዓት በተሰባሰቡት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ አንድ የቤተ ክርስቲያኗ ባለሥልጣን ከሰዋል።
በመስጂድ እና በቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው በይፋ የታወቀ ነገር ባይኖርም አንድ የቡርኪና ፋሶ የግል ጋዜጣ ጥቃቶቹ የተቀነባበሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እምብዛም ያልተለመደ አይደለም ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
ከሰሜናዊቷ ጂቦ ከተማ ከአምስት #ዓመት በፊት ተጠልፈው የተወሰዱ #አንድ ቄስ አስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከሦስት ዓመት በፊት ደግሞ ከዚያው ከተማ በታጣቂዎች የተጠለፉ አንድ ኢማም ከቀናት በኋላ ሞተው ተገኝተዋል። ዘገባው የBBC ነው።

#አስደሳች #ዜና
በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።
ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።
#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።
በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።
በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።
ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።

በደቡብ አፍሪካ ለፋሲካ በዓል መንገደኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ 45 ሰዎች ሞቱ። 8 ዓመት ሕጻን በሕይወት ተገኝታለች።
በደቡብ አፍሪካ ለፋሲካ በዓል መንገደኞችን ከጎረቤት አገር ቦትስዋና ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ 45 #ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ።
ከድልድልይ ላይ ወደ 50 ሜትር ገደል በወደቀው አውቶብስ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች የ8 ዓመት ሴት ልጅ ብቻ በሕይወት መገኘቷን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ከሞት የተረፈችው ብቸኛዋ የስምንት ዓመት ልጅ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት ተገልጿል።
በሰሜን ምስራቅ ሊምፖፖ ግዛት አደጋው የደረሰበት አውቶብስ የድልድዩን መከላከያ ጥሶ ቁልቁል ወርዶ ከመሬት ጋር ሲጋጭ በእሳት መያያዙ ተነግሯል።
ተሳፋሪዎቹ ከቦትስዋና ዋና ከተማ ጋቦሮኔ ወደ ሞሪያ ከተማ ለፋሲካ በዓል መንፈሳዊ አገልግሎት ሲጓዙ የነበሩ ኃይማኖተኞች ነበሩ።
የአውሮፓውያንን የቀን አቆጣጠር የሚከተሉ ክርስቲያኞች የስቅለት በዓልን ዛሬ ዓርብ መጋቢት 20/2016 እያከበሩ ሲሆን የትንሳዔ በዓልን ደግሞ የፊታችን እሁድ መጋቢት 22 ያከብራሉ።
ተሽከርካሪው ከጆሃንስበርግ በስተሰሜን 300 ኪሜ ርቀት ላይ ካለው ድልድይ መውደቁን የደቡብ አፍሪካው ኤስኤቢሲ ቀድሞ ዘግቧል።
የአደጋውን ቦታ የጎበኙት የደቡብ አፍሪካ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሲንዲሲዌ ቺኩንጋ በአውቶብሱ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ገልፀዋል።
"በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ጸሎታችን ከእናንተ ጋር ነው። በዚህ የትንሳኤ በዓል ሰሞን ብዙ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ ስለሚጓጓዙ ሁል ጊዜ በኃላፊነት በማሽከርከር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ" ሲሉ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለትንሳኤ በዓል ባስተላለፉት መልዕክት ዜጐች “ደህንነቱ የተጠበቀ ፋሲካ ለማክበር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ” አሳስበዋል።
@BBC

152 #ሰዎች ተጠመቁ!!!
#በመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን 152 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደው #ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ ።
ቦሰት አካባቢ 62 ሰዎች እና በመካከለኛው ሥምጥ ሸለቆ ዝዋይ አጥቢያ አማካኝነት ደግሞ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 152 ወገኖች በዛሬው ዕለት የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቅለዋል ።
በተጨማሪም #ነገ ዕለት በደቡብ አዳማ ክልል ሌሎች 40 ሰዎች የውሃ ጥምቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
በአጠቃላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን "#አጀንዳ28 19" ወይም "#አጀንዳችን_ወንጌል" የሚለውን እንደ መራህ በመከተል በዓመት እያንዳንዱ አጥቢያ በቁጥር 10% እድገት እንዲያሳዩ በተቀመጠው አቅጣጫ አካል መሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
#ወንጌል ካልሰራን #ምንም አልሰራንም።

በአረብ ሃገሯ #ኢራን እስከ 1 #ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ወደ ክርስትና መጥተዋል ተባለ።
ከ88 ሚሊዮን ህዝቧ 96 በመቶ በላይ የሚሆነው እስልምና ተከታይ በሆነበትና፣ የሃገሪቷ #መንግስት በግልጽ እስላማዊ በሆነባት ኢራን ይሄንን ያክል ቁጥር #ክርስቲያን መገኘቱ ተዓምር ነው ተብሏል።
ሪፖርቱን ይዞት የወጣው The Voice of the Martyrs የተባለው በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስን ስደት የሚከታተል ተቋም ነው። ተቋሙ በሪፖርቱ ከ1970 የኢራን አብዮት ወዲህ በሃገሪቱ ክርስቲያኖች ስደት የበረታ መሆኑን ጠቅሷል።
ምንም እንኳን ስደቱ ቢበዛም በተቃራኒውም የክርስቲያኖች ቁጥር መጨመርን አሳይቷል። ቤተ ክርስቲያን በድብቅ ወይም underground ሆና መስፋፋቷን ቀጥላለች።
ሌላዋ የመካከለኛው ምስራቅ #አረብ ሃገር በሆነችው የመን፣ ጆሽዋ ሚኒስትሪ ሪፖርት እንዳደረገው በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ይልቅ በየመን ወደ #ጌታ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ብልጭን አሳይቷል።
በ2024 ሪፖርት መሰረት ኢራን ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በሚል በ9ኛ ስፍራ የምትገኝ ሲሆን የመን በበኩሏ በ5ኛ ስፍራ ተቀምጣለች።