The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
እግሮች #ሁሉ #ወደ #መስቀል አደባባይ ያመራሉ፥ እጆች ሁሉ ወደ አምላካቸው ይነሳሉ፣ ለአገራችን ይጸልያሉ አምላካቸውን ያመልካሉ!

በመጋቢት 8 ከ 7:0ዐ ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ልንገናኝ ቀጠሮ አለንና ከወዲሁ ሁላችንም እንዘጋጅ!!
#ዛሬ አልቋል።
ምዝገባ ተጠናቋል።

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር። #እያደገ #ሄደ ...ምዝገባ አጠናቀናል።

#ወደ ስልጠና ሲመጡ #አቅጣጫ እንዳይሳሳቱ ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
#መንገድ #ዝግ #ነዉ

#የኢትዮጲያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አሽከርካሪዎች እንደ ተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

#ነገ ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች መረጃው አስቀድሞ ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ #ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

.የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ ዕሁድ መጋቢት 8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የቀድሞው የ #አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ #ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።

ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

#ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

ትራምፕ ዝርዝር #ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።

“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ God Bless The USA Bible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

#አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።
“ክርስቲያናዊ ኢትዮጵኝነት” በሚል ርዕስ በወንድም ዘላለም መንግስቱ ተዘጋጅቶ በሐዋሳ ሐይቅ ዳር ቃለ ሕይወት #ቤተክርስቲያን አሳታሚነት #እና አከፋፋይነት ለቅዱሳን በረከት ሊሆን ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

ሚያዚያ 6/2016 በሐዋሳ ሐይቅ ዳር ቃለ #ሕይወት ቤተክርስቲያን ተገኝተው መጽሐፉን በእጆዎ በማስገባት ከቀዳሚ አንባቢያን መካከል ይሁኑ፡፡

መጽሐፉን ወንድማችን ዘላለም መንግስቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያበረከተው ሲሆን ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የወንጌሉን አገልግሎት ለመደገፍ ይውላል፡፡

ወንድማችን ዘላለም መንግስቱ ከአስር ያላነሱ የታተሙ መጽሐፍትን እና ከአስር ያላነሱ ያልታተሙ #ግን በsoft copy መጽሐፍትን ለቅዱሳን አገልግሎት እንዲውል ያበረከተ እና እያበረከተ ያለ ወንድም ነው፡፡

በእቅበተ ዕምነት አገልግሎት ግንባር ቀደም አገልግሎትን በተለያዩ መንገዶች እያገለገለ ያለ እና ከ25 ዓመታት በላይ #ጊዜ የወሰደውን የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አዘጋጅቶ #ወደ ማተሚያ #ቤት በመላክ በቅርብ ወራት ለቅዱሳን አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ እየተጋ ያለ ትጉህ ወንድማችን ነው፡፡
152 #ሰዎች ተጠመቁ!!!

#በመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን 152 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደው #ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ ።

ቦሰት አካባቢ 62 ሰዎች እና በመካከለኛው ሥምጥ ሸለቆ ዝዋይ አጥቢያ አማካኝነት ደግሞ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 152 ወገኖች በዛሬው ዕለት የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቅለዋል ።

በተጨማሪም #ነገ ዕለት በደቡብ አዳማ ክልል ሌሎች 40 ሰዎች የውሃ ጥምቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን "#አጀንዳ28 19" ወይም "#አጀንዳችን_ወንጌል" የሚለውን እንደ መራህ በመከተል በዓመት እያንዳንዱ አጥቢያ በቁጥር 10% እድገት እንዲያሳዩ በተቀመጠው አቅጣጫ አካል መሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

#ወንጌል ካልሰራን #ምንም አልሰራንም።
#ክርስቶስ እንኳን #ወደ ምድር ቢወርድ #አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም

#ክርስቲያኖች ላይ ስደት በዝቷል።

በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በምትገኘው ኮሶቮ፣ ክርስቲያኖች #ላይ ስደት በርትቷል ተባለ።

በሃገሪቱ ክርስቲያኖች #ምንም አይነት የመሰብሰብ መብት እንደሌላቸው #እና ፈቃድ ለማግኘትም ሁኔታዎች እንደሚወሳሰቡባቸው ገልጸዋል።

የአርሜ #ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባት ኮሶቮ፣ 93 በመቶ ዜጎቿ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።

ምንም #እንኳን የሃገሪቱ ህገ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ላይ ግን መድሎና አመጽ ይበረታባቸዋል።

#ይህ ስደት በግል ደረጃም፣ የቀብር ስፍራ መከልከል፣ ንብረት የማፍራት መብት አለማግኘትና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይ #ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች፣ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ንብረት ማፍራት እና ሰራተኞችን ቀጥሮ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የላቸውም።

በቅርቡ የወጣ #አንድ ህግ ደግሞ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊኮችን እና ሌሎችንም ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ኢላማ ያደረገ ነው ይባልለታል።

በሃገሪቱ ያለፉትን 25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ ቄስ ሲናገሩ፣ ያለው ስቃይ በግልጽ ስላልሆነ ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

ለቀብር እንኳን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ፣ በኢማሞች የተመራ ቀብር ስነ ስርዓት እያደርግን ነው የምንገኘው ብለዋል። ምንም ቢሆን #ግን ለሃገራችን የወንጌል ተስፋ አለን ሲሉም እኚሁ ቄስ ይናገራሉ።

በኮሶቮ በ1980ዎቹ ወንጌላዊያን፣ ክርስቶስ እንኳን ወደ ምድር ቢወርድ አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም የሚል ተደጋጋሚ ዛቻ ከወቅቱ ኮሚኒስት መንግስት ሲደርስባቸው እንደ ነበረ ዘገባዉ አስታዉሷል።
#ወደ ሚወደዉ ጌታ ሄዷል። #ዜና 😭😭

ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል።

የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን.... 🙏🙏🙏
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
#አፍሪካ

አፍሪካ ባለፉት 150 አመታት በርካታ ክርስቲያናት ያሉባት አህጉር ሆናለች።

በ1900 #ላይ በአለም ካለው #ክርስቲያን 82 በመቶው፣ በሰሜን የአለም ክፍል፣ አውሮፓ እና #አሜሪካ ይገኝ ነበረ። በተቃራኒው ደቡባዊ የአለም ክፍል አፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ደግሞ 18 በመቶ ብቻ ነበረ።

#አንድ #መቶ አመታትን #ወደ ፊት፣ ሰሜኑ አለም 33 በመቶው #ብቻ ክርስቲያን ሲሆን፣ ደቡቡ የአለም ክፍል ደግሞ 67 በመቶ ክርስቲያን ነው።

በጋና አክራ፣ በተካሄደ አለም አቀፍ የክርስቲያኖች ፎረም፣ በአለም ላይ የክርስትና ህዝብ ነክ ቁጥር ትልቅ ለውጥ ማሳየቱ ተነስቷል። ከኤፕሪል 16-20 በነበረው በዚህ ፎረም ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ከ240 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ለውጥ ውስጥ ሴቶች ያላቸው ሚና እጅግ ታላቅ ነው ተብሏል። ወደፊት በተቀመጠ ትንበያ መሰረት ደግሞ በ2050፣ 77 በመቶ ክርስቲያኖች በደቡቡ የአለም ክፍል የሚኖሩ ይሆናል።

እነዚህ የአሃዝ ለውጦችና ትንበያዎች ወደፊት የክርስትና ማዕከል የትኛው የአለም ክፍል እንደሚሆን ያሳያል ተብሏል።

ለአብነት በአውሮፓና አሜሪካ የክርስትና ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው በአፍሪካና እስያ ደግሞ በፍጥነት እያደገ
#ታላቁ #የወንጌል #አርበኛ #ወደ #ጌታ ተሰበሰቡ

መጋቢ ሰለሞን ጂኖሎ የሻሸመኔ አጥቢያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መሪ መጋቢ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

በወንጌል ላልተደረሱ አካባቢዎች ወንጌል የማድረስ ሸክም ሲሰሩ ቆይተዋል።

በእንዲህ ሁኔታ በመሰጠት የሚያገለግሉ አባት ማጣት እጅግ ልብን የሚሰብር ዜና ቢሆንም ወዳገለገለው ጌታ ተሰብስቦአልና እንጽናናለን።

መጋቢ ሰለሞም የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በመሆንም ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል።

ጌታ ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
#ቤተ #በአዲስ አበባ

በሆሳዕና ለረጅም አመት እያገለገለች የምትገኘዉ ቤተምህረት #አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል።

#አድራሻ ፦ ከቡልጋሪያ #ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።

#ቤተ ምህረት እንገናኝ 🙏🙏
#እግዚአብሔር ያፅናናሽ።

የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ #ወደ ጌታ ሄደ።

የአርቲስት ዘሪቱ ከበደ የ 17 ዓመት የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው በድንገተኛ ህመም ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለአርቲስት ዘሪቱና ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል።
ምዕመናን #ወደ ፕሮግራሙ እንዳትሄዱ።

"በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም የሚደረገው ኮንፈረንስ እውቅና የለዉም" ስትል የወላይታ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ገለፀች።

ቤተክርስቲያኒቱ ከሰኔ 01 እና 02/2016ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም CJ ኮንፍራንስ ለማድረግ በሶሻል ሚዲያ እና ለአጥቢያዎች ደብዳቤ በመጻፉ የማስታወቂያ ስራዎችን መስራቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑ የሶዶ ከተማ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ኅብረት ይህ ኮንፈረንስ በወላይታ ቀጠና ቃ/ሕ/ጽ/ቤት ፤ የሶዶ ከተማ እና ዞን ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስሉም እንዲሁም የሶዶ ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ያናት ኅብረትም ዕውቅና የሌለው በመሆኑም አጥቢያዎችም ሆነ ምዕመኖቻቸው ወደዚህ ፕሮግራም እንዳይሄዱ በዞን ፕሮግራም ጭምር በማስታወቂያ እንዲነገራቸው በጌታ ፍቅር እናሳውቃለን፡፡ ሲሉ በደብዳቤ ገልፀዋል።

በቀኑ በኅብረቱ እውቅና ኮንፈረንስን ያዘጋጁ አጥቢያዎች ስታዲየም ቃ/ሕ/ቤ/ያን እና መብራት ኃይል ታ/ሕ/ቤ/ያን በእነዚህ አጥቢያዎች ንፁህን የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት እንዲትካፈለ እናሳስባለን፡፡ ሲሉም አሳስበዋል።
#የዛሬ -ሃምሳ #ዓመት

#እኔ #በጌታ ምሪት #ወደ ባሌ ጎባ ገብቼ ቤተክርስቲያን ለመትከል ቤት የተከራየውበት ቀን #በሮቤና በአጋርፋ ይሠሩና ይኖሩ ከነበሩት ሁለት ወንድሞች #አያና መኳንንና #ከአባተ ወላኒዎሰ ጋር ከሮቤ አንድ ታጣፊ አልጋ ከነፍራሹ በ28 ብር ገዝተን ቤቱን ደግሞ በ10 ብር ተከራይተን የኪራይ ውል ፈጸምን።

ኪራዩን ከሁለቱ ወንድሞች ማን እንደከፈለ ትዝ አይለኝም ። ቤቱ ወንዝ ደር ከመሆኑም በላይ ንፋስ ያስገባል እና በጣም ይበርዳል።

በተለይም በማያውቁት አገር ሌሊቱን ለብቻ ማደር እንዴት ያስፈራል። ሃምሳ ዓመት ወደ ኋሊት አሰብኩ ። የአምላኬ ምህረትና ማደን ቸርነቱም ገረመኝ ደነቀኝም።

ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን ። 🙏🙏🙏

ከመጋቢ ጻድቁ አብዶ (የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት ፕረዚዳንት) ገጽ የተወሰደ
#እግዚአብሔር ለሁሉም መጽኛናትን ይስጥ!!

የተወደደው ወንድማችን ሱሬ ርሆቦት አርት ሚኒስትሪ የዛሬ 21 አመት ሲመሠረት ጀምሮ በትወና፣ በቀረጻና ኤዲቲንግ እንዲሁም በዝማሬ ሲያገለግል ቆይቷል።

ሱሬ በሁላችንም ዘንድ #ተወዳጅ፣ ተጫዋችና #መልካም ስብእና ያለው #ወንድም ነበር።

ከጥቂት አመታት ጀምሮ ደግሞ በሚያገለግልባት ቤተ ክርስቲያን ብዙዎቻችሁ በአገልግሎቱ ተጠቅማችኋል ብዬ አስባለሁ።

ሱሬ ልጅነቱንና ወጣትነቱን ሰጥቶ #ወደ ተከተለው፣ ወዳገለገለውና ወደሚወደው #ጌታ እቅፍ ሔዷል። ለወዳጆቹ፣ ለቤተሰቦቹ እና አብረነው ስናጥን ለቆየነው ለእኛም እሱን ማጣት ሀዘን ቢሆንብንም እርሱ ግን ወደተሻለውና እኛም ሁላችን ተራችንን ጠብቀን ወደምንሔድበት ቦታ ሔዷል።

ነገ ሐሙስ 6:00 በዮሴፍ #ቤተክርስቲያን በክብር እንሸኘዋለን🙏

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሁሉም መጽኛናት እንዲሆን እንመኛለን።
በአረብ ሃገሯ #ኢራን እስከ 1 #ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ወደ ክርስትና መጥተዋል ተባለ።

ከ88 ሚሊዮን ህዝቧ 96 በመቶ በላይ የሚሆነው እስልምና ተከታይ በሆነበትና፣ የሃገሪቷ #መንግስት በግልጽ እስላማዊ በሆነባት ኢራን ይሄንን ያክል ቁጥር #ክርስቲያን መገኘቱ ተዓምር ነው ተብሏል።

ሪፖርቱን ይዞት የወጣው The Voice of the Martyrs የተባለው በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስን ስደት የሚከታተል ተቋም ነው። ተቋሙ በሪፖርቱ ከ1970 የኢራን አብዮት ወዲህ በሃገሪቱ ክርስቲያኖች ስደት የበረታ መሆኑን ጠቅሷል።

ምንም እንኳን ስደቱ ቢበዛም በተቃራኒውም የክርስቲያኖች ቁጥር መጨመርን አሳይቷል። ቤተ ክርስቲያን በድብቅ ወይም underground ሆና መስፋፋቷን ቀጥላለች።

ሌላዋ የመካከለኛው ምስራቅ #አረብ ሃገር በሆነችው የመን፣ ጆሽዋ ሚኒስትሪ ሪፖርት እንዳደረገው በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ይልቅ በየመን ወደ #ጌታ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ብልጭን አሳይቷል።

በ2024 ሪፖርት መሰረት ኢራን ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በሚል በ9ኛ ስፍራ የምትገኝ ሲሆን የመን በበኩሏ በ5ኛ ስፍራ ተቀምጣለች።
በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ፓስተር ጻዲቁ አብዶ

የ2017 #አዲስ አመት አስመልክቶ #የኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አንዶ ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ወቅት የራሱን በረከት ይዞ ይመጣል። ወቅቶች የሚፈራረቁት ለሰዎች የሚሰጡት ካለው በረከት አንጻር ነው ብለዋል።

በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ያሉት ፓስተር ጻዲቁ ተገቢ ባልሆነ ድርጊቶቻችን ያመጣናቸው ነገሮች በማራቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሃገራችን ሰላም ለሕዝባችን መቀባበል እና ይቅር መባባል እንድንሰራ አሳስበዋል።