The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አንድ #አመት #ሆነዉ
#ቤተክርስቲያን እንስራ

#በኢትዮጵያ #አማኑኤል ህብረት በሐመር #ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ምሽት ላይ የዛሬ አመት በዚህ ወር በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ የቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ወደቀች።

ይህ ከተፈጠር አንድ አመት ሆነዉ። በአከባቢው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት 75% አርብቶ አደር የሆኑ ሲሆን በወቅቱ የተጀመረዉ ድጋፍ በመቋረጡ እስካሁን አልተገነባችም።

አከባቢው ገና በወንጌል ያልተደረሰበት ከመሆኑም ባሻገር በአከባቢው ላሉ የወንጌል ጣቢያዎች እናት ቤተክርስቲያን በመሆኗ ፈተናውን አብዝቶብናል።

የዛሬ አመት ጥሪዉ እንደቀረበ የተወሰነ እርብርብ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም ድጋፉ ተጠናክር ስላልቀጠለ ዛሬም አከባቢው የነበረችዉ እናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሽ የላትም።

አሁን ደግሞ ክረምት እየደረሰ በመሆኑ ምዕመናን እና መሪዎች ስጋታችዉ ጨምሯል።

ሁላችንም ተረባርበን ቤተክርስቲያንን እንስራ!!!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ
#Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)

Phone Number:-
☎️ +2519111575204
📱+251 912169165
#የዛሬ #ዓመት #በዚህ #ሰዓት
#እግዚአብሔር #ዉሳኔዉን #ወስኗል

የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት በሀገረ አሜሪካ ፅንስ የማቋረጥ መብት ተሽሮ የብዙ ክርስቲያኖች ደስታ እጥፍ ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ሁለቱ የቀድሞ እና የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በወቅቱ ምን አሉ?

#ፕሬዝዳንት_ጆ_ባይደን ውሳኔውን “ቀይ ስህተት” ያሉት ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ “የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲሉ ተችተዋል።

“ውሳኔው የአክራሪ አስተሳሰብ ውጤት ነው። በጣም አሳዛኝና የተሳሳተ ውሳኔ ነው” ብለዋል። ፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈቀድባቸው ግዛቶች ተጉዘው ፅንስ የሚያቋርጡ ሴቶች ክልከላ እንዳይጣልባቸው እንደሚሠሩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዉ ነበር።

ጉዳዪን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው የቀድሞ የአሜሪካ #ፕሬዝደት_ዶናልድ_ትራምፕ በበኩላቸው “እግዚአብሄር ውሳኔውን ወስኗል” ብለዋል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለአምስት አስርት አመታት የዘለቀውን እልባት ያገኘ ህግን ከሻረ በኋላ ፅንስ የማቋረጥ ብሄራዊ መብትን ለማቆም “አምላክ ውሳኔ ወስኗል” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ ከ6-3 በሆነ ድምጽ በድምጽ ብልጫ ካገኘ በኋላ እያንዳንዱ ግዛቶች ፅንስን በማስወረድ ላይ የራሳቸውን ህጎች እንዲያደርጉ መፍቀድ አለባቸው ብለዋል።

#ይህ #ከሆነ #ድፍን #አንድ #አመት ሞላዉ።
#አሜሪካ #ዛሬም #ምንም #እንኳን #In #God #We #trust ቢሉም ...
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#በድል #ተጠናቋል
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ሲካሄድ የቆየው #ልዩ የበዓል #ፕሮግራም በድል ተጠናቋል።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ

#መልካም #አዲስ#አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production #እናመሰግናለን
#በአዲስ #አመት #ሌላ #በረከት
ከግማሽ #ሚልዮን በላይ .. በማዉጣት ለአቅመ ደካሞች ..

የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል አጥቢያ ከጉድለቷ በመቆረስ ከ550,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሶስት የአቅመ ደካሞች ቤት አስመረቁ።

በፕሮግራሙ ላይ የፌይዝ ባይብል #ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ የሆነው ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ እንዲሁም የልደታ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን እና የወረዳ 8 አፈጉባኤ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቀን አስረክበናል::

በዚህ በጎ ተግባር ላይ በገንዘባችሁ እና በሙያችሁ የተሳተፋችሁ የቤተክርስትያናችን አባሎች #ሁሉ #እግዚአብሔር ይባርካችሁ::

Fbi Church Miracle Chaple Mekanisa
#መንግሥት በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚያደርገውን ግፍ ቀጥሏል።

የአልጄሪያ መንግስት በአብያተ ክርስቲያናት #ላይ እየወሰደ ያለውን ስልታዊ እርምጃ ቀጥሏል።

አልጄሪያ 42 ሚሊዮን #ህዝብ እንዳላት የሚነገር ሲሆን 1% ህዝብ በካቶሊኮች እና ፕሮቴስታንቶች የተወከለው የክርስቲያን ማህበረሰብን ናቸዉ።

#እንደ #ክርስቲያን ኮንሰርን ዘገባ ከሆነ በእስራኤል እና በሃማስ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሰሜን አፍሪቃዊቷ ሀገር ላሉ ክርስቲያኖች ህይወትን አስቸጋሪ አድርጎታል።

"የአልጄሪያ መንግስት በግጭቱ #ውስጥ እስራኤልን እንደሚደግፉ እና የውጭ እና የምዕራባውያን ተፅዕኖዎች የአገሪቱን ብሄራዊ አንድነት እንደሚያበላሹ ይገነዘባሉ" ሲል ICC በሪፖርቱ ገልጿል።

ባለፈው #አመት በአጠቃላይ 16 አብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸውን ተከትሎ የአልጄሪያ መንግስት የክርስቲያን አገልግሎቶች እስከ 10 #ሰዎች #ብቻ እንዲስተናገዱ መወሰኑን ዘገባዉ አክሏል።

በተጨማሪም፣ ICC እንዳለው፣ ባለፉት ሳምንታት በርካታ የአልጄሪያ ፓስተሮች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል።

ICC (አይሲሲ) በሪፖርቱ "አብዛኞቹ የአልጄሪያ ክርስቲያኖች ከካቢሌ ጎሳ የመጡ በመሆናቸው የክርስቲያኖች ሁኔታ በአልጄሪያ ያለው ሁኔታ የበለጠ የተወሳሰበ ነው" ሲል ገልጿል።

"በአልጄሪያ ውስጥ ያለው ክርስትና ረጅም #ታሪክ ያለው ነው እና በአልጄሪያ መንግስት በአልጄሪያ ክርስቲያኖች እምነት እና በአካባቢው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መካከል ያለውን ልዩነት በአልጄሪያ መንግስት መለየት አለበት" ሲል አይሲሲ ተናግሯል.

አልጄሪያ በኦፕን ዶርስ የአለም ለክርስትና አስቸጋሪ ከሆኑ ሀገራት የ2023 ዝርዝር መሰረት ክርስትያኖች ከሚሰደዱባቸው 50 ሀገራት 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
#ቤተክርስቲያን ዉስጥ #አንድ ሰዉ ተገደለ።

እውቁ አሜሪካዊ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን የምትመራው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ጥቃት የአንድ #ሰው ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ሌክዉድ ቹርች በመባል በምትታወቀው በዚህች ቤ/ክ ውስጥ ነው ትላንት የሰንበት ፕሮግራም ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው። ጥቃት አድራሿ #ሴት ስትሆን በወቅቱ ስራ ላይ ባልነበሩ ፖሊሶች ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ጥቃቱን ባደረሰችበት ወቅት የ5 #አመት ህጻን #ልጅ ይዛ እንደነበረም ተነግሯል። ህጻኑም ጉዳት ደርሶበት የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል። በጥቃቱ እስካሁን አንዲት ሴት #ብቻ ናት እግሯ ላይ በጥይት የመታችው እና ጉዳት የደረሰባት።

የቤ/ክኗ መሪ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን እንደዚህ ባለ የጨለማ ጊዜ፣ እምነታችን እንጠብቅ መቼም ቢሆን ጨለማ አያሸንፍም #እግዚአብሔር በብርሃን ይመራናል ሲል ለክርስቲያን ፖስት ተናግሯል። በዚህ ወቅትም በፍቅር እና በመያያዝ አብረን መቆም ይገባናል ብለዋል።

ጥቃት አድራሿ በተኩሱ ወቅት ቦምብ ይዣለው በማለት ስታስፈራራ እንደነበረና መርዝ ነው እያለች ስፕሬይ ስትረጭ ነበረ ብሏል ፖሊስ ባደረገው ምርመራ።

ሌክዉድ ቸርች በአሜሪካ ቴክሳስ ሂውስተን የምትገኝ ሲሆን፣ መሪዋ ጆዬል ኦስቲንም በስህተት ትምህርት ስሙ ደጋግሞ ሲነሳ ይታወሳል። ዘገባዉ የThe Christian Post ነዉ።
#እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏

ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ሮሜ 12:9

#FBI #church (ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን) በአንድ #አመት ውስጥ #በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች የአምስት አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦች #ቤት ሰርተን አስረክበናል።

የረዳን #እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው::
በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ፓስተር ጻዲቁ አብዶ

የ2017 #አዲስ አመት አስመልክቶ #የኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አንዶ ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ወቅት የራሱን በረከት ይዞ ይመጣል። ወቅቶች የሚፈራረቁት ለሰዎች የሚሰጡት ካለው በረከት አንጻር ነው ብለዋል።

በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ያሉት ፓስተር ጻዲቁ ተገቢ ባልሆነ ድርጊቶቻችን ያመጣናቸው ነገሮች በማራቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሃገራችን ሰላም ለሕዝባችን መቀባበል እና ይቅር መባባል እንድንሰራ አሳስበዋል።