The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ዘማሪ #በረከት ተስፋዬ #ይቅርታ ጠየቀ።
ንስሀ #ገብቻለሁ

የተወደዳችሁ እህቶቼና ወንድሞቼ ዛሬ ወደ እናንተ የመጣሁት ይቅርታን ስለመጠየቅ ጉዳይ ነዉ።

ባለፈዉ ጊዜ በኮንሰርቴ ጉዳይ ወደናንተ መልእክት አቅርቤ ነበር። እናም ዛሬ የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል መሪዎች ጠርተዉኝ ስለ ጉዳዩ ሲነግሩኝ ስተት እንደሰራዉ አወኩኝ።

አዳራሹ ለአምልኮ ኮንሰርት አገልግሎት የተከፈተ መስሎኝ ነበር ነገር ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ክፍት አለመሆኑን ሲነግሩኝ እኔ የሰማሁት ነገር የዉሸት መረጃ ነበር። ከዚህም የተነሳ ስሜታዊ ሆኜ በለቀቅኩት ፅሁፍ የቤተ ክርስቲያንን መሪዎች አሳዝኛለዉ።

እንዲሁም ሰዎችን ወደተለየ ሀሳብ በለቀቅኩት ፅሁፍ መርቻለዉ። በእዉነት ዛሬ ከመሪዎች ጋር ሳወራ በደልን እንደፈፀምኩ ተረድቼ ንስሀ ገብቻለዉ መሪዎችም ተንበርክኬ መርቀዉ ፀልየዉ ሸኝተዉኛል።

ጌታ ኢየሱስ ይባርካቸዉ እኔን ታናሹን ጠርተዉ ለማቅናት ለሄዱትን እርምጃ ጌታ ይክፈላቸዉ። እኔ በጣም አዝኜ ስሜቴም ተጎድቶ ነበር እወዳቸዉ ስለነበር። ዛሬ ተፈዉሻለዉ። በተረፈ የሙሉወንጌል መሪዎችንና ቤተ ክርስቲያንን ባርኩልኝ።

ወንድማቹ በረከት ተስፋዬ #ነኝ
ስፒከር የመታቸው #ግለሰብ
#እግዚአብሔር #ይመስገን #ደህና #ናቸዉ

#በዘማሪ #በረከት #ተስፋዬ የመድረክ አገልግሎት #ወቅት የሙዚቃ ስፒከር ወድቆ አንድ ሰው ላይ ጉዳት ሲያደርስ የሰሞኑን ማህበራዊ #ሚድያ መቀባበያ ሆኗል።

ከሁለት አመት በፊት በቡታጅራ ከተማ ተደርጎ በነበረ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ አንድ አባት ላይ ትልቅ እስፒከር ሲወድቅ የሚያሳይ ቪድዮ በማህበራዊ ሲመላለስ ነበረ። በወቅቱ ግለሰቡ ላይ ትልቅ ጉዳት አስከትሎ እንደነበረ ዘማሪው ገልጿል።

ሆኖም ድርጊቱ የተፈጸመው ከሁለት አመት በፊት ሲሆን፣ በወቅቱን ከስፒከሩ ክብደት አንጻር እኚህ ግለሰብ ላይ የጤና እክል አድርሶ እንደነበረ ዘማሪው ገልጿል።

በወቅቱም አስፈላጊው የህክምና ክትትል እንደተደረገም ዘማሪ በረከት ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከዚህም የከፋ የመድረክ አካባቢ ጉዳቶችን በአገልግሎት ዘመን አይቻለው ያለው ዘማሪ በረከት፣ አስተባባሪዎች፣ አገልጋዮች ይሄንን አይታችሁ መድረክ አካባቢ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እላለሁ ብሏል።
#በአዲስ #አመት #ሌላ #በረከት
ከግማሽ #ሚልዮን በላይ .. በማዉጣት ለአቅመ ደካሞች ..

የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል አጥቢያ ከጉድለቷ በመቆረስ ከ550,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሶስት የአቅመ ደካሞች ቤት አስመረቁ።

በፕሮግራሙ ላይ የፌይዝ ባይብል #ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ የሆነው ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ እንዲሁም የልደታ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን እና የወረዳ 8 አፈጉባኤ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቀን አስረክበናል::

በዚህ በጎ ተግባር ላይ በገንዘባችሁ እና በሙያችሁ የተሳተፋችሁ የቤተክርስትያናችን አባሎች #ሁሉ #እግዚአብሔር ይባርካችሁ::

Fbi Church Miracle Chaple Mekanisa
#ያቦቅን_ስሻገር
#በረከት_ለማ

ያቦቅ ማለት በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ 32 ፥ 22 ላይ ያዕቆብ ከላባ ቤት ኮብልሎ ወደ አባቶቹ ምድር ሲመለስ በመንገድ ላይ ተሻግሮ ያለፈበትና ከማዶ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የታገለበት #ወንዝ መጠሪያ ስም ነው።

"አንዴ ነክተኸኝ ስሜን ከለወጥከው
እያነከስኩም ቢሆን ሁሉንም ቀድማለሁ"
(ከመዝሙሩ ላይ የተጠቀሰ)

አንተን ባየ አይኔ፡ ያቦቅን ስሻገር፡ ያድናል ኢየሱስ፡ ትሁን ፈቃድህ እና ሌሎችም 9 መዝሙሮችን የያዘ አዲስ የመዝሙር ሰንዱቅ ሊለቀቅ ነው።
ዘማሪ በረከት ለማ ከአልበሙ ዝማሬዎች መካከል የተወደዱና የሚያንጹ መዝሙሮችን ቀድሞ ለቋል።

አልበሙ በቅርብ የሚለቀቅ ሲሆን፡ ሰምታችሁ እንድትጠቀሙ  ተጋብዛችኋል።

ምንጭ፥
https://t.me/bereketlemma