The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት በሐመር ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን የዲመካ አማኑኤል ህብረት ቤ/ክ በትላንትናዉ እለት ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ ቤተክርስቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ ወድቃለች።

የዲመካ አማኑኤል ቤተክርስቲያን በአከባቢው ላይ ከ 4 አመት በላይ የቆየች እና ያገለገለች ነች።

በስሯ 10 ህብረቶች አጥቢያ የሚወጡ 4 የወንጌል ጣቢያዎች ያሏት ሲሆን አባላቶቿ አርብቶ አደሮች እንደመሆናቸው መጠን የቀድመው አዳራሽ የተሰራው 260 የቅጠል ቆርቆሮ ማምለኪያ አዳራሽ ነው።

በትላንትናው እለት በደረሰዉ አደጋ የቤተክርስቲያን የማምለኪያ የሙዚቃ መሳሪያ ኪቦርድ እና ሞንታርቦ የተበላሸ ፣ መቀመጫ ወንበሮች የተሰባበሩ እና ሙሉ የቤተክርስቲያን መገልገያዎች ወድመዋል (ከጥቅም ዉጪ) ሆነዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ ሳምንታዊ ፕሮግራም ማክሰኞ ሀሙስ እና እሁድ ሲሆን በትላንትናዉ እለት ማለትም ማክሰኞ ምሽት የአምልኮ ፕሮግራም አጠናቀዉ ምዕመናን ወደየቤታቸው ከተመለሱ በኋላ አደጋዉ እንደተፈጠረ ከስፍራዉ የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች ለክርስቲያን ዜና ነግረዉናል።

መረጃዉን ያደረሰን መሪ እንደነገሩን ከሆነ በዮሐንስ ወንጌል “ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።

ዮሐንስ 6፥6 በጌታ የእኛን ያውቃል በሚል ቃል ተካፍለዉ የቤተክርስቲያኗ የጀመረችው የወጣቶች ስልጠና ለተከታታይ አንድ ወር መጀመሩን ማስታወቂያ ተናግረዉ በባርኮት ተሸኛኘን "ዝናቡ ሲዘንብ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ ፓ/ር ቤቱ ወደቀ እኮ ብለው ነገሩኝ እራት እየበላን ነበረ ትተን ወጣን አውነትም ወድቋል" ሲሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ቤተክርቲያኒቱ ሙሉ በሙሉ ንብረቱ እና መገልገያዉ በመጥፋቱ እጅግ ድጋፍ የሚያስፈልጋት እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቱን መልሶ ለማቋቋም ከ500 ሺህ ብር የሚያስፈልግ እንደሆነም ሰምተናል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በአከባቢው የምትገኘውን ቤተክርስቲያን ለማገዝ የምትፈልጉ የተቀመጡ አድራሻቻዎች መጠቀም የምትችሉ እንደሆነ እንገልጻለን።

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ #Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
-Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)
Phone Number:- ☎️ +2519111575204 📱+251 912169165
#ወንጌል_ይቀጥላል

ባሳለፊነዉ ማክሰኞ የዲመካ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ የማምለኪያ አዳራሹ ሙሉ በሙሉ መዉደቁ ይታወሳል።

የቤተክርስቲያኒቱ ምዕናን በዛሬዉ እለት የትንሳኤ በዓልን በዚህ መልክ በአምልኮ እና በተለያዩ መሰናዶዎች በዝናብ ውስጥ አክብረዉ የክርስቶስን ትንሳኤ አዉጀዉ አሳልፈዋል።

የወንጌል ስራ እንዲቀጥል ሁላችንም በማንኛውም መንገድ እርብርብ እንድናደርግ ጥሪ እናቀርባለን!!!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23
ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!
#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ #Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
-Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)
Phone Number:- ☎️ +2519111575204 📱+251 912169165
በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት በሐመር ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ስራውን ጀምረናል
የቆሮቆሮ ግዥ አጋራችን እንዲሆኑ 1አንድ ቆሮቆሮ ይግዙልን 700 ብር ለቤቱ የሚያስፈልገው 200 ቅጠል ቆርቆሮ ነው ፡፡ ስለ ልግስናዋ እናመሰግናለን
“እኔም፣ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛ ባርያዎቹ እንደ ገና ሥራውን እንጀምራለን
ነሀምያ 2፥20 (አዲሱ መ.ት)
#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ #Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
-Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)
Phone Number:- ☎️ +2519111575204 📱+251 912169165
#ቤተክርስቲያናችንን_እንሰራለን

አንድ ምሽት ዝናብ እየዘነበ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ ፓ/ር ቤቱ ወደቀ እኮ ብለው ነገሩኝ እራት እየበላን ነበረ ትተን ወጣን አውነትም ወድቋል ፡፡

ይህ መልዕክት ከጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ከዲመካ አማኑኤል ህብረት ቤ/ክ (ሀመር) የቤተክርስቲያኒቱ ህንፃ በጎርፍ ሲወድቅ የቤተክርስቲያኒቱ ፓስተር የደረሰን የስልክ መልዕክት ነበር።

ዉድ የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን በአሁኑ ሰዓት የቤተክርስቲያን ህንፃ በግንባታ ላይ ስትሆን ይህንንም ለማግዝ ቅዱሳን አብረዋቸዉ እንዲቆሙ ትጠይቃለች።

በመሆኑም 200×10.000 ቻለጅ እንድንቀላቀል ጥሪ ያቀርባሉ። ለቤቱ ስራ;ለሚሽነሪ :ለወንበር እና ለሙዚቃ መሣሪያዎች ግዥ ያገለገሉ ሞንታርቦ ስጦታ ያገለገለ ኪቦርድ ስጦታ
ያገለገለ ኮንፕተር ያገለገለ ፕርንተር እና ኮፒ ማሽን ያገለገለ ሚክሰር ስጦታ ቻለጅ ተጀምሯል። በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23
ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ #Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
-Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)
#አንድ #አመት #ሆነዉ
#ቤተክርስቲያን እንስራ

#በኢትዮጵያ #አማኑኤል ህብረት በሐመር #ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ምሽት ላይ የዛሬ አመት በዚህ ወር በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ የቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ወደቀች።

ይህ ከተፈጠር አንድ አመት ሆነዉ። በአከባቢው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት 75% አርብቶ አደር የሆኑ ሲሆን በወቅቱ የተጀመረዉ ድጋፍ በመቋረጡ እስካሁን አልተገነባችም።

አከባቢው ገና በወንጌል ያልተደረሰበት ከመሆኑም ባሻገር በአከባቢው ላሉ የወንጌል ጣቢያዎች እናት ቤተክርስቲያን በመሆኗ ፈተናውን አብዝቶብናል።

የዛሬ አመት ጥሪዉ እንደቀረበ የተወሰነ እርብርብ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም ድጋፉ ተጠናክር ስላልቀጠለ ዛሬም አከባቢው የነበረችዉ እናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሽ የላትም።

አሁን ደግሞ ክረምት እየደረሰ በመሆኑ ምዕመናን እና መሪዎች ስጋታችዉ ጨምሯል።

ሁላችንም ተረባርበን ቤተክርስቲያንን እንስራ!!!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ
#Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)

Phone Number:-
☎️ +2519111575204
📱+251 912169165