The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#እይታ
#Opinion

የሰሞኑን #አንድ #ሁለት ዜናዎች ልንገራችሁ።

የቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ጸሃይ ቶሎሳ ግለ #ታሪክ ተመርቋል። መጽሃፉ “በእቶን እሳት ውስጥ” የሚል ነው። የነዚህ ብርቱ እናት ታሪክ እና ምስክርነት ለአንድ አንድ ሰዎች የእምነት መልህቅ ሊሆን ይችላል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ሌላው #ዜና ደግሞ በፌደራል መንግስትና #መንግስት ሸኔ በሚለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር አሁንም ሳይሳካ ቀርቷል።

ይሄንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን አረጋግጠዋል። ከዚህ የሰላም ድርድር #መልካም ውጤት ይገኛል በሚል፣ ክርስቲያኑ ምነኛ ጓጉቶ እንደነበረ ማሰብ አይከብድም።

በተመሳሳይ ክፍለ ዘመን #ውስጥ ፣ በተመሳሳይ ርዕሳቸው፣ ረግጦ በሚገዛ መንግስት፣ የወንጌልን ነጻ አውጪነት አውጀው፣ የተገደሉ የዘመናት ክስተቶች ላውራችሁ።

#ቄስ_ዴትሪች_ቦንሆፈር በ1906 በጀርመን ብሬስሎው በተባለ ስፍራ የተወለዱ #ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ስነ መለኮት አጥኚ ወይም ቲዎሎጂያን፣ ኮንፌሲንግ በተባለች ሉተራዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቄስ #እና ጸረ ናዚ ሰው ነበሩ።

የአዶልፍ ሂትለር ተቃዋሚ መሆን የዋዛ ነገር አይምሰላችሁ። ከናዚው አዶልፍ ሂትለር የአስተዳደር እቅዶች መካከል “ኢውታናዢያ” የሚባል ፕሮግራም ነበረ ይባላል። በዚህ ፕሮግራማቸው ሰው ከሚሰቃይ ቀድሞ መሸኘት የሚል ነው።

#ትንሽ የታመመ የመዳን ተስፋ ሳይሆን፣ ከህመሙ ማረፊያ መግደል ያሰበ “በጣም ቅን ሰው ናቸው” ነበረ። ይሁዲዎች #ላይ ያደረገውን ጭካኔ፣ አለም ያወቀው ነው። ቦንሆፈር ይሄንን ስርዓት ነበረ በአደባባይ ቆሞ የተቃወመው። ያው በእሳት ፊት ቆሞ ነበረና እሳቱ በላው። በተወለደ በ39ኛ አመቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልን ሰብኮ ተሰቅሎ ተገደለ።

#ቄስ_ጉዲና_ቱምሳ በ1929 በኢትዮጵያ ወለጋ ቦጂ ከተማ የተወለዱ ሰው ናቸው። ተስፋ አደርጋለው ስለ ቄስ ጉዲና የማያውቅ ወንጌላዊ ክርስቲያን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ይከብዳል። ግን ዝም ብዬ ታሪኩን ልንገራችሁ።

እኚህ ቄስ የስነ መለኮት አጥኚ #ወይም ቲዎሎጂያን፣ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በተባለች ሉተራዊ ቤ/ክ ውስጥ ቄስ እና በሃያሉ ደርግ መንግስት ፊት የቆሙ ሰው ነበሩ። የደርግ ተቃዋሚ መሆንም የዋዛ ነገር አይደለም።

ኮለኔል መንግስቱ ማለት፣ በርሳቸው ዘመን በለጋ እድሜው አፈር የገባ ወጣት፣ በቀይ ሽብር ስም ያለቀው ተቀናቃኝ ፖለቲከኛና ለገዛ አጋሮቻቸው ያልተመለሱ ባለ ደም እጅ ሰው ነበሩ። ያ ኮለኔል መንግስቱና አገዛዙም ነበር ሆኗል።

እግዜር ደጉ፣ የማያሳልፈው የለም። ቄሱ ጉዲና በዚህ ለአፍሪካ እንኳን አይመለስም በተባለ ወታደር ፊት ቆመው “ወንጌል ነጻ ያወጣል” ብለው ሰብከዋል። እሳቸውም እሳት ፊት ቆመዋልና እሳት በላቸው። በተወለዱ በ50 አመታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰብከው በደርግ ወታደሮች ተገደሉ።

የነዚህ ሁለት በእሳት ፊት የቆሙ ቀሳውስት ህይወት፣ በሄሮድስ ፊት ቆሞ እውነት ተናግሮ አንገቱ የተቀላውን መጥምቁ ዮሃንስን ህይወት ይመስላል። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በአስፈሪው የሮማ መንግስት ፊት፣ በአይሁድ ካህናት ፊት፣ በፈሪሳዊያንና ግሪካዊያን ፊት “እናንተ የእፉኝት ልጆች እያሉ”፣ መኖር ሳያሳሳቸው፣ መሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን የሰበኩ ጀግኖች ናቸው።

ቄስ ቦንሆፈርና ቄስ ጉዲናም በአፈ ሙዝ እንጂ በአፉ በማያወራ መንግስት ፊት ቆመው፣ መኖር ሳያጓጓቸው፣ ሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን ሳይቀንሱና ሳይጨምሩበት የሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ቅሬታዎች፣ የክርስቶስ ልጆች ናቸው።

ዛሬስ መምህሩ፣ ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ፣ ነብዩ፣ ሐዋርያው፣ ሼፐርዱ፣ ዳዲው የቱ ጋር ቆመሃል? ጌታ ኢየሱስ በጎቼን ጠብቅ ያለው ስመኦን ጴጥሮስ፣ ከአለም 20በመቶ ህዝብን በሚገዛው ግዙፉ የሮማ መንግስት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።

አንተስ በጎቼን ጠብቅ የተባልከው እረኛ ሆይ ፣ ለበጎቹ ስትል፣ እንደ ስመኦን ጴጥሮስ ተዘቅዝቀህ ለመሰቀል፣ እንደ ቦንሆፈር በናዚ ለመሰቀል፣ እንደ ጉዲና በደርግ ወታደር የአሞራ ሲሳይ ለመሆን #ተዘጋጅተሃል?

ክርስቲያን ሆኖ መኖር እራሱ ዋጋ በሚያስከፍልበት በዚህች ምድር ላይ ለወንጌል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ ወይስ፣ ለአገልግሎትና ለእረፍት በV8 እና FORD F150 የምትምነሸነሽ #ሆነሃል? አለም ህይወት የሆነውን ክርስቶስን ለመስቀል ካልራራች፣ አንተ እውነተኛውን የርሱን ህይወት የምትሰብከውን የምትምርህ #ይመስልሃልን?

ዙሪያ ገባህን አይተህ ወንጌል የሚሰበክ ከጠፋ፣ ከተኩላ የምትጠብቀው በግ ከሌለ፣ ምናልባት ወንጌሉ የሚያስፈልገው፣ እረኝነቱ የሚያስፈልገው፣ ላንተው እራስህ እንዳይሆን የቆምክበትን አስተውል?
#እንኳን #አደረሳችሁ

በታላት ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የነቀምቴ ማህበረ ምዕመናን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድምቀት ተካሄደ።

ማህበረ ምዕመኑ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየው 100ኛው ዓመት የምስረታ #እና የአገልግሎት ቆይታን የሚዘክረው ክቡረ በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር፣ ማህበረ ምዕመኑ ስድስት ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ባስገነባው አዲሱ የአምላክ አዳራሽ ተካሂዷል።

ከማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ #አንድ #ቀን አስቀድሞ የማህበሩ ምዕመናን በነቀምቄ #ከተማ በነቂስ በመውጣት የከተማ ፅዳት እና የጎዳና #ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በዓሉንም ለመካፈል ከመላው #ኢትዮጵያ በርካታ እንግዶች፣ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የማኅበረ ምዕመኑ #ልጆች እና ማህበረ ምዕመኗን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሚሲዮናዊያን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የማህበረ ምዕመኑን የ100 ዓመታት አገልግሎት የዳሰሰ #መጽሐፍ ተመርቋል።

በዓሉም በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ ለማህበረ ምዕመኗ አባላት እና ለመላዉ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#ቤተክርስቲያን ዉስጥ #አንድ ሰዉ ተገደለ።

እውቁ አሜሪካዊ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን የምትመራው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ጥቃት የአንድ #ሰው ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ሌክዉድ ቹርች በመባል በምትታወቀው በዚህች ቤ/ክ ውስጥ ነው ትላንት የሰንበት ፕሮግራም ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው። ጥቃት አድራሿ #ሴት ስትሆን በወቅቱ ስራ ላይ ባልነበሩ ፖሊሶች ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ጥቃቱን ባደረሰችበት ወቅት የ5 #አመት ህጻን #ልጅ ይዛ እንደነበረም ተነግሯል። ህጻኑም ጉዳት ደርሶበት የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል። በጥቃቱ እስካሁን አንዲት ሴት #ብቻ ናት እግሯ ላይ በጥይት የመታችው እና ጉዳት የደረሰባት።

የቤ/ክኗ መሪ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን እንደዚህ ባለ የጨለማ ጊዜ፣ እምነታችን እንጠብቅ መቼም ቢሆን ጨለማ አያሸንፍም #እግዚአብሔር በብርሃን ይመራናል ሲል ለክርስቲያን ፖስት ተናግሯል። በዚህ ወቅትም በፍቅር እና በመያያዝ አብረን መቆም ይገባናል ብለዋል።

ጥቃት አድራሿ በተኩሱ ወቅት ቦምብ ይዣለው በማለት ስታስፈራራ እንደነበረና መርዝ ነው እያለች ስፕሬይ ስትረጭ ነበረ ብሏል ፖሊስ ባደረገው ምርመራ።

ሌክዉድ ቸርች በአሜሪካ ቴክሳስ ሂውስተን የምትገኝ ሲሆን፣ መሪዋ ጆዬል ኦስቲንም በስህተት ትምህርት ስሙ ደጋግሞ ሲነሳ ይታወሳል። ዘገባዉ የThe Christian Post ነዉ።
#NewsUpdate

#ማሳሰቢያ

ከትላንት በስቲያ በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች መዉደማቸዉ ይታወሳል።

#ይህንን #ዜና በማስመልከት The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ዓለም አቀፍ ቤ/ክ በሚል መጠርያ የምትጠራዉ ቤተክርስቲያን በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባት የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን መረጃን ዋቢ በማድረግ የተዘገቡ ከተለያዩ የግል ሚዲያ ያገኘነዉን #መረጃ ማሰራጨታችን ይታወሳል።

ሆኖም የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጎና ሲኒማ ህንጻ በሚገኘው አዳራሽ አምልኮ ካቆሙ #አንድ አመት ያለፋቸዉን መሆኑን ጠቅሰዉ መረጃዉ የተሳሳተ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዘገባዉ በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ የተቋሙ ኮሙኒኬሽን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን መናገራቸው ተካቷል።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች በበኩላቸው ወንበሮቹ የራሱ የህንፃው ባለቤቶች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

አደጋዉን በተመለከተ በዘገባዉ ጎልቶ የወጣዉ የሌላ ተቋማት ጉዳት ስለነበር በዚህ ዉስጥ ቤተክርስቲያን ጉዳት ደርሶባት ከነበር እንደ ክርስቲያን ሃላፊነታችንን ለመወጣት በሚል ዘገባዉን አሰራጭተናል።

በተሰራጨዉ የተሳሳተ ዘገባ #The #christian #news ይቅርታ እየጠየቅን ዘገባዉን ከገፃችን ማንሳታችንን እናሳዉቃለን።
#ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጨመ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ።

በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገደሉ።

ቡርኪና ፋሶ #ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ #ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

#እሁድ #ቀን በቡርኪና ፋሶ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ምዕመናን ተገድለዋል።

ኢሳካኔ በተባለው ስፍራ ለእሁድ ጸሎት ሥነ ሥርዓት በተሰባሰቡት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ አንድ የቤተ ክርስቲያኗ ባለሥልጣን ከሰዋል።

በመስጂድ እና በቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው በይፋ የታወቀ ነገር ባይኖርም አንድ የቡርኪና ፋሶ የግል ጋዜጣ ጥቃቶቹ የተቀነባበሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እምብዛም ያልተለመደ አይደለም ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ከሰሜናዊቷ ጂቦ ከተማ ከአምስት #ዓመት በፊት ተጠልፈው የተወሰዱ #አንድ ቄስ አስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከሦስት ዓመት በፊት ደግሞ ከዚያው ከተማ በታጣቂዎች የተጠለፉ አንድ ኢማም ከቀናት በኋላ ሞተው ተገኝተዋል። ዘገባው የBBC ነው።
#አንድ ቀን #ብቻ ቀረዉ..

#አሁኑኑ ይመዝገቡ !!!

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር።

#እያደገ #ሄደ ...ምዝገባ ሊጠናቀቅ የቀረን #1 #ቀን ብቻ ነው።

#ማሳሰቢያ :- ያለ ምዝገባ መግባት አይቻልም።

ስለዚህ ፈጥነዉ በቀሩን #ጥቂት ቦታዎች በተቀመጡት የስልክ እና link አድራሻዎች በመጠቀም ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk

#ወይም  ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።
#ክርስቶስ እንኳን #ወደ ምድር ቢወርድ #አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም

#ክርስቲያኖች ላይ ስደት በዝቷል።

በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በምትገኘው ኮሶቮ፣ ክርስቲያኖች #ላይ ስደት በርትቷል ተባለ።

በሃገሪቱ ክርስቲያኖች #ምንም አይነት የመሰብሰብ መብት እንደሌላቸው #እና ፈቃድ ለማግኘትም ሁኔታዎች እንደሚወሳሰቡባቸው ገልጸዋል።

የአርሜ #ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባት ኮሶቮ፣ 93 በመቶ ዜጎቿ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።

ምንም #እንኳን የሃገሪቱ ህገ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ላይ ግን መድሎና አመጽ ይበረታባቸዋል።

#ይህ ስደት በግል ደረጃም፣ የቀብር ስፍራ መከልከል፣ ንብረት የማፍራት መብት አለማግኘትና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይ #ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች፣ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ንብረት ማፍራት እና ሰራተኞችን ቀጥሮ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የላቸውም።

በቅርቡ የወጣ #አንድ ህግ ደግሞ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊኮችን እና ሌሎችንም ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ኢላማ ያደረገ ነው ይባልለታል።

በሃገሪቱ ያለፉትን 25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ ቄስ ሲናገሩ፣ ያለው ስቃይ በግልጽ ስላልሆነ ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

ለቀብር እንኳን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ፣ በኢማሞች የተመራ ቀብር ስነ ስርዓት እያደርግን ነው የምንገኘው ብለዋል። ምንም ቢሆን #ግን ለሃገራችን የወንጌል ተስፋ አለን ሲሉም እኚሁ ቄስ ይናገራሉ።

በኮሶቮ በ1980ዎቹ ወንጌላዊያን፣ ክርስቶስ እንኳን ወደ ምድር ቢወርድ አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም የሚል ተደጋጋሚ ዛቻ ከወቅቱ ኮሚኒስት መንግስት ሲደርስባቸው እንደ ነበረ ዘገባዉ አስታዉሷል።
#የወንጌል ዘመቻ ሊካሄድ ነዉ።

ጋፕስ አለም አቀፍ አገልግሎት
አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ

ጋፕስ ያለፉትን 14 ዓመታት የአገልጋዮችን የኑሮ ክፍተት መሙላት፡ የመንፈሳዊ ክፍተት መሙላት (ማጎልበት፡ ማስተማር) ላይ ሲሰራ ቆይቷል።

አንጾኪያ የወንጌል እንቅስቃሴ የ10 ቀናት የወንጌል ዘመቻ በነገው እለት ጀምሮ ከሚያዝያ 9-19 ድረስ ይካሄዳል።

ዘመቻው፡ የቡና #ሻይ ሰዓትን ለወንጌል፡ ሙስሊም ኢቫንጀሊዝም፡ የደም ልገሳ፡ የጎዳና ወንጌል፡ #አንድ #ሰው ለኢየሱስ፡ ማህበራዊ ሚድያን ከወንጌል፡ አርትን ለወንጌል፡ በመርዳት ወንጌል መስበክ፡ ሙዚቃን ለወንጌል፡ የርህራሄ አገልግሎት በዘመቻው በየእለቱ የሚሰሩ ስራዎች ናቸው።

የጋፕስ ሚኒስትሪ መስራችና መሪ መጋቢ ዳንኤል ዋለልኝ ሁሉም ሰው የተልዕኮ ሰራተኛ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡ በእነዚህ 10 ቀናት ሁሉም #ክርስቲያን አንጾኪያ በሚያደርገው የወንጌል ዘመቻ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የክርስቲያን መገናኛ ብዙሃንም በዚህ የወንጌል ዘመቻ በትልቅ ተሳትፎ እንዲሰራ፡ የክርስቲያን ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ግርማ ጥሪ አቅርበዋል።

አንጾኪያ ሙቭመንት #አዲስ የወንጌል ተኮር አገልግሎት ነው። አላማው በሐዋ ስራ 11 እንደተገለጸው፡ የአንጾኪያ ቤ/ክ የወንጌል አካሄድ መድገም ነው።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫውን በስፍራዉ በመገኘት አሰናዳንላችሁ።
#አፍሪካ

አፍሪካ ባለፉት 150 አመታት በርካታ ክርስቲያናት ያሉባት አህጉር ሆናለች።

በ1900 #ላይ በአለም ካለው #ክርስቲያን 82 በመቶው፣ በሰሜን የአለም ክፍል፣ አውሮፓ እና #አሜሪካ ይገኝ ነበረ። በተቃራኒው ደቡባዊ የአለም ክፍል አፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ደግሞ 18 በመቶ ብቻ ነበረ።

#አንድ #መቶ አመታትን #ወደ ፊት፣ ሰሜኑ አለም 33 በመቶው #ብቻ ክርስቲያን ሲሆን፣ ደቡቡ የአለም ክፍል ደግሞ 67 በመቶ ክርስቲያን ነው።

በጋና አክራ፣ በተካሄደ አለም አቀፍ የክርስቲያኖች ፎረም፣ በአለም ላይ የክርስትና ህዝብ ነክ ቁጥር ትልቅ ለውጥ ማሳየቱ ተነስቷል። ከኤፕሪል 16-20 በነበረው በዚህ ፎረም ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ከ240 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ለውጥ ውስጥ ሴቶች ያላቸው ሚና እጅግ ታላቅ ነው ተብሏል። ወደፊት በተቀመጠ ትንበያ መሰረት ደግሞ በ2050፣ 77 በመቶ ክርስቲያኖች በደቡቡ የአለም ክፍል የሚኖሩ ይሆናል።

እነዚህ የአሃዝ ለውጦችና ትንበያዎች ወደፊት የክርስትና ማዕከል የትኛው የአለም ክፍል እንደሚሆን ያሳያል ተብሏል።

ለአብነት በአውሮፓና አሜሪካ የክርስትና ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው በአፍሪካና እስያ ደግሞ በፍጥነት እያደገ
ራስን ማጥፋት

የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ Assisted Suicide #ወይም በእገዛ ራስን ማጥፋትን እየተቃወሙ ይገኛሉ።

ይሄንን ያውቁ ነበረ። በአለማችን 15 ሃገራት በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ይፈቅዳሉ። በሃኪም የታገዘ ራስን ማጥፋት ማለት፣ #አንድ #ሰው ራሱን ሲያጠፋ በሃኪም እገዛ ህጋዊ በሆነ መንገድ የህይወት ጉዞውን ማብቃት ማለት ነው።

የስኮትላንድ አብያተ ክርስቲያናት ይሄንኑ ድርጊት በሃገሪቱ ህጋዊ እንዲሆን መጠየቁን ተከትሎ ነው ድምጻቸውን ያሰሙት።

ለ129 የምክር ቤት አባላት በተላከው ደብዳቤ መሰረት፣ በአንድ የምክር ቤቱ አባል የቀረበውን ይሄንኑ አጸያፊ ተግባር ህጋዊ እንዳይደረግ ጠይቀዋል።

በደብዳቤያቸው፣ ይሄ ህግ የሰው ልጅን ሞራላዊነት አሽቀንጥሮ መጣል ነው፣ እንደ ሃገር አለን የምንለውን የሰው ልጆች ዋጋ የሚያሳጣን ነው ብለዋል።

ህጉ የሚጸድቅ ከሆነ ስኮትላንድ ስነምግባር የሌለባት፣ ምክር ቤታችንም ለሰው ልጆች ዋጋ የሌለው አዳራሽ መሆኑ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

በእገዛ ራስን ማጥፋት ማለት የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ የሌለው መሆኑን ማሳያ ነው። ዘፍጥረት ላይ #እግዚአብሔር በአምሳያው የሰውን ልጆች መፍጠሩ፣ ሁሉም የሰው #ልጆች በእግዚአብሔር እንደሚወደድ ማሳያ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ህይወት ዋጋ አለው ብለዋል።

ይሄንን ደብዳቤ የላኩት ቄስ አንድሪው ዶውኒ እና ቄስ ቦብ አክሮይድ የዩናይትድ ፍሪ ቸርች ኦፍ ስኮትላንድ አገልጋዮች ናቸው።

ሃገራችን ስኮትላንድ ሰዎች ራሳቸውን ማጥፋት የማያስቡባት መሆን አለባት ብለዋል። ምናልባት በመሰል ስሜት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ማህበረሰባችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቅርና እንክብካቤ ማሳየት አለበት ብለዋል።

ስኮትላንድ የ1517ቱ ተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ያገዙት ጆን ኖክስ ትውልድ ሃገር መሆኗ ይታወሳል።
የኮርያ እና አይቮሪ ኮስት አብያተ ክርስቲያናት ከእናት ሜቱዲስት ቤ/ክ  መገንጠልን ለምን መረጡ?

በአሜሪካ ከሚገኙ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የዩናይትድ ሜቱዲስት ቸርች ተጠቃሽ ናት። ስር መሰረቷን እንግሊዝ ሃገር ከተነሱ የ18ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ፣ እውቅ የስነ መለኮት መምህራን መካከል የሆኑት ጆን ዌስሊይ ያደረገችው ይህቺ ቤ/ክ ዛሬ በአሜሪካ እና መላው አለም በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን ተክላ ወንጌል ስትሰራ ቆይታለች።

ታሪካዊ በሆነ ውሳኔ፣ ይህቺ ጥንታዊት ቤ/ክ ልክ የዛሬ 1 ወር በፊት ነው፣ ግብረሰዶም የሆኑ አገልጋዮችን በቤቷ የፈቀደችው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየወሩ በአለም ዙርያ ያሉ አብረው ሰራተኛ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ማድረጋቸውን እያቆሙ ነው።

ለአብነትም የኮትዲቯር፣ እና ሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት የሚገኙ ከ4.6 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሏቸው ሃገራት ከአሜሪካዋ ሜቱዲስት ጋር ያላቸውን ህብረት ማቆማቸውን በግልጽ አውጀዋል።

ይሄንኑ የቤ/ክኗ ውሳኔ ተከትሎ፣ በሃገረ አሜሪካ ብቻ የሚገኙ ከ77 መቶ በላይ አብያተ ክርስቲያናትም ህብረት ማቆማቸውን አሳውቀው ነበር።

ይህም የአባላቱን ቁጥር ከአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በድምሩ ከ10 ሚሊዮን በላይ ያደርገዋል።

የኮርያ ሜቱዲስት አብያተ ክርስቲያናትም የቤተ ክርስቲያኗን ውሳኔ ተከትለው “ክርስትና የስሜት ጉዳይ አይደለም!” ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል። መጽሃፍ ቅዱስ በግልጽ ሃጢያት ነው ብለው ያስቀመጠው ጉዳይ ላይ የግለሰቦች ሃሳብ በቤ/ክን ላይ መሰልጠን የለበትም ብለዋል አቋማቸውን ሲገልጡ።

ቤተ ክርስቲያኗ ያላት #አንድ ተስፋ በአፍሪካ ብቻ ነው ብለዋል።

በዚህ ውሳኔዋ ብቻ ከአባላቷ ሩብ ያክል ወደ 11 ሚሊዮን የሚገመቱ አባላትን የያዙ አብያተ ክርስቲያናት፣ ህብረታቸውን ከአሜሪካ ሜቱዲስት ጋር አቋርጠዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እንዳያመልጦት #ልዩ እድል ...
በሙያዎ #አንድ ደረጃ ከፍ የሚሉበት፡
🎓🎓🎓🎓
#ገሊላ #ኢንተርናሽናል ሴሚናርየም ምዝገባ ጀምሯል!
ለበለጠ #መረጃ 9720 ይደውሉ ☎️ 🤳 ...*

ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት አሁኑኑ ማህበራዊ ሚድያችንን ይጎብኙ፡ ይቀላቀሉ
👇👇👇
Web https://gelilaseminary.com/
Facebook: gelilaseminary

Telegram https://t.me/gelilaintenationalseminary

Youtube: https://youtube.com/@gelilainternationalseminary...

Tiktok፡ gelilaseminary ​
ይጎብኙ
የእንግሊዝ #ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ከአሁን በኋላ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ስም አልጠቀምም እያለች ነው።

ይልቅ ማህበር #ወይም ጉባኤ የሚሉ ምትክ ቃላቶችን ለመጠቀም መወሰኗ ተገልጿል። ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው ቤተ ክርስቲያኗ ባደረገችው የስነ መለኮት ጥናት መሰረት የሚመጡ ሰዎችን #ቁጥር ለመጨመር መሆኑ ተገልጿል።

ጥናቱን ከተካሄደባቸው የአስተዳደር ክፍፍሎች መካከል ስድስቱ የአምልኮ ስፍራ፣ ሰባቱ ማህበረሰብ እንዲሁም #ሁለቱ ደግሞ ጉባኤ በሚለውን ስያሜ እንደሚመርጡ አሳውቀዋል።

ባለፉት 10 ዓመታት #ብቻ የቸርች ኦፍ ኢንግላንድ 900 አዳዲስ ቤተ ክርስቲያናትን የተከለች ሲሆን አንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን የሚለው ስም አይጠቀሙም።

#FoxNews እንዳስነበበው አዳዲሶቹም ይሁኑ የቀደሙቱ ማህበር ወይም ማህበረሰብ የሚለውን ስም ሲጠቀሙ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ማለት ምንድነው የሚለውን ጥያቄ መልስ በእንጥልጥል ያስቀረዋል።

የቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ግን ይሄንን አሉባልታ ወሬ ስትል አጣጥላዋለች። ምናልባም የተገኙ ውጤቶች ባይካዱም ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ #አንድ አንድ የወጣቶች ፕሮግራሞችና አንድ አንድ ደብሮች የተለመደ መሆኑን ብቻ ገልጸዋል።

ሌሎች ኢንግሊዛውያን ቀሳቅስትና ጸሃፊዎች፣ ቤተ ክርስቲያኗ በአለም ተቀባይነት ለማግኘት የወሰነችውን ውሳኔ፣ የተሳሳተ ብለውታል።

#እኛ ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል 16፣18 ምን ተደርጎ ነው፣ ማህበር/ጉባኤ በሚል የሚተካው ስንል እንጠይቃለን።

#እናንተም ሃሳባችሁን አካፍሉን!!
በአገራችን #ታሪክ በህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት፣ ጥገና እና አገልግሎት አሰጣጥ መስክ በቁጥር #አንድ ደረጃ በግንባር ቀደምነት አስተዋጽዖ ያበረከቱት (ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ)
በዘርፉ የተለያዩ ኩባንያዎች ያቋቋሙት

በደርግ ዘመን ለቀበሌም ለቤተክርስቲያንም በረከት በመሆን የተሸለሙ #እና ቤተክርስቲያን እንዳትዘጋ መሣሪያ የሆኑ

በኑሮአቸው በቃላቸው እና በሃብታቸው ጌታቸውን በማገልገል ከቤተሰባቸው ጋር እውነተኛ የደቀመዝሙርነት ሕይወትን በብዙ ትጋት ያሳዩት የመርጋ ሰርቤሳ ታሪክ መጽሐፍ ዝግጅት ተጠናቆ እነሆ መስከረም 4 ቀን በአቃቂ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ይመረቃል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።