The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሁሉም #ሊያነበው #የሚገባ #አስቸኳይ #መልዕክት
#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..

ለ5 #ሰከንድ #ኦክሲጅን ከአለም ላይ ቢጠፋ ምን ይፈጠራል?

ግራቪቲ (የመሬት ስበት) ለ5ሰከንድ ከመሬት ላይ ቢጠፋስ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? እኛ ሰዎች ምንድነው የምንሆነው?

ምናልባት ደግሞ #አሁን ያለውን የመሬት ስበት እጥፍ ቢሆን ምን ይፈጠራል?

ሌላኛው ለሰው ልጆች #ሁሉ ጠቃሚ የሆነችው ጸሃይ ድንገት ብትጠፋ ... ቀጥሎ የምድራችን እና #የሰው #ልጆች እጣ ፈንታ ምንድነው? በነገራችን ላይ ይህን #ሁሉ ለ5 ሰከንድ #ብቻ ነው።

እነዚህን ጥያቄዎች የሞኝ ጥያቄዎች ይመስላሉ?

#እኔም ለመጀመሪያ #ጊዜ ስሰማቸው እንደዛ ነው ያሰብኩት ነገር ግን #እጅግ መሰረታዊ እንደሆነ የተመለከትኩበትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ።

ከጥቂት ቀናት በፊት TechTalk With Solomon በተሰኘ ፕሮግራም #EBS #ቴሌቪዥን ላይ ማለት ነው። ሰለሞን እነዚህ ጥያቄዎች እየጠየቀ ነበር።

ከጥያቄዎች በሻገር ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ምናባዊ ምልከታ በሳይንስ አስደግፎ በ2 ተከታታይ ክፍሎች ለተመልካች አቅርቦታል። ለማንኛውም እኔ ያንን ፕሮግራም ስሰማው እጅግ እየዘገነነኝ እና እየተሳቀኩኝ ነበር።

በኋላ #ላይ #ግን ቆም ብዬ ሳስበው እንደዚህ አይነት ፕሮግርሞች ሊበረታቱ የሚገቡ እንደሆነ ገባኝ።

ምክንያቱም እሱ የሚዘረዝራቸው በሙሉ ለ5 ሰከንድ ቢፈጠሩ ምድራችን ላይ የሚፈጠሩት እጅግ ዘግናኝ እልቂቶች እና ነገሮችን ለማስቀረት የሚያስችል አንዳችም ቴክኖሎጂ እስካሁን #በሰው #ልጆች አልተፈጠሩም።

ይህንን ሳስብ እኛ የምናመልከት አምላክ እንዴት #ድንቅ እንደሆነ እና ምድርን #በቃሉ አጽንቶ እና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ያለ አንዳች መፋለስ #ሁሉም ነገር ስረዓታቸው ይዘው እንደሚሄዱ ሳሰብ ደነቀኝ።

ምድር ትንሽ ከሚባሉት ፕላኔቶች መካከል አንዷ ነች። ጸሃይ ደግሞ የምድርን 6ሚሊዮን አከባቢ እጥፍ የሆነች ከግዙፎቹ #መካከል ነች። ታዲያ የጸሃይ ብረሃን እንኳን በልካችን ተመጥኖ የሚደርሰን ለማሰብ የሚከብድ ምን አይነት ጥበብ ነው?

የሰው ልጅ ምናልባትም እየተማረ እና ብዙ እውቀቶችን እየሰበሰብ ሲሄድ ይበልጥ ወደ #አምላኩ እንደሚቀርብ አምናለሁ።

ለማንኛውም እኔ ከምጽፍላችሁ ይልቅ ፕሮግራሙን ገብታችሁ እንድትመለከቱት ሊንኩን አስቀምጬላችኋለሁ። https://www.youtube.com/watch?v=cqZU3b8NDB8&t=89s

#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..
የስኬታማ #ጋብቻ #ሚስጥር (ቀመር) #ምንድነዉ? 🤔

በአይነቱ #ልዩ የሆነ ለባለትዳሮች #ብቻ የተዘጋጀ #ድንቅ ፕሮግራም

በሳፋየር አዲስ #ሆቴል ከሐምሌ 24-28 ከምሽት 11:00 - 2:00 ሰዓት
ሐምሌ 29 ሙሉ ቀን

👉 በጥንዶች መካከል የሚፈጠሩ ተግዳሮቾችን የሚመክት ጋብቻን #እንዴት መገንባት ይቻላል።

👉 የጋብቻ #መሰረታዊ ተግዳሮት

👉 #ገንዘብ በጋብቻ ዉስጥ ያለዉ ድርሻ #ምን መምሰል አለበት?

👉 #ስራ እና ትዳርን በሚዛናዊነት መምራት

አዘናጅ :- ጎጆዬ የጋብቻ ሪፎርሜሽን ሴንተር ከCBMC ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር

#ይታደሙ
#ትዳሮን_ይስሩ!!

ለመመዝገብ እና ለበለጠ #መረጃ

0911136520
0911642595

ይደዉሉልን!!!

"ከስልጠናው የሚገኘው ትርፍ የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለሚያግዛቸው ችግረኛ ጥንዶች የሚውል ይሆናል፡፡"
#ሰው ሸሽቶ #ቤተክርስቲያን ሲገባ #እንዴት ይገደላል? አገዳደሉ አሳቃቂ ነው። ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ

የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት በዚህ ወረ በመካነኢየሱስ ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ #መጽሐፍ #ቅዱስ ግምባራቸው #ላይ ነበር የተገደሉት ምዕመናን ከአንድ #ቀን በኋላ ነው የተገኙት ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለው #እንደ ቤተክርስቲያን መረጃው እስኪጣራ ነው ይፋ ያላደረግነው ያሉ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካሄድ የቻልነውን ያህል ሄደናል ያሉ ሲሆን #መንግስት የሕዝብ የድህንነት #ጉዳይ በእጁ ነውና አሁንም #ተስፋ የምናደርገው መንግስት ገዳዮችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።

#ይህ ጥቃት በማን ነው የተፈጸመው ?

ከአደጋው የተረፉት ትክክለኛው ገዳዮች #ምን እንዳደረጉ እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ። #ነገር #ግን ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። መንግስት ግን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#እንዴት ልንሆን እንችላለን? #ነገ #ምን ይሆናል ?
ጊዜው የማይገቡን ነገሮች የሚነገሩበት ነው።

አለም የምትለው ሌላ ነው እኛ የምንለው ደግሞ #እግዚአብሔር አለልን ነው።

ጠዋትና #ማታ በሚዲያ የምንሰማው #አለም በብዙ ፍረሃት #ውስጥ ያለችበት #ጊዜ ነው።

#እምነት ሁኔታን መካድ አይደለም ከሁኔታ በላይ የሆነውን #አምላክ ከፍ ማድረግ ነው።

ምንዛሬ ከፍ አለ ዝቅ አለ። ኑሮ ተወደደ እረከሰ ስለዘመኑ የሚወራው አብዛኛው አይገባንም።

#እኔ ግን እንዲህ እላችኋለው ለእግዚአብሔር ዘመን ከፍ አይልም ዝቅ አይልም። ኑሮ ስለረከሰ አልኖርንም ኑሮ ስለተወደደ አንጠፋም።

በሰው ካልኩሌሽን አልኖርንም አሁንም አንኖርም። ምንም እንኳን ምድረበዳ ቢሆን #ኢየሱስ አለ።

ዘመኑ አስጨናቂ ነው ? እውነት ነው ግን ኢየሱስ አለ።