The Christian News
5.37K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አዲስ #ዜና

የካናዳ ፍርድ #ቤት አብያተ ክርስቲያናት ላይ የኮቪድ ወቅት እግድን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።

#ፍርድ ቤቱ የካናዳ #ሁለት ግዛቶች #ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በበረታበት ወቅት በአካል መሰብሰብን አግዶ በነበረበት ወቅት በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው ጉዳዩን አልመለከተውም ያለው።

በወቅቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በካናዳ #መንግስት የተወሰነውን በአካል ተገናኝቶ የማምለክ እገዳን ተላልፈው ሲሰበሰቡ ነበር ተብሏል።

ዘ ቸርች ኦፍ ጋድስ የተሰኘችው ቤተ ክርስቲያኗ ይሄንንም በመተላልፏ 240ሺህ ዶላር ቅጣት በግዛቷ ፍርድ ቤት ተጥሎባታል።

በኦንታሪዮ የምትገኘው የቸርች ኦፍ ጋድ መሪዎች በበኩላቸው ይሄ የፍርድ ቤት ውሳኔ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብለውታል።
በሃገሪቱ የፍትህና ነጻነት ታሪክም አሳዛኝ #ቀን ነው ብለውታል።

ሬስቶራንቶችና ስፖርት ቤቶች፣ መክፈት በተፈቀደበት #ጊዜ #ቤተክርስቲያን እንዲዘጋና አቤቱታን አላስተናግድም ማለታቸው የእምነትን ነጻነት የሚጋፋ ነው ብለውታል።

እኛ ሰውን ሰምተን ሳይሆን #እግዚአብሔርን ነው የምንታዘዘው በማለት በወቅቱ በሮቻቸውን ሳይዘጉ የአምልኮ መርሃ ግብሮቻቸውን ሲያካሂዱ እንደነበረ ገልጸዋል።
#ዛሬ በአለም በስደት #ላይ ለሚገኙ #ቤተክርስቲያን ፅሎት የሚደረግበት አለም አቀፍ የፀሎት #ቀን ነዉ። 🙏🙏

በዓለም ዙሪያ ከ7 ክርስቲያኖች አንዱ ማለትም በአፍሪካ ካሉት ከ5 አማኞች አንዱ፣  በእስያ ከሚገኙ 5 ክርስቲያኖች 2ቱ እና በላቲን አሜሪካ ካሉት 15 ሰዎች መካከል አንዱ በእምነታቸው ምክንያት በእጅጉ ይሠቃያሉ።
#ሰው ሸሽቶ #ቤተክርስቲያን ሲገባ #እንዴት ይገደላል? አገዳደሉ አሳቃቂ ነው። ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ

የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት በዚህ ወረ በመካነኢየሱስ ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ #መጽሐፍ #ቅዱስ ግምባራቸው #ላይ ነበር የተገደሉት ምዕመናን ከአንድ #ቀን በኋላ ነው የተገኙት ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለው #እንደ ቤተክርስቲያን መረጃው እስኪጣራ ነው ይፋ ያላደረግነው ያሉ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካሄድ የቻልነውን ያህል ሄደናል ያሉ ሲሆን #መንግስት የሕዝብ የድህንነት #ጉዳይ በእጁ ነውና አሁንም #ተስፋ የምናደርገው መንግስት ገዳዮችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።

#ይህ ጥቃት በማን ነው የተፈጸመው ?

ከአደጋው የተረፉት ትክክለኛው ገዳዮች #ምን እንዳደረጉ እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ። #ነገር #ግን ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። መንግስት ግን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።
#የሀገር ባለውለታው 😢😢😢 #ሽኝት

#አቶ ለማ ለዕመንጎ ባደረባቸው ህመም በሚኖሩበት አሜሪካን #ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ኅዳር 20 #ቀን 2016 ዓ.ም. ከዚህ #ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የአቶ ለማ አስክሬን #ዛሬ ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከማለዳው 1፡00 ሰዓት #ወደ #ሀገር #ቤት የገባ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ የሽኝት ፕሮግራም ሳር ቤት በሚገኝው ዘጸአት #ቤተክርስቲያን እንዲሁም የቀብር ሥነ-ሥርዓት በ9፡00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ የቀብር ይፈጸማል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለመላው ቤተሰቦቻቸው #እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እየተመኘን።

በዘጸዓት ቤተክርስቲያን የሚከነወነውን የአቶ ለማ ለዕመንጎ አንሼቦ የሽኝት መረሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት ከደቂቃዎች በኋላ በፌስ ቡክ እና በዮቲዩብ ገጻችን በቀጥታ ስርጭት #livestreaming የምናስተላልፍ ይሆናል። #ይከታተሉን

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#እንኳን #አደረሳችሁ

በታላት ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የነቀምቴ ማህበረ ምዕመናን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድምቀት ተካሄደ።

ማህበረ ምዕመኑ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየው 100ኛው ዓመት የምስረታ #እና የአገልግሎት ቆይታን የሚዘክረው ክቡረ በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር፣ ማህበረ ምዕመኑ ስድስት ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ባስገነባው አዲሱ የአምላክ አዳራሽ ተካሂዷል።

ከማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ #አንድ #ቀን አስቀድሞ የማህበሩ ምዕመናን በነቀምቄ #ከተማ በነቂስ በመውጣት የከተማ ፅዳት እና የጎዳና #ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በዓሉንም ለመካፈል ከመላው #ኢትዮጵያ በርካታ እንግዶች፣ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የማኅበረ ምዕመኑ #ልጆች እና ማህበረ ምዕመኗን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሚሲዮናዊያን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የማህበረ ምዕመኑን የ100 ዓመታት አገልግሎት የዳሰሰ #መጽሐፍ ተመርቋል።

በዓሉም በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ ለማህበረ ምዕመኗ አባላት እና ለመላዉ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጨመ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ።

በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገደሉ።

ቡርኪና ፋሶ #ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ #ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

#እሁድ #ቀን በቡርኪና ፋሶ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ምዕመናን ተገድለዋል።

ኢሳካኔ በተባለው ስፍራ ለእሁድ ጸሎት ሥነ ሥርዓት በተሰባሰቡት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ተጠርጣሪ ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ አንድ የቤተ ክርስቲያኗ ባለሥልጣን ከሰዋል።

በመስጂድ እና በቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ዕለት የተፈጸመው ጥቃት ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው በይፋ የታወቀ ነገር ባይኖርም አንድ የቡርኪና ፋሶ የግል ጋዜጣ ጥቃቶቹ የተቀነባበሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት እና መሪዎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እምብዛም ያልተለመደ አይደለም ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ከሰሜናዊቷ ጂቦ ከተማ ከአምስት #ዓመት በፊት ተጠልፈው የተወሰዱ #አንድ ቄስ አስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። ከሦስት ዓመት በፊት ደግሞ ከዚያው ከተማ በታጣቂዎች የተጠለፉ አንድ ኢማም ከቀናት በኋላ ሞተው ተገኝተዋል። ዘገባው የBBC ነው።
#ደረሰ #ደረሰ #አሁኑኑ ይመዝገቡ !!!

#እያደገ #ሄደ ... ለምዝገባ የቀረን #4 #ቀን እና ጥቂት ቦታ ብቻ ነው። አሁኑኑ ይመዝገቡ

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

#ማሳሰቢያ :- ያለ ምዝገባ መግባት አይቻልም። ስለዚህ ፈጥነዉ በቀሩን #ጥቂት ቦታዎች በተቀመጡት የስልክ እና link አድራሻዎች በመጠቀም ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk

#ወይም ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
#አንድ ቀን #ብቻ ቀረዉ..

#አሁኑኑ ይመዝገቡ !!!

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር።

#እያደገ #ሄደ ...ምዝገባ ሊጠናቀቅ የቀረን #1 #ቀን ብቻ ነው።

#ማሳሰቢያ :- ያለ ምዝገባ መግባት አይቻልም።

ስለዚህ ፈጥነዉ በቀሩን #ጥቂት ቦታዎች በተቀመጡት የስልክ እና link አድራሻዎች በመጠቀም ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk

#ወይም  ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
♦️ በቅርብ ቀን♦️

"የአማኝ ህይወት" በሚል ርእሰ የተፃፈ ድንቅ መፅሐፍ ወጣት አገልጋይ ካሌብ ይዞልን እየመጣ ሲሆን

በቅርብ #ቀን በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
#አዲስ መጽሐፍ #በቅርብ #ቀን...

ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተ #ድንቅ የአማርኛ መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በዘላለም መንግስቱ ተዘጋጅቶ በቅርብ ቀን ወደ አንባቢያን ይደርሳል።

23 ዓመታት የፈጀው #ይህ #ድንቅ መጽሀፍ በቅርብ ቀን በአዲስ አበባ ሰኔ 15 2016 በኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ (ETC) የምስጋና ጊዜ ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት በድምቀት ይመረቃል።