The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ወንጌላውያን #ክርስቲያኖች #በያቤሎ ቦረና በሚገኘው #ኮረብታ ላይ እንዲያመልኩ #ያስገደዳቸው ምንድን #ነው?

በቦረና ያቤሎ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ኮረብታ ስፍራ ላይ የሚሰግዱ ሰዎች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሲንሸራሸሩ ታይተዋል። የኮረብታው ስም 'ገርቢ ጎጥ' ይባላል።

በኮረብታው ስፍራ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጸልዩ እና ሲዘምሩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ለብዙ ጊዜ በማህበራዊ አውታረ መረቦች ላይ ተሰራጭተዋል።

ቪዲዮው ህጻናት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ሳይቀሩ ለአምልኮ ተራራ ላይ ሲሰበሰቡ ያሳያል። እነዚህ ሰዎች በበጋ ጸሀይ ውስጥ ቆመው ይሰግዳሉ, በክረምት ደግሞ በዝናብ።

የእነዚህ ሰዎች ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨት ከጀመረ በኋላም ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ሙሉ የቪዲዮውን ዝርዝር ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=PTuislRsHeM
#ታላቁ #የወንጌል ..
#ሰላም #ውድ #ቤተሰቦቻችን ከሰሞኑ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ የመጽሐፍ #ቅዱስ ሳምንትን እያከበረች በክብረ በዓሉ የወንጌል አርበኛውን ኦኒስሞስ ነሲብን አስባለች።

ለመሆኑ እኚህ የወንጌል አርበኛ #ማን ናቸው? #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ያበረከቱት አስተዋጾስ ምን ይመስላል? የሚለውን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ።

የክርስትና ስማቸው "ኦነሲሞስ" የሚባል ሲሆን የትውልድ ስማቸው #ግን "ሂካ አዋጅ" የሚባል ሲሆን የተወለዱት በ1856ዓ.ም በቀድሞ የኢሊባቦር #ክፍለ #ሀገር በሁሩም የምትገኝ #ልዩ ስሟ ኦጊ በመባል የምትጠራ መንደር #ነው

ኦነሲሞስ ገና በለጋነቱ በባርነት ከተሸጠ በኋላ ሙዚየንገር የተባለ የፈረንሳይ ቆንጺላ ነሻ አውጥቶት በአከባቢው የነበሩ የስዊድን ሚሲዮኖች እንዲያሳድጓቸው በአደራ እንደ ሰጣቸው በታሪክ ተመዝግቧል።

ኦነሲሞስ ኢርትራ በትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት #የክርስቶስ #ወንጌል ተመስክሮላቸው ጌታን ከተቀበሉ በኋላ ተጠምቀው #ኦነሲሞስ የሚል የክርስትና ስማቸውን ተቀበሉ።

ኦነሲሞስ ልዩ #ስጦታ እና #ክህሎት ያላቸው ስለነበሩ ይህንን አይተው ለትምህርት #ወደ ሲውድን ተላኩ በወቅቱ እድሜያቸው #20 ነበር ስዊድን ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ የኦሮሞ (ኤክስጼዲሽን) የወንጌል ጉዞ ቡድን አባል እና መሪ በመሆን ለ3 #ጊዜ የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ #ጉዞ በኋላ #መጽሐፍ #ቅዱስን ወደ #ኦሮምኛ የመተርጎም ስራቸውን እንደ ጀመሩ አረን የተባለ ጸሐፊ ዘግቦታል።

የኦሮምኛ መጽሐፍ #ቅዱስ ተርጓሚ እና የወንጌል አርበኛ የሆኑትን ኦነሲሞስ ነሲብ ታሪክን ከብዙ በጥቂቱ ቤተክርስቲያኒቱ በ2014ዓ.ም የመጸሐፍ ቅዱስ ቀንን በማስመልከት ለሳቸው በተዘጋጀው የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከቀረበው #ጽሁፍ በዚህ መልክ ቀንጭበን አቀረብንላችሁ።
#ሁሉም #ሊያነበው #የሚገባ #አስቸኳይ #መልዕክት
#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..

ለ5 #ሰከንድ #ኦክሲጅን ከአለም ላይ ቢጠፋ ምን ይፈጠራል?

ግራቪቲ (የመሬት ስበት) ለ5ሰከንድ ከመሬት ላይ ቢጠፋስ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? እኛ ሰዎች ምንድነው የምንሆነው?

ምናልባት ደግሞ #አሁን ያለውን የመሬት ስበት እጥፍ ቢሆን ምን ይፈጠራል?

ሌላኛው ለሰው ልጆች #ሁሉ ጠቃሚ የሆነችው ጸሃይ ድንገት ብትጠፋ ... ቀጥሎ የምድራችን እና #የሰው #ልጆች እጣ ፈንታ ምንድነው? በነገራችን ላይ ይህን #ሁሉ ለ5 ሰከንድ #ብቻ ነው

እነዚህን ጥያቄዎች የሞኝ ጥያቄዎች ይመስላሉ?

#እኔም ለመጀመሪያ #ጊዜ ስሰማቸው እንደዛ ነው ያሰብኩት ነገር ግን #እጅግ መሰረታዊ እንደሆነ የተመለከትኩበትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ።

ከጥቂት ቀናት በፊት TechTalk With Solomon በተሰኘ ፕሮግራም #EBS #ቴሌቪዥን ላይ ማለት ነው። ሰለሞን እነዚህ ጥያቄዎች እየጠየቀ ነበር።

ከጥያቄዎች በሻገር ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ምናባዊ ምልከታ በሳይንስ አስደግፎ በ2 ተከታታይ ክፍሎች ለተመልካች አቅርቦታል። ለማንኛውም እኔ ያንን ፕሮግራም ስሰማው እጅግ እየዘገነነኝ እና እየተሳቀኩኝ ነበር።

በኋላ #ላይ #ግን ቆም ብዬ ሳስበው እንደዚህ አይነት ፕሮግርሞች ሊበረታቱ የሚገቡ እንደሆነ ገባኝ።

ምክንያቱም እሱ የሚዘረዝራቸው በሙሉ ለ5 ሰከንድ ቢፈጠሩ ምድራችን ላይ የሚፈጠሩት እጅግ ዘግናኝ እልቂቶች እና ነገሮችን ለማስቀረት የሚያስችል አንዳችም ቴክኖሎጂ እስካሁን #በሰው #ልጆች አልተፈጠሩም።

ይህንን ሳስብ እኛ የምናመልከት አምላክ እንዴት #ድንቅ እንደሆነ እና ምድርን #በቃሉ አጽንቶ እና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ያለ አንዳች መፋለስ #ሁሉም ነገር ስረዓታቸው ይዘው እንደሚሄዱ ሳሰብ ደነቀኝ።

ምድር ትንሽ ከሚባሉት ፕላኔቶች መካከል አንዷ ነች። ጸሃይ ደግሞ የምድርን 6ሚሊዮን አከባቢ እጥፍ የሆነች ከግዙፎቹ #መካከል ነች። ታዲያ የጸሃይ ብረሃን እንኳን በልካችን ተመጥኖ የሚደርሰን ለማሰብ የሚከብድ ምን አይነት ጥበብ ነው?

የሰው ልጅ ምናልባትም እየተማረ እና ብዙ እውቀቶችን እየሰበሰብ ሲሄድ ይበልጥ ወደ #አምላኩ እንደሚቀርብ አምናለሁ።

ለማንኛውም እኔ ከምጽፍላችሁ ይልቅ ፕሮግራሙን ገብታችሁ እንድትመለከቱት ሊንኩን አስቀምጬላችኋለሁ። https://www.youtube.com/watch?v=cqZU3b8NDB8&t=89s

#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..
በመዲናችን #አዲስ አበባ እጅግ ብዙ #ወንጌል የተሰራ ብዙዎች በወንጌል የተደረሱ ይመስላችኋል?

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተለይም #መገናኛ#ሜክሲኮ#ፒያሳ#ጀሞ#አያት እና ሌሎች አከባቢዎችን ስንመለከት ከተማዋ በወንጌል የተጥለቀለቀች ይመስላል።

#ነገር #ግን ይመስላል #ነው #እንጂ እውነታው #እጅግ ከዚህ የራቀ እንደሆነ በቅርብ #ጊዜ በአንድ መድረክ አስደንጋጭ ሪፖርት ወጥቷል።

#ከተማ ተኮር የወንጌል አገልግሎት በሚል በቀጠና #ሙሉ ወንጌል አጥቢያ #ቤተክርስቲያን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ነበር።

ታዲያ #ይህ ጥናት ሲቀርብ ከ700 በላይ የሆኑ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መጋቢዎች #እና አገልግዮች በቦታው ተገኝተው ነበር።

ጥናቱ #ኢትዮጵያ #ውስጥ የሚገኙ ተለቅ ተለቅ ያሉ 11 ከተሞችን የሚዳስስ የነበረ ቢሆንም እኛ ግን ለጊዜዉ የመዲናችንን አዲስ አበባ #ብቻ የተወሰነ እንበል።

ይህም ጥናት አዲስ አበባ ላይ በወንጌል የተደረሰው ሕዝብ 6 በመቶ ብቻ እንደሆነ ያሳያል።

ይህም በወንጌል ካልተደረሱ የአለማችን ከተሞች መካከል አንዷ አዲስ አበባ እንድትሆን አድርጓታል።

#እንደ ጥናቱ ከሆነ የአዲስ አበባ ከተማ እድገት እጅግ ፈጣን እና ከሌሎች የአለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪነት ባለው መልኩ በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል ነገር ግን ይህቺን ከተማ መድረስ በሚችል መልኩ አገልጋዮቻችን ግን ለዚህ ዝግጁ እንዳልሆኑ ጠቁመዋል።

ይህንን ለመድረስ እጅግ ቅንጅት የሚፈልግ ቢሆንም በከተማችን የሚገኙ አገልጋዮች ግን ወደዚህ መስመር ለመግባት ገና ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል።

ምናልባት ይህንን ለመቅረፍ የቤት ስራ ተወስዶ በየአመቱ ለመሰብሰብ እና ለመነጋገር ቀጠሮ ቢያዝም ውጤቱን ግን ለወደፊት የምናየው ይሆናል።
#አዲስ #ዜና

የሐዋሳ ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታል ከህይወት #ብርሃን #ቤተክርስቲያን #ጋር በመተባበር በኮምፓሽን #ኢንተርናሽናል ድርጅት በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ህጻናት #ሙሉ የጤና ምርመራ ተደረገላቸው።

ለህጻናቱ ሙሉ ምርመራ በነጻ ያደረገው የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው

የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ቡድን (Family Health Team) ከሆስፒታሉ MCC ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ለEP 706 ህጻናት ልማት ኘሮጀክት አጠቃላይ የጤና ምርመራ ህክምና ያደረገው።

#ፓስተር ጌቱ አያሌው የሐዋሳ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መጋቢ በከተማችን ካሉ የደሀ ደሀ ህጻናት መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የቀለብና ሌሎችም ድጋፍ የሚደረግላቸው ህጻናት መኖራቸውን ገልጸዋል።

በህጻናት ላይ መንግስት፣ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት፣ ባለሀብቶች፣ እና ሌሎችም በመተባበር ከሰራን ከፍተኛ የሰው ሀይል በማፍራት እናተርፋለን ሀገርም ትባረካለች ብለዋል።

የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ አቶ ይርዳቸው አናቶ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን እና ኮምፓሽን ከሚረዱ ህጻናት ውስጥ ዛሬ ለ3 መቶ 26 ህጻናት መሉ የጤና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ይህንን መሰል ተግባር ቤት ለቤት የጤና ህክምና በሚሰጡ ባለሙያዎች እየተተገበረ ስለመሆኑ ያስረዱት አቶ ይርዳቸው ምርመራው የህጻናቱን እድገት ክትትል የሚያደርግ #ነው ብለዋል።

በጤና ማዕከል ሄደው መታከም ለማይችሉ ህጻናት ነጻ ምርመራ መደረጉን የገለጹት አቶ ይርዳቸው ሆስፒታሉ ሙሉ ቁሳቁስ ይዞ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ግቢ በመገኘት የበጎ ፍቃድ ስራውን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ሳምራዊት ተፈራ በሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው።

ለእነዚህ ህጻናት የጤና ምርመራ እንዲደረግ በቀረበ ጥሪ መሰረት ተግባራዊ እያደረጉ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በዚህም የህጻናቱ እድገት፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ኤችአይቪ፣ የመሳሰሉት ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑንም አክለዋል።
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው
“ካሁን በኋላ #ሴት #ነኝ የሚሉ ወንዶችን አናስተምርም” ኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ

በአሜሪካ የሚገኘው እውቁ የኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ያስተላለፈውን ውሳኔ ቀለበሰ። በአሜሪካ ኢንድያና ግዛት የሚገኘው የቅድስት #ማርያም ኖተርዳም የሴቶች ስነ መለኮት ኮሌጅ #ነው #ወደ ቀድሞው አቋሜ ተመልሻለው ያለው።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት #እና የቦርድ ሰብሳቢ በጋራ በመሆን “ወደ ካቶሊካዊት እሴታችን ተመልሰናል” ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል።

ከወር በፊት ሴት ሆነው ተፈጥረው #ወንድ ነኝ ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ኮሌጁ እቀበላለው ብሎ ነበረ። ኮሌጁ በውሳኔው ምክኒያት ትችቶች ተዘንዝረውበታል።

የኮሌጁ ቦርድ እና መሪዎች #ምንም #እንኳን በተለዋዋጭ አለም #ውስጥ ብንኖርም፣ የቤተ ክርስቲያንን አቋም ሳንቀያይር እናስቀጥላለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ውሳኔው #ግን በኮሌጁ ተማሪዎች እና መምህራን ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ይሄንን አይነት ምላሽ ከኮሌጃችን ማህበረሰብ ባንጠብቅም፣ ካቶሊካዊ ማንነታችንን ግን አስጠብቀን መሄድ አለብን ሲሉ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ባለፈው #ወር በወሰንነው ውሳኔ በኮሌጃችን ህብረትን የሚያመጣ መስሎን ነበረ፣ #ነገር ግን ልዩነትን ፈጥረናል፣ ለዚህም #ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።