The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ለሙሉ #ጊዜ አገልጋዮች ሲሰጥ የቆየው #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ተጠናቀቀ።

“Biblical Education By Extension (BEE World)” እና በዳላስ ያለችው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በአጋርነት ሲያሠለጥኗቸው የነበሩትን ዐሥራ ሰባት የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመረቁ።

ሥልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ቤተ እምነት ለመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሲሆን፣ ሠልጣኞቹ በአገልግሎት ስፍራቸው ሳሉ አገልግሎታቸውን በተሻለ መልኩ ማካሄድ እንዲችሉ የሚያስችሏቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሥነ መለኮታዊ ኮርሶች እንዲያገኙ የሚያስችሏቸው ናቸው ተብሏል።

ሥልጠናው ላለፉት ሦስት ዓመታት በአዳማ #ከተማ ሲሰጥ የቈየ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ወደ አካባቢያቸው በመሄድ በዐሥራ ስድስት ቡድኖች ውስጥ ያሉ 256 ተማርዎችን በማሠልጠን ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

“BEE World” መቀመጫውን በአሜሪካን አገር ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላሉና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ላላገኙ አገልጋዮች በፓስቶራል ሚኒስትሪ ዲፕሎማ፣ በቲዮሎጂና ቸርች ሊደርሺፕ አሶሺዬት ዲግሪ እንዲሁም በቲዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

#የኢትዮጵያ #ወንጌላውያን #ቤተክርስቲያን በዳላስ ከBEE World ጋር በአጋርነት ሲሰጡ የቆዩት ሥልጠና፣ በቀጣይነት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከአካባቢው የሚመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በሠልጠናው ተካፋይ እንደሚሆኑ ለሕንጸት የተደረሰው መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ @Hintset Christian Society- ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር
#አዲስ #ዜና

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ የልማት እና መሀበራዊ አገልግሎት ኮምሽን ከ99.5 #ሚሊዮን #ብር በላይ በሆነ በጀት #ወደ ስራ የሚገቡ አራት ፕሮጀክቶችን የማስጀመሪያ መርሃግብር በመቀሌ #ከተማ ደስታ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሄደ።

ፕሮጀክቶቹም የምግብ ዋስትናን፣ የኑሮ ማገገሚያ፣ የውሃ ንፅህና እና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የታቀዱ ናቸው።
#አዲስ #ዜና

በመጽሃፍ #ቅዱስ በግብረሰዶም ልምምዷ ምክኒያት የጠፋችው ሰዶም #ከተማ ቅሪቶች ተገኙ።

አሜሪካዊያን የአርኪዮሎጂ ተመራማሪዎች በጆርዳን ባካሄዱት የረጅም አመታት ምርምር በእሳት የጠፋችውን ከተማ ቅሪት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

በግኝቱ አቅራቢያ በእሳት ጉዳት የደረሰባቸው የሸክላ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ግኝቱ በመጽሃፍ ቅዱስ ሰዶም ከተማ ትገኝበታለች በተባለው አካባቢ መገኘቱ ተጨማሪ ማረጋገጫ ሆኗል። ቢያንስ 25 የሸክላ እቃዎች በአካባቢው ተገኝተዋል። ቅሪቱ የተገኘውም በመጽሃፍ ቅዱስ ከተጠቀሰው ስፍራ ጋር ተመሳሳይ ነው።

የተገኙት የሸክላ እቃዎች እድሜያቸው የነሃስ ዘመን (Bronze Age) ጊዜ የነበሩ መሆናቸውም #ሰዶም በእሳት ከወደመችበት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ያደርገዋል።

በአሁኑ ወቅት ታል ኤል ሃማም በሚባልበት የጆርዳን አካባቢ የተገኘው ቅሪት ተመራማሪዎቹ እሳቱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ልክ በሁለተኛ የአለም ጦርነት ወቅት የተደረጉ የኒውክለር ቦምብ ጉዳቶች ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ገልጸዋል።

ውድ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ከሰሞኑ በሃገራን መጤ ባህል የሆነው እና እንደ ክርስትና ምንም ተቀባይነት የሌለው የግብረሰዶም እንቅስቃሴን የክርቲያን ዜና እጅግ የሚያወግዘው ጸያፍ ተግባር እንደሆነ እየገለጽን በዚህ ዙሪያ ከዚህ ቀደም የሰራናቸውን የተለያዩ ዘገባዎች እና ትንታኔዎች የምናደርሳችሁ ይሆናል።
በመዲናችን #አዲስ አበባ እጅግ ብዙ #ወንጌል የተሰራ ብዙዎች በወንጌል የተደረሱ ይመስላችኋል?

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተለይም #መገናኛ#ሜክሲኮ#ፒያሳ#ጀሞ#አያት እና ሌሎች አከባቢዎችን ስንመለከት ከተማዋ በወንጌል የተጥለቀለቀች ይመስላል።

#ነገር #ግን ይመስላል #ነው #እንጂ እውነታው #እጅግ ከዚህ የራቀ እንደሆነ በቅርብ #ጊዜ በአንድ መድረክ አስደንጋጭ ሪፖርት ወጥቷል።

#ከተማ ተኮር የወንጌል አገልግሎት በሚል በቀጠና #ሙሉ ወንጌል አጥቢያ #ቤተክርስቲያን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ነበር።

ታዲያ #ይህ ጥናት ሲቀርብ ከ700 በላይ የሆኑ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መጋቢዎች #እና አገልግዮች በቦታው ተገኝተው ነበር።

ጥናቱ #ኢትዮጵያ #ውስጥ የሚገኙ ተለቅ ተለቅ ያሉ 11 ከተሞችን የሚዳስስ የነበረ ቢሆንም እኛ ግን ለጊዜዉ የመዲናችንን አዲስ አበባ #ብቻ የተወሰነ እንበል።

ይህም ጥናት አዲስ አበባ ላይ በወንጌል የተደረሰው ሕዝብ 6 በመቶ ብቻ እንደሆነ ያሳያል።

ይህም በወንጌል ካልተደረሱ የአለማችን ከተሞች መካከል አንዷ አዲስ አበባ እንድትሆን አድርጓታል።

#እንደ ጥናቱ ከሆነ የአዲስ አበባ ከተማ እድገት እጅግ ፈጣን እና ከሌሎች የአለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪነት ባለው መልኩ በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል ነገር ግን ይህቺን ከተማ መድረስ በሚችል መልኩ አገልጋዮቻችን ግን ለዚህ ዝግጁ እንዳልሆኑ ጠቁመዋል።

ይህንን ለመድረስ እጅግ ቅንጅት የሚፈልግ ቢሆንም በከተማችን የሚገኙ አገልጋዮች ግን ወደዚህ መስመር ለመግባት ገና ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል።

ምናልባት ይህንን ለመቅረፍ የቤት ስራ ተወስዶ በየአመቱ ለመሰብሰብ እና ለመነጋገር ቀጠሮ ቢያዝም ውጤቱን ግን ለወደፊት የምናየው ይሆናል።
#ስላማችሁን #ጠብቁ መጋቢ ደሳለኝ አበበ

#Ethiopiaየመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ክፍል ከፖይሜን ሚኒስትሪ #ጋር በመተባበር #ሠላም_ለወጣቶች_ወጣቶች_ለሠላም በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም የሐገርቷ #ክፍል ከተውጣጡ የአሰልጣኞች ሥልጠና ለ41 #ወጣቶች #በኢትዮጵያ የሠላም ግንባታ ዙሪያ ሥልጠና እና ውይይት በቢሾፍቱ #ከተማ እያካሄዱ ይገኛል።

በመድረኩ የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ #ሠላማችሁን ጠብቁ በማለት ወጣቶቹን አበረታተዋል።

#ሠላም_ነጣቂ_እንጂ_ጠባቅ_አጥታላች ያሉት ፕሬዝዳንቱ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በበኩሏ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው የልዩነት ዘመቻ በተቃራኒ በመቆም ሁሉም ከጥላቻ ፣ ከወቃሽነትና ነቃሽነት ተራ ወጥቶ የሠላም ሰባኪ እንዲሆን በአጽንኦት ተናግሯል።

ውይይቱ #ነገ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#እንኳን #አደረሳችሁ

በታላት ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የነቀምቴ ማህበረ ምዕመናን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድምቀት ተካሄደ።

ማህበረ ምዕመኑ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየው 100ኛው ዓመት የምስረታ #እና የአገልግሎት ቆይታን የሚዘክረው ክቡረ በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር፣ ማህበረ ምዕመኑ ስድስት ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ባስገነባው አዲሱ የአምላክ አዳራሽ ተካሂዷል።

ከማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ #አንድ #ቀን አስቀድሞ የማህበሩ ምዕመናን በነቀምቄ #ከተማ በነቂስ በመውጣት የከተማ ፅዳት እና የጎዳና #ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በዓሉንም ለመካፈል ከመላው #ኢትዮጵያ በርካታ እንግዶች፣ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የማኅበረ ምዕመኑ #ልጆች እና ማህበረ ምዕመኗን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሚሲዮናዊያን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የማህበረ ምዕመኑን የ100 ዓመታት አገልግሎት የዳሰሰ #መጽሐፍ ተመርቋል።

በዓሉም በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ ለማህበረ ምዕመኗ አባላት እና ለመላዉ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።
የወልቂጤ #ከተማ ወንጌላውያን አማኞች የትንሳኤ በአልን በህብረት አደባባይ ላይ አከበሩ።

ምዕመኑ በአብሮነት ለሰላምና ለአንድነት መስራት ይጠበቅበታልም ተብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ሰብሳቢ መጋቤ ብርሃኑ አቅነዳ የበአሉ አከባበርን አስመልክተው እንዳሉት የእምነቱ ተከታዮች በአንድነት እንዲያከብሩ መንግስት ማመቻቸቱ የሚያስደስትና እምነቱም ምእመን በጋራ እንዲያከብር የሚያዝ ነው ብለዋል።

#ህብረቱ በበአል ወቅትም ይሁን ከበአል ውጪ የተቸገሩ ወገኖችን ማገዝ ልምዱ ነው ያሉት መጋቤ ብርሃኑ የትንሳኤ በአል አክባሪዎች ይህን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው በዚህ ወቅት እንዳሉት ትንሳኤ ለህዝበ ክርስቲያኑ ታላቅ በአል ነው ብለዋል።

በዋናነት እምነቱ በሚያዘው መሰረት አብሮነትን በማጠናከር ለተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ እርስ በርስ ከሚሸረሽሩ ተግባሮች ከመታቀብ ባለፈ የ #ሰላም መጠበቅ በሚያጸና መልኩ ሊሆን እንደሚገባም ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን #ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ #አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ፈጣሪ ሁሉን በእኩል የሚያይና በእኩል የሚዳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የትንሳኤ በአል የደስታ በአል ነው ያሉት አቶ አለማየሁ የይሁዳ ፀፀት ቢዘጋም እርስ በርስ ዛሬም በሀገራችን አንዳንዶች በሰው #ደም የመነገድ ተግባር የሚፈፅሙ አሉ ብለው #ይህም ወንጀል መሆኑን መረዳትና ለሰላም መስራት ከምእመኑ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በአል አከባበሩ ላይ የተገኙት አካላትም በአሉን በአደባባይ በህብረት በማክበራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ላመቻቹ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በአሉ ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበትም ገልፀዋል።
#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ #ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ #ደቡብ #ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የልማት ኮሚሽን ፤ ኖሮዌ #ቤተክርስቲያን ተራዕዶ እና UN #women በጋር የሚተገብሩት Creating safe #city #and safe #public #space #project ጾታን መስረት ያደረገን ጥቃት ለመከላከል የሚስችል የግንዛቤ ማሳጨበጫ ፕሮግራም በሀዋሳ #ከተማ አካሄድ፡፡

በፕሮግራሙ #ላይ ከካቶሊክ ፤ ከወንጌል አማኞች #እና ከግሮት ኮሚሽን የተወጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ጾታዊ ጥቃት/በሴቶችና ልጃገረዶች የሚደርሰውን ጥቃት የሚፅየፍ ትወልድ መፍጠር የሚል አላማ የነበረው ፕሮግራም እንደሆነ ተገልጿል።

በፕሮግራሙ ከአቶቴ #እስከ ታቦር መካነ #ኢየሱስ ቤ/ክ ድረስ የእግር ጉዞ የተደረገ ሲሆን በጉዞ ወቅት ተሳታፊዎች የተለያዩ የጹሁፍና የድምፅ መልዕክቶችን በማሰማት በሴቶችንና ልጃገረዶች #ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡

በተጨማሪም በግሬት ኮሚሽንና በሪፍራል መካነየሱስ ወንድ ወጣቶች #መካከል የእግር ኩዋስ #ውድድር የተካሄድ ሲሆን የውድድሩ አላማ ወንዶች ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው።

ይህም ጥቃት የሚያደርስ ወንድ #ብቻ ሳይሆን የሚቃውም መሆኑን በማሳየት ተሳትፎቸውን ለመጨመር ነው፡፡