The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#update #ደም_በመለገስ_ወንጌልን_እሰራለሁ

በሚል መሪ ቃል ሰኔ 2/10/2011 ዓ.ም ማለትም እሁድ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በሀዋሳ ታቦር ህይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የደም ልገሳ ፕሮግራም ተከናውኗል።

ዜናውን ከወደዱት Like
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
ነፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል Share ያድረጉ

ተዓማኒነት እና ፈጣን የሆኑ መረጃዎች እንዲደርሶት በዩቲዩብ ፤ በፌስ ቡክ ፤ በቴሌግራም እና በቲዊተር የክርስቲያን ዜና ቤተሰብ ይሁኑ።

Via ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
https://t.me/TCNEW
#ድንቅ #ተግባር

#ደም በመስጠት ፍቅራችንን እንግለጽ" በሚል መሪ ቃል የሃልዎት #አማኑኤል #ቤተክርስቲያን #የደም ልገሳ እያከናወነች ነው።

የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ደም ከመለገስ ባሻገር በአከባቢያቸው ያሉ አቅመ ደካሞን ሲረዱ የቆየ ሲሆን ከወረዳው ጋር በመነጋገር በቋሚነት አረጋውያንን የማገዝ ስራ እየሰራች ትገኛለች።

ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ እየተከናወነ በሚገኘው የደም ልገሳ የሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላትን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው #ሰዎች ደም በመለገስ ፍቅራቸውን እየገለጹ ይገኛል።

ቤተክርስቲያን #ይህን መልካም ተግባር ሲታከናውን ለ4ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉ አመታት በተመሳሳይ በተከናወነው መሰናዶ በርካታ ሰዎች ደም መለገሳቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መዘገባችን ይታወሳል።

የዛሬው መረሃ ግብር እስከ 10:00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን ምዕመናን በስፍራው ተገኝተው ደም እንዲለግሱ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አቅርባለች።
የወልቂጤ #ከተማ ወንጌላውያን አማኞች የትንሳኤ በአልን በህብረት አደባባይ ላይ አከበሩ።

ምዕመኑ በአብሮነት ለሰላምና ለአንድነት መስራት ይጠበቅበታልም ተብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ሰብሳቢ መጋቤ ብርሃኑ አቅነዳ የበአሉ አከባበርን አስመልክተው እንዳሉት የእምነቱ ተከታዮች በአንድነት እንዲያከብሩ መንግስት ማመቻቸቱ የሚያስደስትና እምነቱም ምእመን በጋራ እንዲያከብር የሚያዝ ነው ብለዋል።

#ህብረቱ በበአል ወቅትም ይሁን ከበአል ውጪ የተቸገሩ ወገኖችን ማገዝ ልምዱ ነው ያሉት መጋቤ ብርሃኑ የትንሳኤ በአል አክባሪዎች ይህን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው በዚህ ወቅት እንዳሉት ትንሳኤ ለህዝበ ክርስቲያኑ ታላቅ በአል ነው ብለዋል።

በዋናነት እምነቱ በሚያዘው መሰረት አብሮነትን በማጠናከር ለተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ እርስ በርስ ከሚሸረሽሩ ተግባሮች ከመታቀብ ባለፈ የ #ሰላም መጠበቅ በሚያጸና መልኩ ሊሆን እንደሚገባም ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን #ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ #አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ፈጣሪ ሁሉን በእኩል የሚያይና በእኩል የሚዳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የትንሳኤ በአል የደስታ በአል ነው ያሉት አቶ አለማየሁ የይሁዳ ፀፀት ቢዘጋም እርስ በርስ ዛሬም በሀገራችን አንዳንዶች በሰው #ደም የመነገድ ተግባር የሚፈፅሙ አሉ ብለው #ይህም ወንጀል መሆኑን መረዳትና ለሰላም መስራት ከምእመኑ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በአል አከባበሩ ላይ የተገኙት አካላትም በአሉን በአደባባይ በህብረት በማክበራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ላመቻቹ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በአሉ ሲከበር የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበትም ገልፀዋል።