The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሰበር_መረጃ
#የቤተክርስቲያን_መሪዎች_ድምጻቸውን_ማሰማት_ጀመሩ
#ሁላችንም_Share_Share_Share_Share_Share_እናድርግ

#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

#እኛ_ጥያቄ_አቅርበናል በህጋዊ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ስለተሰጠን ቦታውን ላመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም የሚል አካል ህጋዊ መሰረት የለውም።

ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝደንት

#ኢትዮጵያ_የሁላችን አገር ናት ስንል በምክንያት ነው፡፡ በህገ መንግስቱ የተሰጠንን መብታችንን ማንም ሊቆርስብንና ሲፈልግ ሊሰጠን ሲያሻው ደግሞ ሊከለክለን አይችልም፡፡ ካውንስሉ በህግ የተቃቋመ ተቋም እንደ መሆኑ መጠን ከሚወክላቸውን ቤተ እምነቶችና ሕብረቶች ቁጥር አንጻር ሲታይ ይህ ግዙፍ ተቋም መብቱ ሊከበርለትና ጥያቄው በህግ እና በአግባቡ ሊመለስለት ይገባል ብለንም እናምናለን፡፡ በዚህ ምክንያት መብታችንን ለመጠቀም የማንንም ደጅ መጥናት አስፈላጊ አይደለም።

መጋቢ ጌትነት ለማ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤት ሐላፊ

#ይሄንን_ጉዳይ እኛ በካውንስሉ ውስጥ መሪዎች ብለን ለሰየምናቸው ሰዎች ብቻ የምንተወው ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም ሁላችንንም የሚወክል ካውንስል ስለሆነ ስለዚህ በቀዳሚነት በሚያስፈልግ ነገር ሁሉ ከካውንስሉ ጋር መቆም አለብን። በሌላ በኩል ምዕመናን በሙሉ በሚጠቀሙት የተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጽ "ፍትህ ይሰጠን" "የተሰጠን ቦታ በህጋዊ ይመለስልን" በማለት በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ ይገባል።

ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ
የፌዝባይብል ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ
#ሁሉም #ሊያነበው #የሚገባ #አስቸኳይ #መልዕክት
#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..

ለ5 #ሰከንድ #ኦክሲጅን ከአለም ላይ ቢጠፋ ምን ይፈጠራል?

ግራቪቲ (የመሬት ስበት) ለ5ሰከንድ ከመሬት ላይ ቢጠፋስ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? እኛ ሰዎች ምንድነው የምንሆነው?

ምናልባት ደግሞ #አሁን ያለውን የመሬት ስበት እጥፍ ቢሆን ምን ይፈጠራል?

ሌላኛው ለሰው ልጆች #ሁሉ ጠቃሚ የሆነችው ጸሃይ ድንገት ብትጠፋ ... ቀጥሎ የምድራችን እና #የሰው #ልጆች እጣ ፈንታ ምንድነው? በነገራችን ላይ ይህን #ሁሉ ለ5 ሰከንድ #ብቻ ነው።

እነዚህን ጥያቄዎች የሞኝ ጥያቄዎች ይመስላሉ?

#እኔም ለመጀመሪያ #ጊዜ ስሰማቸው እንደዛ ነው ያሰብኩት ነገር ግን #እጅግ መሰረታዊ እንደሆነ የተመለከትኩበትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ።

ከጥቂት ቀናት በፊት TechTalk With Solomon በተሰኘ ፕሮግራም #EBS #ቴሌቪዥን ላይ ማለት ነው። ሰለሞን እነዚህ ጥያቄዎች እየጠየቀ ነበር።

ከጥያቄዎች በሻገር ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ምናባዊ ምልከታ በሳይንስ አስደግፎ በ2 ተከታታይ ክፍሎች ለተመልካች አቅርቦታል። ለማንኛውም እኔ ያንን ፕሮግራም ስሰማው እጅግ እየዘገነነኝ እና እየተሳቀኩኝ ነበር።

በኋላ #ላይ #ግን ቆም ብዬ ሳስበው እንደዚህ አይነት ፕሮግርሞች ሊበረታቱ የሚገቡ እንደሆነ ገባኝ።

ምክንያቱም እሱ የሚዘረዝራቸው በሙሉ ለ5 ሰከንድ ቢፈጠሩ ምድራችን ላይ የሚፈጠሩት እጅግ ዘግናኝ እልቂቶች እና ነገሮችን ለማስቀረት የሚያስችል አንዳችም ቴክኖሎጂ እስካሁን #በሰው #ልጆች አልተፈጠሩም።

ይህንን ሳስብ እኛ የምናመልከት አምላክ እንዴት #ድንቅ እንደሆነ እና ምድርን #በቃሉ አጽንቶ እና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ያለ አንዳች መፋለስ #ሁሉም ነገር ስረዓታቸው ይዘው እንደሚሄዱ ሳሰብ ደነቀኝ።

ምድር ትንሽ ከሚባሉት ፕላኔቶች መካከል አንዷ ነች። ጸሃይ ደግሞ የምድርን 6ሚሊዮን አከባቢ እጥፍ የሆነች ከግዙፎቹ #መካከል ነች። ታዲያ የጸሃይ ብረሃን እንኳን በልካችን ተመጥኖ የሚደርሰን ለማሰብ የሚከብድ ምን አይነት ጥበብ ነው?

የሰው ልጅ ምናልባትም እየተማረ እና ብዙ እውቀቶችን እየሰበሰብ ሲሄድ ይበልጥ ወደ #አምላኩ እንደሚቀርብ አምናለሁ።

ለማንኛውም እኔ ከምጽፍላችሁ ይልቅ ፕሮግራሙን ገብታችሁ እንድትመለከቱት ሊንኩን አስቀምጬላችኋለሁ። https://www.youtube.com/watch?v=cqZU3b8NDB8&t=89s

#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..
ሌሎች ቤተ እምነቶችን ከመጽሐፍ #ቅዱስ ውጭ በሆነ ልምምድ እናብጠለጥላለን #እኛ ደሞ ልሳንን እና እንዳንድ ነገሮችን በተመለከተ ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒው በኩራት እናደርጋልን።

በአደባባይ በልሳን መጸለይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ተብሎ እንዲነገረን አንፈልግም።

ባይሆንም መብቴ ነው አይነት አቋም ይዘን ሌሎችን ለምን #መጽሐፉ እንደሚል #ብቻ አታደርጉም እያልን እንናገራለን እንገስጻለን።

እስኪ ወደ እራሳችንም እንመልከት። ሁልጊዜ አስተካካዮች ሆነን ሳንስተካከል እንዳንቀር!!

ዘማሪት ሶፊያ ሽባባዉ
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...

    መነሻ ቃል 1ሳሙ 17

👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::

👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን  ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::

✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም  አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።

✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::

👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም

👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::

✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::

✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::

✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️

#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::

እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።

      👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️

✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና  ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::

✝️ ካፈጠጠብኝ  በአለም ካለው
     እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
     የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️

#መጋቢ ጻድቁ አብዶ
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Please 🙏WATCH me
& #Register

#እግዚአብሔር የለም" በሚልበት በዚህች ዓለም ልጆችን

#እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደግሞም በሰውም ፊት የላቁ አድርጎ ማሳደግ እንዴት ይቻላል?

#ሁሉም ሊሰሙት #እና ሊማሩበት የሚገባ ...

የቀረን ጥቂት #ቦታ ነው #ብቻ በመሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

#ማሳሰቢያ ያለምዝገባ መግባት አይቻልም!!!

ልጆቻችንን የሚጠብቅልን የለም ብላችሁ አትስጉ #ልጆች እየተጫዉቱ የሚጠበቁበት #እኛ በቂ ቦታ አዘጋጅተናል።

#Register #Register #ይመዝገቡ #ይመዝገቡ #ይመዝገቡ

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ /ይደውሉ
https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk
0911136520/0988353423
የእንግሊዝ #ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ከአሁን በኋላ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ስም አልጠቀምም እያለች ነው።

ይልቅ ማህበር #ወይም ጉባኤ የሚሉ ምትክ ቃላቶችን ለመጠቀም መወሰኗ ተገልጿል። ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው ቤተ ክርስቲያኗ ባደረገችው የስነ መለኮት ጥናት መሰረት የሚመጡ ሰዎችን #ቁጥር ለመጨመር መሆኑ ተገልጿል።

ጥናቱን ከተካሄደባቸው የአስተዳደር ክፍፍሎች መካከል ስድስቱ የአምልኮ ስፍራ፣ ሰባቱ ማህበረሰብ እንዲሁም #ሁለቱ ደግሞ ጉባኤ በሚለውን ስያሜ እንደሚመርጡ አሳውቀዋል።

ባለፉት 10 ዓመታት #ብቻ የቸርች ኦፍ ኢንግላንድ 900 አዳዲስ ቤተ ክርስቲያናትን የተከለች ሲሆን አንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን የሚለው ስም አይጠቀሙም።

#FoxNews እንዳስነበበው አዳዲሶቹም ይሁኑ የቀደሙቱ ማህበር ወይም ማህበረሰብ የሚለውን ስም ሲጠቀሙ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ማለት ምንድነው የሚለውን ጥያቄ መልስ በእንጥልጥል ያስቀረዋል።

የቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ግን ይሄንን አሉባልታ ወሬ ስትል አጣጥላዋለች። ምናልባም የተገኙ ውጤቶች ባይካዱም ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ #አንድ አንድ የወጣቶች ፕሮግራሞችና አንድ አንድ ደብሮች የተለመደ መሆኑን ብቻ ገልጸዋል።

ሌሎች ኢንግሊዛውያን ቀሳቅስትና ጸሃፊዎች፣ ቤተ ክርስቲያኗ በአለም ተቀባይነት ለማግኘት የወሰነችውን ውሳኔ፣ የተሳሳተ ብለውታል።

#እኛ ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል 16፣18 ምን ተደርጎ ነው፣ ማህበር/ጉባኤ በሚል የሚተካው ስንል እንጠይቃለን።

#እናንተም ሃሳባችሁን አካፍሉን!!