The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ልብ_ይሰብራል😭
እንዴትስ ማፅናናት ይቻላል?😭

#አባት_ከ4_ህፃናት_ልጆቹ_ጋር_በአንድ_ለሊት በእሳት አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።😭

#አርብ_ቀራንዮ_አካባቢ መብራት ስላልነበር እነ አምሳልም ቤት ሻማ ለኩሰዋል! እራት በልተው ከ5 ልጆቻቸው ጋር ጋደም እንዳሉ ከምሽቱ 5ሰዓት አካባቢ ድንገት ቤታቸው በእሳቱ ይያያዛል።

#አባት_አቶ_ጊዜ_ባለቤቱን እና ያቀፈቻትን የ10ወር ህፃን ልጁን አሜንን እንደምንም ወደ ውጪ ይዟቸው ወጣ! የቀሩትንም የአብራኩ ክፋይ ልጆቹን ለማትረፍ ወደቤት ተመልሶ ገባ! ግን አልደረሰባቸውም😭 እሱም ዳግም በህየወት አልተመለሰም ከ4ሴት ልጆቹ ጋር ውስጥ ቀረ ቤቱም ሙሉ ለሙሉ ተቃጠለ።

#እናት_አምሳል_ይርጋ አይኗ እያየ 4ልጆቿን እና ባለቤቷን በደቂቃ ውስጥ አጣች😭

#ገና_ሮጠው_ያልጠገቡት 4ቱ እህትማማቾች ኑሀሚን፣ ናርዶስ፣ልደትና ፅዮን በአደጋው ሞተው ከአባታቸው ጎን ተቀበሩ!😭

#አፅናኙ_የእግዚአብሔር_መንፈስ_ያፅናናሽ_እህቴ! ሌላ ምን ይባላል😭

ምንጭ:- ሄኖክ ፍቃዱ
#ጉዞ #ወደ #ሞት ... 🚶‍♂️🚶‍♀️🚶‍♂️ ☠️

ከሰሞኑ #BBC ወደ ሞት ጉዞ ብሎ #ልብ ኮርኳሪ ቅስም ሰባሪ ሰፋ #ያለ ዘገባዎችን አስነብቦ ነበር።

በዋናነት ዘገባው #ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ለመግባት በአፋር #እና በጅቡቲ በረሃ የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ እና ተስፋ አስቆራጭ ጉዞ የሚተርክ ነው።

ልብ አንጠልጣይ እና ምስል ከሳች አድርጎ የሚተርከው ዘገባ #ግን ... እውነተኛ የእግር ዳናቸውን ተከትሎ ባህርን ለማቋረጥ በጭላንጭል #ተስፋ ውስጥ የሚገኙ የተስፈኞችን እውነተኛ የተጋድሎ የጉዞ #ታሪክ ይተርካል።

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሕይወትን ለመለወጥ በሚደረገዉ ጉዞ "የቀይ ባሕር ስደተኞችን ማሻገር አልያም በሰፊ ሆዱ ውጦ ማስቀረት አይታክተውም" ሲል ቁጥራቸው እልፍ የሆኑ ተስፈኞች ከነ ተስፋቸዉ ሰጥመዉ እንደቀሩ ፅፏል።

#ታዲያ አሁንም ቢሆን በርካቶች ወደ አገራቸው የሚመልሳቸው እንዳጡ በሚናገሩባት ኦቦክ (የጅቡቲ የባሕር ዳርቻ) ሌሎች በርካቶች ደግሞ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል በሚል ጂቡቲ ድንበር ሆነው የመንን ይናፍቃሉ።

ከየመን ለመውጣት ቀዳዳ የጠፋባቸውን በርካታ ስደተኛ እንዳሉም ዘጋቢዉ ያነሳል ወደ ኦቦክ ለአዲስ ስደት የሚተመውን ወጣት እየተመለከቱ ለእኛ ግን ከዚህ ሁሉ አገር ቤት ገብቶ የሚሆነውን መጠበቅ ይሻለናል ብለዉ ከብዙ ስቃይ በኋላ የእግር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ የሚያደርጉም በርካታ ናቸዉ።

#ዛሬ በዚህ ምልከታዬ #ብዙ #ገንዘብ ስለሌላቸዉ አልያም በሕጋሚ #መንገድ ከሀገር መዉጣት ባለመቻላቸዉ የባህር ተጓዦችን አነሳዋቸዉ እንጂ ፖስፖርት አሰናድተዉ የቋጠሩትን ጥሪት ይዘዉ ልባቸዉ ቀዶሞ የሄደ አካላቸዉ ብቻ የቀረ ቤት ይፍጃቸዉ።

#ታዲያ ከዘገባዉ የተረዳሁት ስደትን ምርጫዉ ያላደረገ ትዉልድ ለመቅረፅ #ቤተክርስቲያን አሁንም #ስራ አለባት መልዕክቴ ነዉ።
የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...

    መነሻ ቃል 1ሳሙ 17

👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::

👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን  ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::

✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም  አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።

✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::

👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም

👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::

✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::

✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::

✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️

#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::

እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።

      👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️

✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና  ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::

✝️ ካፈጠጠብኝ  በአለም ካለው
     እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
     የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️

#መጋቢ ጻድቁ አብዶ
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#መልካም እናት ለመሆን ትፈልጊያለሽ .. ?
እንግዲያዉስ #አሁን ደዉይ እና ተመዝገቢ

ለ #20 #ሰዉ #ብቻ የተዘጋጀ #ልዩ እድል እንዳያመልጥሽ አሁኑኑ ፈጥነሽ ተመዝገቢ!!!

#Register #NOW
ያዘጋጀነው ቦታ ለ20 ሚስቶች ብቻ ነው #ዕንቁ #ልብ የሚስቶች ት/ቤት

በእነዚህ ጊዜያት ለባልሽ የሚመች ረዳት ፣ ለልጆችሽ #መልካም #እናት ለመሆን የሚያሰችልሽን ጥበብ ፣ ዕውቀትና ማስተዋል ታገኛለሽ።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdDOfrOP-NSFpgl_vZRYfUq6NtPVVC-57e4GUOJONfkczjWAw/viewform?usp=pp_url

ለበለጠ መረጃ 09-11-13-65-20 ደውይ!! 🤳

በቴሌግራም እኛን ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ልባምን #ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል?

ለሚስቶች #ብቻ የተዘጋጀ #ድንቅ ፕሮግራም
እንግዲያዉስ #አሁን ደዉይ እና ተመዝገቢ

#ኑ አብረን እንማር

ለ #20 #ሰዉ #ብቻ የተዘጋጀ #ልዩ እድል እንዳያመልጥሽ አሁኑኑ ፈጥነሽ ተመዝገቢ!!!

#Register #NOW ለ 10 ቀናት ብቻ ...

ያዘጋጀነው ቦታ ለ20 ሚስቶች ብቻ ነው #ዕንቁ #ልብ ❤️የሚስቶች ት/ቤት

በእነዚህ ጊዜያት ለባልሽ የሚመች ረዳት ፣ ለልጆችሽ #መልካም #እናት ለመሆን የሚያሰችልሽን ጥበብ ፣ ዕውቀትና ማስተዋል ታገኛለሽ።

https://docs.google.com/.../1FAIpQLSdDOfrOP.../viewform...

ለበለጠ መረጃ 09-11-13-65-20 ደውይ!! 🤳

በቴሌግራም እኛን ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk