#አዲስ
#ጎንደር #ድንቅ #ጊዜ #ጌታ #ተመስገን
የጎንደር ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።
በዓሉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ያስተላለፉት የጎንደር ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ሰብሳቢ ፓስተር ሀይሌ አስፋው እንደገለፁት ህብረቱ ከዋናው የወንጌል አገልገሎት ተልኮው ባሻገር በተለያዩ ማህበራዊና ልማታዊ ስራዎች በንቃት እየተሳተፈ ነው።
ህብረቱ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ኮምፓክሽን ኢንተርናሽናል ከተባል መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርድት ጋር በመተባበር ለ1ሽ500 ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን ህፃናት የትምህርት ወጭ በመሸፈን መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ህብረቱ በተለያዩ ምክኒያቶች በህክምና ላይ ሆነው ደም የሚያጥራቸውን ዜጎች ለማገዝ 108 ከረጢት ደም ከእምነቱ ተከታዮች ማሰባሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
ህብረቱ በጦርነቱ ምክኒያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የ7 ሚሊየን ብር የምግብ እህልና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም አስተውሰዋል።
ህብረቱ በአድርቃይ ዉረዳ በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶች ስራ እንዲጀምሩ የሚያግዝ የ4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ፓስተር ሃይሌ ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባን በመወከል በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አስቻለው መልካሙ በበኩላቸው #ህብረቱ በከተማዋ የልማትና #የሰላም ስራዎች በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን ወገኖች በመደገፍ፣የደም እጦት ለማያጋጥማቸው ወገኖች ደም በመለገስ፣የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጦርነት ምክኒያት የወደሙ የትምህርት ተቋማት መልሰው ስራ እንዲጀምሩ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

#ወደ #ጌታ #ሄደች
አንጋፋዋ እና ተወዳጇ ዘማሪት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡
ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡
ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡
ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች፡
(ታዲያስ አዲስ)
The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለቤተሰቦቿ፤ለወዳች ዘመዶቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ከህክምና በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአርቲስት ጋሽ ስዩም ጋር የተደረገ ቆይታ #ጌታን አመስግኑልኝ #ጌታ በበዙ መንገድ እረድቶኝ ዛሬ እዚህ ደርሻለሁ https://youtu.be/sbM9I2TNvv4
YouTube
#ጌታን አመስግኑልኝ #ጌታ በበዙ መንገድ እረድቶኝ ዛሬ እዚህ ደርሻለሁ ከአርቲስት ጋሽ ስዩም ጋር የተደረገ ቆይታ
ከህክምና በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአርቲስት ጋሽ ስዩም ጋር የተደረገ ቆይታ #ጌታን አመስግኑልኝ #ጌታ በበዙ መንገድ እረድቶኝ ዛሬ እዚህ ደርሻለሁ ወዳችሁ እና ፈቅዳችሁ ስለምትመለከቱን ከልብ እናመሰግናለን!!! Like, Share ማድረጎን አይርሱ!!...
#ወደ #ጌታ #ሄዱ
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ መሪ የነበሩት አቶ ወራቦ መኑ በ75 ዓመታቸው ወደ ጌታ ሄዱ።
አቶ ወራቦ በቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ብሔራዊ ቦርድ አባልነት፣ በዋና ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊነት ብሎም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው በተለይም በጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሽምግልና በማገልገል ቤተ ክርስቲያኒቱ ካፈራቻቸው አንጋፋ አገልጋይ መሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
የአቶ ወራቦ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም የሚፈጸም ሲሆን ከቀኑ በ7:30 ሳር ቤት በሚገኘው አይ ኢ ሲ (ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን) የሽኝት መርሃ ግብር ከተካሄደ በኋላ ዊንጌት አደባባይ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ የመቃብር ስፍራ ከቀኑ 9:30 ላይ ስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል።
“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” ሮሜ 8:28

#አሳዛኝ #ዜና
#ቄስ #ወደ #ጌታ #ተሰብስበዋል 🙏🙏🙏
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት የመሩት ቄስ ዓለሙ ሼጣ በዛሬው ዕለት ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ዕቅፍ ተሰብስበዋል።
ኅብረቱን በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበሩት ወንድማችንና አባታችን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም በማረፍ ሞቶ ወደ ተቤዣቸው #ጌታ ክብር ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በወንድማችን፣ በሥራ ባልደረባችንና በአባታችን እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለሁሉም መፅናናትን ይመኛል። 🙏🙏🙏 😭😭😭

ላለፋት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን በጎማ ወረዳ በኪሎሌ ቀበሌ ውስጥ በምትገኘው ቃለ ሕይወት #ቤተክርስቲያን በወንጌል #አገልግሎት መስዋዕትነት የከፈሉ የሕይወት ዘመናቸውን #በሙሉ ለወንጌል አገልግሎት የሰጡት ወንጌላዊው ሀይሉ ሌታሞ ወደ ሚወዱት እና ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል።
ለብዙዎቻችን በረከት የሆኑ እና ብዙዎቻችንን በቃሉ ያሳደጉና ያፈሩ አባታችን ወንጌላዊ ሀይሉ ሌታሞ ዛሬ ህዳር 25 ቀን2016 ዓ/ም ወደሚወዱትና ወደ ሚናፍቁት ጌታቸው በመሰብሰባቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰብ፣ ለወዳጆች እና ለመላው ቃለ ሕይወት ቤተክርስትያን ምዕመናን መጽናናትን እንመኛለን
የተወዳጁ አገልጋይ ስረዓተ ቀብር በነገዉ እለት የሚፈፀም ይሆናል።

የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...
መነሻ ቃል 1ሳሙ 17
👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::
👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::
✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።
✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::
👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም
👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::
✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::
✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::
✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️
#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::
እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።
👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️
✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::
✝️ ካፈጠጠብኝ በአለም ካለው
እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️
#መጋቢ ጻድቁ አብዶ

#ወደ #ጌታ #ሄደ
ወንድዬ ዓሊ
ገጣሚ፣ ደራሲ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና የግለታሪኮች ጸሐፊ፣ የድንቅ መዝሙራት ደራሲና ዘማሪ፣ የብዙዎች የሙያ አባት፣ … ወንድዬ ዓሊ በስተመጨረሻ ለሞት እጅ ሰጠ።
በክርስቶስ #ኢየሱስ አምኖ በመዳኑ መዳረሻውን ስለሚያውቅ ከባድ ህመም ቢያደቀውም በጽናት እና ያለ ሀዘን ነፍሱን ሰጠ።
የዘለአለም #ሕይወት ወራሽ ያደረገው የሞተለት #ጌታ ኢየሱስ በወንድዬ ሕይወት አልፎ ለቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ ለአገራችን ስነጽሑፍ ወዳጆች እና ለመላው የወንጌል አማኝ ስለሠራው #ሁሉ ስሙ ብሩክ ይሁን።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለመላው ወዳጆቹ #እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጥ ይመኛል።

#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...
#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭
ከ1945 - 2016 ...
ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።
ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።
ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።
ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።
ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።
በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።
#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።
በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።
ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም
እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ
በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም
የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...
ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።

#ታላቁ #የወንጌል #አርበኛ #ወደ #ጌታ ተሰበሰቡ
መጋቢ ሰለሞን ጂኖሎ የሻሸመኔ አጥቢያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መሪ መጋቢ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።
በወንጌል ላልተደረሱ አካባቢዎች ወንጌል የማድረስ ሸክም ሲሰሩ ቆይተዋል።
በእንዲህ ሁኔታ በመሰጠት የሚያገለግሉ አባት ማጣት እጅግ ልብን የሚሰብር ዜና ቢሆንም ወዳገለገለው ጌታ ተሰብስቦአልና እንጽናናለን።
መጋቢ ሰለሞም የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በመሆንም ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል።
ጌታ ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

#እግዚአብሔር ለሁሉም መጽኛናትን ይስጥ!!
የተወደደው ወንድማችን ሱሬ ርሆቦት አርት ሚኒስትሪ የዛሬ 21 አመት ሲመሠረት ጀምሮ በትወና፣ በቀረጻና ኤዲቲንግ እንዲሁም በዝማሬ ሲያገለግል ቆይቷል።
ሱሬ በሁላችንም ዘንድ #ተወዳጅ፣ ተጫዋችና #መልካም ስብእና ያለው #ወንድም ነበር።
ከጥቂት አመታት ጀምሮ ደግሞ በሚያገለግልባት ቤተ ክርስቲያን ብዙዎቻችሁ በአገልግሎቱ ተጠቅማችኋል ብዬ አስባለሁ።
ሱሬ ልጅነቱንና ወጣትነቱን ሰጥቶ #ወደ ተከተለው፣ ወዳገለገለውና ወደሚወደው #ጌታ እቅፍ ሔዷል። ለወዳጆቹ፣ ለቤተሰቦቹ እና አብረነው ስናጥን ለቆየነው ለእኛም እሱን ማጣት ሀዘን ቢሆንብንም እርሱ ግን ወደተሻለውና እኛም ሁላችን ተራችንን ጠብቀን ወደምንሔድበት ቦታ ሔዷል።
ነገ ሐሙስ 6:00 በዮሴፍ #ቤተክርስቲያን በክብር እንሸኘዋለን🙏
The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሁሉም መጽኛናት እንዲሆን እንመኛለን።

በአረብ ሃገሯ #ኢራን እስከ 1 #ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ወደ ክርስትና መጥተዋል ተባለ።
ከ88 ሚሊዮን ህዝቧ 96 በመቶ በላይ የሚሆነው እስልምና ተከታይ በሆነበትና፣ የሃገሪቷ #መንግስት በግልጽ እስላማዊ በሆነባት ኢራን ይሄንን ያክል ቁጥር #ክርስቲያን መገኘቱ ተዓምር ነው ተብሏል።
ሪፖርቱን ይዞት የወጣው The Voice of the Martyrs የተባለው በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስን ስደት የሚከታተል ተቋም ነው። ተቋሙ በሪፖርቱ ከ1970 የኢራን አብዮት ወዲህ በሃገሪቱ ክርስቲያኖች ስደት የበረታ መሆኑን ጠቅሷል።
ምንም እንኳን ስደቱ ቢበዛም በተቃራኒውም የክርስቲያኖች ቁጥር መጨመርን አሳይቷል። ቤተ ክርስቲያን በድብቅ ወይም underground ሆና መስፋፋቷን ቀጥላለች።
ሌላዋ የመካከለኛው ምስራቅ #አረብ ሃገር በሆነችው የመን፣ ጆሽዋ ሚኒስትሪ ሪፖርት እንዳደረገው በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ይልቅ በየመን ወደ #ጌታ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ብልጭን አሳይቷል።
በ2024 ሪፖርት መሰረት ኢራን ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በሚል በ9ኛ ስፍራ የምትገኝ ሲሆን የመን በበኩሏ በ5ኛ ስፍራ ተቀምጣለች።