#አስደሳች #ዜና #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን
#የአማርኛ #መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በድል ተጠናቋል።
ይሄንን ዜና እንደሰማው በቅድምያ እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ ምክንያቱም ለቤተክርስቲያን የአሁኑን ጨምሮ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሆን በረከት እየመጣ እንደሆነ አምናለሁ።
ዜናው ለ23 ዓመታት ሲለፋበት የነበረው "የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" በእግዚአብሄር እርዳታ እንደተጠናቀቀ የሚገልጽ ነው።
ምንም እንኳን የሕትመት ስራው በቅርብ ጊዜ የሚከናወን ቢሆንም የአንድ ወጣት እድሜ የሚያክል ተለፍቶበት የተሰራ ስራ እንደመመልከት ግን የሚያስደስት ነገር ያለ አይመስለኝም።
ለማንኛውም መጽሐፉ ገና ስላልታተመ ዝርዝር ጉዳይ የለኝም ነገር ግን ስለጸሃፊው እና ከዚህ ቀደም ስለነበሩት ስራዎች ግን የተወሰነ ልበል።
ጸሐፊው ዘላለም መንግስቱ ይባላል። ብዙዎች በምላቴ #ክርስትና ስራዎቹ ያውቁታል። ላለፉት ከ3 አስርት አመታት በላት #የኢትዮጵያን #ቤተክርስቲያን በበርካታ መልኩ እያገለገለ የሚገኝ ወንድም ነው።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ስለ ጌታ ከሰማ በኋላ ከዲያቆንነት እስከ ወንጌላዊነት ... በበርካታ የአገልሎት ስራዎች በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን አገልግሎ ተገልግሎ ዘልቋል።
ወንድም ዘላለም በ1984 የታተመች እና "አዲስ ሕይወትን የማዳረስ ዘዴ" የሚል ርዕስ ያላት በወንጌል ስርጭት እና በደቀመዝሙርነት ላይ የምታተኩር መጽሐፍ ጀምሮ የነህምያ መጽሐፍ ማጥኛ እና ቀላል ማብራሪያ "መፍረስ እና መታደስ" "መጽሐፍ ቅዱስ እና የአፈታት ስሕተቶች " የሚሉ መጽሀፍትን ለቤተክርስቲያን አበርክቷል።
ብዙዎች "መንፈስ #ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች" በሚል 1988 ለሕትመት በበቃውን መጽሐፍ ያውቁታል። ምንም እንኳን ይህ መጽሀፍ የዛሬ 27ዓመት ገደማ ቢጻፍም ዛሬም ድረስ መነጋገሪያ ነው።
"ክርስቲያናዊ ኢትዮጰኝነት" "እንዝፍን ወይስ እንዘምር" "የሃሰተኞች እሳተ ገሞራ" የተሰኙት ደግሞ የቅርብ ጊዜ የወንድም ዘላለም ስጦታዎች ናቸው።
አብዛኛው #ሰው ደግሞ በአንድ ወቅት "ይድረስ ለዘማሪዎች" በሚል በወጣው ሲዲ ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል። በነገራችን ላይ ወንድም ዘላለም "ይድረስ ለዘማሪዎች" የሚለውን ሃሳብ ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ቢሰራው ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት እጅግ ይከብደኛል።
በምካቴ ክርስትና ብዙዎችን ከሃሰተኛ ነብያት እና ትምህርቶቻቸው ለመታደግ ለአመታት ሲታገል ቆይቷል።
መኖሪያውን በባህር ማዶ ላስ ቬጋስ ያደረገው ወንድም ዘላለም ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነገ እጣ ፈንታ ዘውትር ሲያስጨንቀው እመለከታለሁ።
ከ30 ዓመት በላይ በመጽሀፍ ስራ ውስጥ የቆየው ወንድም ዘላለም ከሰሞኑ ላለፉት 23 ዓመታት ሲደክምበት የነበረውን ስራ መጨረሱን አብስሯል። ይህ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እጅግ ትልቅ የምስራች ነው።
ምክንያቱም እስከዛሬ በቤተክርስቲያን ይህን የመሰለ መፅመፍ አልነበረም ታዲያ ለመጽሀፍ ቅዱስ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን የቋንቋ እድገትም አንድ ሃሳብ እንዳዋጣ አምናለሁ።
ከዚህ ቀደም #የክርስቲያን #ዜና ወንድም ዘላለምን ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድል ያገኘን ሲሆን ምናልባት ለወደፊት በድጋሜ እንደምናገኘው ተስፋ እናደርጋለንን።
ለማንኛውም ለዚህ ድንቅ ስራ ግን እግዚያብሄርን እያመሰገንን በትዕግስት ስለጨረሰው ለወንድም ዘላለም አድናቆታችን ይድረሰው። ምንልባት ጥቂት በሚባል ጊዜ ውስጥ የእርማት ስራው ተጠናቆ ለህትመት እንደሚበቃ እና ሁላችንም ጋር እንደሚደርስ እምነታችን ትልቅ ነው።
ለማንኛውም ስለ ሁሉም #እግዚያብሄር ክብሩን ይውሰድ።

#አስደሳች #ዜና
#ካዉንስሉ እና #ሕብረቱ #ታረቁ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት፣ ከሙሉ ወንጌል፣ ከመሰረተ ክርስቶስ፣ ከህይወት ብርሃንና፣ ከገነት አብያተክርስቲያናት ጋር የነበረውን ግጭት ላለፉት ሁለት ወራት ሲወያይባቸው በመቆየት ችግሮቹን የፈታ ሲሆን፣ በቀጣዩም አብረውም የሚሰሩባቸውን መንገድ ዘርግተው። እርቅም አድርገዋል።
ይህን አስመልከቶ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በጋራ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ የአምልኮና የአንድነት ጊዜ አድርገዋል። የአምልኮ ጊዜ በሐዋሪያው ዮሐንስ ግርማ (ጆን) የቀረበ ሲሆን፣ መክፈቻ ጸሎት በፓስተር መስፍን ሙልጌታ፣ የእግዚአብሔር ቃል በቄስ ሌሊሳ ቀርቧል።
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ክፍተቶችዋን እያጠበበች መሔድዋ ለወንጌል ስራ እጅግ ትልቅ ጥቅም አለው። ለወንጌል ስራ በሚሆን መልኩ አንድነታችንን መጠበቅ ቀጣዩን የቤተ ክርስቲያን ስራ በጋራ ለመስራት ይረዳል። ይህ ታላቅ ጅማሬ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን።
ዘሪሁን ግርማ
Christian ዜማ Tube
ዝርዝር መረጃ በቪዲዬ በዩቲዪብ ቻናላችን ይዘን እንመለሳለን።

የወንጌል አርበኞች #ዓለም አቀፍ ቤ/ክ ለ5 ቀናት የቆየ የምስጋናና አመታዊ የወንጌል አባቶችን የመባረክ ኮንፍራንስ አካሂዳለች።
ቤተክርስቲያኒቱ ላለፉት 9 ዓመታት ወንጌልን ለፍጥረት ከማድረስ ባሻገር ለተከታታይ 7 ዓመታት በኢትዮጵያ 4ቱም ማዕዘናት የሚገኙና ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ አባቶችንና እናቶችን በመጥራት የማመስገን ፕሮግራም ስታካሂድ ቆይታለች።
ዘንድሮም ከ35 በላይ የወንጌል አርበኞችን በመጥራት ሙሉ ልብስ ያለበሰች ሲሆን የክብር ሰርተፍኬትና የገንዘብ ስጦታ አበርክታለች።
ለ5 ቀናት በቆየው የምስጋናና አባቶችን የመባረክ ኮንፍራንስ #ላይ የወንጌል አርበኞች ቤ/ክ ባለአደራ ፓ/ር ተመስገን አቡቴ እንደገለፀው.. ''የወንጌል አባቶች በከፈሉት #ዋጋ ነው #ዛሬ የደረስነው በእኛ #ዘመን #ወንጌል ሊቀል አይገባም..ደግሞም የወንጌል አርበኞችን ባገኘነው አጋጣሚ ልንባርካቸውና ባለን ነገር ሁሉ ከጎናቸው ልንሆን ይገባል'' ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።
በምስጋናና አባቶችን በመባረክ ኮንፍራንስ ላይ የተጋበዙ ሰባኪያንና ዘማሪያን ያገለገሉ ሲሆን የወንጌል አርበኛ አባቶችና እናቶችም ለተገኙ ቅዱሳን በዘይት ፀልየዋል።
ይህ አባቶችን የመባረክ አመታዊ ፕሮግራም ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ በቋሚነት እንደሚቀጥልና ከዚህ መልካም ራዕይ ጎን ቅዱሳን እንደዲቆሙ ጥሪ ቀርቧል።
ዜናውን ከወደዱት #LikeAndShare
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት #comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል #share ያድረጉ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።
መረሃ ግብሩን በማስመልከት በዛሬው እለት በሕብረቱ ጽ/ቤት The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መጪውን የ2016ዓ.ም ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የአንድነት ጊዜ አዘጋጅቷል።
ሕብረቱ ይህንን ያለንበትን የጻጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን ጸሎት እንዲደረግ አውጆ እንደ ነበር በመግለጫው ያስታወሱ ሲሆን ጾም እና ጸሎቱ በቀሩት ቀናትም ተጠናክረው በመላው ወንጌል አማኞች ዘንድ እንዲደረግ አሳስበዋል።
በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም እንደሚያሄድ የገለጹት መሪዎቹ በአዲስ አበባ እና አከባቢው የሚገኙ ምዕመናን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንዲሳተፉም ጥሪ አቀርበዋል።
ተጨማሪ የቪዲዮን ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንመለሳለን።

የወንጌላውያን #ሚድያ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ።
በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት በተካሄደ ምስረታ ጉባኤ #ላይ ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመረሀ ግብሩ ምስረታ ወቅት ማህበሩን ለመመስረት የተካሄደባቸውን የስራ ሪፖርቶች ለተሳታፊዎቹ ያቀረበ ሲሆን በመሀበሩ መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቋል።
በእለቱም የማህበሩን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቦርድ አባላት የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመሆን ወንድም ዘሪሁን ግርማ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንድም መሳይ አለማየሁ የተመረጡ ሲሆን ዘጠኝ የማህበሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል።
በእለቱም የጸሎትና #የእግዚአብሄር ቃል በመካፈል ፕሮግራምም ተካሄዷል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በማሕበሩ ምስረታ ሒደት ዉስጥ በበጎ ፍቃደኝነት ከፍተኛ ስራ ለሰሩ አባላት ምስጋናውን እያቀረበ።
በዛሬዉ እለት ማሕበሩን በቀጣይ ለመምራት ሃላፊነት ለተቀበሉ መሪዎች #መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።

#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ
#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።
በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።
በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።
አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡
በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።
#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።
ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።
#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።
በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።
በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።
ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።

#አስደሳች #ዜና ካህን #የክርስቲያን ባዛር ሊደረግ ነው።
በመልህቅ ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት አዘጋጅነት "ካህን" የተሰኘ እና ጀማሪ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ #ክርስቲያን ነጋዴዎች የሚሳተፉበት የክርስቲያን ባዛር ሊካሄድ ነው።
ሚያዝያ 12/2016ዓ.ም ቅዳሜ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ ወጣት እና አንጋፋ ዘማሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተው በድምቀት እንደሚከፍቱት አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።
በመረሃ ግብሩ የክርስቲያን ባዛር የአምልኮ #ጊዜ የተለያዩ ጨዋታዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲሁም ለክርስቲያን ቲክቶከሮች ማበረታቻ የሚሰጥበት ጊዜ እንደሚኖር ታውቋል።
#ቦታ ብሔራዊ ትያትርን ተሻግሮ በከተማና ልማት አዳራሽ ከማለዳው 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00ሰዓት ይከወናል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይጎብኙ ፤ ይሸምቱ ፤ አብረውን ያምልኩ።