The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ትላንት ይሄንን #የተቀባ_ዉሃ ስመለከት ከአንድ ሳምንት በፊት ያሰፈርነዉ "ፀልየህበት ጠጣ" የተሰኘዉ ፅሁፍ ትዝ አለኝ ለማንኛውም ፀልያችሁበት ጠጡ🙏🙏🙏

"ጸልየህበት ጠጣ"

#ታላቅ_ተብሎ_የተለፈፈለት_ኮንፍራንስ_እየተካሄደ ነው። በየአቅጣጫው የተሰቀሉ ድምጽ ማጉያዎች ድምጹን አባዝተው በሩቅ ለተቀመጠው ሳይቀር ያለምንም የድምጽ መቆራረጥ ያደርሳሉ። ከሕዝቡ መሙላት ባሻገር ለራበው ምግብ የሚያሰናዱ ድንኳኖችና ለጠማው ውሃ የሚቸረችሩ ውሃ ሻጮች በየአቅጣጫው ተኮልኩለዋል።

የተለያየ ቤተ ክርስቲያናትን የህንጻ ማሰፋፊያ የሚያሳዩ "ባነሮችም" ተሰቅለው ገንዘብ ይሰበሰብባቸዋል። ለወንጌል ነው ተብሎ ከሚሸጠው ከትንሹ ከረሜላ አንስቶ እስከ ትልቁ ዘይትና ቲሸርት ሜዳውን አካሎታል። ከዚህ ስፍራ የሚሸጠው ለወንጌል የሚጋውንም የተጸለየበት እንደሆነ ነው።

አንድ ጎልማሳ ከጸሀይ ለመጠለል እንዲሆነው ከተቀመጠበት ከአንድ "ባነር" ውስጥ ሸቅብ እያየ የታሸገ ውሀ የያዘውን ብላቴና "ሀይላንድ... ሀይላንድ" በማለት ተጣራ። ልጁም ወደ ስፍራው ደረሰና የታሸገውን ውሀ ሰጥቶች ገንዘቡን ተቀብሎ ሊሄድ ሲል፤ ሰውዬው "ስማ ግን የተጸለየበት ነው? በማለት ጠየቀው። ብላቴናው ግን በሹፈት "#ጸልየህበት_ጠጣ" ብሎት ሄደ። ...

"ፓሳህ" ከተሰኘው መጽሃፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ...

በዚህ አጋጣሚ መፅሐፉን ገዝታችሁ እንድታነቡ ጋበዝኳችሁ 🙏🙏🙏
#ታላቅ_የመክፈቻና_የምስጋና_ኮንፈረንስ
"እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን"
ከታህሳስ 7-14 / ክርስቶስ ይሰበካል፣ እግዚአብሔር ይከብራል።

#Everlasting_Christ_Revelation_Church

አድራሻ፦ አዲሱ ስታዲየም ፊትለፊት በአቢሲኒያ ባንክ ባለው መግቢያ 100 ሜትር እንደሄዱ በስተግራ እንደታጠፉ ያገኙናል

ለበለጠ መረጃ- 0911759812
ኤፌሶን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
³² ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።
እግዚአብሔር #ወንድ እና #ሴት አድርጎ በ #ጋብቻ ስላጠመረበት ምክንያት -  #ታላቅ  ምስጢር የምንማማርበትን #መድረክ #ይቀላቀሉ 👇👇👇
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
#ታላቅ ክሩሴድ በወታደሮች

የዩጋንዳ ጦር አባላት በሰሜናዊ ዩጋንዳ የ5 ቀናት ታላቅ ክሩሴድ ማድረጋቸው ተሰማ።

የወታደሮች #ክርስቲያን ፌሎሺፕ የሚል ህብረት ያላቸው የሃገሪቱ ጦር አባላት “ወታደራዊ ሃዋርያ” በሚል ቅጽል ስምም ይታወቃሉ።

ክሩሴዱን ኔቢ በምትባለው ሰሜን ዩጋንዳ በምትገኘው ላይፍ ላይን ሚኒስትሪ ጋር በመሆን ነው ያዘጋጁት።

ወንጌልን #ሁሉም መስማት አለበት በሚል የተጀመረው ይሄ ክሩሴድ የጦር አዛዥ የሆኑ ሜጀር ጀነራል ዴቪድ ዋካሎ የተባሉ ከፍተኛ መኮንንም ተገኝተዉበታል።
#መሰረተ #ክርስቶስ #ታላቅ የሕብረት #ጊዜ ላይ ናቸዉ

በአዲስ አበባ እና አከባቢው የሚገኙ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን #ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን በመዝጋት በጋራ በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እያመለኩ ይገኛል።

መረሃ ግብሩ "በሕይወት ታድሶ በህብረት ፀንቶ ወደ ፍፃሜዉ መገስገስ" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ይገኛል።

በመሰናዶዉ በአዲስ አበባ በ11ዱም ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሙሉ ምዕመናን እየተካፈሉ ይገኛል።
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።