The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ቢሾፍቱ ደብረዘይት አጥቢያ የድምፅ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ስለወደሙባት የእናንተን ቅዱሳንን እገዛ ትሻለች።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ ደብረ ዘይት ቅርንጫፍ
1000011507698
#ብርሃን ባንክ
2602750022834
#አቢሲኒያ ባንክ
83161717
#ኦሮሚያ ኮፕሬቲቭ
1017100056104
#ለበለጠ መረጃ፦ +251912299228
0114335375
#አዲስ #ዜና

የሐዋሳ ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታል ከህይወት #ብርሃን #ቤተክርስቲያን #ጋር በመተባበር በኮምፓሽን #ኢንተርናሽናል ድርጅት በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ህጻናት #ሙሉ የጤና ምርመራ ተደረገላቸው።

ለህጻናቱ ሙሉ ምርመራ በነጻ ያደረገው የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው።

የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ቡድን (Family Health Team) ከሆስፒታሉ MCC ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ለEP 706 ህጻናት ልማት ኘሮጀክት አጠቃላይ የጤና ምርመራ ህክምና ያደረገው።

#ፓስተር ጌቱ አያሌው የሐዋሳ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መጋቢ በከተማችን ካሉ የደሀ ደሀ ህጻናት መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የቀለብና ሌሎችም ድጋፍ የሚደረግላቸው ህጻናት መኖራቸውን ገልጸዋል።

በህጻናት ላይ መንግስት፣ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት፣ ባለሀብቶች፣ እና ሌሎችም በመተባበር ከሰራን ከፍተኛ የሰው ሀይል በማፍራት እናተርፋለን ሀገርም ትባረካለች ብለዋል።

የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ አቶ ይርዳቸው አናቶ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን እና ኮምፓሽን ከሚረዱ ህጻናት ውስጥ ዛሬ ለ3 መቶ 26 ህጻናት መሉ የጤና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ይህንን መሰል ተግባር ቤት ለቤት የጤና ህክምና በሚሰጡ ባለሙያዎች እየተተገበረ ስለመሆኑ ያስረዱት አቶ ይርዳቸው ምርመራው የህጻናቱን እድገት ክትትል የሚያደርግ #ነው ብለዋል።

በጤና ማዕከል ሄደው መታከም ለማይችሉ ህጻናት ነጻ ምርመራ መደረጉን የገለጹት አቶ ይርዳቸው ሆስፒታሉ ሙሉ ቁሳቁስ ይዞ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ግቢ በመገኘት የበጎ ፍቃድ ስራውን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ሳምራዊት ተፈራ በሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው።

ለእነዚህ ህጻናት የጤና ምርመራ እንዲደረግ በቀረበ ጥሪ መሰረት ተግባራዊ እያደረጉ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በዚህም የህጻናቱ እድገት፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ኤችአይቪ፣ የመሳሰሉት ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑንም አክለዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አዲስ #ጫማ - 1000 ብር
#አዲስ #ደብተር- 720 ብር
#አዲስ #ቦርሳ- 500 ብር
የፅፈት መሣሪያዎች 204 ብር
አካውንት ቁጥሮች
የብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን
#ንግድ_ባንክ 1000414483228
#ብርሃን ባንክ 1600550004325
የዊን ሶልስ ፎር ጓድ ኢቫንጀሊካል ሚኒስትሪስ
ንግድ ባንክ 1000000391526
ብርሃን ባንክ 1000835472170
ለበለጠ መረጃ
+251929917573
+251912156166 ይደውሉ
#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የቦሌ #አማኑኤል ህብረት #ቤተክርስቲያን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የተስፋ #ብርሃን የምገባ ማዕከል ማዕድ የማጋራት መርኃግብር አካሂዷል።

ከአስርት አመታት በላይ በዚህ የበጎ ፍቃድ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን የተናገሩት የቦሌ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ፓስተር አመሉ ጌታ ዘንድሮም ይህንን አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

በበጎ ፍቃደኞች የሚከናወኑ መሰል ተግባራት አቅም ያነሳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ዓመትን ብቸኝነት እንዳይሰማቸውና ከጎናቸው ሰው እንዳለ እንዲሰማቸው ያደርጋልም ብለዋል።

#አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ1ሺ 200 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ማዕድ ማጋራታቸውን የተናገሩት ፓስተር አመሉ፣ መሰል በጎ ተግባር ከሚሰጠው የህሊና እርካታ በተጨማሪ ከፈጣሪ የሚሰጠው በረከት ሀገርን የሚያሻግር መሆኑን ገልፀዋል።

መርዳትን ሳይሆን ማካፈልን ባህል አድርገን ልንሰራ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።