The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አሜሪካ

ራንክሊን ግራሃም በፍርድ ቤት አሸነፈ።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ወንጌላዊው ፍራንክሊን ግራሃም በዚህ ሳምንት ትልቅ የሃይማኖት ነፃነት ድል አስመዝግበዋል። የስኮትላንድ ፍርድ ቤት ድርጅታቸው ኢፍትሃዊ እና ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ ይስተናገዳል በማለት ከባድ ብይን ሰጥቷል።

የቢሊ ግራሃም የወንጌላውያን ማህበር በ2020 በእስኮትላንድ ሊያከናውን የነበረውን ትልቅ ዝግጅት መሰረዙን ተከትሎ ነው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የሄደው ባሳለፍነው ሰኞም 280 ገጾችን በያዘው ዝርዝር ውሳኔ ተሰቷል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ወንጌላዊ ግሬሃም ምስጋናውን በመግለጽ እና “በዩናይትድ ኪንግደም የመናገር እና የሃይማኖት ነፃነት ግልጽ ድል" ሲል ተናግሯል።
#የዛሬ #ዓመት #በዚህ #ሰዓት
#እግዚአብሔር #ዉሳኔዉን #ወስኗል

የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት በሀገረ አሜሪካ ፅንስ የማቋረጥ መብት ተሽሮ የብዙ ክርስቲያኖች ደስታ እጥፍ ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ሁለቱ የቀድሞ እና የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በወቅቱ ምን አሉ?

#ፕሬዝዳንት_ጆ_ባይደን ውሳኔውን “ቀይ ስህተት” ያሉት ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ “የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲሉ ተችተዋል።

“ውሳኔው የአክራሪ አስተሳሰብ ውጤት ነው። በጣም አሳዛኝና የተሳሳተ ውሳኔ ነው” ብለዋል። ፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈቀድባቸው ግዛቶች ተጉዘው ፅንስ የሚያቋርጡ ሴቶች ክልከላ እንዳይጣልባቸው እንደሚሠሩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዉ ነበር።

ጉዳዪን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው የቀድሞ የአሜሪካ #ፕሬዝደት_ዶናልድ_ትራምፕ በበኩላቸው “እግዚአብሄር ውሳኔውን ወስኗል” ብለዋል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለአምስት አስርት አመታት የዘለቀውን እልባት ያገኘ ህግን ከሻረ በኋላ ፅንስ የማቋረጥ ብሄራዊ መብትን ለማቆም “አምላክ ውሳኔ ወስኗል” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ ከ6-3 በሆነ ድምጽ በድምጽ ብልጫ ካገኘ በኋላ እያንዳንዱ ግዛቶች ፅንስን በማስወረድ ላይ የራሳቸውን ህጎች እንዲያደርጉ መፍቀድ አለባቸው ብለዋል።

#ይህ #ከሆነ #ድፍን #አንድ #አመት ሞላዉ።
#አሜሪካ #ዛሬም #ምንም #እንኳን #In #God #We #trust ቢሉም ...
#አሜሪካ #ሜሪላንድ

በአሜሪካ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን ከሰሞኑን ያሉበት ስቃይ የሁላችንንም #ፀሎት ይሻል። ካለበለዚህ የነገ ኢትዮጵያውያን #ልጆች እጣ ፈንታ አስፈሪ ነው።

ከሰሞኑ "የሞንጎምሪ የህዝብ #ትምህርት ቤቶች" ባወጣው #መግለጫ የተመሳሳይ ፆታና ተጓዳኝ አርዕስቶችን የያዙ ከ22 በላይ መፅኃፍትን በስርዓተ ትምህርት እንዳካተተ አስታውቋል::

ታዲህ #ይህ #ዜና ለወላጆች በተለይም ለኢትዮጵያውያን የራስ ምታት ሆኖ ሰንብቷል። በፈቃደኝነት የተሰባሰቡ የሞንጎምሪ ካውንቲ ወላጆችና ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች ባሳለፍነው ማክሰኞ Hungerford Dr. Rockville, MD የተቃውሞ ሰልፍ አከናውነዋል።

በወቅቱ የሰልፉ አላማ የካውንቲው የትምህርት ቦርድ ከpre-k ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትንና ጾታ መቀየርን የሚያስተማርና የሚያስተዋውቅ፤ ተማሪዎችም ያለወላጅ ፈቃድ ጾታቸውን መቀየርን የሚደግፍና የሚያበረታታ ስርዓተ-ትምህርት ቀርጾ እየተገበረ በመሆኑና ይህንንም ያለወላጅ ፈቃድ የሚተገበር ስርዓተ-ትምህርት ለመቃወም የተጠራ ነበር።

ምንም እንኳን አንዳንዶች በቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ ጥረት ሲያደርጉ አካውንታቸው እየታገዱ ማስተላልፈ ባይቻልም የተወሰኑ ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውት ዘግበውታል።

በዚህ ሰልፍ ላይም ወላጆች ልጆቻቸውን ከእንደዚህ አይነት ትምህርቶች ያለመሳተፍ መብታቸው እንዲጠበቅ ሲጠይቁ ተስተውሏል።

የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ይህንን ሃሳብ የማይደግፉ ሌሎች ቤተሰቦች ተሳትፈዋል።

ነገር ግን የሚያሳዝነው ወላጆች ልጆቻቸውን ከእነዚህ ትምህርቶች እንዲመርጡ ደጋግመው ቢጠይቁም፣ ተማሪዎቹ በእነዚህ ትምህርቶች ውስጥ “መሳተፍ” እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ቤቱ ቦርድ ገልጿል።
#አሜሪካ

እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል

በተደጋጋሚ እምነት አልባ ትውልድ እየተነሳ ነው በሚባልባት ምድረ አሜሪካ አሁን ደግሞ በእግዚዓብሔር እናምናለን የሚል #ወጣት ትውልድ እየተነሳ ነው።

በ2001 በተደረገ ጥናት እድሜያቸው ከ18-34 የሚገኙ መካከል 90 በመቶው በእግዚአብሔር አማኝ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። ከ21 ዓመታት በኋላ በተደረገው ተመሳሳይ ጥናት ደግሞ ቁጥሩ ወደ 59 በመቶ ወርዷል።

መረጃውን የተመለከቱ የሃገሬው #ክርስቲያን ጋዜጠኞች ይሄ በሃገሪቱ ኢ-አማኒ ነኝ፣ በእግዚአብሔር አላምንም እና የህብረት አምልኮን የማይፈልጉ ሰዎች ቁጥር መብዛትን ለተመለከተ ይሄ መሆኑ ብርቅ አይደለም ብለዋል።

ሰው እንደ ሲኦል፣ ሰይጣን፣ ገነትና መላዕክትን በተመለከተ የሚያንጸባርቀውን አስተሳሰብ ስትመለከት ደግሞ ቀድሞውኑ ወዴት እየሄድን እንደነበርን ጠቋሚ ነበር ተብሏል።
የቀድሞው የ #አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ #ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።

ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

#ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

ትራምፕ ዝርዝር #ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።

“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ God Bless The USA Bible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

#አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።
#አፍሪካ

አፍሪካ ባለፉት 150 አመታት በርካታ ክርስቲያናት ያሉባት አህጉር ሆናለች።

በ1900 #ላይ በአለም ካለው #ክርስቲያን 82 በመቶው፣ በሰሜን የአለም ክፍል፣ አውሮፓ እና #አሜሪካ ይገኝ ነበረ። በተቃራኒው ደቡባዊ የአለም ክፍል አፍሪካ፣ እስያና ላቲን አሜሪካ ደግሞ 18 በመቶ ብቻ ነበረ።

#አንድ #መቶ አመታትን #ወደ ፊት፣ ሰሜኑ አለም 33 በመቶው #ብቻ ክርስቲያን ሲሆን፣ ደቡቡ የአለም ክፍል ደግሞ 67 በመቶ ክርስቲያን ነው።

በጋና አክራ፣ በተካሄደ አለም አቀፍ የክርስቲያኖች ፎረም፣ በአለም ላይ የክርስትና ህዝብ ነክ ቁጥር ትልቅ ለውጥ ማሳየቱ ተነስቷል። ከኤፕሪል 16-20 በነበረው በዚህ ፎረም ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ከ240 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በዚህ ለውጥ ውስጥ ሴቶች ያላቸው ሚና እጅግ ታላቅ ነው ተብሏል። ወደፊት በተቀመጠ ትንበያ መሰረት ደግሞ በ2050፣ 77 በመቶ ክርስቲያኖች በደቡቡ የአለም ክፍል የሚኖሩ ይሆናል።

እነዚህ የአሃዝ ለውጦችና ትንበያዎች ወደፊት የክርስትና ማዕከል የትኛው የአለም ክፍል እንደሚሆን ያሳያል ተብሏል።

ለአብነት በአውሮፓና አሜሪካ የክርስትና ቁጥር በፍጥነት እየቀነሰ ሲሆን፣ በተቃራኒው በአፍሪካና እስያ ደግሞ በፍጥነት እያደገ