The Christian News
5.37K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አሜሪካ #ሜሪላንድ

በአሜሪካ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን ከሰሞኑን ያሉበት ስቃይ የሁላችንንም #ፀሎት ይሻል። ካለበለዚህ የነገ ኢትዮጵያውያን #ልጆች እጣ ፈንታ አስፈሪ ነው።

ከሰሞኑ "የሞንጎምሪ የህዝብ #ትምህርት ቤቶች" ባወጣው #መግለጫ የተመሳሳይ ፆታና ተጓዳኝ አርዕስቶችን የያዙ ከ22 በላይ መፅኃፍትን በስርዓተ ትምህርት እንዳካተተ አስታውቋል::

ታዲህ #ይህ #ዜና ለወላጆች በተለይም ለኢትዮጵያውያን የራስ ምታት ሆኖ ሰንብቷል። በፈቃደኝነት የተሰባሰቡ የሞንጎምሪ ካውንቲ ወላጆችና ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች ባሳለፍነው ማክሰኞ Hungerford Dr. Rockville, MD የተቃውሞ ሰልፍ አከናውነዋል።

በወቅቱ የሰልፉ አላማ የካውንቲው የትምህርት ቦርድ ከpre-k ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትንና ጾታ መቀየርን የሚያስተማርና የሚያስተዋውቅ፤ ተማሪዎችም ያለወላጅ ፈቃድ ጾታቸውን መቀየርን የሚደግፍና የሚያበረታታ ስርዓተ-ትምህርት ቀርጾ እየተገበረ በመሆኑና ይህንንም ያለወላጅ ፈቃድ የሚተገበር ስርዓተ-ትምህርት ለመቃወም የተጠራ ነበር።

ምንም እንኳን አንዳንዶች በቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ ጥረት ሲያደርጉ አካውንታቸው እየታገዱ ማስተላልፈ ባይቻልም የተወሰኑ ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውት ዘግበውታል።

በዚህ ሰልፍ ላይም ወላጆች ልጆቻቸውን ከእንደዚህ አይነት ትምህርቶች ያለመሳተፍ መብታቸው እንዲጠበቅ ሲጠይቁ ተስተውሏል።

የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ይህንን ሃሳብ የማይደግፉ ሌሎች ቤተሰቦች ተሳትፈዋል።

ነገር ግን የሚያሳዝነው ወላጆች ልጆቻቸውን ከእነዚህ ትምህርቶች እንዲመርጡ ደጋግመው ቢጠይቁም፣ ተማሪዎቹ በእነዚህ ትምህርቶች ውስጥ “መሳተፍ” እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ቤቱ ቦርድ ገልጿል።