The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አስደሳች_ዜና 🙏🙏🙏
#ወጣት_አብረሃም_ለህክምና_ቱርክ_ሄዷል
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

አንድ ሰሞን እጅግ ልብን የሚነካ እና ብዙዎች ያስለቀሰ የወጣቱን የአብረሃምን ታሪክ ሰምተን ብዙዎቻችን አዝነን በቻልነው አቅም ሁሉ ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል።

በታሪኩ መላዉ ኢትዬጲያውያን ከመነካታቸዉ የተነሳ ለወጣቱ ህክምና የተጠየቀዉን ሚሊዬን ብሮች በጥቂት ቀናት ተሰብስቦለት ተጠናቀቀ።

በአሁኑ ሰዓት የነበረው ፕሮሰስ ሁሉ ተጠናቆ በአሁኑ ሰዓት በቱርክ ለህክምና የሚያስፈልጋቸውን ምርመራ ኩላሊቱን ከሚደግፈው ልጅ ጋር እያከናወነ ይገኛሉ።

ይህንን ያረጋገጠችልን Betachn ቤታችን አዘጋጅ #Senait_Mulugeta ስትሆን
በሀልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስትያን እሁድ በነበረው መርሃ ግብር በነብይ ዘነበ ግርማ በዛ ስለሚኖረው የህክምና ሂደት ጌታ እየሱስ እንዲቀድምለት አጥብቀው በመጸለይ በዚህም መልካም ስራ የተባበሩትን በውጭም በአገር ውሳጥ ያሉትን ሁሉ ባርከው አመስግነዋል። ስትል በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስፍራለች።

#አሁንም ወጣቱ በእናንተ ቅዱሳን ጸሎት እና የገንዘብ ድጋፍ እዚህ ደርሷል ህክምናው የተሳካ እንዲሆን እና ለምስጋና እንድንገናኝ አሁንም በጸሎታችሁ እንድታግዙት ጥሪ እናቀርባለን።
#እግዚአብሔርን_አመስግኑ
#አብረን_ለማመስገንም_እንዘጋጅ
#ወጣት_አብረሃም_በሰላም_ወደ_ሀገሩ_ተመልሷል

ከጥቂት ወራት በፊት ሁለቱም ኩላሊቱ ተግባራቸውን መለገስ የተሳናቸውን እንዲሁም በዚሁ ምክንያት በተያያዥ በሽታ ማለትም በሳምንት ሁለት ግዜ ብቻ ዲያሊስስ በማድረጉ . . . በርካታ ችግሮች በአንድ ላይ የተጋፈጠ ወጣትን ታሪክ ሰምተን ብዙዎቻችን አዘነን እንደነበር ይታወሳል።

ወጣት አብርሃም ጌታቸው ወደ እስክሪን ከቀረበ በኋላ የእናንተም ቅጽበታዊ ምላሽ በፍጥነት ከተጠየቀው ገንዘብ በላይ እንዲያገኝ አግዞት ወደ ቱርክ ለቀዶ ህክምና ከሁለት ወንድሞቹ ጋር እንደሄደ የሚታወስ ነው!

በዛም ያለው ቆይታቸው ብዙ ፈተና ቢበዛውም ከቤተክርስትያን ጀምሮ በእናንተንም ጥብቅ ጸሎት ያሉትን ችግሮች ሁሉ አቅም ያሳጣ የእግዚአብሄር ደግነትና ምህርት ፈጥኖለት በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገናውን አድርጎ አሁን እሱም እንዲሁም ኩላሊቱን የሰጠው ወንድሙ ጌድዮን ጌታቸውም በጥሩ ጤንነት በሰላም ወደ ሀገራቸው በዛሬው እለት ገብተዋል።

የክርስቲያን ዜና ከ ቤታችን ቴሌቪዥን ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በኢትዮጵያ አየር ማረፊያ ተገኝተን ከወዳጅ ቤተሰቦቹ ጋር መልካም አቀባበልን አድርገንለታል።

እሱም ለቅዱሳን አጭር መልዕክት በቪዲዮ ያስተላለፈ ሲሆን እሱን በዝርዝር በቪዲዮ ዜና ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።

በቅርብ ቀን ደግሞ በቤታችን ቲቪ ሙሉ ቃለ መጠይቁን በተለይም በቱርክ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ተወዳጅ ቆይታ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
ምንም አይነት ወጣት በገንዘብ ማጣት ምክንያት ከመልካም ወጣት ፕሮግራም አይቀርም።

በትላንትናው እለት የ2015ዓ.ም መልካም ወጣትን በማስመልከት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዘንድሮ መልካም ወጣት ምዝገባ ምንም እንኳን 1500 ብር እንደሆነ ቢገለጽም ስልጠናውን መካፈል ፈልገው ነገር ግን ምንም ገንዘብ የለንም በሚል ምክንያት ከመሳተፍ እንደያግዳቸው ተገልጿል።

የአዲስ ኪዳን ካሕናት ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በመግለጫው እንደጠቀሱት ከሆነ መሳተፍ ፈልገው ገንዘብ የሌላቸው ወጣቶች ወደ ቢሮ በመምጣት በመመዝገብ መሳተፍ እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

"የመልካም ወጣት አገልግሎት የተዘጋጀው ለሱሰኞች ብቻ አይደለም ነገር ግን በውስጣቸው ራዕይ ላላቸው ወጣቶች ጭምር የተዘጋጀ አገልግሎት ነው" ያሉት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በዘንድሮው መልካም ወጣት ለሀገር እና ለቤተሰብ ጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚሰሩ በመግለጫው ጠቅሰዋል።

"እንቀጥላለን አልያም እንቀጣጠላለን"

#መረጃ #መልካም #ወጣት
#አዲስ #ኢትዮጵያ #ኢየሱስ
ከቀኑ 6:00 ምንድ ነው?

የ2015ዓ.ም የዘንድሮ #መልካም #ወጣት መሪ ቃል ከቀኑ 6:00 ሰዓት የሚል መጠሪያ ተሰቶታል።

ለመሆኑ ከቀኑ 6 ሰዓት ምንድነው? ለምንስ ይህ መሪ ቃል ተመረጠ?

ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመሸጋገሪያ ሰዓት ነው። የለውጥ ፤ ጠዋት ለከሰዓት ሰዓቱን የሚለቅበት የሽግግር ፤ የዕርቅ ሰዓት ነው። በዩሐንስ ወንጌል መጽሐፍ በሳምራውያን እና በአይሁዳውያን መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ ሊፈርስ ሳምራዊቷ ሴት እና ኢየሱስ የተገናኙበት ሰዓት ነው።

ስለዚህ ከቀኑ 6:00 ሰዓት የልውጥ የሽግግር ፤ የእርቅ ፤ የፍቅር ሰዓት ነው። መልካም ወጣት የሚያተኩረው ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ ነው። መንፈሳዊ ፤ ስነልቦናዊ አካላዊ ለውጥ ማምጣት ነው።

የመልካም ወጣት አገልግሎት የተዘጋጀው ለሱሰኞች ብቻ አይደለም ነገር ግን በውስጣቸው ራዕይ ላላቸው የተዘጋጀ አገልግሎት ጭምር ነው።

የዘንድሮ መልካም ወጣት ለብዙ በአሉታዊ ነገር የሚታወቁ ወጣቶች ከአሁን በኋላ በመልካም ነገር የሚታወቁት በአዲስ መንገድ ይሆናል።

የመልካም ወጣት ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።
#አሜሪካ

እግዚአብሔርን የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል

በተደጋጋሚ እምነት አልባ ትውልድ እየተነሳ ነው በሚባልባት ምድረ አሜሪካ አሁን ደግሞ በእግዚዓብሔር እናምናለን የሚል #ወጣት ትውልድ እየተነሳ ነው።

በ2001 በተደረገ ጥናት እድሜያቸው ከ18-34 የሚገኙ መካከል 90 በመቶው በእግዚአብሔር አማኝ እንደነበረ መረጃዎች ያሳያሉ። ከ21 ዓመታት በኋላ በተደረገው ተመሳሳይ ጥናት ደግሞ ቁጥሩ ወደ 59 በመቶ ወርዷል።

መረጃውን የተመለከቱ የሃገሬው #ክርስቲያን ጋዜጠኞች ይሄ በሃገሪቱ ኢ-አማኒ ነኝ፣ በእግዚአብሔር አላምንም እና የህብረት አምልኮን የማይፈልጉ ሰዎች ቁጥር መብዛትን ለተመለከተ ይሄ መሆኑ ብርቅ አይደለም ብለዋል።

ሰው እንደ ሲኦል፣ ሰይጣን፣ ገነትና መላዕክትን በተመለከተ የሚያንጸባርቀውን አስተሳሰብ ስትመለከት ደግሞ ቀድሞውኑ ወዴት እየሄድን እንደነበርን ጠቋሚ ነበር ተብሏል።
#ሬማ በድምቀት #ተመረቀ

ለዝማሬ አገልግሎት ከፍተኛ አሶተዋፅኦ የሚሰጥ ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ሚያዚያ 12 ቀን 2016ዓ/ም ተመርቆ ለአገልግሎት በቃ።

የስቱዲዮዉ ባለቤት ሙዚቀኛ ዳዊት ወርቁ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለረዥም አመታት ያገለገለ #ወጣት አገልጋይ ሲሆን ሬማ ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በዋነኝነት ተማሪዎችን እና የዝማሬ ፀጋ ያላቸዉን ለማገልገል የተዘጋጀ መሆኑን ገልፃል።

በምረቃ ስነስረአቱ ላይ ስቱዲዮዉን በፀሎት የመረቁት አፖስትል ብስራት ብዙአየን(ጃፒ) “አሁንም ቤተክርስቲያን ለሙዚቀኞች ትኩረት ልትሰጥ ይገባል የቤተክርስቲያን ሙዚቃ የአለምን ሙዚቃ መዋጥ አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወንድማችን ሙዚቀኛ ዳዊት የተሰማን ደስታ እንገልፃለን።
#መልካም #ወጣት ወደ ብርታት...

በዘንድሮ መልካም ወጣት 30ሺ ወጣቶችን ለማሰልጠን ዝግጅት ተጠናቋል።

የኢትዮጲያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ-ክርስቲያን "በመልካም ወጣት" በሰባት አመት 180ሺ ወጣቶችን ማሰልጠን እንደተቻለ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ዛሬ ሐምሌ 09/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ተገልጿል።

ቤተ ክርስቲያኗ በየአመቱ የምታካሂደው የመልካም ወጣት መርሃ ግብር ዘንድሮም "መልካም ወጣት ወደ ብርታት" በሚል መሪ ሃሳብ በዚህ አመትም 30ሺ ወጣቶችን በሐዋሳ ለማሰልጠን እንደተዘጋጁ ፓስተር ዮናታን ገልጿል።

በሐዋሳ ከተማ ከ1.2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ፓስተር ዮናታን ተናግሯል፣ ቀሪው በሁለት አመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብሏል።
በተጨማሪም በወላይታ ሶዶ የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን በ100ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ በ50 ሚሊዮን ብር ጥራቱን የጠበቀ በሱስ የተጠቁ ወጣቶች የማገገሚያ ተቋም የሚሆን እና ለመቶ ሺዎች ተደራሽ መሆን የሚችል የሆስፒታል ግንባታ እንደተጀመረ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

በዘንድሮ መልካም ወጣት ምዝገባ ለአንድ ሰው 1,500 ብር መሆኑ ተገልጿል።
👉የቀድሞ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ዛሬ

#መልካም ወጣት ላይ ለብዙዎች ምስክር ለመሆን እና ሱስ ምን ያሕል ብዙዎችን እንደሚያወርድ ምስክርነት ሰጥቷል።

#ወጣት በረከት አዲሱ ብዙዎች የአዳማ ከነማ ወደ ፕሪሜር ሊግ እንዲቀላቀል በ2006 የዋለውን ውለታ ብዙዎች ያስታውሱታል።

በ1997 ወጣት ብሔራዊ ቡድንን አሻንፎ ዋንጫ ይዘው ሲመለሱ የማሸነፊዋን ጎን ያገባ ወጣት ነበር።

በ2001 ከ100ሺህ ብር በላይ እየተከፈለው ይጫወት ነበር። #ዛሬ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በሱስ ውስጥ ተደብቆ ነበር!!

አቤት ሱስ😭😭
ኢየሱስ ነፃ ያወጣል ከሱስ!