The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የሁለት_አመት #ልጅ #የእድሜ ልክ_እስራት_ተፈረደበት
70,000 የሚጠጉ #ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት #ታስረዋል

The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የ2ዓመት ሕጻንን ጨምሮ ቤተሰቦቹ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።

ይህ የሆነው በሰሜን ኮርያ ነው። ለክርስትና ከማይመቹ እና እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል በ1ኛ ስፍራ የምትገኘው #ሰሜን ኮርያ #አዲስ #ዜና ተሰምቷል።

በሰሜን ኮሪያ አንድ የሁለት #ዓመት #ልጅ እና መላው ቤተሰቡ ባለሥልጣኖች በልጁ ወላጆች እጅ #መጽሐፍ #ቅዱስ ማግኘታቸውን ተከትሎ የእድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ዲፓርትመንት የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን የ2022 ዓመታዊ ሪፖርቱን ገልጿል።

ሰሜን ኮሪያ “ሰዎችን በሃይማኖታዊ ተግባራቸው ምክንያት መግደሏን፣ ማሰቃየትን፣ ማሰርን እና አካላዊ ማጎሳቆሏን ቀጥላለች። በሰሜን ኮሪያ ወደ 70,000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።

"አግኖስቲዝም" እምነትን የምትከተለዉ ሰሜን ኮርያ ካላት ሕዝብ 400 ሺዎቹ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ይነገራል።

ከፈረንጆቹ 2022 ዉጪ በተከታታይ አመታት ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ በመባል በ1ኛ ደረጃ ተቀምጣ ቆይታለች።
#ቤተክርስቲያን ዉስጥ #አንድ ሰዉ ተገደለ።

እውቁ አሜሪካዊ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን የምትመራው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተከፈተ ጥቃት የአንድ #ሰው ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ሌክዉድ ቹርች በመባል በምትታወቀው በዚህች ቤ/ክ ውስጥ ነው ትላንት የሰንበት ፕሮግራም ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው። ጥቃት አድራሿ #ሴት ስትሆን በወቅቱ ስራ ላይ ባልነበሩ ፖሊሶች ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ጥቃቱን ባደረሰችበት ወቅት የ5 #አመት ህጻን #ልጅ ይዛ እንደነበረም ተነግሯል። ህጻኑም ጉዳት ደርሶበት የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል። በጥቃቱ እስካሁን አንዲት ሴት #ብቻ ናት እግሯ ላይ በጥይት የመታችው እና ጉዳት የደረሰባት።

የቤ/ክኗ መሪ ፓስተር ጆዬል ኦስቲን እንደዚህ ባለ የጨለማ ጊዜ፣ እምነታችን እንጠብቅ መቼም ቢሆን ጨለማ አያሸንፍም #እግዚአብሔር በብርሃን ይመራናል ሲል ለክርስቲያን ፖስት ተናግሯል። በዚህ ወቅትም በፍቅር እና በመያያዝ አብረን መቆም ይገባናል ብለዋል።

ጥቃት አድራሿ በተኩሱ ወቅት ቦምብ ይዣለው በማለት ስታስፈራራ እንደነበረና መርዝ ነው እያለች ስፕሬይ ስትረጭ ነበረ ብሏል ፖሊስ ባደረገው ምርመራ።

ሌክዉድ ቸርች በአሜሪካ ቴክሳስ ሂውስተን የምትገኝ ሲሆን፣ መሪዋ ጆዬል ኦስቲንም በስህተት ትምህርት ስሙ ደጋግሞ ሲነሳ ይታወሳል። ዘገባዉ የThe Christian Post ነዉ።
ሰላሌ ቢቸግረው ነው!! ሰላሌ ኮ!

ድሮ #ልጅ ሆነን ምድሪቱ ላይ ዝናብ ሲጠፍ ሰማዩ ሲቆጣና ዝናቡን ሲነፍገው በሞሎክሴዎ የዝንበላቸው እናት አስተባባሪነት ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት ቀየው ሁሉ ከቦሶቄ:አባዳካ :ኩማንዶ :ዶዩ ገንደጉዳ...ከሚባል ያለ ነዎሪ ሁሉ ያኔ ዘር ፃታ እድሜ ሳይለይ ሁላችንም ፊታችንን ወደ አለተ ማርያም አቅጣጫ በማዞር በዝንበላቸው #እናት መሪነት እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በዜማ ሲሉ እኛም እየተቀበልን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ኪራላይሶ ኦክርስቶስ ኦክርስቶስ ኦ አምላክ እያልን የዝናቡን አምላክ ዝናቡን እስኪሰጠን ሁሌ ምሽት በእሚያራራ ዜማ የስማዩን አምላክ እንማፀነው ነበር።

አንዳንድ እናቶች ድንጋይ በትከሻ ይዘው ምድር እንዳትራብ ከብቶች እንዳይሞቱ ሰላሌ አምላኩን ዘር ሳይለየው ቆለኛ ከደገኛ ተቀላቅሎ ሲፀልይ ከነ ዜማው አሁን ድረስ ድምፁ በልቦናዬ ይሰማኛል።

በቀደም ሰላሌ ሰውና በሬ ልጁንና እንሰውን ጠምዶ ከፍቶት ሊፀልይ አምላኩን ሊለምን አደባባይ ተሰበሰበ።

አሁን ግን ለዝናብ አይደለም ዝናብ አለ በየቀኑ ይዘንባል ሰላሌ ካረሰ ሶስት አመት ሆኖታል ሰላም ሰላም እያለ ይለምናል።

አምላክ ሆይ ሰላሌን ተለመነው አርሶ ዘርቶ ይኑር።

ሰላሌ ቢክፍው ነው። ሰው እና እንሰሳ አንድ ላይ ጠምዶ የለመነህ። ዛሬ የዝንበላቸው እናት የሉም ያኔ የለሙኑ አባቶች እና እናቶች የሉም ሰላሌ ዛሬ ዝናብ ሳይሆን ሰላም ማጣቱን ሳያዩ ወደ አንተ ተሰብስበዎል።

ሰላሌ ዛሬ ዝናብ ሳይሆን ዝናብ ያጨቀየው መሬት ላይ ቆሞ ሰላም ይለምናል:: ዝናብ እያለ ማረስ እንዳልቻለ አባቶቹ አላዩም። ልጅ ልጆችቻቸው ሰላም ለመለመን ይህው እግዚኦ እያሉ ነው ያኔ የተለመንካቸው ዛሬ ተለመናቸው አሜንንን 🙏🙏🙏

መጋቢ ሔኖክ ሲንገሌ