STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
"...ተማሪዎቻችንን ለመመለስ ሌትና ቀን የሐይማኖት ቦታዎችና የተማሪዎች መኖሪያ ድረስ በመግባት ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን!" - ጅማ ዩኒቨርሲቲ

#JimmaUniversity

መልካም ምክራችሁን ለወንድምና እህቶቻችሁ በመለገስ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርት እንዲጀምሩ ከፍተኛ ጥረት ለምታደርጉ የተማሪዎች ህብረት፣GDASAO ክበብ አባላት እና ቅን ልቦና ያልተለያችሁ ውድ ተማሪዎቻችን እንዲሁም አባገዳዎች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ወቅቱ የሚፈልገውን በማድረግ ላይ ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የደረሱትን የሞት፣ የአካልና የስነልቦና ጉዳቶች በከፍተኛ ደረጃ እያወገዝን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ስንገልጽ በርካታ አስተዋይ ልቦና ያላቸው ሰዎች አጠገባችን በመሰለፋቸው እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ተማሪዎቻችን ለመመለስ ሌትና ቀን የሐይማኖት ቦታዎችና የተማሪዎች መኖሪያ ድረስ በመግባት ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡

ውድ ተማሪዎቻችን በተከታታይ ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች እየተጠናቀቁ ስለሆነ በቅርቡ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን!

Via #(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)
@nationalexamsresult
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጠይቀው የነበረውን ጥያቄዎች ለሚመለከተው አካል ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡በተጨማሪም ከነገ ጀምሮ ሁሉም ተማሪ በትምህርት ገበታው ላይ እንዲገኝ አስጠንቅቋል፡፡

Via መረጃ

@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ JIT ግቢ በሮች አሁንም እንደተዘጉ ነው፡፡ተማሪዎችም እንዲከፈትላቸው እየጠየቁ እንደሆነ እና በሩ ይከፈት በሚል ሰበብ ሌላ ግጭት እንዳይነሳ መፍራታቸውን ገልፀዋል፡፡

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ !

#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም እያስመረቀ ነው።

የዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ 3013፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

#KebridharUniversity

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ለዚሁ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የፌዴራል እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ትላንት ወደቀብሪድሃር መጓዛቸው ይታወቃል።

#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 338 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 3,950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 530 ሴቶች ናቸው። በ2ተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ 3 ተማሪዎች በ3ተኛ ዲግሪ እና 4 ተማሪዎች ደግሞ የ 'ሰብ ስፔሻሊቲ' ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 24 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

#KotebeMetropolitanUniversity

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ 2039 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፤ 1 ሺህ 104 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 222 በ2ኛ ዲግሪና 711 በዲፕሎማ።

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ SRTV፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ኤፍ ቢሲ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23,192 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

መረጃውን በማጋራት ላልሰሙ እናሰማ


ለበለጠ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JimmaUniversity

የጂማ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥቅምት 22/2014 መሆኑን ከጂማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ተራዝሟል‼️

ጥቅምት 22/2014 እና ጥቅምት 23/2014 የነበረው የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ እና ድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ #ህዳር 06/2014 እና #ህዳር 07/2014 መራዘሙን ከዩንቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#JIMMAUNIVERSITY

የጂማ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን #ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

Waamichi yuunibarsiitii jimmaa yeroo hin murtoofneef dheeraffameera

@NATIONALEXAMSRESULT
#JimmaUniversity

ተራዝሞ የነበረው የ2014 የትምህርት ዘመን ምዝገባቸው በመጪው ህዳር 20 እና 21/14 የሚካሄድ ስለሆነ ትምህርታችሁን በምትከታተሉባቸው የኮሌጅ ወይም የኢኒስቲትዩት ሬጂስትራር ጽህፈት ቤቶች በግንባር በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድትፈፅሙ ተብላቹሃል። #ጅማ_ዩኒቨርሲቲ

@nationalexamsresult
#Update
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 04 እና 05/2014 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚያደርጉባቸው እና ትምህርታቸውን የሚከታተሉባቸውን ካምፓሶች ዩኒቨሲቲው አሳውቋል።

Freshman Social Science, Freshman Teachers Education in Social Science እና
Freshman Teachers Education in Natural Science የተመደባችሁ በዋናው ግቢ።

Freshman in Natural Science የተመደባችሁ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት እና በጅማ ግብርና እና ሕክምና ኮሌጅ ካምፓሶች።

https://portal.ju.edu.et ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ እንደምትችሉ ተገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የነባር እና አዲስ ገቢ #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 18 እና 19/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 211 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት እና በሳምንት መጨረሻ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ግዜ በ'Water Resource Engineering', በ 'Reproductive Health' እና በ 'Climate Change Adaptation and Mitigation' በሦሥተኛ ዲግሪ እንዲሁም በ 'Gastro-Intestinal Cancer Treatment' በሰብ ስፔሻሊቲ ዲፕሎማ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።

ከዛሬው ተመራቂዎች መካከል በሶማሊላንድ ሀርጌሳ በሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 30 የሶማሊላንድ ዜጎች ይገኙበታል። #ጅዩ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JimmaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል።)


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JimmaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ10ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

የተመደባችሁበትን ካምፓስ ለማየት ተከታዩን ሊንክ ተጠቀሙ ➧ https://portal.ju.edu.et

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JimmaUniversity

በ2016ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት በመደበኛ ፕሮግራም ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ 👉ምዝገባችሁ በመጪው ጥር 27 - 28/2016ዓ.ም በዩኒቨርስቲው በተመደባችሁባቸው ካምፓሶች ማለትም የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በአጋሮ ካምፓስ (አጋሮ ከተማ ላይ) እና የሶሻል ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ደግሞ በጅማ ግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ (ጅማ ከተማ ላይ) እንደሚካሄድ እየገለጽን ለምዝገባ ስትቀርቡ የሚከተሉትን መረጃዎች አሟልታችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፤

1. የ12ኛ ክፍል ኦሪጅናል የት/ት ማስረጃ ከአንድ ኮፒ ጋር
2. ለመታወቂያ የሚሆን ጉርድ ፎቶግራፍ
3. ብርድልብስ፤ አንሶላ፤ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot