STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ አመት መደበኛ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
ከዚህ በፊት በተገለፀው የመግቢያ ቀን ከመስከረም 25 - 27 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የተማሪዎች ምደባ ዘግይቶ በመገለፁ ምክንያት የመግቢያውን ቀን ማራዘም አስፈልጓል። በዚሁ መሠረት የምዝገባው ቀን ከጥቅምት 3 - 5 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

#share and join
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ08-12/2012 ዓ/ም ትምህርት አይኖርም በማለት አንድ አንድ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ደርሼበታለሁ፤ እንዲያህ ያለ ነገር እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል። በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ግቢው ለቀው እየወጡ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ አረጋግጠናል ብሏል ተቋሙ። የትምህርት ስርዓቱ እንደማይቋረጥ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ጥለው የሄዱ ተማሪዎችም በትምህርታቸው ላይ በሚደርስባቸው እክል ሃላፊነቱን እራሳቸው ይወስዳሉ ሲል ገልጿል።

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው 6,263 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 4,119 ወንዶች ሲሆኑ 2,144 ሴቶች ናቸው።

ተመራቂዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የክብር እንግዶች የስነ ስርዓቱ ተሳታፊ ናቸው።

PHOTO : SRTA


#SHARE
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23,192 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

መረጃውን በማጋራት ላልሰሙ እናሰማ


ለበለጠ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜን አሳውቋል።

የአንደኛ ዓመት መደበኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 18 እና 19/2014 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

የአንደኛ ዓመት የማታና እረፍት ቀናት ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 20 እና 21/2014 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን የተቋሙ ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

[Tikvah]

@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የ2ኛ ሴሚስተር የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

የመደበኛ ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 14 እና 15/2014 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ትምህርት የካቲት 16/2014 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

የዕረፍት ቀናት ፕሮግራም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 16 እስከ 18/2014 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ትምህርት የካቲት 19/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ ሬዝደንት ሀኪሞች ምዝገባ ከየካቲት 22 እስከ 29/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባውን ለማድረግ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር በፖስታ ሳጥን ቁጥር 05 አስቀድሞ ማስላክ ያስፈልጋል።

ኦሬንቴሽን የካቲት 29/2014 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን ትምህርትም በተመሳሳይ ቀን እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
❗️#HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት
ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• የሌሊት አልባሳት
• የስፖርት ትጥቅ

ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
4_5940274679032842609 (2).docx
3.4 MB
#HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ አዲስ የመጀመሪያ ድግሪ መደበኛ ተማሪዎች የOnline ምዝገባ አካሄድ፤
ሙሉ stepu በዚክ pdf አለ ተከተሉት አንድ በአንድ Hawassa University
ድረ-ገጽ
https://sis.hu.edu.et

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች #ዳግም_ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪዎች ሪፖርት የሚያደርጉባቸው ካምፓሶች፦

👉 Natural Science & Teacher Education in Natural Science የተመደባችሁ ~ በዋናው ግቢ፣

👉 Social Sciences & Teacher Education in Social Science የተመደባችሁ ~ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት መሆኑን ዩኒቨርስቲው አሳውቋል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

የ2014 ዓም የተማሪዎች ምረቃ ቀን ከሰኔ 18, 2014 ዓ. ም ወደ ሰኔ 25, 2014 ዓ. ም የተቀየረ መሆኑን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ሰኔ 25/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

ሰኔ 18/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የምረቃ መርሃ ግብሩ "ሀገራዊ በሆነ ምክንያት" በአንድ ሳምንት መራዘሙን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምታለች።

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ እስከ ሦሥተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 6 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

አዲሱ ካሪክለም በመጀመሩ ምክንያት (የዲግሪ መርሃ ግብር ቆይታ ወደ አራት ዓመት ተራዝሟል) የተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ዘንድሮ ምርቃት እንደማይኖር የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክተር ዘሪሁን ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትማቸው ሁለት የምርምር ጆርናሎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ተሰጣቸው።

ዩኒቨርሲቲው ለሚኒስቴሩ እውቅና እንዲሰጣቸው ካቀረባቸው የምርምር ጆርናሎች መካከል በግምገማ ሂደቱ ላይ ያነሳውን ቅሬታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመመርመር ስህተት እንደተሰራ ገልጿል።

ሁለቱ ጆርናሎች “Hawassa Journal of Law” እና “Journal of Science and Development” የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ የግምገማ መስፈርት ያሟሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

በዚህም ሁለቱ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጆርናሎች ለሦሥት ዓመታት የሚቆይ አገር አቀፍ እውቅና ማግኘታቸው ተገልጿል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ የሚያሳትመው ሌላኛው የትምህርት ጆርናል Ethiopian Journal of Education Studies የመጀመሪያ ቅፅ ባለፈው የካቲት ለሕትመት መብቃቱ ይታወሳል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የድህረ ምረቃ ፕግራሞች (2ኛ ዲግሪ እና 3ኛ ዲግሪ) የማመልከቻ ጊዜ እስከ ነሐሴ 06/2014 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#HawassaUniversity

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ሆነው እንዲቀጥሉ ተወሰነ።

ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ ዲራ ደግሞ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተወስኗል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ/ም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው።

ከላይ ከተገለፀው ውሳኔ በተጨማሪ ለአራት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የደረጃ ዕድገት በየደረጃው ተገምግሞ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የፀደቀውን ውጤት ቦርዱ በዝርዝር ከመረመረ በኃላ ጥያቄውን አፅድቋል።

ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑት ፦

- ከወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ፕሮፌሰር መሰለ ነጋሽ በ"Forest Ecology and Agroforestry"

- ከማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ዘለቀ አርፊጮ በ "TEFL"

- ፕሮፌሰር መብራቱ ሙላቱ በ"TEFL" እንዲሁም

- ከተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ጀመረ በቀለ በ"Veterinary Parasitology" ናቸው።

መረጃው ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት እና ለ2015 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም‼️

#ቲክቫህ_ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራርን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጋርቷል።

አሁን ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ገዢው ፓርቲ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝና ስልጠናው እስከ ህዳር 30/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ኃላፊው ገልፀዋል።

በመሆኑም በታህሳስ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው ኃላፊው የገለፁት።

Note:
ከላይ በምስሉ የሚታየው መልዕክት ለነባር መደበኛ ፕሮግራም የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የተላለፈ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።

በነሐሴ 2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ገብተው የነበሩ የ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች፥ ወደ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት መዘዋወራቸውን ተከትሎ
የተላለፈ የምዘገባ ጊዜ መልዕክት መሆኑን ገልፀዋል።

[ዘገባው የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot