STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የ 2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤትን እስመልክቶ ምንም የወጣ ነገር የለም!

ነገር ግን አሁን ባለን መረጃ የፈተናው ውጤት ቶሎ ቢመጣም እንኳን ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ሊቆዩ ይችላሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ከ ትግራይና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተበተኑ ተማሪዎችን ተቀብለው እያስተማሩ ስለሆነ ቦታ የላቸውም።

አሁንም በድጋሚ የ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ና መቅደለ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ይበተናሉ። ስለዚህ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የ አንደኛ አመት ተማሪዎችን ለመቀበል ቦታ አይኖራቸውም።

ሌላው ምክንያት ሁለተኛ ዙር የሚፈተኑ ተማሪዎች ገና ፈተናዎችን አልወሰዱም። ስለዚህ 12ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ትንሽ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

አዲስ መረጃ ሲኖር ተከታትለን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃን።

#Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Share #ሼር

ለጠቅላላ ሀኪሞች የወጣ የኮንትራት ቅጥር ፦

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በዞን ጤና መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ ሀኪሞችን በኮንትራት ቅጥር አወዳድሮ መመደብ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

👉 የስራው መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የሙያ መስመር /ተፈላጊ ችሎታ - በጠቅላላ ህክምና በዲግሪ የተመረቀ/ች
👉 የስራ ልምድ- #ዜሮ_ዓመት
👉 ብዛት - 379 (#ሶስት_መቶ_ሰባ_ዘጠኝ )
👉 ደመወዝ - 9,056
👉 የስራ ቦታ - በእጣ ነው የሚለየው

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በሚመደብበት በማንኛውም ዞን / ልዩ ወረዳ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች።

2ኛ. በዕጣ ከጤና ቢሮ ለዞን/ልዩ ወረዳ ሲመደቡ ዞን/ልዩ ወረዳ በሚሰጠው በማንኛውም ጤና ተቋማ /ምደባ / ቦታ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።

3ኛ. በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ ያልተቀጠረ /ያልተቀጠረች

የመመዝግቢያ ጊዜ ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት። (ከተሰጠው ቀን ውጭ የሚመጣ አይስተናገድም)

የመመዝገቢያ ቦታ ፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ሲሆን ኦርጂናል የትምህርት እና የሙያ ፍቃድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር መያዝ እንዳትዘነጉ።

የፈተናው ቀን : በቀጣይ ይገለፃል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AmharaRegion

የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል።

👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር)
👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ)
👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች
👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ ሀኪም የመጀመሪያ ዲግሪ እና 0 (#ዜሮ) ዓመት የስራ ልምድ
👉 የሞያ ፍቃድ ያለው / ያላት

የመመዝገቢያ ቦታ በአብክመ ጤና ቢሮ እና በሁሉም ዞን ጤና መምሪያዎች ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የዞን ጤና መምሪያዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በማንኛውም ጤና ተቋም ዕጣ በደረሰው ቦታ ላይ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች
2ኛ. ከዚህ በፊት በመንግስት ጤና ተቋም በቋሚ ቅጥር ያልተቀጠረ/ያልተቀጠረች

#ሼር #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#Repost

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህ መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ ነው።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር ይችላል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2014 ዓ.ም ብሔራዊ እና ክልላዊ ፈተናዎች መስጫ የጊዜ ሰሌዳ

🗓 የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም ይሰጣል።

🗓 የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20/2015 ዓ.ም በኋላ ወደፊት በሚለገጽ ቀን የሚሰጥ ሲሆን

ፈተናው ከዚህ በፊት ከተለመደው በተለየ መልኩ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት ይዘት የሚያካትት ሆኖ ይዘጋጃል።

#SHARE

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#አስቸኳይ


ለኮተቤ የትምህርት ዪንቨርሲቲ ተማሪዎች

ለተማሪዎች ሰላም እና ደህንነት ሲባል ከዛሬ ከ21/08/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ቀን ትምህርት የሌለ መሆኑ እና ወደ ግቢ መግባት እና መውጣት የማይቻል መሆኑን እናሳውቃለን በዚህም የተነሳ የዪንቨርሲቲው ተማሪዎች ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሳትረበሹ በጊቢው አዲስ ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች በጊቢው በምትንቀሳቀሱበት ጊዜ የጊቢው ማህተብ ያለበት መታወቂያ ይዛችሁ ተንቀሳቀሱ በተጨማሪም በጊቢው የፀጥታ አካላትን በማዳመጥ የተለመደውን የአብሮነትና የአክባሪነት ትብብራችሁን እንድታሳዪ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

#SHARE

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
📌 ወለጋ ጠርቷል !

#Share

📚 Sagantaan simannaa barattotaa haaraa kan Yunvarsitii Wallaggaati Ramadaman gaafa Caamsaa guyyaa 15-17/2014 kan raawwatamu ta'uu kabajaan isin beeksifna.

📚 በወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች ቅበላ የሚከናወነው ግንቦት 15-17/ 2014 መሆኑን እናሳውቃለን።

📚 ሙሉ ጥሪው በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ በTV እና በሬድዮ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ኦፊሰላዊ ማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል የሚተላለፍ ስለሆነ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን። ዩኒቨርሲቲያችንም በጥሪው መሰረት በደመቀ ሁኔታ ልቀበላችሁ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ያሳውቃል።

@ Hasan Yusuf (Phd) president of Wollega University

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
❗️የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት 21 እስከ 25 ይሰጣል። ትምህርት ሚንስቴር ባወጣው የ2015 ዓ.ም ካላንደር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከግንቦት 21 እስከ 25 እንደሚሰጥ አሳውቋል። የ 2014 ብሔራዊ ፈተና መስከረም ወር 2015 እንደሚሰጥ ይታወሳል ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን @NATIONALEXAMSRESULT
ማብራሪያ❗️

( ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮዎች የላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዛል)

⚠️ የ2014 ዓ.ም ተፈታኞች መስከረም አጋማሽ የሚፈተኑ ሲሆን ፥

⚠️ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎች የትምህርት ቢሮዎች በላከው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ሰሌዳ መሰረት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ልፍል ተማሪዎች ( ማለትም ወደ 12ኛ ክፍል ዘንድሮ ያለፉ ተማሪዎች) ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም ድረስ መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

⚠️ የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ክልላዊ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 9/2015 ዓ.ም ይሰጣል

⚠️ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ደግሞ ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 16/2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

#SHARE

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#share‼️‼️‼️

የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ በአስቸኳይ እንዲቆም ድጋሚ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሁሉንም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች አሳስቧል። ክፍያ በሚጠይቁ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል። እስካሁን በደረሰኝ ጥቆማ እስከ 400 ብር ለምዝገባ ያስከፈሉ ትምህርት ቤቶች አሉ።


ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
Exam Administration Implementation Manual (zz)-2(1).pdf
1.4 MB
#share ለፈተና አስተዳደር ሥራ ያግዝ ዘንድ የተለያዩ የግብረ ኃይል አደረጃጀቶችን፣ የተፈታኞችና የፈተና አስፈጻሚዎች መብት፣ ግዴታ፣ የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች የያዘ ማኑዋል ነው፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ተፈላጊ #Share

ዛሬ መሰከረም 29/01/2015 ከንጋቱ 11:45 ላይ ወ/ት ባህር ሼህሀሰን  ወደ ስራ ስትሄድ መሳለሚያ  አካባቢ ወጣት ፋንታሁን ይመር የተባለ ግለሰብ  የፍቅር ጥያቄዬን አልተቀበልሽኝም በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ በመሮ 6 ቦታ የተለያየ የሰዉነቷንና ክፍሎቿንና ጭንቅላቷን በመዉጋት ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

ይህ ግለሰብ ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ተሰዉሯል ። ጉዳዪን ፖሊስ እየተከታተለዉ ሲሆን መልእክቱን ሼር በማድረግ ግለሰቡ ለህግ እንዲቀርብ  ተባበሩን እንላለን ቤተሰቦቿ።

ግለሰቡን ያያችሁ በዚህ ስልክ ወይም አቅራቢያችሁ በሚገኝ የፖሊስ መስሪያ ቤት ጥቆማ በማድረግ ይተባበሩን
0940028545 ወይም 0925926563

(Wasu) #Share #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
List of the Fully Funded Scholarships for International Students

1) ADB-JSP Scholarship Program at AIT Thailand 2023 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/adb-jsp-scholarship-program-thailand/

2) Brunei Darussalam Government Scholarship 2023-2024 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/brunei-darussalam-scholarship/

3) ECNU Shanghai Government Scholarship in China 2023 | Fully Funded
Link:

4) Romania Government Scholarship 2023 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/romania-government-scholarship/

5) GIST Scholarship in South Korea 2023 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/gist-scholarship-south-korea/

6) Stipendium Hungaricum Scholarship 2023-2024 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/stipendium-hungaricum-scholarship/

7) GSK Scholarship 2023 in the United Kingdom | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/gsk-scholarship/

8) Dalian University CSC Scholarship in China 2023 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/dalian-university-csc-scholarship-china/

9) Singapore International Graduate Award 2023-24 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/fully-funded-singapore-international-graduate-award/

10) Ireland Government Scholarship 2023 | Fully Funded
Link: https://scholarshipscorner.website/ireland-government-scholarship/

#Share #Share #Share
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወልድያ‼️

ግቢውን ለቃችሁ ለወጣችሁ 2ኛ አመት የወልድያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ዩንቨርስቲው ከላይ የተያያዘውን ማስታወቂያ አውጥቷል።

#share #ሼር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
⚠️⚠️⚠️ አስቸኳይ ⚠️⚠️⚠️
⚠️⚠️⚠️ #SHARE ⚠️⚠️⚠️

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ሁለት ዓመት ያልሞላትን ህጻን ልጅ ሞግዚቷ ይዛት መሰወሯ ተሰማ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ሰፈር ልዩ ስሙ ኤልቤተል ቁጥር 2 ትምህርት ቤት ጀርባ ከሚገኘው የህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት ሶሊያና ዳንኤል የተባለችዋን ሁለት ዓመት ያልሞላትን ህጻን ቤዛዊት በቀለ የተባለችው ሞግዚቷ ይዛት መሰወሯን የህጻኗ አክስት የሆኑት መድሃኒት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በደላላ አማካይነት ባሞግዚትነት  የተቀጠረችው ግለሰቧ ገና 20 ቀኗ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የልጅቷ አያት በተኙበት ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ አዲስ ሰፈር ከሚገኘው መኖሪያ በት ይዛት መሰወሯ ተነግሯል፡፡

በትራንስፖርትና መንገድ ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን ህብረተሰቡ ከተመለከተ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ፈላጊ ቤተሰብ ጥሪ አቅርበዋል።


#ዳጉ_ጆርናል
@NATIONALEXAMSRESULT
⚠️⚠️⚠️ አሽቸኳይ ⚠️⚠️⚠️
🙏ለብዙዎች እንዲደርስ ያጋሩ🙏

ህጻን ሶሊያና እስከአሁን አልተገኘችም! እንደታገተች ናት! እናትና አባት በጭንቅ ውስጥ ሆነው  ያመሹት ነፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ነው።

ይህችን ምንም የማታውቅ የ2 ዓመይ ህጻን ልጅ የሆነችውን ህጻን ሶሊያናን  ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ መልኳ ቀይ፣ መካከለኛ ቁመት ያላት እና ቀጠን ያለች ስትሆን አብዛኛውን ጊዜ ታይትና ሻሽ የምትለብስ ናት።

ትንሿ ሶሊያናም ቢጫ ኮፍያ ያለው ሹራብ ከክፍት ጫማ ጋር አድርጋ ነበር። እባካችሁን በፈጣሪ ስም አፋልጉን ጸልዩልንም🙏

0951090999 - ዳንኤል
0947365252- የውብዳር
#በስልካችን_ብቻ_ወንድማችንን_እንታደገው

#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን 💪

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢያቸው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነ እና በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቹ #Fail አድርገው የህክምና እርዳታ ለማግኘት ገንዘብ በማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚገኝ ጓደኛቸውን ለመርዳት በሚል "ዶንኪ ቲዩብ" የተሰኘ የዩትዩብ ገፅ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን ማለትም ለአሸናፊው #500ሺህ ብር የሚያሸልመውን ውድድር በመወዳደር የሽልማቱን ገቢ ለጓደኛቸው ድጋፍ ለማዋል አስበዋል።


ቻሌንጁ "Donkey Tube" የተሰኘውን የዩትዩብ ገፅ ሰብስክራይብ በማድረግ ከላይ በምስሉ በሚታየው መልኩ screenshot 👉 @legesecharitybot ላይ መላክ ብቻ ነው።

📌የውድድሩ አዘጋጆች እስከ 1.5k Subscribe ያስደረጉ አስር ሰዎችን በማወዳደር ለአሸናፊው ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚሸልሙ በመሆኑ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት ክበብ አባላት ለአንድ ዓላማ እድላቸውን ለማስፋት በሚል በርካታ Subscription Screenshot እንደሚያስፈልጋቸው ነግረውናል። በመሆኑም ይህንን መልዕክት የሰማቹህ በሙሉ መልካም ስራቸውን ለመጋራት ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ Screenshot --> @legesecharitybot ላኩላቸው🙏


፨ይህን መልዕክትም በብዛት #Share አድርጉት።


፨ውድድሩ የፊታችን #ሰኞ ይጠናቀቃል።

#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን 💪


@NATIONALEXAMSRESULT
ለትውስታ በድጋሜ የተለጠፈ

#ለተማሪዎች_የቤትስራ_መስጠት_የማይቻልባት_ሀገር_ፊንላንድ

#SHARE

በአውሮፓ ውስጥ የምትገኘው ፊንላንድ ሀገር የትምህርት ፖሊሲ እና ህግ መሰረት  ማንኛውም መምህር በየትኛውም የክፍል ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች #የቤት_ስራ መስጠት አይችልም፥አይፈቀድለትም፡፡

"ተማሪዎች የቀለም ትምህርት መማር ያለባቸው ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡ ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ በቁጥር ነክ እና ሌሎችም የቀለም ትምህርት ሃሳቦች ሊጨናነቁ አይገባም ስለሆነም ምንም አይነት የቤት ስራ ሊሰጣቸው አይገባም፡ ትምህርታቸውን እዚሁ ት/ቤት ጨርሰው ይሄዳሉ" ይላሉ ፊንላንዶች፡፡

በጣም የሚያስገርመው ነገር ደግሞ በፊንላንድ ሀገር ማንኛውም ት/ቤት ተማሪዎችን ከበዛ ከ3 ሰአት በላይ ካነሰ ደግሞ ከ2ሰአት በላይ ማስተማር አይችልም። ይኸውም ተማሪዎቹ አእምሮ እንዳይጨናነቁ በማሰብ ነው።
@nationalexamsresult
ሌላው ፊንላንድ ሃገር የግል ት/ቤት የሚባል ነገር ፈጽሞ አይገኝም። ይኸውም የግል ት/ቤቶች የሚያስከፍኩትን ከመጠን በላይ የሆነ ክፍያ እና ጭማሪ ለመከላከል ነው። የሃብታሙም የድሃውም፡ የባለስልጣኑም የህዝቡም ልጆች እኩል በአንድ ዴስክ ላይ ተቀምጠው በመንግስት ት/ቤቶች  የሚማሩት በዚህቹ አስገራሚ ሃገር በፊንላንድ ውስጥ ብቻ ነው።ስለዚህ ወላጆች ስለት/ቤቱ ጥራት እንጂ ስለክፍያ አያሳስባቸውም።
@Nationalexamsresult
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
ታድያ 3 ወይም 4 ሰአት ብቻ ተምረው፥ የቤት ስራ ሳይሰጣቸው፥ጭራሽ ደግሞ በመንግስት ት/ቤት እየተማሩ እንዴት ጎበዝ ተማሪ ሊገኝ ይችላል?
😳😳😳🤔🤔🤔🤔🤔🤔😳😳😳
ብለው ካሰቡ በጣም ተሳስተዋል😜
ምክንያቱም 👇👇👇👇👇👇👇👇

💡🔔 ከፊንላንድ ተማሪዎች ውስጥ በጣም ምንም አያውቅም የሚባል ተማሪ ካለ
👉 8ኛ ክፍል ከመድረሱ በፊት  ቢያንስ 4 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ ይናገራል
👉 የሂሳብ ቀመሮችን በትክክል ያሰላል
👉 ባዮሎጂ እና ፊዚክስ ትምህርቶች ላይ ሰቃይ ነው

በጣም ጎበዝ የሚባለውን ተማሪ ደግሞ ማሰብ ነው😎

የፊንላንድ ተማሪ ከት/ቤት ሲመለስ ከ1ሰአት በላይ ደብተሩ ላይ እንዲቀመጥ ቤተሰቦቹ ፈጽሞ አይፈቅዱለትም😍
ፊንላድ ተማሪዎችን በማጨናነቅ ሳይሆን
ራሳቸውን ከመጨናነቅ ነጻ አድርገው እንዲማሩ በማድረግ የተማረ የሰው ኃይሏን የምታጠናክር ድንቅ ሃገር ናት፡፡

ምንጭ: Bright Coloniziasion


ከወደዳችሁት #SHARE / #FORWARD በማድረግ ለጓደኞቻችሁ አጋሩ


ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#አሽቸኳይ #SHARE #FORWARD
#ጥንቃቄ #ሴትልጅ #ጠለፋ

ዛሬ ከቀኑ 6:40 አከባቢ ይህቺ 15 ዓመቷ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ከምትማርበት ሀዋሳ ጉዱማሌ ት/ቤት ወጥታ ቤቷ ልትገባ የተወሰኑ ሜትሮች ሲቀራት ሞኖፖል ሰፈር ጋር በሁለት ዳማስ መኪና ሆነው አፍነሞት ከነለበሰችው ዩኒፎርም እና ከያዘችው ደብተር ጋር ጠልፈዋት ተሰውረዋል።
አከባቢው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች መኪናዎች ላይ ድንጋይ ወርውረው በመከተል ለማስጣል ቢሞክሩም አልደረሱባቸውም።

ህፃን ሜላት በቅርቡ የሚኒስትሪ ተፈታኝ ስትሆን ከቤት ተልካ እንኳን ወታ አታውቅም! እየጮሀች እና እያለቀሰች ይዘዋት የሄዱበት የመኪና ታርጋ ቁጥር

ዐ1894 ሲ.ዳ እና
05234 ሲዳ ነው።

@NATIONALEXAMSRESULT
የ12ኛ ክፍል ውጤት ቅሬታ ፎርም አሞላል ቅደም ተከተል እንዴት ነው?

🌐 በቅድሚያ ወደ http://eaes.et ግቡ

ℹ️ በመቀጠል እንደተለመደው ሬጂስትሬሽን ቁጥር እና ስማችሁን አስገቡ

🟩 ከዚያም ከውጤት ማሳያው ሥር በታች በኩል በአረንጓዴ ቀለም ላይ ያረፈ submit your complain if any የሚለውን ተጫኑ

📌 በመቀጠል ከሚመጡት የቅሬታ አይነቶች ውስጥ እናንተ ቅሬታ ማቅረብ የገለጋችሁበትን አንዱን ምረጡ።

🔖 የስም ስህተት ፣ የተሳሳተ ፎቶ ግራፍ ፣ የተሳሳተ የትምህርት መስክ (ሶሻል/ናቹራል) ፣ የተሳሳተ ጾታ ፣ የተሳሳተ ውጤት ፣ የተሳሳተ የዕይታ ሁኔታ (ማየት የሚችል/ማየት የተሳነው) ምርጫ እና ሌላ የሚል ይሰጣችኋል።

📝 ለምሳሌ፦

🟢 ውጤቱ ላይ ከሆነ ቅሬታ ማቅረብ የፈለጋችሁት  Result problem  የሚለውን ተጫኑ

🟢 ከዚያም ከእያንዳንዱ ትምህርት ውጤት ጎን  ቅሬታ መጻፊያ ያመጣላችኋል

🟢 ከዚያም ቅሬታ ማስገባት የፈለጋችሁበት የትምህርት አይነት ጋር በመሄድ ቅሬታችሁን መጻፍ እና ስትጨርሱ submit የሚለውን ተጫኑ።

🔰 ማስታወሻ 🔰

ቅሬታ የምታስገቡት በሥራ ሰአት ቢሆን ይመረጣል።

#SHARE በማድረግ ሌሌሎች ያድርሱ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT