STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
❗️#HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት
ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• የሌሊት አልባሳት
• የስፖርት ትጥቅ

ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የ2014 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከነሐሴ 26 እስከ 28/2014 ዓ.ም #በኦንላይን ብቻ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)




  ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ፦

" የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ።  "


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ #tikvah

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሀገረ አቀፍ ፈተናዎች . . .

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ :

የሬሜዲያል ፈተና ፦

- በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ሰኔ 30/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል።

(አሁን ላይ ያልተፈተኑ የግል ተማሪዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ በመስከረም 2016 ዓ/ም እንደሚፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል)

- በ2016 ዓ/ም ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የሚገኙ በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመንግስት እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ፦

- መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። ውጤት ሐምሌ 10 ይገለፃል። (የጤና ተማሪዎች መውጫ ፈተና ዛሬ ተካሂዷል)

- በዘንድሮው ዓመት 169 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

- ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች ተዘጋጅቷል።

- ሃምሳ (50) በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ያልፋሉ።

- ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ። የመጀመሪያው ዙር ፈተና መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ሲሆን ከዛ በኃላ ግን ልክ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በግል እንደሚፈተኑት መውጫ ፈተና ላይም ተፈታኞች ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት / በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ #ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

- የመውጫ ፈተና ሙሉ በሙሉ #በኦንላይን ይሰጣል።

- የተፈታኝ ተመራቂ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል ገብቷል።

- ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተከናውኖ ፤ የሞዴል ፈተና እየወሰዱ ነው።

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦

- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

- ለብሔራዊ ፈተናው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ ይሆናሉ።

- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

- ፈተናው ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን ተመዝግበዋል።

- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

- የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል።

TikvahEthiopia

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot