STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#WolloUniversity

ለወሎ የኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ
• የኮንስትራክሽ ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት
• የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
• የኤሌትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
• የኬሚካል ኢንጂነሪንግ
• የአርክቲክቸር ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የኢንተርንሽፕ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወነው #የካቲት 10 እና 11 2014 ዓ.ም ሲሆን የሆሊስቲክ ፈተና የካቲት 16 እና 17 2014 ዓ. ም የሚሰጥ ይሆናል::

ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎቹን ከየካቲት 30 ጀምሮ ሊቀበል መሆኑን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ብርሀኑ አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ዩኒቨርሲቲው በሸብር ቡድኑ ከፍተኛ ውድመት ቢደርስበትም በመልሶ ግንባታ የመማር ማሰተማር ስራን መከወን የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል ብለዋል። (ኤፍ ቢ ሲ)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#wollouniversity

ማስታወቂያ
ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ድህረ ምረቃ ተማሪዎች
በሙሉ።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው የካቲት 14 እና 15 2014 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሰው ቀን በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እና ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳውቃለን፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ
ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ👇

ወሎ ዩኒቨርሲት ተማሪዎቹን ከ #የካቲት 30 ጀምሮ በሁለት ዙር እንደሚያስገባ አሳስቦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛም(ህብረቱ) ተማሪዎች የሚገቡበት ቀን እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ የመግቢያ ቀንን በማስታወቂያ ሊገለፅ ይገባል በማለት ለዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ለሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

የማኔጅመንት አካላት ተማሪዎችን በማስታወቂያ እንደሚገልፁ የነገሩን ቢሆንም #የካቲት21 ቀን በነበራቸው ስብሰባ እንደ ዩኒቨርሲቲ በቴሌቬዥን እንደሚያስነግሩና ከተባለው ቀን #አንድ_ሳምንት በመጨመር(👉መጋቢት 07 አካባቢ) እንደሚያስገቡ ገልፀውልናል‼️

፨ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?

ተማሪዎች ባልተዘጋጀ ዶርምና ካፌ መተው እንዳይንገላቱብን አስቀድመን መጨረስ ያለብንን ነገር መጨረስና ማረጋገጥ ስላለብን እንዲሁም መብራት በማይኖርበት ጊዜ ተማሪዎችን በዳቦ አቅርቦትና በጥናት ጊዜ እንዳይጉላሉ ጀነሬተሮች በህውሓት ሃይሎች ስለተበላሹ ይሄንንም ለማሰራት ጊዜ ስለሚፈልግ ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ህብረቱ ገልጿል።

፨ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ እንደገለፃችሁት በሁለት ዙር ወይስ አንድ ላይ ትጠራላቹህ ብለን የጠየቅን ሲሆን ፡ የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር እንደ ተማሪዎች አገልግሎት በቂ የመኝታ በሮች ስለተገጠሙልኝ በተጨማሪም የምግብ ቤት ግብዓቶች ስለተሟሉ በአንድ ላይ ቢገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይቻላል ያለ ሲሆን የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚጠሩ ገልፀው በቅድሚያ አንደኛ ዓመት እና ሁለተኛ ዓመት የነበሩትን ጠርቶ አንድ ሳምንት ባልሞላ ልዩነት ቀሪዎችን የሚጠራ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

📌የደሴ ካምፓስ ዳይሬክተሮችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም እንደ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ላይ ስለሚጠራ ልዩነት እንደማይኖረው አረጋግጠናል፡፡

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ #መጋቢት15 ባሉት ቀናት ሁሉንም ተማሪዎች የሚያስገባ ስለሆነ ተማሪዎች ማስታወቂያ እንድትከታተሉ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ለወሎ ዩኒቨረሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጨምሮ) ምዝገባ የሚከናወነው #መጋቢት 12 እና 13/2014 ዓ.ም ሲሆን ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከመግቢያ ቀን በፊት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግደሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

የወሎ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከነገ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ዩኒቨርሲቲው ከአንደኛ ዓመት እስከ ተመራቂ ተማሪዎች በጠቅላላው ከአስር ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

የተረጋገጡ
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ደሴ ግንቦት 14/2014 ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡ ከተመራቂዎች መካከል 293ቱ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ መማር ማስተማር ስራውን ዳግም ጀምሮ ተማሪዎቹን ለዛሬው ምረቃ አብቅቷል።

ለዛሬ ምርቃ የደረሱ ተማሪዎች የሽብር ቡድኑ በፈጸመወ ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጎጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 106ቱ ሁለተኛ ዲግሪ ናቸው።

በምርቃን ስነ ስርዓቱ የተለያዩ ባድርሻ አካላት ተገኝተዋል
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በክረምት መርሃ ግብር የሳይንስ ትምህርት መስኮች የሚሰለጥኑ ተማሪዎች መግቢያ ሐምሌ 25 እና 26/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም አመልካቾች የመገጣጠሚያ ደብዳቤ እና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ ምዝገባ አድርጉ ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርስቲ የጤና ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት የፋርማሲ/ Pharmacy /ተማሪ የነበረው ተማሪ ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤል በ26/12/2014 ዓ.ም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከማደሪያ ቤቱ/ዶርሙ/ውስጥ እራሱን በመስቀል ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የኤክስቴንሽን ተማሪዎች (ቅድመ እና ድኅረ ምረቃ) የ2015 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 26 እና 27/2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት ኅዳር 03/2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 914 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በክረምት፣ በተከታታይ እና በርቀት ትምህርታቸውን በደሴ ካምፓስ ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በኮምቦልቻ ካምፓስ ያስመረቃቸውን 1 ሺህ 394 ተመራማሪዎች ጨምሮ በአጠቃላይ 6 ሺህ 308 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ635 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 10 ተማሪዎች የላፕቶፕ ሽልማት ሰጥቷል።

ተሻሚዎቹ ስምንቱ ከየይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆኑ ሁለቱ ከደሴ ከተማ ትምህርት ቤት መሆናቸው ተገልጿል።

ለሽልማቱ ዩኒቨርሲቲው ከ8 መቶ 50 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጓል።

በተመሳሳይ ከ600 እስከ 634 ውጤት ላስመዘገቡ 19 ተማሪዎች የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቦርድ እና የደሴ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለእያንዳንዳቸው ተማሪዎች የ6 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥተዋል።

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity

በ2015 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ጊዜ 👉መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አስውቋል።

፨ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity
New #Updated Academic Calendar

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል፣ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና በመውጫ ፈተና ምክንያት የ2015 ዓ.ም አካዳሚክ ካሌንደርን ማሻሻያ አድርጓል።

በተሻሻለው አዲስ ካሌንደር መሰረት 👇

፨ከሰኔ 10-15/2015 ድረስ የሪሚዲያል ፈተና ይሰጣል።(Tentative)

፨ሰኔ 29 እና 30 የዩንቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎች ለኢንትራንስ ፈተና ሲባል ግቢው ለቀው እንዲወጡ ይደረጋል።

፨ከሀምሌ 05-14/2015 ድረስ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል።(Tentative)

፨ሀምሌ 15 እና 16/2015 የግቢው ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ወደ ግቢ ይገባሉ።

፨ከሀምሌ 17-27/2015 ድረስ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

📌 በዚህ አካዳሚክ ካሌንደር መሰረት የወሎ ዩኒቨርስቲ የተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ቀን 👉መስከረም 19-20/2016 እንደሆነ ተገልጿል።


⭕️ዝርዝር መረጃ ለምትፈልጉ ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity
#ጥሪው_ተራዝሟል‼️


ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን ማሳወቁ ይታወሳል። ሆኖም ግን ከዩንቨርሲቲው ዛሬ ባገኘነው መረጃ መሰረት ለመደበኛ ተማሪዎች ተደርጎ የነበረው ጥሪ #ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰምተናል።

⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️⛔️
አማራ ክልል ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ይህን መረጃ ለዩንቨርሲቲው ተማሪዎች በተለይም አማራ ክልል ላይ ለሚገኙ የወሎ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በስልክ በመደወል ታሳውቋቸው ዘንድ የወሎ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ጠይቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።

የተማሪዎቹ ምዝገባ ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ "በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጓተት ምክንያት" የተማሪዎቹ ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለነባር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ እንዳለስተላለፈ ገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ጥሪ እስካሁን እንዳልተላለፈ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ፤ ተደጋጋሚ የመግቢያ ቀንን የተመለከቱ ጥያቄዎች በተማሪዎች እየቀረቡለት መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በመሆኑም ትክክለኛውን የመግቢያ ጊዜ እስከሚያሳውቅ ድረስ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolloUniversity #Remedial

በወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ 👉ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ

1. የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋና እና ፎቶ ኮፒ
2. ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
3. የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋና እና ፎቶ ኮፒ
4. አራት(4) ጉርድ ፎቶግራፍ
5. ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ሌሎች የግል መገልገያ ቁሳቁሶችን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡



📌 ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ግቢ (Campus) ለማወቅ ከላይ በተቀመጠው ፖርታል (Portal) እና የቴሌግራም ቻት ቦት (Telegram Chat bot) መጠቀም ትችላላችሁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update #WolloUniversity

በወሎ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓም በ Remedial program አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓም በ Remedial program አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 16 እና 17/05/16 ዓም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።በመሆኑም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ኮምቦልቻ ግቢ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ደሴ ግቢ የተመደባችሁ መሆኑን እንገልፃለን።

         ©ተማሪዎች ህብረት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot