STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.8K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ትላንትና አጠቃላይ የትምህርት ክፍል ዲፓርትመንትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ከጤና ሳይንስ የፋርማሲን ብቻ በ30 የተማሪዎች ብዛት የቅበላ አቅሙን ለዚህ የትምህርት መንፈቅ አመት ያቀረበ ሲሆን

ከቴክኖሎጂ ሳይንስ(TOT) ደግሞ
በኮሌጅነት #Computing እና #engineering
#computing ውስጥ
Computer science
Information system
Information Technology
Software engineering
በአጠቃላይ የቅበላ ድምር 240

እንዲሁም በ # engineering ውስጥ
Mechanical
Civil
Electrical&Computer
Chemical
Construction Technology& management
Food
Industrial
Surveying
Hydraulic&water Resource engineering ዲፓርትመንቶችን በአጠቃላይ የኢንጅነሪንግ የቅበላ አቅም ድምር 975 መሆኑን ገልፇል።

ለዚህም መግቢያ ነጥብ 50% የሴሚስተር ውጤት

20% የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት

30% ግቢው በሚሰጠው መመዘኛ ፈተና የሚወሰን ይሆናል።ይህንንም የምዘና ፈተና በፋርማሲን #የካቲት 11 ለቴክኖሎጂ የካቲት 13 የሚሰጥ ይሆናል።

ምርጫውን እንደአማራጭ ሁለቱንም መምረጥና ፈተናውንም ሁለቱንም መፈተን ይቻላል።

ተማሪ ነክ ብቻ ለሆኑ የተጣሩ እውነተኛ መረጃዎች ቻናላችንን ተቀላቀሉን 👇
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#DebreBirhanUniversity

ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመጀመሪያና የድህረምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

1. ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ በጊዜያዊነት ወደ ደብረ ብርሃን ዩነቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች

2. በ2013 ዓ.ም. የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ የነበራችሁ የ3ኛ ዓመች የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ

3. በ2014 ዓ.ም. በምህንድስና ኮሌጅ ስር Intemship የምትወጡ ተማሪዎች

4. በ2014 ዓ.ም. በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ስር ለመስክ ትምህርት የምትወጡ
➢ የ4ኛ ዓመት የጂኦሎጂ ተማሪዎች እና
➢ የ4ኛ ዓመት የባዮ ቴክኖሎጂ ተማሪዎች በሙሉ 👉 የምዝገባ ቀን #የካቲት 14 እና 15 2014 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን፤

5. ከላይ ከተገለጹት ውጭ ያላችሁ የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም አዲስና ነባር የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ቀናት #የካቲት 19 እና 20 2014 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

#ማሳሰቢያ

የመመዝገቢያ ቦታ በዋናው ግቢ በየኮሌጃችሁ ሬጂስትራር ክፍል ይሆናል።
• ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ ወደ ዩኒቨርስቲያችን የተመደባችሁ ተማሪዎች የ8ኛ፣ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ዋና እና ፎቶ ኮፒውን ! በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ በእጃችሁ የሚገኙ ማንኛውንም የግል የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን (ግሬድ ሪፖርትና የተማሪ መታወቂያ) ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል።

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሬጂስተራር እና
አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ለወሎ የኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ
• የኮንስትራክሽ ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት
• የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
• የኤሌትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
• የኬሚካል ኢንጂነሪንግ
• የአርክቲክቸር ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የኢንተርንሽፕ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወነው #የካቲት 10 እና 11 2014 ዓ.ም ሲሆን የሆሊስቲክ ፈተና የካቲት 16 እና 17 2014 ዓ. ም የሚሰጥ ይሆናል::

ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ👇

ወሎ ዩኒቨርሲት ተማሪዎቹን ከ #የካቲት 30 ጀምሮ በሁለት ዙር እንደሚያስገባ አሳስቦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛም(ህብረቱ) ተማሪዎች የሚገቡበት ቀን እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ የመግቢያ ቀንን በማስታወቂያ ሊገለፅ ይገባል በማለት ለዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ለሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

የማኔጅመንት አካላት ተማሪዎችን በማስታወቂያ እንደሚገልፁ የነገሩን ቢሆንም #የካቲት21 ቀን በነበራቸው ስብሰባ እንደ ዩኒቨርሲቲ በቴሌቬዥን እንደሚያስነግሩና ከተባለው ቀን #አንድ_ሳምንት በመጨመር(👉መጋቢት 07 አካባቢ) እንደሚያስገቡ ገልፀውልናል‼️

፨ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?

ተማሪዎች ባልተዘጋጀ ዶርምና ካፌ መተው እንዳይንገላቱብን አስቀድመን መጨረስ ያለብንን ነገር መጨረስና ማረጋገጥ ስላለብን እንዲሁም መብራት በማይኖርበት ጊዜ ተማሪዎችን በዳቦ አቅርቦትና በጥናት ጊዜ እንዳይጉላሉ ጀነሬተሮች በህውሓት ሃይሎች ስለተበላሹ ይሄንንም ለማሰራት ጊዜ ስለሚፈልግ ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ህብረቱ ገልጿል።

፨ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ እንደገለፃችሁት በሁለት ዙር ወይስ አንድ ላይ ትጠራላቹህ ብለን የጠየቅን ሲሆን ፡ የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር እንደ ተማሪዎች አገልግሎት በቂ የመኝታ በሮች ስለተገጠሙልኝ በተጨማሪም የምግብ ቤት ግብዓቶች ስለተሟሉ በአንድ ላይ ቢገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይቻላል ያለ ሲሆን የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚጠሩ ገልፀው በቅድሚያ አንደኛ ዓመት እና ሁለተኛ ዓመት የነበሩትን ጠርቶ አንድ ሳምንት ባልሞላ ልዩነት ቀሪዎችን የሚጠራ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

📌የደሴ ካምፓስ ዳይሬክተሮችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም እንደ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ላይ ስለሚጠራ ልዩነት እንደማይኖረው አረጋግጠናል፡፡

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ #መጋቢት15 ባሉት ቀናት ሁሉንም ተማሪዎች የሚያስገባ ስለሆነ ተማሪዎች ማስታወቂያ እንድትከታተሉ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ArbaMinchUniversity

የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2014 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን #የካቲት_29/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን #የካቲት_30 እና #መጋቢት_01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

* የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆነ አራት ጉርድ ፎቶ፣
* አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ እንዲሁም
* ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል

የምደባ ቦታ
👉 ዓባያ ካምፓስ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ (ዓባያ ግቢ)፣

👉 ጫሞ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣

👉ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እና የአቅም ማሻሻያ ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
   
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot