STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ !

#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም እያስመረቀ ነው።

የዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ 3013፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

#KebridharUniversity

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ለዚሁ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የፌዴራል እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ትላንት ወደቀብሪድሃር መጓዛቸው ይታወቃል።

#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 338 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 3,950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 530 ሴቶች ናቸው። በ2ተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ 3 ተማሪዎች በ3ተኛ ዲግሪ እና 4 ተማሪዎች ደግሞ የ 'ሰብ ስፔሻሊቲ' ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 24 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

#KotebeMetropolitanUniversity

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ 2039 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፤ 1 ሺህ 104 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 222 በ2ኛ ዲግሪና 711 በዲፕሎማ።

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ SRTV፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ኤፍ ቢሲ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በሴሚስተር ዕረፍት ላይ የሚገኙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል።

የቀጣይ ሴሚስተር ምዘገባ የሚከናወንበት ጊዜን በማስታወቂያ እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#WollegaUniversity

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጊምቢ ካምፓስ የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ ማጠናቀቁን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ስድስት የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶችን ግንባታ ሲያከናውን ቆይቷል።

ከስድስቱ አፓርትመንቶች ሁለቱ ለመምህራን መከፋፈለቸውም ተገልጿል።

በግንባታ መሳሪያዎች ዋጋ መናር እና በቴክንካዊ ችግሮች ምክንያት የአፓርትመንቶቹ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉ ተነግሯል።

የመምህራን መኖሪያ ቤቶቹ መጠናቀቅ ብቁና ልምድ ያካበቱ መምህራን ፍልሰትን ለመከላከል እንደሚረዳ ታምኖበታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update
#WollegaUniversity

በ2014 ዓ.ም ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም እንደሆነ መገለጹ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

• መነሻ ከተማ፦ ደምቢ ዶሎ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ለገሰ ግርማ ~ 0916640790
ዱሬሳ አለማየሁ ~ 0919521309

• መነሻ ከተማ፦ መንዲ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
መሀመድ ዑመር ~ 0912700614
ሚልኬሳ ታከለ ~ 0935063833

• መነሻ፦ አያና ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ገመቹ ገለታ ~ 0930770690
ኒሞና ከበደ ~ 0918171173

• መነሻ፦ ሻምቡ ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ሸሚን ኢብራሂም ~ 0917434355
አዳነች ደገፋ ~ 0964629049

• መነሻ፦ አዲስ አበባ (አስኮ)
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦
በ15/09/2014 ዓ.ም (2 አውቶቡሶች)
በ16/09/2014 ዓ.ም (1 አውቶቡስ)
አስተባባሪዎች ጀማል አደም ~ 0916700774
ደጋጋ ፈቀደ ~ 0917033569
ጃቤሳ አመንቴ ~ 0912290387
ቦንቱ ተመስገን ~ 0917675546
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ አርማ በአፋን ኦሮሞ የዩኒቨርሲቲውን ስያሜ ተጨማሪ አድርጎ አካቷል።

የተሻሻለው የዩኒቨርስቲው አርማ የተወሰኑ የቀለም ለውጥም ተደርጎበታል።

ዩኒቨርሲቲው የተሻሻለውን አርማ ከትላንት ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መጠቀም ጀምሯል።

ውሳኔው ተቋሙ የሚገኝበት የአካባቢውን ቋንቋ በአርማው ላይ ለማካተት በማሰብ የተደረሰ እንደሚሆን ይገመታል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የቅድመ እና ድህረ ምረቃ የክረምት ተማሪዎች (የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ጨምሮ) የ2014 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 14 እና 15/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የቅጣት ምዝገባ ሐምሌ 16 እና 17/2014 ዓ.ም ይከናወናል የተባለ ሲሆን የሁሉም የቅድመ እና ድህረ ምረቃ የክረምት ተማሪዎች ትምህርት ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT