الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
386 photos
18 videos
8 files
919 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር_በኢስላ☜   #ክፍል_ስድስት/⑥ ☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ   #በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር። #በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው…
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜

 
#ክፍል_ሰባት_⑦ት

     
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም

   ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን ምንም የሚያስጨንቃቸው አልነበረም።

    የሰው ልጅ አይነታ የሆኑት
#የአላህ_መልእክተኛ_ሰአወ ኢስላምን ለማደስ ከመጡ በኃላ በጃሂልያ ይተገበር የነበረው ፈር የለቀቀው በሴቶች ላይ ይደረግ የነበረው #ግፍና_መከራ ገፈው ጣሉት።ከአንድ በላይ ሚስትን በተመለከተ እስልምና ቁጥርን ብቻ መገደብ ሳይሆን በሚስቶችም መካከል ፍትሀዊነትም ጭምር ትኩረት ሰጥቶ አስተካክሏል

#በፍትህ_ማስተዳደር_ያልቻለ_አንድ_ትብቃው_እሷንም_ማስተዳደር_ያልቻለ_ማስተዳደር_እስኪችል_ድረስ እንዲፆም_እና_እንዲታገስ በማድረግ ከእንግዲህ ሴት ልጅን እንደፈለጉ ማድረግና መጨቆን እንዳከተመለት ለሴት ልጅ ኢስላም ሙሉ የሆነ ዋስትና እንደሰጣት ታወጀ።አዋጁም ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ተስተጋባ።

    ከዚህም በተጨማሪ ሴት ልጅ ውጭ ወጥታ ከወንድ ጋር እንዳትጋፋ የወንዶች ዘለፋ እንዳያገኛት ሂጃቧን ጠብቃ ቤቷ እንፍትሆን በማድረግ እሷን የመንከባከብ ግዴታውን በወንዶች ላይ አደረገ።እየቻለ ቢያስቸግራት ፀቡ ከማንም ጋር ሳይሆን ከአላህ ጋር እንደሆነ ነብዩ ሰአወ አስጠነቀቁ። በኢስላም ውስጥ
#ሴት_ መሆን_መታደል ነው።እንዲሉ በአጠቃላይ እስላም ለሴቶች ምሽግ ነው።ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች ኢስላም ከአንድ በላይ በመፍቀዱ የሴቶችን መብት ይጋፋል። የሚል የእብድ ወሬ ሲያናፍሱ ይደመጣሉ።ኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ማስገደድ ሳይሆን በአለፉ እምነቶችና ባህሎች ፈር ለቆ የነበረውን ከአንድ በላይ ሴቶችን ማግበስበስ በገደብ እና በፍትህ እንዲሆን ህግ ማሰረቀመጥ እንደሆነ በዝርዝር አሳልፈናል..

እስከ አራት የተፈቀደ ለመሆኑ ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

    ☞ይህ የቁርአን አንቀፅ፣ በኢስላም ውስጥ
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድ መሆኑን ግልፅ ማስረጃ ነው።ነገር ግን በሴቶች መካከል በፍትህ ማስተዳደርን ቅድመ መስፈርት አድርጎ ደንግጓል። #ፍትህ ዋና ቅድመ መስፈርት ለመሆኑ የቁርአን አንቀፁ የወረደበት ሰበብ ማወቅ መልክቱ ግልፅ ያደርገዋል..

    እናታችን አኢሻ ረአ እንዲህ ይላሉ፣ "አንድ ሰው በውስጡ የሚያሳድጋት ብዙ ንብረት ያላት የቲም ሴት ልጅ ነበረችው፣ ንብረቷን ፈልጎ ጥሎሹን በትክክል ሳይሰጣት አገባት።ከዚያ ይቺ የቁርአን አንቀፅ ወረደች.።

   ☞  በሌላ ዘገባ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር ወደ እናታችን አኢሻ ዘንድ መጣና ስለ
"وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ"
ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ ብለውታል፣ "የወንድሜ ልጅ ሆይ;አንድ ወንድ ሃላፊ ሆኖ የሚያሳድጋት የቲም ሴት ልጅ ገንዘቧ እንዲሁም መልኳ አስቀንቶት መህሯን በትክክል ሳይሰጣት እንዳያገባት ማለት ነው፣ ይህ ነው የተከለከለው። እሷን ማግባት የሚፈልግ ከሆነ መህሯን ለሌሎቹ እንደሚሰጠው አድርጎ በፍትህ መህሯን ለሌሎች ሚስቶች የሚገባውን ሰጥቶ ያግባት።ነገር ግን ፍትህ ማጓደልን ከፈራ እሷን ትቶ ሌሎችን የሚያስደስቱትን እስከ አራት ማግባት ይችላል ማለት ነው።" ቡኻሪ ዘግበውታል።.

#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ሼር_ያድርጉ👇👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜   #ክፍል_ሰባት_⑦ት       #ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም    ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜

  .
#ክፍል_ስምንት/⑧ት
     
#ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም

#እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

#ከአንቀፁ_የምንማራቸው_ቁም_ነገሮች

_አንቀፁ አንድ ወንድ ማግባት የሚችለው ከፍተኛው ቁጥር አራት መሆን እንዳለበት ይደነግጋል።ከአራት ሚስት በላይ ከነብዩ ሰአወ  ውጭ ማንኛውም ሰው መጨመር እንደማይፈቀድለት ኢማም አሻፊኢይ ኢጅማእ (የሙስሊም ሊቃውንት የጋራ አቋም)) አለው ይላሉ።ነብዩ ሰአወ ለምን ከአራት በላይ እንደተፈቀደላቸው እና
ከአንድ በላይ የማግባታቸው ጥበብ ሌላው ተራው ሰው ከአንድ በላይ ከሚያገባበት ምክንያት የተለየ ነው።ይህን በተመለከተ እራሱን የቻለ ምዕራፍ ስላለው ከማውጫው ላይ በመፈለግ በዝርዝር ማንበብ ጠቃሚ ነው።

_አንቀፁ
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የፈለገ ሰው #ፍትሃዊነት ቅድመ መስፈርት መሆን እንዳለበት ያስተምራል።በፍትህ ማስተዳደር የማይችል ወይም ፍትሃዊነት ሊጎለኝ ይችላል
ብሎ የሚያስብ ወንድ ከሆነ
ከአንድ በላይ ማግባት እንደማይፈቀድለት አንቀፁ ከሚሰጠን ግንዛቤ የተወሰኑት ናቸው።

    ☞ ፍትሃዊነት ሲባል አንድ ሰው ማድረግ በሚችለው
#እንደቀለብ_ልብስ_መኖሪያቤት_እና_አብሮማደርን የሚያካትት ነው።ነገር ግን ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ በማይችለው እና ከአቅሙ በላይ በሆነው እንደ #ፍቅር_መስጠት ያሉ ነገሮች ሁሉንም ሚስቶቹን እኩል ላድርግ ቢል ማድረግ አይችልም።ምክንያቱም አላህ በልቡ ላይ #ትወደድ_ያላት_ሴት_እሱ_ዘንድ_የበለጠ_ትወደዳለች።ለዚህ ሲባል አላህ እንዲህ ይላል፣

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡[ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129 ]

☞ ከቁርአን አንቀፁ የምንማረው ቁምነገር፣ አንድ ሰው በሚስቶቹ መካከል በልብ ላይ ባለው ነገር(ፍቅር) ማስተካከል የማይችል መሆኑን ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ የሚችለውን ማስተካከል ጠብቆ መያዝ እንዳለበት ካለፈው የቁርአን አንቀፅ ለማየት ሞክረናል። እንደውም በሚስቶች መካከል ፍትሃዊ መሆን የመጀመሪያ መስፈርት ከሚባሉት ውስጥ ነው።

#ማሳሰቢያ፣ አንዳንድ አዕምሯቸው እንዳያገናዝብ የተዘጋባቸው ሰዎች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም ብለው የሚከራከሩ በኢስላምም ውስጥ ብቅ ብለዋል።ማስረጃ ብለው ያቀረቡት ከላይ ያሳለፍነውን የቁርአን አንቀፅ ነበር።እንደነሱ አባባል የቁርአኑ አንቀፅ "በሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ ለማስተካከል አትችሉም" ብለው በመተርጎም * በሴቶች መካከል ማስተካከል ደግሞ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም* የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ። #ትርጉሙን_ለስሜታቸው_እንዲመቻቸው_አድርገው_በመተርጎም_እነሱ_ይህን_ይበሉ_እንጂ_ትክክለኛ_የአንቀፆቹ_መልእክት_እንዳሳለፍነው_ነው

    📚 የመጀመሪያው የቁርአን አንቀፅ የሚለው በየቲሞች መካከል ፍትህን እናጓድላለን ብላችሁ ከፈራችሁ ሌሎች ሴቶችን እስከ አራት ማግባት ትችላላችሁ የሚል ሲሆን የሁለተኛው የቁርአን አንቀፅ የሚያስረዳው ደግሞ በሴቶች መካከል ፍቅርን እኩል ማካፈል አትችሉም።ነገር ግን በምትችሉት ነገር ሴቶቻችሁን ችላ ብላችሁ እንዳትተዋቸው የሚል መልክ አዝሏል።
#ትክክለኛውም_የቁርአኑ_መልእክት_ይህ_ነው
  ☞ በሚችለው ነገር በሚስቶቹ መካከል ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ አላህ ዘንድ ትልቅ ቅጣት እንደሚጠብቀው ነብዩ ሰአወ ተናግረዋል።

    ☞አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰአወ እንዲህ አሉ፣ "ሁለት ሚስቶች እሱ ዘንድ ያሉት እና በመካከላቸው ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የተዘነበለ ሆኖ ይመጣል"  (ቲርሚዝይ ዘግበውታል

      ❗️ሙስሊም ሲባል ከዚህም ባለፈ በሁሉም ነገር ላይ በሚችለው አቅሙ በፈቀደው ፍትሃዊ መሆን መለያ ባህሪይው ሲሆን በተለይ ደግሞ በውስጡ ባሉት የኑሮ አጋር ከሆኑት ሚስቶቹ ጋር ሲሆን በእጅጉ ትኩረት የሚሰጠው ነው.።

  
#ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜   .#ክፍል_ስምንት/⑧ት       #ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም #እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ                 #ቁርአናዊ_ማስረጃ    አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣ وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

  ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

    አላህ ለወንድ ልጅ
ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።

    በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን አራት ሆነ፣የመግሪብ  ሶላት ለምን ሶስት ሆነ፣ሱብሂ ለምን ሁለት ሆነ፣ ለምን 5ወይ6 ወይም አንዳንድ አልሆነም? ሁሉም ሶላቶች ለምን ተመሳሳይ ቁጥር አልኖራቸውም?እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።ነገር ግን የእነዚህን የተለያየ ቁጥር ያላቸውን የኢባዳ አይነቶች ሚስጥር የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው።የሰውነት የአካል ክፍላችን ብዛት ብናስተነትን እና እያንዳንዱን የቁጥር መጠን ለምን ሆነ ብንል፣አይናችን ለምን 2 ሆነ፣ጆሮስ ለምን 2 ሆነ፣የእጅ ጣቶች ለምን 5 ሆኑ፣ለምን 4 ወይም 6 ዘልሆነም?? የሚለውን የብዛቱን ሚስጥር አዋቂው አላህ ብቻ ነው።

   ☞
ከአንድ በላይ ሚስት ያውም ደግሞ 4 የሚለው ቁጥር ለምን ተመረጠ ቢባል መልሱ ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታችን ብቻ የዚህ ሚስጥር ባለቤት ነቅ የሚል ምላሽ ይሆናል።

  
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የራሱ የሆነ ጥበብ መኖሩ እንዳለ ሆኖ ኡለሞች የሚዘረዝሯቸው አስደናቂ ጥበቦች አሉት እነዚህ ጥበቦች እንደሚከተለው አንድ ሁለት እያልን እንዘረዝራለን፣

1/
#የአላህ_መልእክተኛን_ሰአወ_ሱና_ለመከተል_ሲባል

   እንደሚታወቀው የአላህ መልእክተኛ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስ
ከአንድ በላይ ሚስቶች ነበራቸው።የአላህ መልእክተኛ ከአንዳንድ እሳቸው ብቻ ከሚለዩባቸው ተግባራቸው በስተቀር የእሳቸውን ፈለግ እንድንከተል ታዘናል።ይህንን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሎናል፣

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 21)

    ☞የአላህ መልእክተኛ የደነገጉትን መቀበል እና ሃቅ ነው ብሎ ማመን የሙስሊሞች ግዴታ ነው።
ከአንድ በላይ ሚስት በሸሪዓ የተፈቀደ እና የተወደደ ነው የሚለውን መቀበል በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አያስፈልግም ብሎ የጠላ ወይም መሆን አልነበረበትም ብሎ የተቃወመ ከኢስላም እንደሚወጣ የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።

     ነብዩ ሰአወ ለዱኒያም  ለአኼራም ለኡመታቸው የተሻለውን ነገር ሳያመላክቱ መጥፎን ነገር ሳያሰረጠነቅቁ አላለፉም። መጥፎውን እና ደጉን የማስተማር ሀላፊነት አላህ አስቀምጦላቸዋል።ነብዩ ሰአወ በንግግራቸው፣በተግባራቸው እና አይተው በማፅደቅ ያስተምራሉ።
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚወደድ እና የተሻለ እንደሆነ በተግባራቸው አስተምረውናል።ለሰዎች ሚስጥሩ በግልፅ ያልተገለፀው ከአንድ በላይ ሆኖ መግባትም እንደዚሁ ለሴቶች ትልቅ ጥቅም እንዳለው ያስገነዝባል።ለዚህም በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይችላሉ።ከእነዚህም ውስጥ ነብዩ ለህዝባቸው ሲያስተምሩ የተሻለውን ወይም የበለጠ ጥቅም የሚያስገኘውን ነው ካልን ለሴቶች ኡመቶቻቸው የሚጎዳ ወይም የበለጠ ጥቅም የማያስገኝ በፍፁም ሊደነግጉ ወይም ሊያመላክቱ አይችሉም።ሌላው እናታችን አኢሻ ረአ ከሁሉም ሴቶች እንደምትበልጥ ነብዩ መስክረዋል።እሷ ከነብዩ ሚስቶች ከዘጠኝ አንዷ ናት ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ሆና መግባት ደረጃን የሚቀንስ ከሆነ ከሴቶች ሁሉ የምትበልጠው እናታችን አኢሻ ረአ ለምን በእሷ ላይ ሌላ ተገባባት።በሌላ አነጋገር ከአንድ በላይ ሚስት ሆኖ ሴቶችን ክብር ይቀንሳል ወይም ሴቶችን ከጓደኞቻቸው የበታችነት እንዲሰማቸው ያደርጋል ብሎ ማሰብ አኢሻን ረአ የበታች ነበረች ብሎ እንደማሰብ ይቆጠራል።ይህ አስተሳስብ ደግሞ ከኢስላም ጋር ይጋጫል።

    ☞
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከአንድ በላይ ካላገባው ጋር ሲነፃፀር በደረጃ የተሻለ እንደሚሆን ነብዩ ሰአወ በሃዲሳቸው እንዲህ ሲሉ  ተናግረዋል፣

     
#ሰኢድ_ኢብኑ_ጁበይር_ረአ ባስተላለፉት ሀዲስ"አብደላህ ኢብኑ አባስ አግብተሃል?ሲል ጠየቀኝ እኔም አላገባሁም አልኩት፣አግባ ከዚች ኡማ የተሻለው ብዙ ሚስቶች ያሉት ነው"" አለኝ ይላሉ። ሀዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል።

2
#ሳያገቡ_እድሜያቸው_የገፉና_የሚፈቱ_ሴቶች_መኖርና_መበራከት

  እነዚህ ሁለት አይነት ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እድሜያቸውን ከገፉ በኃላ ለመጀመሪያ ሚስት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ነው።ወይም ደግሞ እንደሚታወቀው ወንዶች ለማግባት መሰረታዊ የሚባል የቤት ወጪን የሚሸፍኑበት ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ገንዘብ በልጅነት እድሜያቸው ካላገኙ እስቲሳካላቸው የተወሰነ ጊዜ መጠበቃቸው አይቀሬ ነው።በዚህም የተነሳማግባት ከነበረባቸው እድሜያቸው ከገፉ በኃላ ይሆናል። የእነሱ አለማግባት በእኩያታቸው ያሉ ሴቶች ቶሎ ላያገቡ ይችላሉ።እነዚህ በእድሜያቸው ብዙ ከሄደ በኃላ ሚስት ሊያገቡ የሚያስቡ ወንዶች በእድሜ ከእነሱ ጋር እኩል የሆኑ ሴቶች ሳይሆን ለጋ የሆነችውን ሴት ይመርጣሉ። በዚህም ምክንያት እነዚህን ሴቶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ይሆናል ማለት ነው። ያለባል እንዳይቀሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ
ከአንድ በላይ መፈቀዱ ኢስላማዊ ጥበብ ነው። በተመሳሳይ የተፈታችንም ሴት ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጓት ወንዶች እጅግ አናሳ ናቸው።ለዚህም መፍትሄው ያለባል ከመቅረት ሁለተኛ ማግባት ነው
  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
            3_4_&_5

👇በቀጣይ ርዕሳችን ይቀጥላል ሺንሻአላህ
#ሼር_ያድርጉ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜   ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ     አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።     በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜

  ክፍል አስር/⑩

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

3/
#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና
     
#በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ

  በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል እንጥቀስ፣

ሀ/. በአለም ላይ የወንዶች ሞት በተለያዩ ምክንያቶች መጨመር የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (medical school of harvard) በ2016 ይፋ ባደረገው ጥናት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በውል ተለይተው ለማይታወቁ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው።ይህም የሚሆንበት ምክንያት የሴቶች x ክሮሞዞም ካንሰርን የመቋቋም እድሉ ከፍተኛ ነው ይላል ጥናቱ።ከዚህም በተጨማሪ ሰውን በከፍተኛ ገዳይ ከሆኑት የልብና የጭንቅላት በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በይበልጥ የተጋለጡ ናቸው ይላል ።

ለ/. ወንዶች በተለያዩ ሱሶች እና አደንዛዥ እፆች የመለከፍ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ነው። በዚህምየተነሳ የጉበት፣የሳንባ እና የመሳሰሉት ካንሰሮች ተጠቂ መሆናቸው የመሞት እድላቸው እንዲጨምር አድርጎታል።

ሐ/ . ከወንዶች ውልደት የሴቶች ውልደት የበዛ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው። የሴቶችን እና የወንድ ቁጥር የሚወስነው እንዲሁም ሴት ወይም ወንድ ይወለድ ብሎ የሚያዘው አምላካችን አላህ ብቻ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደመንስኤ ነው የሚሉት "x" ክሮሞዞም ከያዘው በፍጥነት ዝግ ያለ መሆን እና ማህፀን ውስጥ የመቆየት እድሜው ከፍተኛ መሆን የሴቷን የዘር ፍሬ የማግኘት እድሉ ከፍተኛ ነው።በዚህም ምክንያት ሴቶች በውልደት ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ።
…… አንዳንድ ይህ ሚስጥር የገባቸው የኢስላም ጠላቶች ሃቁን ሽምጥጥ አድርገው በውልደትም ሆነ በቁጥር ወንዶች ይበልጣሉ። በማለት በኢንተርኔት አሰራጭተዋል መፅሀፍም ፅፈዋል። እያወቁ የዋሹት እንጅ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ
#ሊሰመርበት ይገባል።

    ………እውነታው እንደዚህ ከሆነ እያንዳንዱ ወንድ ማግባት የሚችለው አንድ ሴት ብቻ ተብሎ ቢደነገግ ይህ ትክክለኛ ፍትህ ነው??? አንቺ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሳታገቢ የቀረሽ አንቺ ብትሆኝ ደስ ይልሻል??ይቺን አለም ያለቤተሰብ ያለባል ያለ ልጅ መኖር ያስደስትሻል?? ሙስሊሟ እህቴ ራስሽ ላይ አድርገሽ ፍርድ ስጭ።ወላሂ በጣም ልብ የሚያደማው አንዳንድ ጋጠ ወጥ ሴቶች የሌላ ሰው ህጋዊ  ባልን በድብቅ ለአራት ለአምስት ቀምተው ውስጥ ለውስጥ ባል አድርገው ይዘው በህጋዊ መንገድ ሁለተኛ ሆና ለገባችው ሙስሊም ተቆርቋሪ መስለው በኢስላም ላይ የሰላ ትችትን ሲሰነዝሩ ከማመም በላይ ያማል።

☞ ሙስሊም እህቴ ሆይ ካፊሮች አላህ በሚጠላው መንገድ አንድን ወንድ ብዙ ሆነው ሲጋሩት እያየሽ አንቺ በክብር ሁለተኛ ሚስት መሆንሽን እንደነውር የሚቆጥሩት በኢስላም ላይ ጦርነት እንጂ ለአንቺ ክብር ተቆርቁረው አይምሰልሽ።
#የአንቺን_ባል_ቢያገኙ_ለአስርም_ለሀያም_ቢሆን_የሚቀራመቱት_መሆኑን_ማን_በነገረሽ?????

የሆነው ይሁን ብለሽ የማያስተማምን ወንድ ለብቻ ከማግባት ከሁለነገሩ ለሚታመነው ወንድ አራተኛ ህጋዊ ሚስት ሆነሽ ብትገቢ እመክርሻለሁ። (ኡስታዝ ግን በአሁኑ ሰአት አይደለም አራተኛ ለመሆን ለሁለተኛስ ቢሆን እውነት የሚስቱን ሀቅ በትክክል የሚወጣ ወንድ አለ?????? )

4/
#ወንድ_ልጅ_እድሜ_ልኩን_
#የመውለድ_አቅም_መኖር

   አንድ ወንድ ልጅ ግንኙነት ማድረግ እስካላቆመ ድረስ የማስረገዝ አቅምን አላህ ሰጥቶታል። በተቃራኒ ሴት ልጅ መውለድ የምትችለው በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ ብቻ ነው። ስለሆነም አንድ ወንድ ሚስቱ ማርገዝ በማትችልበት የእድሜ ክልል ውስጥ ከገባች በኃላ ተጨማሪ ልጆች የመውለድ ፍላጎት እና የማሳደግ አቅም ካለው የሚፈለገውም ዘርን ማብዛት ስለሆነ የመጀመሪያ ሚስቱን ሳይፈታ ተጨማሪ ሚስት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለመውለድ እንዲችል
ከአንድ በላይ የመፈቀዱ ሸሪአዊ ጥበብ ነው።ዘርን ማብዛት በእስልምና የሚበረታታ ተግባር ነው።ለዚህም ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

{النكاح من سنتي،فمن لم يعمل بسنتي فليس مني،وتزوجوا فإني مكاثر بكم الآمم} (رواه ابن ماجه)

"ሚስት ማግባት ፈለጌ(ሱናዬ) ነው፣ በሱናዬ ያልሰራ ከእኔ አይደለም፣ተጋቡ፣የትንሳኤ ቀን ከሌሎች ነብያት በቁጥራችሁ እፎካከርባቹሀለሁ" ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

5
#ሴት_ልጅ_በተደጋጋሚ_በወር_አበባና_በወሊድ_ደም_ላይ_መቆየቷና_የባል_ስጋዊ_እርካታ_መፈለግ

     ወንድም ሆነ ሴት የሚያገቡበት ዋነኛ አላማ እራሳቸውን ሀራም ላይ እንዳይጥሉ እና ለጥፋት እንዳይዳረጉ ሲባል መሆኑን ለሁሉም ግልፅ ነው። ይህ አላማ በየትኛው መንገድ እንከን እንድገጥመው አይፈለግም።

#ሴት_ልጅ_በወር_አበባ_እና_በወሊድ_ደም_ላይ_እያለች_ከባሏ_ጋር_የግብረ_ስጋ_ግንኙነት_መፈፀም_አይፈቀድላትም።  በወር አበባ ሰአት ግንኙነት መፈፀም ከታላቅ ወንጀል ውስጥ የሚቆጠር ነው።በተጨማሪም በዚህ ሰአት የግብረ ስጋ ግንኙነት ለሴቷም ጤንነት ጥሩ አይደለም። በዚህ ጊዜ መላ ሰውነቷ ስለሚላላ እና ማህፀኗ ስለሚደማ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያጋጣት ይችላል። ባል ሚስቱ የወሊድ እና የወር አበባ ደሟን እስከምትጨርስ የመታገስ ልምድ ከሌለውና ስሜቱ የሚያስቸግረው ከሆነ በወር አበባ እና በወሊድ ደም ምክንያት #ወደ_ዝሙት_እንዳያመራና ችግር ላይ እንዳይወድቅ እንዲሁም ሚስቱን በወር አበባ ሰአቷ ተገናኝቶ ከባድ ወንጀል ውስጥ እንዳይዘፈቁ ሲባል አቅም ካለው ከአንድ በላይ በማግባት ከጥፋት ለመታደግ ሲባል የተፈቀደ አማራጭ ነው።. ይቀጥላል#ሼረ_ያድርጉ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜   #ክፍል ⑪ ...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_ ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ…
☞::::::ትዳር_በኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ሁለት

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

9)
#ብዙ_ልጅ_የመውለድ_ፍላጎት

   አንድ ሰው ብዙ ልጅ የመውለድና ዝርያውን የማብዛት አቅምና አላማ ካለው እና የመጀመሪያ ሚስቱ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ልጆችን ወልዳ ያቆመች ከሆነ ሌላ ሴት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለማግኝት በማሰብ ሁለተኛ ሚስት ማግባት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ሰአወ በዚህ ተግባር ላይ እንዲህ ሲሉ አበረታተዋል፣

"ወላድ እና ተወዳጅ የሆኑትን አግቡ የቂያም ቀን ከሌሎች ነብያቶች ጋር በብዛታችሁ እወዳደርባችሁ አለሁ።በሌላ ዘገባ ተጋቡም ተባዙም፣እኔ ሌሎችን ህዝቦች እፎካከርባቹሀለሁና።"

10 )
#ሌላ_ሀገር_ለረጅም_ጊዜ_እየቆየ
#የሚመለስና_የመጀመሪያ_ሚስቱ_አብሮ_ለመውሰድ_የማይችል_ሰው

   ይህ ሰው በሄደበት አገር ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ሰው ነውና
#ፆታዊ_ፍላጎት ሊያስፈልገው ይችላል።በዚህ ሰአት አማራጭ በሸሪአዊ መንገድ ተስማሚ ሆነችውን ሴት መርጦ ማግባት ወይም ሀላል ባልሆነ መንገድ በዝሙት ስሜቱን ማርካት። የትኛው እንደሚሻል ማንም የሚጠፋው አይመስለኝም። #ዚናና የሀላል ኒካህ እንዴት ሊወዳደር ይችላል? በፍፁም ይህን በተመለከተ #ዚዋጅ_አልሚስያር የሚለውን ንዑስ ርእስ ማንበብ ጠቃሚ ነው።

11/
#በተለያዩ_ምክንያቶች_የመጀመሪያ_
#ሚስቱ_ጋር_ፍቅር_ከጠፋ

   ምክንያቱ በሚታወቅም ሆነ ባልታወቀ ሚስቱን የሚጠላ ከሆነ ምን አልባትም መልኳ ወይም ፀባይዋ የማይመቸው ከሆነ እና በዚህም ምክንያት ለፆታዊ ፍላጎት የማታነሳሳ እና የእሱን ስሜት የማታረካ ብሎም ሃራም ላይ ልወደቅ እችላለሁ ብሎ የሚሰጋ ከሆነ ቤት ያለችውን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሚስት ማግባት የሚችልበት ሁኔታ ነው።ቤት ያለችው ሚስቱ ለተለያዩ ለእሷም ሆነ ለእርሱ ጥቅም ሲባል በኒካሁ ሊያቆያት ከፈለገ እና እሷም መፈታትን ካልፈለገች ሁለተኛ ሚስት መፈቀዱ ሸሪዓዊ ጥበቡ ነው።

12)
#ባል_በሌላቸው_ሴቶች_ላይ_የሚከሰትን
    
#ችግር_ለመታደግ_ሲባል

   በኢስላም
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት መፈቀዱ በርካታ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ አስችሏል። ከእነዚህም ውስጥ;

ሀ/ ባሏ ለሞተባት እና በርካታ የቲሞችን ለያዘች ሴት፣ ይቺ ሴት የእሷን ልጆች ወዶ ለመጀመሪያ ሚስትነት  የሚያገባት ወንድ እጅግ በጣም አናሳ
ነው።ስለሆነም አንድ ሰው እሷን በሁለተኛ ሚስትነት ሲያገባት ሁለት ታላላቅ መልካም ስራዎችን በአንድ ጊዜ እየሰራ ነው።አንዱ ይቺ የቲም የታቀፈች እና ፈቃጅ የሌላትን ሴት በማግባት መጠለያና ምሽግ ሆኖ ያገለገላት ሲሆን በዝያዘውም የፆታዊ ፍላጎቷን በማሟላት ከሀራም እንድትርቅ ያደርጋል።ሁለተኛው የታቀፈቻቸውን የቲሞች አባታቸውን በመተካት የአባትነት ሃላፊነት ወስዶ ይንከባከባቸዋል። በዚህም ትልቅን ምንዳ ከአላህ ይለግሰዋል።
የቲም  የተንከባከበ ሰው ጀነት ውስጥ የነብዩን ሰአወ ጉርብትና እንደሚያገኝ ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

"ጀነት ውስጥ እኔ እና የቲምን የሚንከባከብ ሰው እንደዚህ ነን(ተጎራባች ነን)" በአመልካች እና በመካከለኛ ጣቶቻቸው በማመልከት በሁለቱ መካከል ለያይተው አሳዩ(ልዩነታችን የዚህን ያህል ነው እንደማለት ነው)።

ለ/ ብዙም ውበት የሌላት ሴት ወንዶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የማይመርጧት ወይም አካል ገየዳተኛ ሆና የመጀመሪያ ሚስት ለመሆን የማትችል እና የመሳሰሉ ችግሮች ያለባቸው ሴቶች፣ ይቺን ሴት ይህ አይነት ችግር ስላለባቸው የትዳርን ህይወት ሊነፈጉ አይገባም።በዚህም የተነሳ የመጀመሪያ ሚስት መሆን ቢያቅታቸው ሁለተኛ ሚስት ሆነው የትዳርን ህይወት ማግኘት አለባቸው ሲል ኢስላም ደነገገው።
ሐ/ የአንድ ሰው ወንድሙ ወይም የቅርብ ዘመዱ ሚስትና ልጆቹን ጥሎበት ቢሞት ልጆቹን አባታቸውን ተክቶ ለመንከባከብና የወንድሙ ሚስት ያለባል የቲም ይዛ ጉዳት ላይ እንዳትወድቅ ሲባል በሁለተኛ ሚስትነት መያዝ በአመዛኙ ለሟች ልጆች እና ሚስት ትልቅ እረፍት እና ደስታን ይሰጣል።ለዚህም ሲል አላህ በጥበቡ ፈቀደው።እነዚህ እና መሰል በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ሁለተኛ ሚስት መፈቀድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶች

ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::ትዳር በኢስላም::::::☜ ክፍል #አስራ_አራት/⑭ት ከላይ ከቁርዓን አንቀፁ እና ከሀዲሱ እንደምንረዳው ማንኛውም ሰው በሰዎች ዘንድ በጣም የተመሰገነ እና የተከበረ ጨዋ ቢሆን የፈለገውን ያክል ሀብት ቢኖረው ወይም እጅግ ደግ ሰው ሆኖ ብዙ ሴቶች እሱን ለማግባት ቢፈልጉ የመጨረሻው ጣራ አራት ነው። ከአራት በላይ አምስተኛ ቢጨምር እንደ ሴት ሁለት ወንድ እንደማግባት ማለት ነው። አምስተኛዋን ሴት…
☞:::ትዳር በኢስላም::::::☜

     ክፍል~አስራአምስት/⑮
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶቹ

5.3
#በሚስቶች_መካከል_ፍትሃዊ_መሆን

   አላህ ሱወ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)
    በዚህ በተከበረው የአላህ ሱወ ቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ማስተካከል የሚለው ፅንሰ ሀሳብ የሰው ልጅ የሚችለው የሆነው እንደ ምግብና መጠጥ፣አልባሳት፣ መኖሪያቤት፣ ሚስቶች ጋር ማደር፣በመልካም መኗኗርና በመሳሰሉት ለሚስቶች ፍትሀዊ መሆን ማለት ነው። ነገር ግን ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ የሆነው እና አላህ ብቻ የሚቆጣጠረውን እንደ ፍቅርና የልብ ወደአንዷ መዘንበል የመሳሰሉትን ሰው ፈልጎት የሚያደርገው ነገር ስላልሆነና ለሁሉም ሚስቶቹ እኩል ማከፋፈል ስለማይችል ካላስተካከልክ ተብሎ በዚህ አይወቀስም።አላህም ከሚችለው በላይ አያስገድደውም። አላህ ሱወ እንዲህ ይላል፣

لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ

አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡
(አል-በቀራህ - 286)

    ባል ሚስቶቹን በፍቅር ማስተካከል እንደማይችል አላህ በሌላ የቁርአን አንቀፅ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡  [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129 ]

  ከቁርአን አንቀፁ እንደምንረዳው አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት ሁለቱን እኩል በፍቅር ማስተካከል እንደማይችል ነው።ነገር ግን ሁሉ ነገሩን ከሚወዳት ሚስቱ ጋር አድርጎ ሌላኛዋን ሚስቱን እንደትርፍ እቃ በመቁጠር ዝምብሎ እንዳይተዋት ሲል አላህ ያስጠነቅቃል።

   ☞ አንዳንድ ሰዎች ከላይ ያየነውን የቁርአን አንቀፅ በቅጡ ሳይረዱ
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደማይፈቀድ አድርገው ለማቅረብ ሲጣጣሩ ይስተዋላሉ።ይህ አይነቱ ማምታቻ በሚቀጥለው ምዕራፍ በስፋት የሚዳስስ ቢሆንም ለመግቢያ ያህል ትንሽ ማለቱ አይከፋም።የሚያቀርቡትም ምክንያት "በሚስቶች መካከል ማስተካከል ሸሪአው ቅድመ መስፈርት አድርጎ አስቀምጦታል፣በዚህ የቁርአን አንቀፅ ደግሞ አንድ ወንድ በሚስቶች መካከል ማስተካከል አትችሉም ስለተባለ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም" የሚል የማሀይም አረዳድ የተረዱ አሉ።እነዚህ ሰዎች የቁርአን የአቀራረብ ሲስተሙን ያልተረዱ ሰዎች ናቸው።ሌሎችንም የዲን ጉዳዮዎች ላይ ቁርአንን በዚህ መልኩ የሚረዱ ከሆነ አደጋ ውስጥ ናቸው። የቁርአኑ ትርጉም እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ማስተካከል አትችሉም የተባለው በፍቅር እና በልባዊ ዝንባሌ እንጂ የሰው ልጅ ማስተካከል በሚችለው  ውጫዊ ተግባርንም ጭምር ማለት አይደለም። ቁርአን አንድ ቦታ ፈቅዶ ሌላ ቦታ የሚከለክል እንዲሁም እርስ በርሱ የሚጋጭ ሳይሆን አንዱ ሌላውን የሚደግፍ እና የሚያብራራ ነው።የእነዚህም የሁለት የቁርአን አንቀፆች ቁርኝት አንዱን ሌላው የሚያብራራ ሆነው እነገኛቸዋለን።

   የሁለቱ የቁርአን አንቀፆች አጠር ያለው መልክ በአንድ ላይ ሲቀመጥ የሚከተለውን ይመስላል፣

  " ከሴቶች ለእናንተ  ተዋቡላችሁን እስከ አራት ማግባት ትችላላችሁ ፣ የሰው ልጅ በሚችለው ነገር ላይ ማስተካከል የምትፈሩ ከሆነ አንድ ብቻ አግቡ።የሰው ልጆች በማይቆጣጠሩት እንደፍቅር እና የልብ ፍላጎት ማስተካከል አትችሉም።ይህ በአላህ እጅ ያለ ነገር ነው፣ ያም ቢሆን በቻላችሁት ሁሉ ፍትሃዊ ሁኑ።ሴቶችን አንጠልጥላችሁ አተዋቸው።የሚል መልእክትን ይሰጣል።

………ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆነው የነብዩ ሰአወ ሀዲስ ነው፣ ከሰዎች ልጆች ሁሉ ፍትሃዊ በሚስቶቻቸው መካከል ከሌሎች ወንዶች የበለጠ የሚያስተካክሉት እንዲህ ብለዋል፣

(اللهم هذا قسمي فيما أملك فلا تلمني فيما تملك ولا أملك)

"አላህ ሆይ ይህ እኔ የምችለው (በሚስቶቼ መካከል) ማከፋፈል ነው፣አንተ በምትቆጣጠረው (ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነው) ነገር አትውቀሰኝ።" ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር።

   ☞√ በልብ ውስጥ ያለው ፍቅር እኩል ማዳረስ ስለማይቻልና ይህም የሰው ልጆች ስልጣን ስላልሆነ የአላህ መልእክተኛ ሰአወ እንኳን በማይችሉት ነገር አላህ እንዳይወቅሳቸው ዱአ አድርገዋል።

    ☞በሁለት ሚስቶች መካከል ፍትሀዊ መሆንን ነብዩ ሰአወ ትኩረት ሰጥተው  አበክረው ተናግረዋል።ፍትሃዊ ያልሆነ  ወንድ የሚጠብቀውንም ቅጣት እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣

(إذا كان عند الرجل إمرأتآن فلم يعدل بينهما جاء يوم القيامة وشقه ساقط )
  አንድ ወንድ ሁለት  ሚስቶች እያሉት በመካከላቸው ሳያስተካክል የሞተ ከሆነ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የሰለለ(ሽባ)ሆኖ ይቀርባል። (ሀዲሱን ነሳኢና ቲርሚዝይ ዘግበዉታል።
ይቀጥላልኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
  ☞::::ትዳር በኢስላም:::::☜ #ክፍል_አስራ_ስድስት/⑯ አንድ ወንድ ሚስቶቹን በሚችለው አቅም በመካከላቸው በፍትህ የማያስተዳደር ከሆነ ተበደልኩ የምትለው ሚስት ለቃዲ ስሞታ ማቅረብ ትችላለች።ቃዲውም  በፍትህ እንዲያዝ ወይም እንዲፈታት ያዘዋል ለዚህም የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ማስረጃ ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፣ وَإِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ…
☞::::ትዳር→በኢስላም:::::☜

    
#ክፍል_አስራ_ሰባት/⑰

#ሚስቶችን_በድርሻቸው_ማስተካከል

   ባል በሚስቶቹ መካከል ድርሻቸውን ማስተካከል ሸሪአዊ ግዴታ ለመሆኑ ሁሉም የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ነው፣

وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ

በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡(አል ኒሳእ 19)
   በዚህ  የቁርአን ምዕራፍ እንደተጠቀሰው ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲኖሩ በመልካም እንድኗኗሯቸው አላህ ግዴታ አድርጓል።ስለሆነም አንድ ወንድ ከሁለት ሚስቶቹ ወደ አንዷ የሚያዘነብል ከሆነ በመልካም ተኗኗረ አይባልም። አላህም እንዲህ ይላል፣

فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ
እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡
(አል ኒሳእ 129)

   በሀዲስም በኩል በርካታ ሀዲሶች መጥተዋል።

   ኢማም ኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ በሚባለው ኪታባቸው 7ኛው ጥራዝ ከገፅ 301_305 ድረስ የሚከተለውን አስፍረዋል፣

"
ከአንድ በላይ ሚስቶች ያሉት ወንድ ከሚስቶቹ ጋር ማደር ሲጀምር እጣ አጣጥሎ እጣዋ የወጣላት ጋር መጀመር አለበት።በዚህ ጉዳይ ላይ ሚስቶቹን እኩል ማድረግ በእርሱ ላይ ዋጅብ ነው። በመረጣት ሴት ቢጀምር ይቺን ሴት የመጀመሪያ ማድረጉ እሷን እንደማስበለጥ ስለሚቆጠር ይህን ባለማድረጉ ዋጅብን እንደተወ ይቆጠራል።በተመሳሳይ መልኩ ለጉዞ ሚስት ይዞ መጓዝ ካስፈለገው በእጣ  ማድረግ ግድ ይለዋል።ነገር ግን ባል ለሁለተኛ ጊዜ ጉዞ ቢወጣ
የቀሩት  መዳረስ ስላለባቸው የመጀመሪያዋ እጣ የወጣላት ሚስቱ መልሳ እጣ ውስጥ አትካተትም። ባል በአንድ ጊዜ የሁሉንም እጣ በማውጣት የመጀመሪያ ሲጓዝ አብራዉ የምትጓዘው የሁለተኛ ሲጓዝ አብራው የምትጓዘው የሶስተኛና የአራተኛ ብሎ ለአራቱም ሚስቶቹ በአንድ ጊዜ የሁሉንም ማውጣት ይችላል።

  ☞ ባል በእብደት ወይም በሌላ ነገር አቅሉን ስቶ የሚስቶቹን ተራ መቆጣጠር ካልቻለ የቅርብ ዘመዶቹ እየተከታተሉ በየሚስቶቹ ቤት እንዲያድር ያደርጉታል።ባል ከሚስቶቹ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ማድረግ ግዴታ ነው።ነገር ግን ለሁሉም እኩል ማድረግ አለብህ አይባልም ቢያደርግ ግን የተወደደ ነው።

    አንድ ባል ያለችግር ሚስቱን ለረጅም ጊዜ ሊለያት አይገባም።" ንግግራቸው እዚህ ላይ አበቃ።
#ባል_በሚስቶቹ_መካከል_እኩል_ማካፈል_ግዴታ_የሚሆኑበት_እና_ግዴታ_የማይሆኑበት_ነገሮች

     ይህን በተመለከተ ኢማም ኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ በሚባለው ኪታባቸው 7ኛ ጥራዝ ከገፅ 305_306 ድረስ ከኢማም አህመድ ተወርቷል ብለው የሚከተለውን አስፍረዋፅ፣ *ባል ለሚስቶቹ የሚበቃቸውን ያክል እስከሰጠ ድረስ በመካከላቸው በቀለብ፣በልብስ እና በስሜት እኩል እንዲያደርግ ግዴታ የለበትም  
#ባል_ወደ_ሚስቶቹ_ቤት_የሚሄድበትን_ቀን_እኩል_ማካፈል_አለበት

☞ ባል ለሚስቶቹ እኩል ማካፈል ያለበት ሌሊቱን??ወይስ ቀኑንም ጭምር??

   አንድ ወንድ ቀኖቹን ለሚስቶቹ ሲያካፍል መነሻ የሚያደርገው ሌሊቱን ነው።ምክንያቱም ሰው ወደ ቤቱ የሚገባው እና ከስራ የሚያርፈው ሌሊት ስለሆነ ነው።ሰው በተለምዶ ቀን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለኑሮ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሲከስብ ይውል እና ማታ መጥቶ ከባለቤቱ ጋር ያርፋል።ይህንን የሚጠቁመው የቁርአን አንቀፅ የሚከተለው ነው።አላህ እንዲህ ይላል፣

"ሌሊቱንም ማረፊያ አደረገ፣" (አል አንአም 96)
በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ ሱወ እንዲህ ይላል፣ "ሌሊቱንም ልባስ አደረግን"(አል ነበእ 10)

በሌላ የቁርአን አንቀፅ፣እንዲህ ይላል
"ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ አደረግን" (አል ነበእ 11)
በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ ሱወ እንዲህ ይላል

"ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊቱንና ቀኑን ልታርፉበት ከቱርፋቱም ልትፈልጉበት፣አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ።"(አል ቀሰስ 73)

  ነገር ግን የባል ስራው የሌሊት ከሆነ ቀኑ መነሻ በማድረግ ለሚስቶቹ እኩል በማካፈል በየተራቸው ሁሉንም በእኩል ይጎበኛል።

   ……አንድ ባል ለሚስቶቹ ቀኖቹን በሚያካፍልበት ሰአት ያ ቀን ከነሌሊቱ የባለድርሻዋ ሀቅ ነው። በዚያን ቀን እሌላዋ ቤት መሄድ  አይችልም።ነገር ግን ለአሳሳቢ ጉዳይ መግባት ይችላል።ለምሳሌ የታመመ ለመጠየቅ ሚስቱ ቀለብ አልቆባት ከሆነ ለመስጠት እና ለመሳሰሉት ችግሮች ሳይቆይ ጉዳዩን ፈፅሞ ቶሎ መመለስ አለበት።ተረኛዋ ያልሆነችው ሚስቱ ቤት ሲገባ ከመሳም የዘለለ ግንኙነት ማድረግ አይችልም።
#በዚችኛዋ_ተራ_እዛች_ዘንድ_ሄዶ_ግንኙነት_ቢፈፅም_ወንጀለኛ_ነው ማካካሻ ይጠበቅበታል። ምክንያቱም የሌላ ሰው ሃቅ አሳልፎ ሰቷልና።

(ከኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ ከሚለው ኪታባቸው ወደ አማረኛ የተተረጎመ)
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች

ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ስምንት_/⑱_ት

#ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች

    1/
#ማምታቻ_አጭር_መልስ
   "አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ በሚስቶቻችሁ መካከል ማስተካከል አትችሉም ብሏል የሚል ነው።"  የቁርአኑን ፅንሰ ሀሳብ እንመልከት

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129)

   ይህን የቁርአን አንቀፅ በመጥቀስ እንዲህ ይላሉ፣ "ወንዶች በሴቶቻቸው መካከል ማስተካከል እንደማይችሉ ተነግሯል፣ ማስተካከክ አለመቻል
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደማይቻል ያመለክታል።ምክንያቱም በሚስቶች መካከል ማስተካከል አንዱ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ"

#አጭር_ምላሽ፣ አላህ በዚህ በተከበረው አንቀፁ የጠቆመው በሴቶች መካከል በውስጣዊ ፍላጎት (እንደፍቅርና የልብ ዝንባሌ) እኩል ማድረግ ወንዶች ለማስተካከል ቢጓጉም እንኳ እንደማይቻል ነው።ምክንያቱም የሰው ልጅ ቀልብ የሚቆጣጠረው አላህ እራሱ ብቻ ስለሆነ ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ ነው።ቢሆን እንኳ የሰው ልጅ በሚችለው እና በሚቆጣጠረው ነገር ሚስቶችን ማስተካከል በእርሱ ላይ ግዴታ መሆኑ ነው።በፍቅር እና ዝንባሌም ቢሆን ለማስተካከል ያቅማችሁን መሞከራችሁ የሚያስመሰግን እና ለእናንተ የተሻለ ነው ፣ በፍቅር በልባዊ ዝንባሌ እንዲሁም በግንኙነት ሴቶቻችሁን እኩል አለማድረጋችሁ ከአንድ በላይ ከማግባት አይከለክላችሁም ከዚህ ያለፈውን አላህ መሀሪ እና አዛኝ ጌታ ነው የሚል ነው የአንቀፁ ትንታኔ የያዘው።ታዲያ ከየት መጥቶ ነው የቁርአኑ አንቀፅ ከአንድ በላይ አታግቡ ብሎ የሚከለክለው???የዚህ የቁርአን አንቀፅ ትርጓሜ አብደላህ ኢብኑ አባስ ረአ ሲተነትኑት  ማስተካከል አሉም የተባሉ ነገሮች #እንደፍቅር እና #ግንኙነት ማለት ነው ይላሉ።

    ☞ የቁርአን ባህሪው አንዱን አንዱ የሚያብራራ እንጅ አንዱ ከሌላው የተቃረነ ሆኖ አልወረደም።አላህ ሱወ በሌላ የቁርአን አንቀፅ
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ መሆኑ ሲገልፅ እንዲህ

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

   በዚህ የቁርአን አንቀፅ
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ ሲሆን በቁሳዊ አካል ማለትም ባል ማስተካከል የሚይችለው ነገር እንደ ቀለብ ልብስ ሚስቶች ጋር ማደር ማስተካከል የማይችል ሰው ከሆነ አይደለም 2 እና ከዚያ በላይ #አንድም ማግባት አይችልም።ስለዚህ ማስተካከል በተመለከተ እኛን የሚያስጠይቀን እና የምንችለው በሆነው ማስተካከል የማይሳካልን ከሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእኛ ላይ እርም ተደርጓል።ነገር ግን አላህ የሚቆጣጠረውና እኛ የማንችለው ማስተካከል ከሆነ እኛ እናስተካክላለን ብለን ብንቀና እንኳ ማስተካከል እንደማንችል አላህ ነግሮናል።ይህ ከመሆኑም ጋር በቻልነው መጠን እንድንጠናከር አስገንዝቦናል።ከአቅማችን በላይ ለሆነው አላህ መሀሪ አዛኝ ነው።ነብዩም ሰአወ በሚስቶቻቸው መካከል ማስተካከል በተመለከተ ከሚችሉት በላይ የሆነው ባለቤቱ አላህ እንደሆነ እና በማይችሉት ነገር እንደ ፍቅር ባሉት አላህ ይቅር እንዲላቸው እንዲህ ይላሉ

(اللهم هذا قسمي فيما أملك فلا تلمني فيما تملك ولا أملك)

"አላህ ሆይ ይህ እኔ የምችለው (በሚስቶቼ መካከል) ማከፋፈል ነው፣አንተ በምትቆጣጠረው (ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነው) ነገር አትውቀሰኝ።" ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር።

2/
#ማምታቻ_እና_አጭር_መልስ

   አንዳንድ
ከአንድ በላይ ሚስት አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቡት የአልይ ኢብኑ አቡ ጧሊብን ቂሷ ነው፣በዚህ ቂሷ ውስጥ የነብዩ ሰአወ ሀዲስ አለ።ይህ ሀዲስ እንደመረጃ ያገለግለናል በሚል ሙሉ ሳይሆን ለእነሱ የሚመቻቸውን ወይም ከሀሳባቸው ጋር አብሮ የሚሄደውን ቆርጠው ያቀርባሉ።ይህ ተግባር በእጅጉ የሚወገዝ ነው።ነብዩ ሰአወ ላይ እንደመዋሸት የሚቆጠር ነው።እነሱ መረጃ ብለው ያቀረቡት፣"አሊይ ረአ የነብዩን ሰአወ ልጅ ፋጡማ እቤታቸው እያሉ የአቡ ጀህልን ልጅ ለማግባት ነብዩን ሰአወ ፈቃድ ሲጠይቋቸው አልፈቀዱላቸውም እንዲህም አሏቸው "ፈቃድ አልሰጥህም በድጋሜም ፈቃድ አልሰጥህም የእኔን ልጅ ፍታ እና የአቡ ጀህልን ልጅ አግባ፣ ልጄን የሚያስጨንቃት ጉዳይ እኔንም ያስጨንቀኛል።ልጄ የእኔ አካል ናት እና" ብለው መለሱላቸው።ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይፈቀድም ብለው ይህን እንደማስረጃ ያቀርባሉ። ኢንሻአላህ ይቀጥላል።
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜  #ክፍል_አስራ_ስምንት_/⑱_ት #ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች     1/ #ማምታቻ_አጭር_መልስ    "አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ በሚስቶቻችሁ መካከል ማስተካከል አትችሉም ብሏል የሚል ነው።"  የቁርአኑን ፅንሰ ሀሳብ እንመልከት وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ…
    ☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ_/⑲ኝ

#ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች

#አጭር_መልስ፣ በመጀመሪያ እነዚህ አካላት የዚህን ሀዲስ መልእክት ወይም ትርጉም ሙሉውን ሳይሆን ለእነሱ መረጃ ይሆነናል ብለው ያሰቡትን ብቻ ቆርጠው ለማቅረብ ሞክረዋል።የሀዲሱ ሙሉ ይዘቱ ሲቀርብ ለእነሱ መረጃነቱ ይቀርና በእነሱ ላይ መረጃ ይሆናል። የሀዲሱ ሙሉ ትርጉም ይህን ይመስላል፣
"እኔ ሀላልን ሀራም፣ ሀራምን ሀላል የማደርግ አይደለሁም ነገር ግን በጌታዬ ይሁንብኝ በፍፁም የአላህ መልእክተኛ ልጅ እና የአላህ ታላቅ ጠላት ልጅ በአንድ ቤት ሊሆኑ አይችሉም።" የሚል ነበር።

    ☞ የአላህ መልእክተኛ ለአልይ የአቡ ጀህልን ልጅ እንዲያገባ ፈቃድ ያልሰጡት ከዲን አንፃር ስለማይፈቀድ ሳይሆን ከማህበራዊ ኑሮ አንፃር ነው።ይህ የአላህ ታላቅ ጠላት የኢስላም ቁጥር አንድ ከሚባሉት ጠላቶች ውስጥ የሆነ እና ነብዩን በከፍተኛ ኢ_ሰብአዊ በሆነ መልኩ ሲያሰቃይ የነበረ እና ቀጥተኛውን መንገድ እንደማይዝ  ነብዩ ሰአወ ያውቁ ስለነበር ነው።ስለዚህ ይህ የሂዳያ ተስፋ የሌለው ከነብዩ ጋር ተቀራርቦ እርሳቸውንም ሆነ ልጃቸው ፋጡማን ረአ ለአደጋ እንዳያጋልጥ ከእርሱ ጋር የሚያገናኛቸውን ጉዳይ የበለጠ መራቅ ነበረባቸው።ምን አልባት ልጁ የአላህን መልእክተኛ ልጅ ባል በማግባቷ በልጁ ሰበብ በነብዩም ላይ ሆነ በፋጡማ ላይ ጉዳት ለማድረስ አጋጣሚውን ሊያሰፋ ይችላል።በዚህ እና መሰል ማህበራዊ ጉዳዮች ለአልይ የአቡ ጀህልን ልጅ እንዳያገባ ከልክለውታል ትክክለኛው ይህ ነው።

   3/
#ማመወታቻ እና አጭር ምላሽ

"
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በሚስቶች መካከል ጥላቻ እና መቃቃር ይፈጥራል አልፎም ልጆች በጥላትነት እንዲተያዩ ያደርጋል"
#አጭር_መልስ፣ ይህ አይነቱ ድምዳሜ ከሀቅ የራቀ ለመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን ብቻ መመልከት በቂ ይመስለኛል።በተለያዩ የሀሳብአለመግባባቶች በአንድ ቤት ውስጥ ያሉ እናት እና ልጅ ጭምር ሊጣለየ ይችላሉ በተመሳሳይ በሁለቱ ሚሰወቶች መካከል ግጭቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ እነዚህ ግጭቶች በሰው ልጅህይወት ውስጥ አልፎ አልፎ መከሰታቸው አይቀርም። ነገር ግን ሁለተኛ ሚስቶች ሁሉ  ይጣላሉ ማለት አይቻልም።እንደዚህ ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ኢስላምን ከመጥላት የመነጨ እንጂ በትክክለኛ አእምሮ የተመዘነ አይደለም።ምክንያቱም የአንድ አባወራ ሁለት ሚስቶች እንደእህትማማች የሚተያዩ በልጆቻቸው መካከል ምንም ልዩነት የማያውቁ በርካቶች አሉ።የአንድን አባወራ ቤተሰብ የመምራት አቅም ማነስ ችግርን ከሁለተኛ ሚስት ጋር ማያያዝ ፍርደ ገምድልነት ነው።

#የኢስላም_ጠላቶች_ከአንድ_በላይ_ሚስትን_አስመልክተው_የሚያነሱት_ትችቶችና_መልሶቻቸው

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳር በኢስላም::::👈 ክፍል ሀያ/⑳ #የኢስላም_ጠላቶች_ከአንድ_በላይ_ሚስትን_አስመልክተው_የሚያነሱት_ትችቶችና_መልሶቻቸው    ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ድንጋጌ ሲሆን ከፊቱም ሆነ ከኃላው መጥፎ ነገር  የማይመጣበት ነው። በቁርአን እና በሀዲስ  ተደግፎ የሚመጣ ማንኛውም ድንጋጌ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ በሁሉም ዘመን ትልቅ ጥቅም ያዘለ እንጅ የሚጎዳ ነገር ፈፅሞ አይቀላቀለውም።…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

#ክፍል_ሀያ_አንድ/②①

2#አንድ_ወንድ_ከአንድ_በላይ_የሚያገባ_ከሆነ_በእያንዳንዱ_ቤት_ያለው_ቤተሰብ_አንዱ_ለሌላው_የጠላትነት_ስሜት_እንድኖር_ያደርጋል_ይላሉ

#መልስ፣ በመሰረቱ ይህን ሙስሊም የሚባሉትም ሰዎች እንደሚያነሱ አሳልፈናል። ይህ ሁሉ ፈር የለቀቀ አስተሳሰብ ኢስላምን በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው።በመካከላቸው አንድ የሚያደርጋቸው አባት መኖሩ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ የስጋ ዝምድና ተቀላቅሎ እያለ እንዴት ስለጠላትነት ሊነሳ ይችላል??ነገሩማ ሰው የሚገምተው ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ተነስቶ ስለሆነ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የለመዱት መጠጥ ቤት ገብተው አንድ ሴት ለአራት ወይም ለአምስት ይዘው በዝሙት ሲጨማለቁ አድረው ጠዋት ላይ ተፈነካክተው ይለታያሉ ፣የለመዱት ይህን ስለሆነ ይህ ቆሻሻ ተግባራቸው ኢስላም ውስጥ የሚከሰት ይመስላቸዋል።ሲቀጥል እኛ ሙስሊሞች ለሁሉም የማያዳላ በፍትህ የሚፈርድ ኢስላም አለን።ሁሉም የራሱን ሀቅ ጠብቆ ሌላ ሰው ሳይጎዳና ሳይጨቁን እንዲኖር ያስገድደናል።ይህን ሁሉ አልፎ እንዴት ስለመጨቃጨቅ ይወራል??? ቅሬታ እንኳ የሚኖር ከሆነ ሊከሰት የሚችለው በባላቸው ስር ባሉ ሚስቶች ወይም እናቶችቻቸው በአባቶቻቸው ስር ባሉ ልጆች ሳይሆን ሁለተኛ ሚስት ባለመቀበል ምክንያት በተፈታችው ሴት ወይም ልጆችና እናታቸወ ቤት ባሉ ልጆች መካከል ነው። #የእኛን_እናት_ፈቶ_የናንተን_እናት_ይዟል፣ የእኛ እናት ተቸግራ የእናንተ እናት ከባሏ ጋር ትኖራለች በማለት በተፈታችውና አዲስ በተገባችው ሚስት ቤተሰብ መካከል መጨቃጨቅ ሊኖር ይችላል። ይህ መጨቃጨቅ ራስን በኢስላም ካለማስገዛት የመነጨ ነው።ምክንያቱም #ሁለተኛ_ሆኖ_መኖርን_ብትቀበል ይህ ሁሉ ንትርክ ከየት ይመጣል።

3/
#ከአንድ_በላይ_ሴቶችን_ማግባት_ክብራቸውን_የሚነካና_የመበደል_ተግባር_ነው_ይላሉ

#መልስ፣ ሴቶችን ክብር አልባ የሚያደርገው በተለያየ ምክንያት ባል ሳታገባ ቀርታ ወይም ለመጀመሪያ ሚስትነት ለመመረጥ ያልታደለች ሆና የሚንከባከባትና ቁጥብነቷን የሚያረጋግጥላት ሀላፊነቱን የሚወስድ ባል ባለማግኘቷ ክብሯ ተነክቶ የወንድም የሴቱን ስራ ራሷ ተሸክማ ኑሮን መግፋት ለክብሯ የማይበጀውና ፍትሀዊያልሆነው ስርአት ይህ ነው።
።ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ሚስትነት መስፈርት ሳታሟላ ቅ ታ የሚፈልጓት ወንዶች ባየወገኙ ያገኘ ባለጌ ከሚደፍራት ሁለተኛ ሆና በማግባት ክብሯን ማስጠበቅ የተከበረች የሙስሊም ሴት መገለጫ እንጂ የአላህ እርግማን የወረደባቸው ጋጠወጥ ሴቶች  መገለጫ አይደለም።

4
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_ማግባት_ለህዝብ_ብዛት_ዋና_መንስኤው_ሲሆን_ለአንድ_ሀገር_ደሀ_ የመሆን_ዋና_ምክንያት_ነው_ይላሉ፣

#መልስ፣ ይህ አባባል መመዘኛው የተንጋደደ ሰው አስተሳሰብ እንጂ የሌላ አይደለም።የህዝብ ብዛት ለድህነት መንስኤ ቢሆን #ቻይና የመጨረሻዋ ደሀ አገር ትሆን ነበር።ነገር ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒው ነው።በርካተሰ መውለድ በኢስላም የሚበረታታ የሚደገፍ ከመሆኑም ባሻጋር የሁሉም ሰው የሲሳይ አዳይ አላህ ብቻ ነው።ሲሳይ በሰው እጅ ቢሆን እማ ስንት ብልጥ ድሆች ነበሩ ሁለየንም ቀድመው ትልቅ ሀብት በያዙ ነበር።

   ☞ እነዚህ የኢስላም ጠላቶች
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ለመቃወም የሚያመጧቸው በርካታ ተልካሻ ምክንያቶች አሉ።ሁሉንም እያነሱ መልስ መስጠት ጊዜው አይበቃም።በጥቅሉ ሁሉም መቃወሚያዎቻቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ተልካሻ ሀሳቦች ናቸው።ሙስሊም ላደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው።

5/
#የኢስላም_ጠላቶች_ድብቅ_አላማቸውን_ለማስፈፀም

   ሙስሊም ሴቶች አላህ የዋለላቸው ታላቅ ኒእማ(ፀጋ) ማስተዋል አቅቷቸው ለምእራባዊያን እጅ ሲሰጡ ይስተዋላሉ።ምእራባዊያን
ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ሲቃወሙ ከበስተጀርባው የሚፈልጉት አላማ ለሙስሊም ሴቶች ብቻ ተደብቆባቸዋል።የሙስሊም ሴቶች ቁጥብነት ያስቆጫቸው ምእራባዊያን የእነሱ የእርቃን እና የአደባባይ የዝሙት አባል ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድናጋይ የለም።አንዳንድ የዋህ የሙስሊም ሴቶች ለጥሪያቸው አቤት ብለው እጅ ሰጥተው ኢስላም የሰጣቸውን ክብር ጥለው እንደ እነርሱ የውርደትን ህይወት ተቀላቅለዋል።በኢስላም ጥላ ስር ስትኖር እንዴት ሁለተኛ የክብር ሚስት ትሆኛለሽ ሲሏት የነበሩት እነሱን ስትቀላቀል እንደ ረከሰ ሸቀጥ በጅምላ አንድ ለአስር ወይም አንድ ለአምስት ካልሆነ አንድ ለመቶ የረከሰ የዝሙት ወንድ ተጋሪ ትሆናለች።የሚያሳዝነው ሰላሳ አርባ ሴት በዝሙት የሚያንጋጋ ወንድ ጋር ስትማግጥ (ሙስሊም ሴቶችን አላህ ይጠብቅልን) የማይሰማት ሴት ወደ ኢስላም ተመለሽ ባል ከጠፋ በክብር ሁለተኛ ሚስት ሁኚ ስትባል እምቧ ከረዩ ስትል ትስተዋላለች።ይህ የጤነኝነት አይመስለኝም። "አላሁል ሙስተአን ወኢላሂቱክላን" ትርጉሙን ፀሀፊውን ጠትቁልኝ!!!!!

#የነብዩ_(صلى الله عليه وسلم)_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ..
#ኢንሻአላህ_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam