الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳር በኢስላም::::👈 ክፍል ሀያ/⑳ #የኢስላም_ጠላቶች_ከአንድ_በላይ_ሚስትን_አስመልክተው_የሚያነሱት_ትችቶችና_መልሶቻቸው    ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ድንጋጌ ሲሆን ከፊቱም ሆነ ከኃላው መጥፎ ነገር  የማይመጣበት ነው። በቁርአን እና በሀዲስ  ተደግፎ የሚመጣ ማንኛውም ድንጋጌ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ በሁሉም ዘመን ትልቅ ጥቅም ያዘለ እንጅ የሚጎዳ ነገር ፈፅሞ አይቀላቀለውም።…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

#ክፍል_ሀያ_አንድ/②①

2#አንድ_ወንድ_ከአንድ_በላይ_የሚያገባ_ከሆነ_በእያንዳንዱ_ቤት_ያለው_ቤተሰብ_አንዱ_ለሌላው_የጠላትነት_ስሜት_እንድኖር_ያደርጋል_ይላሉ

#መልስ፣ በመሰረቱ ይህን ሙስሊም የሚባሉትም ሰዎች እንደሚያነሱ አሳልፈናል። ይህ ሁሉ ፈር የለቀቀ አስተሳሰብ ኢስላምን በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው።በመካከላቸው አንድ የሚያደርጋቸው አባት መኖሩ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ የስጋ ዝምድና ተቀላቅሎ እያለ እንዴት ስለጠላትነት ሊነሳ ይችላል??ነገሩማ ሰው የሚገምተው ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ተነስቶ ስለሆነ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የለመዱት መጠጥ ቤት ገብተው አንድ ሴት ለአራት ወይም ለአምስት ይዘው በዝሙት ሲጨማለቁ አድረው ጠዋት ላይ ተፈነካክተው ይለታያሉ ፣የለመዱት ይህን ስለሆነ ይህ ቆሻሻ ተግባራቸው ኢስላም ውስጥ የሚከሰት ይመስላቸዋል።ሲቀጥል እኛ ሙስሊሞች ለሁሉም የማያዳላ በፍትህ የሚፈርድ ኢስላም አለን።ሁሉም የራሱን ሀቅ ጠብቆ ሌላ ሰው ሳይጎዳና ሳይጨቁን እንዲኖር ያስገድደናል።ይህን ሁሉ አልፎ እንዴት ስለመጨቃጨቅ ይወራል??? ቅሬታ እንኳ የሚኖር ከሆነ ሊከሰት የሚችለው በባላቸው ስር ባሉ ሚስቶች ወይም እናቶችቻቸው በአባቶቻቸው ስር ባሉ ልጆች ሳይሆን ሁለተኛ ሚስት ባለመቀበል ምክንያት በተፈታችው ሴት ወይም ልጆችና እናታቸወ ቤት ባሉ ልጆች መካከል ነው። #የእኛን_እናት_ፈቶ_የናንተን_እናት_ይዟል፣ የእኛ እናት ተቸግራ የእናንተ እናት ከባሏ ጋር ትኖራለች በማለት በተፈታችውና አዲስ በተገባችው ሚስት ቤተሰብ መካከል መጨቃጨቅ ሊኖር ይችላል። ይህ መጨቃጨቅ ራስን በኢስላም ካለማስገዛት የመነጨ ነው።ምክንያቱም #ሁለተኛ_ሆኖ_መኖርን_ብትቀበል ይህ ሁሉ ንትርክ ከየት ይመጣል።

3/
#ከአንድ_በላይ_ሴቶችን_ማግባት_ክብራቸውን_የሚነካና_የመበደል_ተግባር_ነው_ይላሉ

#መልስ፣ ሴቶችን ክብር አልባ የሚያደርገው በተለያየ ምክንያት ባል ሳታገባ ቀርታ ወይም ለመጀመሪያ ሚስትነት ለመመረጥ ያልታደለች ሆና የሚንከባከባትና ቁጥብነቷን የሚያረጋግጥላት ሀላፊነቱን የሚወስድ ባል ባለማግኘቷ ክብሯ ተነክቶ የወንድም የሴቱን ስራ ራሷ ተሸክማ ኑሮን መግፋት ለክብሯ የማይበጀውና ፍትሀዊያልሆነው ስርአት ይህ ነው።
።ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ሚስትነት መስፈርት ሳታሟላ ቅ ታ የሚፈልጓት ወንዶች ባየወገኙ ያገኘ ባለጌ ከሚደፍራት ሁለተኛ ሆና በማግባት ክብሯን ማስጠበቅ የተከበረች የሙስሊም ሴት መገለጫ እንጂ የአላህ እርግማን የወረደባቸው ጋጠወጥ ሴቶች  መገለጫ አይደለም።

4
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_ማግባት_ለህዝብ_ብዛት_ዋና_መንስኤው_ሲሆን_ለአንድ_ሀገር_ደሀ_ የመሆን_ዋና_ምክንያት_ነው_ይላሉ፣

#መልስ፣ ይህ አባባል መመዘኛው የተንጋደደ ሰው አስተሳሰብ እንጂ የሌላ አይደለም።የህዝብ ብዛት ለድህነት መንስኤ ቢሆን #ቻይና የመጨረሻዋ ደሀ አገር ትሆን ነበር።ነገር ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ በተቃራኒው ነው።በርካተሰ መውለድ በኢስላም የሚበረታታ የሚደገፍ ከመሆኑም ባሻጋር የሁሉም ሰው የሲሳይ አዳይ አላህ ብቻ ነው።ሲሳይ በሰው እጅ ቢሆን እማ ስንት ብልጥ ድሆች ነበሩ ሁለየንም ቀድመው ትልቅ ሀብት በያዙ ነበር።

   ☞ እነዚህ የኢስላም ጠላቶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ለመቃወም የሚያመጧቸው በርካታ ተልካሻ ምክንያቶች አሉ።ሁሉንም እያነሱ መልስ መስጠት ጊዜው አይበቃም።በጥቅሉ ሁሉም መቃወሚያዎቻቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ተልካሻ ሀሳቦች ናቸው።ሙስሊም ላደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው።

5/
#የኢስላም_ጠላቶች_ድብቅ_አላማቸውን_ለማስፈፀም

   ሙስሊም ሴቶች አላህ የዋለላቸው ታላቅ ኒእማ(ፀጋ) ማስተዋል አቅቷቸው ለምእራባዊያን እጅ ሲሰጡ ይስተዋላሉ።ምእራባዊያን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ሲቃወሙ ከበስተጀርባው የሚፈልጉት አላማ ለሙስሊም ሴቶች ብቻ ተደብቆባቸዋል።የሙስሊም ሴቶች ቁጥብነት ያስቆጫቸው ምእራባዊያን የእነሱ የእርቃን እና የአደባባይ የዝሙት አባል ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድናጋይ የለም።አንዳንድ የዋህ የሙስሊም ሴቶች ለጥሪያቸው አቤት ብለው እጅ ሰጥተው ኢስላም የሰጣቸውን ክብር ጥለው እንደ እነርሱ የውርደትን ህይወት ተቀላቅለዋል።በኢስላም ጥላ ስር ስትኖር እንዴት ሁለተኛ የክብር ሚስት ትሆኛለሽ ሲሏት የነበሩት እነሱን ስትቀላቀል እንደ ረከሰ ሸቀጥ በጅምላ
አንድ ለአስር ወይም አንድ ለአምስት ካልሆነ አንድ ለመቶ የረከሰ የዝሙት ወንድ ተጋሪ ትሆናለች።የሚያሳዝነው ሰላሳ አርባ ሴት በዝሙት የሚያንጋጋ ወንድ ጋር ስትማግጥ (ሙስሊም ሴቶችን አላህ ይጠብቅልን) የማይሰማት ሴት ወደ ኢስላም ተመለሽ ባል ከጠፋ በክብር ሁለተኛ ሚስት ሁኚ ስትባል እምቧ ከረዩ ስትል ትስተዋላለች።ይህ የጤነኝነት አይመስለኝም። "አላሁል ሙስተአን ወኢላሂቱክላን" ትርጉሙን ፀሀፊውን ጠትቁልኝ!!!!!

#የነብዩ_(صلى الله عليه وسلم)_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ..
#ኢንሻአላህ_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam