الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
23.1K subscribers
352 photos
16 videos
7 files
905 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር_በኢስላ☜   #ክፍል_ስድስት/⑥ ☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ   #በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር። #በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው…
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜

 
#ክፍል_ሰባት_⑦ት

     
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም

   ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን ምንም የሚያስጨንቃቸው አልነበረም።

    የሰው ልጅ አይነታ የሆኑት
#የአላህ_መልእክተኛ_ሰአወ ኢስላምን ለማደስ ከመጡ በኃላ በጃሂልያ ይተገበር የነበረው ፈር የለቀቀው በሴቶች ላይ ይደረግ የነበረው #ግፍና_መከራ ገፈው ጣሉት።ከአንድ በላይ ሚስትን በተመለከተ እስልምና ቁጥርን ብቻ መገደብ ሳይሆን በሚስቶችም መካከል ፍትሀዊነትም ጭምር ትኩረት ሰጥቶ አስተካክሏል

#በፍትህ_ማስተዳደር_ያልቻለ_አንድ_ትብቃው_እሷንም_ማስተዳደር_ያልቻለ_ማስተዳደር_እስኪችል_ድረስ እንዲፆም_እና_እንዲታገስ በማድረግ ከእንግዲህ ሴት ልጅን እንደፈለጉ ማድረግና መጨቆን እንዳከተመለት ለሴት ልጅ ኢስላም ሙሉ የሆነ ዋስትና እንደሰጣት ታወጀ።አዋጁም ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ተስተጋባ።

    ከዚህም በተጨማሪ ሴት ልጅ ውጭ ወጥታ ከወንድ ጋር እንዳትጋፋ የወንዶች ዘለፋ እንዳያገኛት ሂጃቧን ጠብቃ ቤቷ እንፍትሆን በማድረግ እሷን የመንከባከብ ግዴታውን በወንዶች ላይ አደረገ።እየቻለ ቢያስቸግራት ፀቡ ከማንም ጋር ሳይሆን ከአላህ ጋር እንደሆነ ነብዩ ሰአወ አስጠነቀቁ። በኢስላም ውስጥ
#ሴት_ መሆን_መታደል ነው።እንዲሉ በአጠቃላይ እስላም ለሴቶች ምሽግ ነው።ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች ኢስላም ከአንድ በላይ በመፍቀዱ የሴቶችን መብት ይጋፋል። የሚል የእብድ ወሬ ሲያናፍሱ ይደመጣሉ።ኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ማስገደድ ሳይሆን በአለፉ እምነቶችና ባህሎች ፈር ለቆ የነበረውን ከአንድ በላይ ሴቶችን ማግበስበስ በገደብ እና በፍትህ እንዲሆን ህግ ማሰረቀመጥ እንደሆነ በዝርዝር አሳልፈናል..

እስከ አራት የተፈቀደ ለመሆኑ ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

    ☞ይህ የቁርአን አንቀፅ፣ በኢስላም ውስጥ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድ መሆኑን ግልፅ ማስረጃ ነው።ነገር ግን በሴቶች መካከል በፍትህ ማስተዳደርን ቅድመ መስፈርት አድርጎ ደንግጓል።
#ፍትህ ዋና ቅድመ መስፈርት ለመሆኑ የቁርአን አንቀፁ የወረደበት ሰበብ ማወቅ መልክቱ ግልፅ ያደርገዋል..

    እናታችን አኢሻ ረአ እንዲህ ይላሉ፣ "አንድ ሰው በውስጡ የሚያሳድጋት ብዙ ንብረት ያላት የቲም ሴት ልጅ ነበረችው፣ ንብረቷን ፈልጎ ጥሎሹን በትክክል ሳይሰጣት አገባት።ከዚያ ይቺ የቁርአን አንቀፅ ወረደች.።

   ☞  በሌላ ዘገባ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር ወደ እናታችን አኢሻ ዘንድ መጣና ስለ
"وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ"
ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ ብለውታል፣ "የወንድሜ ልጅ ሆይ;አንድ ወንድ ሃላፊ ሆኖ የሚያሳድጋት የቲም ሴት ልጅ ገንዘቧ እንዲሁም መልኳ አስቀንቶት መህሯን በትክክል ሳይሰጣት እንዳያገባት ማለት ነው፣ ይህ ነው የተከለከለው። እሷን ማግባት የሚፈልግ ከሆነ መህሯን ለሌሎቹ እንደሚሰጠው አድርጎ በፍትህ መህሯን ለሌሎች ሚስቶች የሚገባውን ሰጥቶ ያግባት።ነገር ግን ፍትህ ማጓደልን ከፈራ እሷን ትቶ ሌሎችን የሚያስደስቱትን እስከ አራት ማግባት ይችላል ማለት ነው።" ቡኻሪ ዘግበውታል።.

#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ሼር_ያድርጉ👇👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam