الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.9K subscribers
356 photos
16 videos
7 files
907 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜   #ክፍል_ሰባት_⑦ት       #ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም    ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜

  .
#ክፍል_ስምንት/⑧ት
     
#ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም

#እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡
ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

#ከአንቀፁ_የምንማራቸው_ቁም_ነገሮች

_አንቀፁ አንድ ወንድ ማግባት የሚችለው ከፍተኛው ቁጥር አራት መሆን እንዳለበት ይደነግጋል።ከአራት ሚስት በላይ ከነብዩ ሰአወ  ውጭ ማንኛውም ሰው መጨመር እንደማይፈቀድለት ኢማም አሻፊኢይ ኢጅማእ (የሙስሊም ሊቃውንት የጋራ አቋም)) አለው ይላሉ።ነብዩ ሰአወ ለምን ከአራት በላይ እንደተፈቀደላቸው እና ከአንድ በላይ የማግባታቸው ጥበብ ሌላው ተራው ሰው ከአንድ በላይ ከሚያገባበት ምክንያት የተለየ
ነው።ይህን በተመለከተ እራሱን የቻለ ምዕራፍ ስላለው ከማውጫው ላይ በመፈለግ በዝርዝር ማንበብ ጠቃሚ ነው

_አንቀፁ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የፈለገ ሰው
#ፍትሃዊነት ቅድመ መስፈርት መሆን እንዳለበት ያስተምራል።በፍትህ ማስተዳደር የማይችል ወይም ፍትሃዊነት ሊጎለኝ ይችላል
ብሎ የሚያስብ ወንድ ከሆነ ከአንድ በላይ ማግባት እንደማይፈቀድለት አንቀፁ ከሚሰጠን ግንዛቤ የተወሰኑት ናቸው።

    ☞ ፍትሃዊነት ሲባል አንድ ሰው ማድረግ በሚችለው
#እንደቀለብ_ልብስ_መኖሪያቤት_እና_አብሮማደርን የሚያካትት ነው።ነገር ግን ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ በማይችለው እና ከአቅሙ በላይ በሆነው እንደ #ፍቅር_መስጠት ያሉ ነገሮች ሁሉንም ሚስቶቹን እኩል ላድርግ ቢል ማድረግ አይችልም።ምክንያቱም አላህ በልቡ ላይ #ትወደድ_ያላት_ሴት_እሱ_ዘንድ_የበለጠ_ትወደዳለች።ለዚህ ሲባል አላህ እንዲህ ይላል፣

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ
ነው፡፡[ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129 ]

☞ ከቁርአን አንቀፁ የምንማረው ቁምነገር፣ አንድ ሰው በሚስቶቹ መካከል በልብ ላይ ባለው ነገር(ፍቅር) ማስተካከል የማይችል መሆኑን
ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ የሚችለውን ማስተካከል ጠብቆ መያዝ እንዳለበት ካለፈው የቁርአን አንቀፅ ለማየት ሞክረናል። እንደውም በሚስቶች መካከል ፍትሃዊ መሆን የመጀመሪያ መስፈርት ከሚባሉት ውስጥ ነው

#ማሳሰቢያ፣ አንዳንድ አዕምሯቸው እንዳያገናዝብ የተዘጋባቸው ሰዎች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም ብለው የሚከራከሩ በኢስላምም ውስጥ ብቅ ብለዋል።ማስረጃ ብለው ያቀረቡት ከላይ ያሳለፍነውን የቁርአን አንቀፅ ነበር።እንደነሱ አባባል የቁርአኑ አንቀፅ "በሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ ለማስተካከል አትችሉም" ብለው በመተርጎም * በሴቶች መካከል ማስተካከል ደግሞ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም* የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ። #ትርጉሙን_ለስሜታቸው_እንዲመቻቸው_አድርገው_በመተርጎም_እነሱ_ይህን_ይበሉ_እንጂ_ትክክለኛ_የአንቀፆቹ_መልእክት_እንዳሳለፍነው_ነው

    📚 የመጀመሪያው የቁርአን አንቀፅ የሚለው በየቲሞች መካከል ፍትህን እናጓድላለን ብላችሁ ከፈራችሁ ሌሎች ሴቶችን እስከ አራት ማግባት ትችላላችሁ የሚል ሲሆን የሁለተኛው የቁርአን አንቀፅ የሚያስረዳው ደግሞ በሴቶች መካከል ፍቅርን እኩል ማካፈል አትችሉም።ነገር ግን በምትችሉት ነገር ሴቶቻችሁን ችላ ብላችሁ እንዳትተዋቸው የሚል መልክ አዝሏል።
#ትክክለኛውም_የቁርአኑ_መልእክት_ይህ_ነው
  ☞ በሚችለው ነገር በሚስቶቹ መካከል ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ አላህ ዘንድ ትልቅ ቅጣት እንደሚጠብቀው ነብዩ ሰአወ ተናግረዋል።

    ☞አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰአወ እንዲህ አሉ፣ "ሁለት ሚስቶች እሱ ዘንድ ያሉት እና በመካከላቸው ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የተዘነበለ ሆኖ ይመጣል"  (ቲርሚዝይ ዘግበውታል

      ❗️ሙስሊም ሲባል ከዚህም ባለፈ በሁሉም ነገር ላይ በሚችለው አቅሙ በፈቀደው ፍትሃዊ መሆን መለያ ባህሪይው ሲሆን በተለይ ደግሞ በውስጡ ባሉት የኑሮ አጋር ከሆኑት ሚስቶቹ ጋር ሲሆን በእጅጉ ትኩረት የሚሰጠው
ነው.።

  
#ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam