الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::ትዳር በኢስላም::::::☜ ክፍል #አስራ_አራት/⑭ት ከላይ ከቁርዓን አንቀፁ እና ከሀዲሱ እንደምንረዳው ማንኛውም ሰው በሰዎች ዘንድ በጣም የተመሰገነ እና የተከበረ ጨዋ ቢሆን የፈለገውን ያክል ሀብት ቢኖረው ወይም እጅግ ደግ ሰው ሆኖ ብዙ ሴቶች እሱን ለማግባት ቢፈልጉ የመጨረሻው ጣራ አራት ነው። ከአራት በላይ አምስተኛ ቢጨምር እንደ ሴት ሁለት ወንድ እንደማግባት ማለት ነው። አምስተኛዋን ሴት…
☞:::ትዳር በኢስላም::::::☜

     ክፍል~አስራአምስት/⑮
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶቹ

5.3
#በሚስቶች_መካከል_ፍትሃዊ_መሆን

   አላህ ሱወ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)
    በዚህ በተከበረው የአላህ ሱወ ቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ማስተካከል የሚለው ፅንሰ ሀሳብ የሰው ልጅ የሚችለው የሆነው እንደ ምግብና መጠጥ፣አልባሳት፣ መኖሪያቤት፣ ሚስቶች ጋር ማደር፣በመልካም መኗኗርና በመሳሰሉት ለሚስቶች ፍትሀዊ
መሆን ማለት ነው። ነገር ግን ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ የሆነው እና አላህ ብቻ የሚቆጣጠረውን እንደ ፍቅርና የልብ ወደአንዷ መዘንበል የመሳሰሉትን ሰው ፈልጎት የሚያደርገው ነገር ስላልሆነና ለሁሉም ሚስቶቹ እኩል ማከፋፈል ስለማይችል ካላስተካከልክ ተብሎ በዚህ አይወቀስም።አላህም ከሚችለው በላይ አያስገድደውም። አላህ ሱወ እንዲህ ይላል፣

لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ

አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡
(አል-በቀራህ - 286)

    ባል ሚስቶቹን በፍቅር ማስተካከል እንደማይችል አላህ በሌላ የቁርአን አንቀፅ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

በሴቶችም
መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡  [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129 ]

  ከቁርአን አንቀፁ እንደምንረዳው አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት ሁለቱን እኩል በፍቅር ማስተካከል እንደማይችል ነው።ነገር ግን ሁሉ ነገሩን ከሚወዳት ሚስቱ ጋር አድርጎ ሌላኛዋን ሚስቱን እንደትርፍ እቃ በመቁጠር ዝምብሎ እንዳይተዋት ሲል አላህ ያስጠነቅቃል።

   ☞ አንዳንድ ሰዎች ከላይ ያየነውን የቁርአን አንቀፅ በቅጡ ሳይረዱ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደማይፈቀድ አድርገው ለማቅረብ ሲጣጣሩ ይስተዋላሉ።ይህ አይነቱ ማምታቻ በሚቀጥለው ምዕራፍ በስፋት የሚዳስስ ቢሆንም ለመግቢያ ያህል ትንሽ ማለቱ አይከፋም።የሚያቀርቡትም ምክንያት "
በሚስቶች መካከል ማስተካከል ሸሪአው ቅድመ መስፈርት አድርጎ አስቀምጦታል፣በዚህ የቁርአን አንቀፅ ደግሞ አንድ ወንድ በሚስቶች መካከል ማስተካከል አትችሉም ስለተባለ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም" የሚል የማሀይም አረዳድ የተረዱ አሉ።እነዚህ ሰዎች የቁርአን የአቀራረብ ሲስተሙን ያልተረዱ ሰዎች ናቸው።ሌሎችንም የዲን ጉዳዮዎች ላይ ቁርአንን በዚህ መልኩ የሚረዱ ከሆነ አደጋ ውስጥ ናቸው። የቁርአኑ ትርጉም እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ማስተካከል አትችሉም የተባለው በፍቅር እና በልባዊ ዝንባሌ እንጂ የሰው ልጅ ማስተካከል በሚችለው  ውጫዊ ተግባርንም ጭምር ማለት አይደለም። ቁርአን አንድ ቦታ ፈቅዶ ሌላ ቦታ የሚከለክል እንዲሁም እርስ በርሱ የሚጋጭ ሳይሆን አንዱ ሌላውን የሚደግፍ እና የሚያብራራ ነው።የእነዚህም የሁለት የቁርአን አንቀፆች ቁርኝት አንዱን ሌላው የሚያብራራ ሆነው እነገኛቸዋለን።

   የሁለቱ የቁርአን አንቀፆች አጠር ያለው መልክ በአንድ ላይ ሲቀመጥ የሚከተለውን ይመስላል፣

  " ከሴቶች ለእናንተ  ተዋቡላችሁን እስከ አራት ማግባት ትችላላችሁ ፣ የሰው ልጅ በሚችለው ነገር ላይ ማስተካከል የምትፈሩ ከሆነ አንድ ብቻ አግቡ።የሰው ልጆች በማይቆጣጠሩት እንደፍቅር እና የልብ ፍላጎት ማስተካከል አትችሉም።ይህ በአላህ እጅ ያለ ነገር ነው፣ ያም ቢሆን በቻላችሁት ሁሉ
ፍትሃዊ ሁኑ።ሴቶችን አንጠልጥላችሁ አተዋቸው።የሚል መልእክትን ይሰጣል።

………ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆነው የነብዩ ሰአወ ሀዲስ ነው፣ ከሰዎች ልጆች ሁሉ
ፍትሃዊ በሚስቶቻቸው መካከል ከሌሎች ወንዶች የበለጠ የሚያስተካክሉት እንዲህ ብለዋል፣

(اللهم هذا قسمي فيما أملك فلا تلمني فيما تملك ولا أملك)

"አላህ ሆይ ይህ እኔ የምችለው (በሚስቶቼ
መካከል) ማከፋፈል ነው፣አንተ በምትቆጣጠረው (ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነው) ነገር አትውቀሰኝ።" ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር።

   ☞√ በልብ ውስጥ ያለው ፍቅር እኩል ማዳረስ ስለማይቻልና ይህም የሰው ልጆች ስልጣን ስላልሆነ የአላህ መልእክተኛ ሰአወ እንኳን በማይችሉት ነገር አላህ እንዳይወቅሳቸው ዱአ አድርገዋል።

    ☞በሁለት ሚስቶች
መካከል ፍትሀዊ መሆንን ነብዩ ሰአወ ትኩረት ሰጥተው  አበክረው ተናግረዋል።ፍትሃዊ ያልሆነ  ወንድ የሚጠብቀውንም ቅጣት እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣

(إذا كان عند الرجل إمرأتآن فلم يعدل بينهما جاء يوم القيامة وشقه ساقط )
  አንድ ወንድ ሁለት  ሚስቶች እያሉት በመካከላቸው ሳያስተካክል የሞተ ከሆነ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የሰለለ(ሽባ)ሆኖ ይቀርባል። (ሀዲሱን ነሳኢና ቲርሚዝይ ዘግበዉታል።
ይቀጥላልኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam