☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜
#ክፍል_አስራ_ስምንት_/⑱_ት
#ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች
1/ #ማምታቻ_አጭር_መልስ
"አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ በሚስቶቻችሁ መካከል ማስተካከል አትችሉም ብሏል የሚል ነው።" የቁርአኑን ፅንሰ ሀሳብ እንመልከት
وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129)
ይህን የቁርአን አንቀፅ በመጥቀስ እንዲህ ይላሉ፣ "ወንዶች በሴቶቻቸው መካከል ማስተካከል እንደማይችሉ ተነግሯል፣ ማስተካከክ አለመቻል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደማይቻል ያመለክታል።ምክንያቱም በሚስቶች መካከል ማስተካከል አንዱ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ"
#አጭር_ምላሽ፣ አላህ በዚህ በተከበረው አንቀፁ የጠቆመው በሴቶች መካከል በውስጣዊ ፍላጎት (እንደፍቅርና የልብ ዝንባሌ) እኩል ማድረግ ወንዶች ለማስተካከል ቢጓጉም እንኳ እንደማይቻል ነው።ምክንያቱም የሰው ልጅ ቀልብ የሚቆጣጠረው አላህ እራሱ ብቻ ስለሆነ ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ ነው።ቢሆን እንኳ የሰው ልጅ በሚችለው እና በሚቆጣጠረው ነገር ሚስቶችን ማስተካከል በእርሱ ላይ ግዴታ መሆኑ ነው።በፍቅር እና ዝንባሌም ቢሆን ለማስተካከል ያቅማችሁን መሞከራችሁ የሚያስመሰግን እና ለእናንተ የተሻለ ነው ፣ በፍቅር በልባዊ ዝንባሌ እንዲሁም በግንኙነት ሴቶቻችሁን እኩል አለማድረጋችሁ ከአንድ በላይ ከማግባት አይከለክላችሁም ከዚህ ያለፈውን አላህ መሀሪ እና አዛኝ ጌታ ነው የሚል ነው የአንቀፁ ትንታኔ የያዘው።ታዲያ ከየት መጥቶ ነው የቁርአኑ አንቀፅ ከአንድ በላይ አታግቡ ብሎ የሚከለክለው???የዚህ የቁርአን አንቀፅ ትርጓሜ አብደላህ ኢብኑ አባስ ረአ ሲተነትኑት ማስተካከል አሉም የተባሉ ነገሮች #እንደፍቅር እና #ግንኙነት ማለት ነው ይላሉ።
☞ የቁርአን ባህሪው አንዱን አንዱ የሚያብራራ እንጅ አንዱ ከሌላው የተቃረነ ሆኖ አልወረደም።አላህ ሱወ በሌላ የቁርአን አንቀፅ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ መሆኑ ሲገልፅ እንዲህ
فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)
በዚህ የቁርአን አንቀፅ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ ሲሆን በቁሳዊ አካል ማለትም ባል ማስተካከል የሚይችለው ነገር እንደ ቀለብ ልብስ ሚስቶች ጋር ማደር ማስተካከል የማይችል ሰው ከሆነ አይደለም 2 እና ከዚያ በላይ #አንድም ማግባት አይችልም።ስለዚህ ማስተካከል በተመለከተ እኛን የሚያስጠይቀን እና የምንችለው በሆነው ማስተካከል የማይሳካልን ከሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእኛ ላይ እርም ተደርጓል።ነገር ግን አላህ የሚቆጣጠረውና እኛ የማንችለው ማስተካከል ከሆነ እኛ እናስተካክላለን ብለን ብንቀና እንኳ ማስተካከል እንደማንችል አላህ ነግሮናል።ይህ ከመሆኑም ጋር በቻልነው መጠን እንድንጠናከር አስገንዝቦናል።ከአቅማችን በላይ ለሆነው አላህ መሀሪ አዛኝ ነው።ነብዩም ሰአወ በሚስቶቻቸው መካከል ማስተካከል በተመለከተ ከሚችሉት በላይ የሆነው ባለቤቱ አላህ እንደሆነ እና በማይችሉት ነገር እንደ ፍቅር ባሉት አላህ ይቅር እንዲላቸው እንዲህ ይላሉ
(اللهم هذا قسمي فيما أملك فلا تلمني فيما تملك ولا أملك)
"አላህ ሆይ ይህ እኔ የምችለው (በሚስቶቼ መካከል) ማከፋፈል ነው፣አንተ በምትቆጣጠረው (ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነው) ነገር አትውቀሰኝ።" ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር።
2/ #ማምታቻ_እና_አጭር_መልስ
አንዳንድ ከአንድ በላይ ሚስት አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቡት የአልይ ኢብኑ አቡ ጧሊብን ቂሷ ነው፣በዚህ ቂሷ ውስጥ የነብዩ ሰአወ ሀዲስ አለ።ይህ ሀዲስ እንደመረጃ ያገለግለናል በሚል ሙሉ ሳይሆን ለእነሱ የሚመቻቸውን ወይም ከሀሳባቸው ጋር አብሮ የሚሄደውን ቆርጠው ያቀርባሉ።ይህ ተግባር በእጅጉ የሚወገዝ ነው።ነብዩ ሰአወ ላይ እንደመዋሸት የሚቆጠር ነው።እነሱ መረጃ ብለው ያቀረቡት፣"አሊይ ረአ የነብዩን ሰአወ ልጅ ፋጡማ እቤታቸው እያሉ የአቡ ጀህልን ልጅ ለማግባት ነብዩን ሰአወ ፈቃድ ሲጠይቋቸው አልፈቀዱላቸውም እንዲህም አሏቸው "ፈቃድ አልሰጥህም በድጋሜም ፈቃድ አልሰጥህም የእኔን ልጅ ፍታ እና የአቡ ጀህልን ልጅ አግባ፣ ልጄን የሚያስጨንቃት ጉዳይ እኔንም ያስጨንቀኛል።ልጄ የእኔ አካል ናት እና" ብለው መለሱላቸው።ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይፈቀድም ብለው ይህን እንደማስረጃ ያቀርባሉ። ኢንሻአላህ ይቀጥላል።✍
✅ቴሌግራማችን
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-