الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
386 photos
18 videos
8 files
919 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::::☜      ክፍል~አስራአምስት/⑮ #ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶቹ 5.3 #በሚስቶች_መካከል_ፍትሃዊ_መሆን    አላህ ሱወ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ…
 
☞::::ትዳር በኢስላም:::::☜

#ክፍል_አስራ_ስድስት/⑯

አንድ ወንድ ሚስቶቹን በሚችለው አቅም በመካከላቸው በፍትህ የማያስተዳደር ከሆነ ተበደልኩ የምትለው ሚስት ለቃዲ ስሞታ ማቅረብ ትችላለች።ቃዲውም  በፍትህ እንዲያዝ ወይም እንዲፈታት ያዘዋል ለዚህም የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ማስረጃ ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፣

وَإِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ سَرِّحُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ ۚ وَلَا تُمْسِكُوهُنَّ ضِرَارًا لِّتَعْتَدُوا ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ ۚ وَلَا تَتَّخِذُوا آيَاتِ اللَّهِ هُزُوًا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمَا أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنَ الْكِتَابِ وَالْحِكْمَةِ يَعِظُكُم بِهِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ሴቶችን በፈታችሁና (የዒዳ) ጊዜያቸውን በደረሱ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፤ (ተማለሷቸው) ወይም በመልካም ኹኔታ አሰናብቱዋቸው፡፡ ለመጉዳትም ወሰን ታልፋባቸው ዘንድ አትያዙዋቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ነፍሱን በእርግጥ በደለ፡፡ የአላህንም አንቀጾች ማላገጫ አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን ከመጽሐፍና ከጥበብም በርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በናንተ ላይ ያወረደውን አስታውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን ዕወቁ፡፡አል-በቀራህ - 231)
ከሚስቶቹ ጋር አዳርን በተመለከተ እንደሚስቶቹ  ብዛት አንዳንድ ቀን፣ሁለት ሁለት ወይም ሶስት ሶስት ቀን ሊያከፋፍላቸው ይችላል። የሚጠበቅበት ከሚስቶቹ ጋር ማደር እንጂ በእያንዳንዱ አዳር ከሚስቶቹ ጋር
ግንኙነት የማድረግ ግዴታ የለበትም።

    ኢብኑ ቀይም(አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፣ "ባል በእያንዳንዱ ሚስቶች ዘንድ ባደረ ቁጥር
#ግንኙነት_ማድረግም ሆነ በእኩል ቁጥር #ጅማዕ ማድረግ አይጠበቅበትም። ለግንኙነት ፍላጎት መኖር የሰውየው ምርጫ ሳይሆን የቀልብ ስራ ነው። ልቡ የፈለጋትን ሚስቱን ሁለት  ሶስት ጊዜ ግንኙነት ሊያደርግ ይችላል።በአንፃሩ ሌላኛዋ ሚስቱ ዘንድ ሲያድር ግንኙነት ላይፈልግ ይችላል።ይህን ቢፈፅም በሚስቶች መካከል ፍትህ እንዳጓደለ ተደርጎ አይታይም።በሌላ አነጋገር ሚስቶቹን #በጅማዕ እኩል ማድረግ በእርሱ ላይ ግዴታ አይደለም። ነገር ግን በተቻለ መጠን በጅማዕ ሚስቶቹን እኩል ቢያደርግ ይወደድለታል" (ዛዱል መዓድ ቅፅ 1 ገፅ 151)

    ባል ከሚስቶቹ አንዷን ወይም ከአንድ በላይ ሚስቱን አብራው እንድትጓዝ ቢፈልግ ሚስቶቹን ሰብስቦ እጣ ማጣጣል ይጠበቅበታል። ሚስቶቹን ሰብስቦ አንዷ ከእርሱ ጋር እንድትሄድ ቢፈቅዱላት የግድ እጣ ማውጣት አይጠበቅበትም። ይህ የአብዛኛው የኢስላም ሊቃውንት አቋም ነው። ባል ከሄደበት ጉዞ ሲመለስ እንደ አዲስ በሚስቶቹ መካከል አብራው የሄደችውን ጨምሮ ቀኖቹን ማከፋፈል ይኖርበታል።ከእርሱ ጋር ያልሄዱት ሴቶች የብቻቸው ማካካሻ መጠየቅ አይችሉም። ነብዩ ሰአወ ከሚስቶቻቸው መካከል እጣ የወጣላቸው ሚስቶቻቸውን ይዘው ይጓዛሉ፣ሰገር ደርሰው ሲመለሱ ላልሄዱ ሴቶች የተለየ ማካካሻ ቀን ሰጥተው አያውቁም። ከመንገድ ሲመለሱ አብረው የተጓዙትን ሚስቶቻቸውንም ጨምረው እንደ አዲስ ተራ ያቋጥሯቸው ነበር።
   የሚከተለውን ሀዲስ እንመልከት፣

  "ነብዩ ሰአወ መንገድ መውጣት ባሰቡ ሰአት በሚስቶቻቸው መካከል እጣ ያጣጥላሉ ፣እጣዋ የወጣላትን   ዘው ይወጣሉ።"

     ☞ አንድ ወደ ጉዞ ሊወጣ ያሰበ ባል ሚስቶቹን እጣ አጣጥሎ እጣ የወጣላት ሚስቱ እጣዋን ለምትፈልገው የባሏ ሌላኛዋ ሚስት በስጦታ መልክ ማበርከት ትችላለች።

    ☞ በሚስቶች መካከል ፍትሀዊ መሆን ማለት ሁሉንም ሚስቶች እንደጓደኞቻቸው እና እንፈ አምሳያቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት ማለት እን ጂ የግድ በሁሉም ነገር አንድ አይነት ይሆናሉ ማለት እንዳልሆነ የኢስላም ሊቃውንት ይናገራሉ።

   አንድ አይነት ከመሆን የሚከለክላቸው ውስጥ የሚኖሩበት አካባቢ፣ የተወለዱበት ቤተሰብ፣ የእድሜ ክልል፣በውስጣቸው የያዙት የቤተሰብ ብዛት እና የመሳሰሉ መለያየት አንድ አይነት ከመሆን ይከለክላቸዋል።

#ሚስቶችን_በድርሻቸው_ማስተካከል
⇧⇡⇡⇡⇡⇡በቀጣይ ርዕሳችን
ይቀጥላል ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ስምንት_/⑱_ት

#ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች

    1/
#ማምታቻ_አጭር_መልስ
   "አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ በሚስቶቻችሁ መካከል ማስተካከል አትችሉም ብሏል የሚል ነው።"  የቁርአኑን ፅንሰ ሀሳብ እንመልከት

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129)

   ይህን የቁርአን አንቀፅ በመጥቀስ እንዲህ ይላሉ፣ "ወንዶች በሴቶቻቸው መካከል ማስተካከል እንደማይችሉ ተነግሯል፣ ማስተካከክ አለመቻል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደማይቻል ያመለክታል።ምክንያቱም በሚስቶች መካከል ማስተካከል አንዱ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ"

#አጭር_ምላሽ፣ አላህ በዚህ በተከበረው አንቀፁ የጠቆመው በሴቶች መካከል በውስጣዊ ፍላጎት (እንደፍቅርና የልብ ዝንባሌ) እኩል ማድረግ ወንዶች ለማስተካከል ቢጓጉም እንኳ እንደማይቻል ነው።ምክንያቱም የሰው ልጅ ቀልብ የሚቆጣጠረው አላህ እራሱ ብቻ ስለሆነ ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ ነው።ቢሆን እንኳ የሰው ልጅ በሚችለው እና በሚቆጣጠረው ነገር ሚስቶችን ማስተካከል በእርሱ ላይ ግዴታ መሆኑ ነው።በፍቅር እና ዝንባሌም ቢሆን ለማስተካከል ያቅማችሁን መሞከራችሁ የሚያስመሰግን እና ለእናንተ የተሻለ ነው ፣ በፍቅር በልባዊ ዝንባሌ እንዲሁም በግንኙነት ሴቶቻችሁን እኩል አለማድረጋችሁ ከአንድ በላይ ከማግባት አይከለክላችሁም ከዚህ ያለፈውን አላህ መሀሪ እና አዛኝ ጌታ ነው የሚል ነው የአንቀፁ ትንታኔ የያዘው።ታዲያ ከየት መጥቶ ነው የቁርአኑ አንቀፅ ከአንድ በላይ አታግቡ ብሎ የሚከለክለው???የዚህ የቁርአን አንቀፅ ትርጓሜ አብደላህ ኢብኑ አባስ ረአ ሲተነትኑት  ማስተካከል አሉም የተባሉ ነገሮች #እንደፍቅር እና #ግንኙነት ማለት ነው ይላሉ።

    ☞ የቁርአን ባህሪው አንዱን አንዱ የሚያብራራ እንጅ አንዱ ከሌላው የተቃረነ ሆኖ አልወረደም።አላህ ሱወ በሌላ የቁርአን አንቀፅ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ መሆኑ ሲገልፅ እንዲህ

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

   በዚህ የቁርአን አንቀፅ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተፈቀደ ሲሆን በቁሳዊ አካል ማለትም ባል ማስተካከል የሚይችለው ነገር እንደ ቀለብ ልብስ ሚስቶች ጋር ማደር ማስተካከል የማይችል ሰው ከሆነ አይደለም 2 እና ከዚያ በላይ
#አንድም ማግባት አይችልም።ስለዚህ ማስተካከል በተመለከተ እኛን የሚያስጠይቀን እና የምንችለው በሆነው ማስተካከል የማይሳካልን ከሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእኛ ላይ እርም ተደርጓል።ነገር ግን አላህ የሚቆጣጠረውና እኛ የማንችለው ማስተካከል ከሆነ እኛ እናስተካክላለን ብለን ብንቀና እንኳ ማስተካከል እንደማንችል አላህ ነግሮናል።ይህ ከመሆኑም ጋር በቻልነው መጠን እንድንጠናከር አስገንዝቦናል።ከአቅማችን በላይ ለሆነው አላህ መሀሪ አዛኝ ነው።ነብዩም ሰአወ በሚስቶቻቸው መካከል ማስተካከል በተመለከተ ከሚችሉት በላይ የሆነው ባለቤቱ አላህ እንደሆነ እና በማይችሉት ነገር እንደ ፍቅር ባሉት አላህ ይቅር እንዲላቸው እንዲህ ይላሉ

(اللهم هذا قسمي فيما أملك فلا تلمني فيما تملك ولا أملك)

"አላህ ሆይ ይህ እኔ የምችለው (በሚስቶቼ መካከል) ማከፋፈል ነው፣አንተ በምትቆጣጠረው (ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነው) ነገር አትውቀሰኝ።" ብለው ዱአ ያደርጉ ነበር።

2/
#ማምታቻ_እና_አጭር_መልስ

   አንዳንድ ከአንድ በላይ ሚስት አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች የሚያቀርቡት የአልይ ኢብኑ አቡ ጧሊብን ቂሷ ነው፣በዚህ ቂሷ ውስጥ የነብዩ ሰአወ ሀዲስ አለ።ይህ ሀዲስ እንደመረጃ ያገለግለናል በሚል ሙሉ ሳይሆን ለእነሱ የሚመቻቸውን ወይም ከሀሳባቸው ጋር አብሮ የሚሄደውን ቆርጠው ያቀርባሉ።ይህ ተግባር በእጅጉ የሚወገዝ ነው።ነብዩ ሰአወ ላይ እንደመዋሸት የሚቆጠር ነው።እነሱ መረጃ ብለው ያቀረቡት፣"አሊይ ረአ የነብዩን ሰአወ ልጅ ፋጡማ እቤታቸው እያሉ የአቡ ጀህልን ልጅ ለማግባት ነብዩን ሰአወ ፈቃድ ሲጠይቋቸው አልፈቀዱላቸውም እንዲህም አሏቸው "ፈቃድ አልሰጥህም በድጋሜም ፈቃድ አልሰጥህም የእኔን ልጅ ፍታ እና የአቡ ጀህልን ልጅ አግባ፣ ልጄን የሚያስጨንቃት ጉዳይ እኔንም ያስጨንቀኛል።ልጄ የእኔ አካል ናት እና" ብለው መለሱላቸው።ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይፈቀድም ብለው ይህን እንደማስረጃ ያቀርባሉ። ኢንሻአላህ ይቀጥላል።
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam