الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::::☜      ክፍል~አስራአምስት/⑮ #ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶቹ 5.3 #በሚስቶች_መካከል_ፍትሃዊ_መሆን    አላህ ሱወ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏል፣ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ…
 
☞::::ትዳር በኢስላም:::::☜

#ክፍል_አስራ_ስድስት/⑯

አንድ ወንድ ሚስቶቹን በሚችለው አቅም በመካከላቸው በፍትህ የማያስተዳደር ከሆነ ተበደልኩ የምትለው ሚስት ለቃዲ ስሞታ ማቅረብ ትችላለች።ቃዲውም  በፍትህ እንዲያዝ ወይም እንዲፈታት ያዘዋል ለዚህም የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ማስረጃ ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፣

وَإِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ سَرِّحُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ ۚ وَلَا تُمْسِكُوهُنَّ ضِرَارًا لِّتَعْتَدُوا ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُ ۚ وَلَا تَتَّخِذُوا آيَاتِ اللَّهِ هُزُوًا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمَا أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنَ الْكِتَابِ وَالْحِكْمَةِ يَعِظُكُم بِهِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ሴቶችን በፈታችሁና (የዒዳ) ጊዜያቸውን በደረሱ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፤ (ተማለሷቸው) ወይም በመልካም ኹኔታ አሰናብቱዋቸው፡፡ ለመጉዳትም ወሰን ታልፋባቸው ዘንድ አትያዙዋቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ነፍሱን በእርግጥ በደለ፡፡ የአላህንም አንቀጾች ማላገጫ አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን ከመጽሐፍና ከጥበብም በርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በናንተ ላይ ያወረደውን አስታውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ መኾኑን ዕወቁ፡፡አል-በቀራህ - 231)
ከሚስቶቹ ጋር አዳርን በተመለከተ እንደሚስቶቹ  ብዛት አንዳንድ ቀን፣ሁለት ሁለት ወይም ሶስት ሶስት ቀን ሊያከፋፍላቸው ይችላል። የሚጠበቅበት ከሚስቶቹ ጋር ማደር እንጂ በእያንዳንዱ አዳር ከሚስቶቹ ጋር ግንኙነት የማድረግ ግዴታ የለበትም።

    ኢብኑ ቀይም(አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፣ "ባል በእያንዳንዱ ሚስቶች ዘንድ ባደረ ቁጥር
#ግንኙነት_ማድረግም ሆነ በእኩል ቁጥር #ጅማዕ ማድረግ አይጠበቅበትም። ለግንኙነት ፍላጎት መኖር የሰውየው ምርጫ ሳይሆን የቀልብ ስራ ነው። ልቡ የፈለጋትን ሚስቱን ሁለት  ሶስት ጊዜ ግንኙነት ሊያደርግ ይችላል።በአንፃሩ ሌላኛዋ ሚስቱ ዘንድ ሲያድር ግንኙነት ላይፈልግ ይችላል።ይህን ቢፈፅም በሚስቶች መካከል ፍትህ እንዳጓደለ ተደርጎ አይታይም።በሌላ አነጋገር ሚስቶቹን #በጅማዕ እኩል ማድረግ በእርሱ ላይ ግዴታ አይደለም። ነገር ግን በተቻለ መጠን በጅማዕ ሚስቶቹን እኩል ቢያደርግ ይወደድለታል" (ዛዱል መዓድ ቅፅ 1 ገፅ 151)

    ባል ከሚስቶቹ አንዷን ወይም ከአንድ በላይ ሚስቱን አብራው እንድትጓዝ ቢፈልግ ሚስቶቹን ሰብስቦ እጣ ማጣጣል ይጠበቅበታል። ሚስቶቹን ሰብስቦ አንዷ ከእርሱ ጋር እንድትሄድ ቢፈቅዱላት የግድ እጣ ማውጣት አይጠበቅበትም። ይህ የአብዛኛው የኢስላም ሊቃውንት አቋም ነው። ባል ከሄደበት ጉዞ ሲመለስ እንደ አዲስ በሚስቶቹ መካከል አብራው የሄደችውን ጨምሮ ቀኖቹን ማከፋፈል ይኖርበታል።ከእርሱ ጋር ያልሄዱት ሴቶች የብቻቸው ማካካሻ መጠየቅ አይችሉም። ነብዩ ሰአወ ከሚስቶቻቸው መካከል እጣ የወጣላቸው ሚስቶቻቸውን ይዘው ይጓዛሉ፣ሰገር ደርሰው ሲመለሱ ላልሄዱ ሴቶች የተለየ ማካካሻ ቀን ሰጥተው አያውቁም። ከመንገድ ሲመለሱ አብረው የተጓዙትን ሚስቶቻቸውንም ጨምረው እንደ አዲስ ተራ ያቋጥሯቸው ነበር።
   የሚከተለውን ሀዲስ እንመልከት፣

  "ነብዩ ሰአወ መንገድ መውጣት ባሰቡ ሰአት በሚስቶቻቸው መካከል እጣ ያጣጥላሉ ፣እጣዋ የወጣላትን   ዘው ይወጣሉ።"

     ☞ አንድ ወደ ጉዞ ሊወጣ ያሰበ ባል ሚስቶቹን እጣ አጣጥሎ እጣ የወጣላት ሚስቱ እጣዋን ለምትፈልገው የባሏ ሌላኛዋ ሚስት በስጦታ መልክ ማበርከት ትችላለች።

    ☞ በሚስቶች መካከል ፍትሀዊ መሆን ማለት ሁሉንም ሚስቶች እንደጓደኞቻቸው እና እንፈ አምሳያቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት ማለት እን ጂ የግድ በሁሉም ነገር አንድ አይነት ይሆናሉ ማለት እንዳልሆነ የኢስላም ሊቃውንት ይናገራሉ።

   አንድ አይነት ከመሆን የሚከለክላቸው ውስጥ የሚኖሩበት አካባቢ፣ የተወለዱበት ቤተሰብ፣ የእድሜ ክልል፣በውስጣቸው የያዙት የቤተሰብ ብዛት እና የመሳሰሉ መለያየት አንድ አይነት ከመሆን ይከለክላቸዋል።

#ሚስቶችን_በድርሻቸው_ማስተካከል
⇧⇡⇡⇡⇡⇡በቀጣይ ርዕሳችን
ይቀጥላል ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
  ☞::::ትዳር በኢስላም:::::☜ #ክፍል_አስራ_ስድስት/⑯ አንድ ወንድ ሚስቶቹን በሚችለው አቅም በመካከላቸው በፍትህ የማያስተዳደር ከሆነ ተበደልኩ የምትለው ሚስት ለቃዲ ስሞታ ማቅረብ ትችላለች።ቃዲውም  በፍትህ እንዲያዝ ወይም እንዲፈታት ያዘዋል ለዚህም የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ማስረጃ ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፣ وَإِذَا طَلَّقْتُمُ النِّسَاءَ فَبَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ…
☞::::ትዳር→በኢስላም:::::☜

    
#ክፍል_አስራ_ሰባት/⑰

#ሚስቶችን_በድርሻቸው_ማስተካከል

   ባል በሚስቶቹ መካከል ድርሻቸውን
ማስተካከል ሸሪአዊ ግዴታ ለመሆኑ ሁሉም የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ነው፣

وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ

በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡(አል ኒሳእ 19)
   በዚህ  የቁርአን ምዕራፍ እንደተጠቀሰው ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲኖሩ በመልካም እንድኗኗሯቸው አላህ ግዴታ አድርጓል።ስለሆነም አንድ ወንድ ከሁለት ሚስቶቹ ወደ አንዷ የሚያዘነብል ከሆነ በመልካም ተኗኗረ አይባልም። አላህም እንዲህ ይላል፣

فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ
እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡
(አል ኒሳእ 129)

   በሀዲስም በኩል በርካታ ሀዲሶች መጥተዋል።

   ኢማም ኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ በሚባለው ኪታባቸው 7ኛው ጥራዝ ከገፅ 301_305 ድረስ የሚከተለውን አስፍረዋል፣

"ከአንድ በላይ ሚስቶች ያሉት ወንድ ከሚስቶቹ ጋር ማደር ሲጀምር እጣ አጣጥሎ እጣዋ የወጣላት ጋር መጀመር አለበት።በዚህ ጉዳይ ላይ ሚስቶቹን እኩል ማድረግ በእርሱ ላይ ዋጅብ ነው። በመረጣት ሴት ቢጀምር ይቺን ሴት የመጀመሪያ ማድረጉ እሷን እንደማስበለጥ ስለሚቆጠር ይህን ባለማድረጉ ዋጅብን እንደተወ ይቆጠራል።በተመሳሳይ መልኩ ለጉዞ ሚስት ይዞ መጓዝ ካስፈለገው በእጣ  ማድረግ ግድ ይለዋል።ነገር ግን ባል ለሁለተኛ ጊዜ ጉዞ ቢወጣ
የቀሩት  መዳረስ ስላለባቸው የመጀመሪያዋ እጣ የወጣላት ሚስቱ መልሳ እጣ ውስጥ አትካተትም። ባል በአንድ ጊዜ የሁሉንም እጣ በማውጣት የመጀመሪያ ሲጓዝ አብራዉ የምትጓዘው የሁለተኛ ሲጓዝ አብራው የምትጓዘው የሶስተኛና የአራተኛ ብሎ ለአራቱም ሚስቶቹ በአንድ ጊዜ የሁሉንም ማውጣት ይችላል።

  ☞ ባል በእብደት ወይም በሌላ ነገር አቅሉን ስቶ የሚስቶቹን ተራ መቆጣጠር ካልቻለ የቅርብ ዘመዶቹ እየተከታተሉ በየሚስቶቹ ቤት እንዲያድር ያደርጉታል።ባል ከሚስቶቹ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ማድረግ ግዴታ ነው።ነገር ግን ለሁሉም እኩል ማድረግ አለብህ አይባልም ቢያደርግ ግን የተወደደ ነው።

    አንድ ባል ያለችግር ሚስቱን ለረጅም ጊዜ ሊለያት አይገባም።" ንግግራቸው እዚህ ላይ አበቃ።
#ባል_በሚስቶቹ_መካከል_እኩል_ማካፈል_ግዴታ_የሚሆኑበት_እና_ግዴታ_የማይሆኑበት_ነገሮች

     ይህን በተመለከተ ኢማም ኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ በሚባለው ኪታባቸው 7ኛ ጥራዝ ከገፅ 305_306 ድረስ ከኢማም አህመድ ተወርቷል ብለው የሚከተለውን አስፍረዋፅ፣ *ባል ለሚስቶቹ የሚበቃቸውን ያክል እስከሰጠ ድረስ በመካከላቸው በቀለብ፣በልብስ እና በስሜት እኩል እንዲያደርግ ግዴታ የለበትም  
#ባል_ወደ_ሚስቶቹ_ቤት_የሚሄድበትን_ቀን_እኩል_ማካፈል_አለበት

☞ ባል ለሚስቶቹ እኩል ማካፈል ያለበት ሌሊቱን??ወይስ ቀኑንም ጭምር??

   አንድ ወንድ ቀኖቹን ለሚስቶቹ ሲያካፍል መነሻ የሚያደርገው ሌሊቱን ነው።ምክንያቱም ሰው ወደ ቤቱ የሚገባው እና ከስራ የሚያርፈው ሌሊት ስለሆነ ነው።ሰው በተለምዶ ቀን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለኑሮ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሲከስብ ይውል እና ማታ መጥቶ ከባለቤቱ ጋር ያርፋል።ይህንን የሚጠቁመው የቁርአን አንቀፅ የሚከተለው ነው።አላህ እንዲህ ይላል፣

"ሌሊቱንም ማረፊያ አደረገ፣" (አል አንአም 96)
በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ ሱወ እንዲህ ይላል፣ "ሌሊቱንም ልባስ አደረግን"(አል ነበእ 10)

በሌላ የቁርአን አንቀፅ፣እንዲህ ይላል
"ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ አደረግን" (አል ነበእ 11)
በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ ሱወ እንዲህ ይላል

"ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊቱንና ቀኑን ልታርፉበት ከቱርፋቱም ልትፈልጉበት፣አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ።"(አል ቀሰስ 73)

  ነገር ግን የባል ስራው የሌሊት ከሆነ ቀኑ መነሻ በማድረግ ለሚስቶቹ እኩል በማካፈል በየተራቸው ሁሉንም በእኩል ይጎበኛል።

   ……አንድ ባል ለሚስቶቹ ቀኖቹን በሚያካፍልበት ሰአት ያ ቀን ከነሌሊቱ የባለድርሻዋ ሀቅ ነው። በዚያን ቀን እሌላዋ ቤት መሄድ  አይችልም።ነገር ግን ለአሳሳቢ ጉዳይ መግባት ይችላል።ለምሳሌ የታመመ ለመጠየቅ ሚስቱ ቀለብ አልቆባት ከሆነ ለመስጠት እና ለመሳሰሉት ችግሮች ሳይቆይ ጉዳዩን ፈፅሞ ቶሎ መመለስ አለበት።ተረኛዋ ያልሆነችው ሚስቱ ቤት ሲገባ ከመሳም የዘለለ ግንኙነት ማድረግ አይችልም።
#በዚችኛዋ_ተራ_እዛች_ዘንድ_ሄዶ_ግንኙነት_ቢፈፅም_ወንጀለኛ_ነው ማካካሻ ይጠበቅበታል። ምክንያቱም የሌላ ሰው ሃቅ አሳልፎ ሰቷልና።

(ከኢብኑ ቁዷማ አል ሙግኒ ከሚለው ኪታባቸው ወደ አማረኛ የተተረጎመ)
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች

ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam