الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜  #ክፍል_አስራ_ስምንት_/⑱_ት #ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች     1/ #ማምታቻ_አጭር_መልስ    "አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ በሚስቶቻችሁ መካከል ማስተካከል አትችሉም ብሏል የሚል ነው።"  የቁርአኑን ፅንሰ ሀሳብ እንመልከት وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ…
    ☞::::ትዳርበ ኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ_/⑲ኝ

#ከአንድ_በላይ_ሚስት እና_የተሳሳቱ_አመለካከቶች_እና_የሚነሱ_ማምታቻዎች

#አጭር_መልስ፣ በመጀመሪያ እነዚህ አካላት የዚህን ሀዲስ መልእክት ወይም ትርጉም ሙሉውን ሳይሆን ለእነሱ መረጃ ይሆነናል ብለው ያሰቡትን ብቻ ቆርጠው ለማቅረብ ሞክረዋል።የሀዲሱ ሙሉ ይዘቱ ሲቀርብ ለእነሱ መረጃነቱ ይቀርና በእነሱ ላይ መረጃ ይሆናል። የሀዲሱ ሙሉ ትርጉም ይህን ይመስላል፣
"እኔ ሀላልን ሀራም፣ ሀራምን ሀላል የማደርግ አይደለሁም ነገር ግን በጌታዬ ይሁንብኝ በፍፁም የአላህ መልእክተኛ ልጅ እና የአላህ ታላቅ ጠላት ልጅ በአንድ ቤት ሊሆኑ አይችሉም።" የሚል ነበር።

    ☞ የአላህ መልእክተኛ ለአልይ የአቡ ጀህልን ልጅ እንዲያገባ ፈቃድ ያልሰጡት ከዲን አንፃር ስለማይፈቀድ ሳይሆን ከማህበራዊ ኑሮ አንፃር ነው።ይህ የአላህ ታላቅ ጠላት የኢስላም ቁጥር አንድ ከሚባሉት ጠላቶች ውስጥ የሆነ እና ነብዩን በከፍተኛ ኢ_ሰብአዊ በሆነ መልኩ ሲያሰቃይ የነበረ እና ቀጥተኛውን መንገድ እንደማይዝ  ነብዩ ሰአወ ያውቁ ስለነበር ነው።ስለዚህ ይህ የሂዳያ ተስፋ የሌለው ከነብዩ ጋር ተቀራርቦ እርሳቸውንም ሆነ ልጃቸው ፋጡማን ረአ ለአደጋ እንዳያጋልጥ ከእርሱ ጋር የሚያገናኛቸውን ጉዳይ የበለጠ መራቅ ነበረባቸው።ምን አልባት ልጁ የአላህን መልእክተኛ ልጅ ባል በማግባቷ በልጁ ሰበብ በነብዩም ላይ ሆነ በፋጡማ ላይ ጉዳት ለማድረስ አጋጣሚውን ሊያሰፋ ይችላል።በዚህ እና መሰል ማህበራዊ ጉዳዮች ለአልይ የአቡ ጀህልን ልጅ እንዳያገባ ከልክለውታል ትክክለኛው ይህ ነው።

   3/
#ማመወታቻ እና አጭር ምላሽ

"ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በሚስቶች መካከል ጥላቻ እና መቃቃር ይፈጥራል አልፎም ልጆች በጥላትነት እንዲተያዩ ያደርጋል"
#አጭር_መልስ፣ ይህ አይነቱ ድምዳሜ ከሀቅ የራቀ ለመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን ብቻ መመልከት በቂ ይመስለኛል።በተለያዩ የሀሳብአለመግባባቶች በአንድ ቤት ውስጥ ያሉ እናት እና ልጅ ጭምር ሊጣለየ ይችላሉ በተመሳሳይ በሁለቱ ሚሰወቶች መካከል ግጭቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ እነዚህ ግጭቶች በሰው ልጅህይወት ውስጥ አልፎ አልፎ መከሰታቸው አይቀርም። ነገር ግን ሁለተኛ ሚስቶች ሁሉ  ይጣላሉ ማለት አይቻልም።እንደዚህ ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ ኢስላምን ከመጥላት የመነጨ እንጂ በትክክለኛ አእምሮ የተመዘነ አይደለም።ምክንያቱም የአንድ አባወራ ሁለት ሚስቶች እንደእህትማማች የሚተያዩ በልጆቻቸው መካከል ምንም ልዩነት የማያውቁ በርካቶች አሉ።የአንድን አባወራ ቤተሰብ የመምራት አቅም ማነስ ችግርን ከሁለተኛ ሚስት ጋር ማያያዝ ፍርደ ገምድልነት ነው።

#የኢስላም_ጠላቶች_ከአንድ_በላይ_ሚስትን_አስመልክተው_የሚያነሱት_ትችቶችና_መልሶቻቸው

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam