ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
197K subscribers
281 photos
1 video
16 files
209 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


የመርቪን ላቭሌይ ባለቤት ዳያና በደስታ ተፍነክንካለች በመጀመሪያ የሰማይ በራሪው ጀልባ መሬት ለቆ ሰማይ ላይ ሲወጣ ፈርታ ነበር አሁን ግን እየለመደችው መጣችና ደስ ይላት ጀመር ላቭሴይ በአይሮፕላኑ እንድትበር ዕድል ባይሰጣትም አይሮፕላኗን ብዙ ቀናት ፈጅታ ቀለም የቀባቻት እሷ ነች አንድ ጊዜ እስኪወጣ ነው እንጂ የሚያስፈራው እየተለመደ ሲመጣ ከሰማይ ሆኖ እርሻዎችን መንገዶችን የባቡር ሃዲዶችን፣ ቤተክርስ
ቲያኖችን፣ ፋብሪካዎችን ቁልቁል ሲያዩ የሚፈጥረው ደስታ ልክ የለውም
አሁን ነፃነት ተሰምቷታል፡፡ መርቪንን ጥላ ከማርክ ጋር ኮብልላለች፡፡
ትናንት ማታ ሳውዝሃምፕተን ከተማ በሳውዝ ዌስተርን ሆቴል ሚስተርና ሚስስ ማርክ አልደር በማለት ተመዝግበው የመጀመሪያውን
ሙሉ ምሽት አብረው
ሲፈጽሙ ያደሩት ወሲብ አልበቃ ብሏቸው ጧትም ደገሙት፡፡ ከዚህ ቀደም አዩኝ አላዩኝ እያሉ
እየተሳቀቁ ለአጭር ጊዜ ወሲብ ሲፈጽሙና ሲሳሳሙ ከነበረው ጋር ሲወዳደር
ይሄ ዓለም ነው በሰማይ በራሪው ጀልባ ሲበሩ ልክ ፊልም የሚያዩ ያህል
ነው የሚሰማው የአይሮፕላኑ የውስጥ ክፍል ያጌጠ፣ ተሳፋሪዎቹ ደግሞ
አለባበሳቸው የሚያምር ሲሆን ሁለቱ አስተናጋጆች ደግሞ ከአይን የቀደሙ ተፌዎች ናቸው ሁሉም እንቅስቃሴ በቅደም ተከተልና በቅልጥፍና
የሚካሄድ ሲሆን ዙሪያ ገባውን ታዋቂ ሰዎችም ይታያሉ፡ የይሁዲ ዝርያ ያለውና የጽዮናዊነት ንቅናቄ አራማጁ ባሮን ጋቦን አጠገባቸው ከተቀመጡ
ጎስቋላ ሰው ጋር በወሬ ተጠምደዋል ታዋቂው ፋሺስት የኦክስፎርዱ ባላባት ሎርድ ኦክሰንፎርድ ውቧን ሚስታቸውን አጠገባቸው ሻጥ አድርገው
ተኮፍሰዋል ልዕልት ላቪኒያ ባዛሮቭ ከዳያና ጋር ተቀምጠዋል

ከልዕልቷ ትይዩ ደግሞ በጥግ በኩል ታዋቂዋ የሆሊውድ ፊልም
ተዋናይ ሉሉ ቤል ቦታ ይዛለች፡፡ ዳያና በበርካታ ፊልሞች ላይ ያየቻት ሲሆን
ከማርክ ጋር እውቂያ አላት፡፡ ገና እንደተቀመጡ አንድ የአሜሪካዊያን አነጋገር ቅላጼ ያለው ድምጽ ‹‹ማርክ አልደር አንተ ነህ?! እኔ አላምንም››
ሲል ተሰማ፡፡ ዳያና ለማየት ዞር ከማለቷ አንዲት ከአፍ የወደቀች ፍሬ የምታክል ሴት ማርክ ላይ እንደ ጆፌ አሞራ ስትከመርበት ተመለከተች
በኋላ ታሪኩን እንዳጫወቷት ሉሉ እንደዚህ እንዳሁኑ ታዋቂ የፊልም አክተር ከመሆኗ በፊት ከማርክ ጋር የሬዲዮ ቶክ ሾው ላይ አብረው ሰርተዋል፡፡ ማርክም ዳያናንና ሉሉን አስተዋወቃቸው፡፡ ሉሉም ዳያና ቆንጆ መሆኗንና እሷን የመሰለች ማግኘት መቻሉ እድለኛ እንደሆነ ነገረችው፡፡
በእርግጥም ሉሉ ትኩረቷ ማርክ ላይ ስለነበር አይሮፕላኑ ከተነሳ ጀምሮ
ወጣት ሳሉ በችግር እንዴት እንዳሳለፉ እዚህ ግባ የማይባል ቤት ውስጥ
ሲኖሩ እንደነበሩና የመንደር አረቄ እየጠጡ ሌሊቱን ያሳለፉ እንደነበር
የጥንቱን አኗኗራቸውን እያነሱ ተጨዋወቱ፡፡

ዳያና ፊልሞቿ ላይ ረጅም ትምሰል እንጂ በእውን አጭር ናት፡ጸጉሯም በተፈጥሮ ቃጫ የመሰለ ሳይሆን ቀለም የተቀባ ነው፡፡ ሆኖም ፊልሟ ላይ እንደምትታየው እዚህም ያንኑ ፎልፏላነትና ልታይ ልታይ ባይነት ባህሪዋን ታንጸባርቃለች፡፡ ከማርክ ጋር እያወራች ሳለ ሁሉም እሷን
እሷን ይመለከታል፡፡

በሬዲዮ ድራማ ላይ አንድ ገጠመኝ አንስታ ስታወራ ሁሉም በሳቅ አውካካ፡፡ ‹‹አንድ ተዋናይ እሱ የሚናገረው የድራማው ክፍል አልቋል ብሎ በማሰብ ከስቱዲዮ ወጥቶ ሄዷል፡፡ መጨረሻ ላይ ግን የሚናገረው አንድ መስመር ንግግር ቀርቶታል፡፡ እኔም የፋሲጋውን ኬክ ማን በላው?
የሚለውን የራሴን ድርሻ ተናገርኩ፡ የኔን ድርሻ እንደገና ደግሜ ተናገርኩ፡፡

ዞር ብዬ ሳይ ተዋናዩ የለም፡፡ ቀጥሎ ያለውን የሚናገረው ሰው ሄዷል።አንድ ዘዴ በአእምሮዬ አውጠነጠንኩና በወንድ ድምጽ ድመቷ ናት
የበላችው በማለት ትርዒቱን አጠናቀቅኩ እላችኋለሁ›› ብላ አሳቀቻቸው::

ለማርክ ለመንገር ታሪኩን ስትጀምር አቋረጣትና ፊቱን ወደ ሉሉ አዙሮ ዳያናም አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም ስትከታተል የሰማችውን
ከማርክ ጋር በቆየችባቸው ሶስት ወር ያህል ማርክ ፊት ነስቷት አያውቅም በኋላ ማርክን የብቻዋ ማድረግ የማትችል መሆንዋን
መረዳት ሊኖርባት ነው፡ አዳማጭ መሆንዋ ሰለቻትና ወደ ልዕልት ላቪኒያ ዞራ

‹ሬዲዮ ያዳምጣሉ ልዕልት?› ብላ ወሬ ጀመረች።

አሮጊቷ ራሻዊት አገጫቸውንና እንደ
አሞራ የተቆለመመ
አፍንጫቸውን በንቀት ከፍ አድርገው አቀራረባቸው ጨዋነት ይጎድለዋል›
አሉ፡፡

ዳያና ከዚህ ቀደም አመለ ቢስ አሮጊቶች ቢገጥሟትም እኚህኛዋ ግን የባሱ ናቸው፡ ‹‹ይደንቃል! ትናንት ግን የሰማነው የቤቶቨን ሙዚቃ ጥሩ ነው›› አለች ዳያና፡፡

‹‹የጀርመን ሙዚቃ ደረቅ ነው›› አሉ አሮጊቷ በማንቋሸሽ፡
እኚህን ሴት ምንም የሚያስደስታቸው ነገር የለም አለች ዳያና በሆዷ።
ልዕልቲቷ ከዚህ ቀደም እጅግ በጣም የተከበረ መደብ አባል የነበሩ ሲሆን
ይህንንም ዓለም በሙሉ እንዲያውቅላቸው ይፈልጋሉ የሚቀርብላቸው ነገር
ሁሉ ከዚህ ቀደም ሲቀርብላቸው ከነበረው ጋር ሲወዳደር እንደሳቸው
አስተሳሰብ እዚህ ግባ የሚባል ይደለም።

በኋለኛው የአይሮፕላኑ ክፍል የተመደበው አስተናጋጅ የሚፈልጉት
መጠጥ ካለ ለመታዘዝ ተሳፋሪዎቹ ፊት ቆሟል፡ ስሙ ዴቪ ሲሆን ሲራመድ ነጠር ነጠር የሚል የደስ ደስ ያለው ወጣት ነው፡፡ ዳያና ጠጥታው ባታውቅም የአሜሪካ ፊልሞች ላይ ሲጠጡት ስላየች ማርቲኒ አዘዘች፡

ከእሷ ቀጥሎ የተቀመጡትን ሁለት ሰዎች መልከት ስታደርግ በመስኮት ወደ ውጭ ያያሉ፡፡ ለጥቆ ደግሞ ረከስ ያለ ነገር ግን የሚያምር ልብስ የለበሰ ወጣት ሰው ተቀምጧል እንደ ስፖርተኛ ደልደል ያለ ትከሻ ያለው ሲሆን በርካታ ቀለበቶች አስሯል፡ ጠየም ያለ ፊቱ ደቡብ አሜሪካዊ መሆኑን
ይጠቁማል።

ከእሱ ትይዩ የተቀመጠው ሰው ደግሞ ለየት የሚል ሲሆን ኮሌታው የነተበ ሰፊ ኮት ለብሷል፡ በራው ደግሞ እንደ ስጋ ቤት አምፑል ዓይን
ያጥበረብራል፡ ሁለቱ ሰዎች ሲነጋገሩ ባይታዩም ዳያና አንድ ላይ እንደሆኑ
ገምታለች፡

መርቪን በአሁኑ ጊዜ ምን እየሰራ ይሆን? ስትል አሰበች፡፡ መቼም
ያስቀመጠችለትን ማስታወሻ ሳያነብ አይቀርም ያለቅስ ይሆናል አይ
አያደርገውም እሱ እንደዚህ አይነት ሰው አይደለም፡፡ መቼም በንዴት ጠጉሩን እየነጨ ይሆናል፡ በማን ላይ ይናደዳል ምናልባት በሰራተኞቹ ላይ? የጻፈችው ማስታወሻ ለስለስ ያለ ቢሆን ተመኘች ነገር ግን ከዚህ የተሻለ እንዳትጽፍ ሁኔታዎች አልፈቀዱም፡፡ እቤት ሲያጣት እህቷ ቲያ ጋ
ይደውልና አንቺጋ ናት? ብሎ ይጠይቅ ይሆናል የሄደችበትን መቼስ
ታውቃለች ብሎ፡ ወደ አሜሪካ እንደምትሄድ ስላልነገረቻት ቲያ ጠፋች
ሲባል ትደነግጣለች፡ የዳያናን አገር ጥሎ መጥፋት ለመንትያ ልጆቿ ምን ብላ ትነግራቸዋለች? ይህን ስታስበው ሆዷ ተምቦጫቦጨባት፡፡ የመንትዮቹን ልጆች ናፍቆት መቼም አትችለውም::

ዴቪ ያዘዙትን መጠጥ ይዞላቸው መጣ፡፡ ማርክ በመጀመሪያ ለሉሉ
ቀጥሎ ለዳያና ብርጭቆውን አነሳ በዚያው ቅጽበት ዳያና ማርቲኒውን
አንስታ ተጎነጨች፤ ስላንገፈገፋት ‹ህቅ› ብላ ተፋችና ‹‹ጂን ጂን ይላል››
ስትል ሁሉም አንዴ ሳቁባት፡፡ ማርክም ቀበል አድርጎ ‹‹ማርቲኒ እኮ ባብዛኛው ጂን ነው ከዚህ በፊት ጠጥተሽ አታውቂም ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

ሰዎቹ ስለሳቁባት ዳያና በሃፍረት ተሸማቀቀች። ልክ ቡና ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደገባች ተማሪ የምታዘውን መጠጥ አታውቅም፡፡ እነዚህ
ከሰለጠነ ዓለም የመጡ ተሳፋሪዎች ደግሞ ፋራነቷን አወቁባት፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_አንድ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

የበረራ መሃንዲሱ ኤዲ ዲከን የስማይ በራሪ ጀልባውን የሚያየው
ጥንቃቄ የሚፈልግ ነገር አድርጎ ነው፡፡ የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች ገና በቅጡ
ያልዳበሩ መሆናቸውንና በአትላንቲክ ውቅያኖስ በምሽት በሚደረገው በረራ
ወቅት ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ተሳፋሪዎቹ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያውቃል፡፡ ሆኖም ኤዲ የካፒቴኑ የመሾፈር ብቃት፣ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ከልብ መስራትና የአሜሪካ ኢንጂነሪንግ የደረሰበት ደረጃ ተዳምረው አይሮፕላኑን በሰላም አሜሪካ እንደሚያደርሱት ይተማመናል።

ይህ ጉዞም እስካሁን ካደረጋቸው ጉዞዎች ሁሉ አስፈሪ ሆኖበታል፡በተሳፋሪዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ቶም ሉተር የሚባል ሰው መኖሩን አይቷል፡፡ ተሳፋሪዎቹ አንድ በአንድ አይሮፕላኑ ላይ ሲሳፈሩ ከእነዚህ ውስጥ ካሮል አንን ያገታት ቶም ሉተር የቱ ይሆን? አለ በሆዱ¨
አዕምሮውን ወጥሮ የያዘውን የካሮል አንን ጉዳይ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ትቶ አይሮፕላኑን ለበረራ ለማዘጋጀት ተነሳ፡፡ የአይሮፕላኑ የተለያዩ መሳሪያዎች የሚሰሩና የማይሰሩ መሆናቸውን መፈተሽ፣ አራቱን ግዙፍ ሞተሮች መቆጣጠር ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ናቸው፡ አይሮፕላኑ ተነስቶ በጥሩ ሁኔታ መብረር ከጀመረ በኋላ ብዙም የሚሰራው ነገር አይኖርም፡፡ በዚህ ጊዜ የአይሮፕላኑ ፍጥነትና
የሞተሮቹ ሙቀት መጠን
በትክክል መስራቱንና ነዳጁን መቆጣጠር
ይሆናል። ሆኖም አዕምሮው እንደገና ወደ ካሮል አን እየሄደበት ተቸገረ፡፡
ካሮል አን በሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ በእነዚህ አረመኔዎች እጅ በተለይም ከጠጡ ምን ሊደርስባት እንደሚችል አይታወቅም:

እነዚህ ሰዎች ምንድነው
ከእሱ የሚፈልጉት? የስራ ጓደኞቹ የተቸገረበትን ነገር እንዳያውቁበት መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሁሉም ግዴታውን
ለመወጣት ተፍ ተፍ ስለሚል ላያውቁበት ይችላሉ፡ ካፒቴን ቤከርና ረዳት ካፒቴን ጆኒ ዶት የአይሮፕላኑ ጋቢና ውስጥ ተመቻችተው ተቀምጠዋል
ከተሳፋሪዎች ክፍል የሚመጣው ብርሃን ፓይለቶቹን እንዳያስቸግራቸው
ማታ ማታ ወፍራም መጋረጃ ይጋረዳል፡ ማፖችንና መሳሪያዎች በመጠቀም
አይሮፕላኑን ትክክለኛውን አቅጣጫ እንዲይዝ የሚያደርገው ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ማፑ ላይ አፍጥጧል፡

ይህን አይሮፕላን ከሌሎች አይሮፕላኖች የሚለየው አይሮፕላኑ መሬት
ሳይወርድ ዘይት የሚያፈስን የሞተር ክፍል ጥገናን የመሳሰሉ ቀላል የጥገና
ስራዎችን መስራት ማስቻሉ ነው፡፡ ቀጥሎ የሚገኘው ቦታ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ
የቤን ቶምሰን ሲሆን ከእሱ ኋላ ደግሞ የኤዲ የስራ ቦታ ይገኛል።

ኤዲ ጀርባቸውን ለእሱ ሰጥተው በተመስጦ የሚሰሩ ጓደኖቹ የእሱን
ጭንቀትና ፍርሃት ባለማስተዋላቸው ተረጋጋ:: ለጊዜው ማንነቱ ያልታወቀው ሚስተር ሉተር እኔ ነኝ እንዲል ለማድረግ ፍላጎት አደረበት፡፡
በተሳፋሪዎች ክፍል መተላለፊያ መንጎራደድ ፈለገና ከመቀመጫው ተነስቶ ‹‹እስቲ አንድ ቼክ የማደርገው ነገር አለ›› ብሎ ለናቪጌተሩ ነገረና ደረጃውን
ወርዶ ሄደ፡፡ የሆነ ሰው ለምን ቼክ ማድረግ እንደፈለገ ቢጠይቀው ዝም ብሎ እንደሚያልፍ ወስኗል፡፡

ኤዲ በመተላለፊያው ላይ ቀስ ብሎ ተራመደ፡ ኒክና ዴቪ ለተሳፋሪዎች ምግብና መጠጥ እያደሉ ነው፡፡ ተሳፋሪዎቹ በተለያዩ ቋንቋዎች ያወራሉ፡፡
የተወሰኑ ሰዎች ካርታ ጨዋታ አጧጡፈዋል፡ ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታዋቂ ሰዎች ቢያይም ሃሳቡ ስለተበታተነበት እነማን እንደሆኑ መለየት አልቻለም፡፡እያንዳንዱ ሰው ላይ ተራ በተራ ቢያፈጥም ማንም ሰው ‹ቶም ሉተር እኔ
ነኝ›› አላለውም፡፡ ማየት የፈለገውን ነገር እንደነገሩ አይቶ በሩን ሲዘጋ አንድ
አስራ አራት አመት የሚሆነው ልጅ የሚሰራውን በተመስጦ ሲመለከት አየና
ፈገግ አለ፡፡

የፓይለቶቹን ጋቢና ማየት ይቻላል?›› ሲል ጠየቀው ልጁ፡
‹‹ይቻላል›› አለ ኤዲ፡ በዚህ ሰዓት ማንም እንዲያስቸግረው ባይፈልግም ተሳፋሪውን በትህትና ማናገር አለበት፡
‹በጣም አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡
‹‹ወደ መቀመጫህ ተመለስና ጥቂት ጊዜ ቆይቼ እጠራሃለሁ›› አለው
ልጁ በኤዲ መልስ ግራ ቢጋባም ራሱን በእሺታ ነቀነቀና ፈጠን ብሎ
ሄደ፡፡

ኤዲ በመተላለፊያው ላይ እየተንጎራደደ አንድ ሰው እንዲያናግረው ጠበቀ፡፡ የሚያናግረው ሰው አለመኖሩን ሲረዳ ሰውየው ሰው የማይኖርበትን
አጋጣሚ እየጠበቀ መሆኑን ገመተ፡ አስተናጋጁን ሉተር የተባለው ሰው የቱጋ እንደተቀመጠ መጠየቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን ለምንህ ነው የምትጠይቀው?› ብሎ ቢለው ምን መልስ እንደሚሰጥ አያውቅም በዚህ ጊዜ የስራ ባልደረቦቹ በእሱ ላይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዲያድርባቸ
የሚያደርግ ነገር ማድረግ የለበትም፡፡

ልጁ ከአባትና ከእናቱ ጋር ነው የተቀመጠው፡፡ ኤዲም ‹‹ማሙሽ አሁን ና›› ሲል ተጣራ፡ አባትና እናቱም በመቀበል ራሳቸውን ነቀነቁ። አንዲት ጸጉረ ረጅም ልጅ የልጁ እህት ሳትሆን አትቀርም ሞቅ ያለ ፈገግታ
ስትመግበው ልቡ ደንገጥ አለ፡፡ ልጅቷ ስትስቅ ታምራለች፡

‹‹ማነው ስምህ ማሙሽ?›› አለው፡

‹‹ፔርሲ ኦክሰንፎርድ›› አለ፡
‹‹እኔ ኤዲ ዲኪን እባላለሁ፡፡ የበረራ መሀንዲስ ነኝ፡፡ ሞተሮቹን በትክክል መስራታቸውን መከታተል ነው ስራዬ››

የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደረሱ፡ ‹‹ይሄ ሁሉ ደውልና መሳሪያ ምን ያደርጋል?››

‹‹የሽክርክሪቱን ፍጥነት፣ የሞተሩን የሙቀት መጠን እና የነዳጁን ቅልቅል ይቆጣጠራል፡፡›› ለልጁ በይበልጥ እንዲገባው ‹‹እዚህ ወንበር ላይ
ቁጭ በል›› አለው፡ ፔርሲም ቁጭ አለ፡፡ ‹‹ይሄ ደውል የቁጥር ሁለት ሞተርን የሙቀት መጠን ያሳያል፡ አሁን ሙቀቱ ከፍ ብሏል፡ ትንሽ ማቀዝቀዝ ያስፈልጋል፡››

‹‹እንዴት ነው ይሄን የምታደርገው?››

‹‹እጀታውን ያዝና ትንሽ ወደታች ግፋው ይህን ያህል ይበቃል፡ አሁን ተጨማሪ አየር እየገባ ነው ከትንሽ ደቂቃ በኋላ የሙቀት መጠኑ ሲወርድ
ታያለህ፡፡ ፊዚክስ ተምረሃል?›› ሲል ጠየቀው ኤዲ፡፡

‹‹እኔ የምማረው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ውስጥ አይደለም›› አለ ፔርሲ፣ ‹‹ትምህርት ቤቱ ላቲንና ግሪክ ቋንቋዎች ላይ ነው በይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው፡፡ ሳይንስ ላይ እስከዚህም ነው፡፡››
‹‹ሌሎቹ የስራ ባልደረቦችህስ ምንድነው ስራቸው?››
‹ዋናው ትልቅ ስራ ያለበት ናቪጌተሩ ነው፤ ቻርቱ ላይ ያፈጠጠው ጃክ አሽፎርድ ይባላል አይሮፕላኑ የት እንዳለ የሚቆጣጠረው እሱ ነው! በተለይ መሃል አትላንቲክ ላይ ስንበር፡፡››

ጃክ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ፈገግ አለ፡፡ ‹‹አይሮፕላኑ እየበረረ የሚገኝበትን ቦታ የሚጠቁመንን መሳሪያ የሚቆጣጠረው ጃክ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ከባህር በላይ ሲበር ቦታውን ማወቅ አስቸጋሪ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡››

ጃክም ስለስራው ሲናገር ‹‹ብመጀመሪያ መሳሪያውን በመጠቀም በመስታወት እያየህ አንድ ኮከብ ፈልገህ ኮከቡ በአድማስ ላይ ትክክል እስኪመጣ ጠብቀህ የመስታወቱን አንግል ታስተካክላለህ›› አለ፡

‹‹ይሄማ ቀላል ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹ይሄ በቲዮሪ ደረጃ ነው›› አለ ጃክ እየሳቀ ‹‹የዚህ የጉዞ መስመር ችግር ጠቅላላ በረራውን ድፍን ባለ ደመና ልንጓዝ የምንችልበት አጋጣሚ
የሚፈጠርበት ጊዜ መኖሩ ነው፡፡ የተነሳህበትን ነጥብ ካወቅህና በተመሳሳይ
አቅጣጫ የምትጓዝ ከሆንክ ልትሳሳትበት የምትችልበት አጋጣሚ ባይኖርም
ይሄ የሚሆነው ግን ነፋስ በሌለበት ጊዜ ነው፡፡ሀይለኛ ንፋስ በሚኖርበት ጊዜ
አይሮፕላኑን ወዲህና ወዲያ የሚያላጋው ስለሆነ መስመር ጠብቆ መጓዝ
አስቸጋሪ ነው:፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሁለት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አይሮፕላኑን ባህሩ ላይ እንድጥለው ትፈልጋለህ?››
‹‹እንደዚያማ ማድረግ አትችልምº እኔ አይሮፕላኑ ውስጥ አለሁ
ፓይለቱ እዚያ ቦታ ላይ በድንገት እንዲያርፍ የሚያስገድደው አንድ ችግር ፍጠር›› አለው በሚገባ በተከረከመ ጥፍሩ ፖስት ካርዱ ላይ ያለውን ቦታ እያመለከተው፡፡
የበረራ መሃንዲሱ ፓይለቱ በድንገት አይሮፕላኑን ለማሳረፍ የሚያስገድደው ችግር መፍጠር አያቅተውም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍ ችግር መፍጠር ለጊዜው ኤዲ አልከሰትልህ አለው፡፡

‹‹ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን የማይሆን ነገር ግን አይደለም
እኔም ይህን ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጫለሁ››
‹‹ማነው ይህን የነገረህ? እናንተስ እነማን ናችሁ? አለ ኤዲ ንዴቱ ተቀስቅሶ፡

‹‹ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ መጠየቅ አትችልም›› አለው ሉተር::

ኤዲ መጀመሪያ ሉተርን ሊያስፈራራው ሞከረ፣ አሁን ግን አቅመ ቢስ ሆኗል፡ አሁን በፍርሃት መሸበብ የእሱ ተራ ሆኗል፡ ሉተር ይህን ጉዳይ በሚገባ ያቀደ የወሮበላ ቡድን አባል ነው፡፡ ኤዲን ለእኩይ ተግባራቸው
በመሳሪያነት ሊጠቀሙበት ነው የመረጡት፡ ውጥናቸውን ዳር ለማድረስ
ደግሞ ካሮል አንን እመዳፋቸው ስር አውለዋታል፡

ኤዲ ፖስት ካርዱን ኪሱ ከተተና ትተባበራለህ ወይስ አትተባበርም?›› ሲል ሉተር በጉጉት ጠየቀ፡፡

ኤዲ ዞር አለና አፈጠጠበት፡ ከዚያም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ፡

ኤዲ በጠላቶቹ ፊት ፈርጠም ያለ ባህሪ ለማሳየት ቢሞክርም እውነታው ግን እንዳንበረከኩት ነው የሚያሳየው እነዚህ ወሮበሎች ለምንድነው ይህን ማድረግ የፈለጉት? ባንድ ወቅት ጀርመኖች ቦይንግ 314 አይሮፕላንን
ሰርቀው ዲዛይኑን ኮፒ ለማድረግ ፈልገው እንደነበር ያውቃል፡ አሁን ይህን ማድረግ ቢፈልጉ አይሮፕላኑን ሜይን ስቴት ውስጥ ሳይሆን አውሮፓ
ውስጥም ሰርቀው መውሰድ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡

አይሮፕላኑን በሚፈልጉበት ቦታ ላይ እንዲወርድ ለማድረግ ማሰባቸው
ቦታው ላይ የሚጠብቅ ጀልባ እንዳላቸው ይጠቁማል፡ ‹ግን ለምን?› ሉተር ሻንጣ ሙሉ ሃሺሽ፣ ባዙቃ፣ ኮሚኒስት አብዮተኛ ወይስ የናዚ ሰላይ ነው
ወደ አሜሪካ ማስገባት የፈለገው? እነ ሉተር እዚህ ችግር ውስጥ ለመግባት
የወሰኑት መቼም ሊያስገቡት ያሰቡት ሰው ወይም ነገር በጣም ጠቃሚ
ስለሆነ ነው፡፡

ኤዲ ከሌሎቹ የስራ ባልደረቦቹ ይልቅ እሱን የመረጡበት ምክንያት
አሁን ገብቶታል፡አይሮፕላኑን አንድ ቦታ በድንገት እንዲያርፍ ከተፈለገ
ይህን ማድረግ የሚችለው የበረራ መሀንዲሱ ነው፡፡ ናቪጌተሩ ምንም ማድረግ አይችልም የሬዲዮ ኦፕሬተሩም እንዲሁ፤ ፓይለቱ ደግሞ የረዳት
ፓይለቱ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡ የበረራ መሀንዲሱ ግን ብቻውን
የአይሮፕላኑን ሞተር ቀጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ሉተር የፓን አሜሪካንን አየር መንገድ መሀንዲሶች ስም ዝርዝር ሳያገኝ አልቀረም፡ ስም ዝርዝሩንም ማግኘት ከባድ አይደለም:፡ የአየር መንገዱን መረጃ ለማየት አንድ ምሽት ላይ አንዱ የሉተር ጓደኛ የአየር መንገዱን ቢሮ ሰብሮም ቢሆን ሊያገኘው ይችላል ወይም አንዷን ጸሐፊ በጉቦ መደለል ነው፡፡ ለምን ግን ኤዲን መረጡ? ሉተር በዚህ ቀን የሚበረው የበረራ
መሃንዲስ ስም እጁ ገብቷል ከዚያም ኤዲ ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር
እንዲሆን ለማድረግ ሲያስብ አንድ መላ ያገኛል፤ ሚስቱን ማገት፡፡
እነዚህን ወንበዴዎች መርዳት ለኤዲ ልብ የሚሰብር ጉዳይ ሆኖበታል፡
ወንበዴዎች እጣ ክፍሎቹ አይደሉም፡ ሰርተው ከማግኘት ይልቅ ሌት ተቀን
ከሚለፉ ሰዎች አፍ እየነጠቁና እያጭበረበሩ ተንደላቀው ይኖራሉ፡ ህግ
አክባሪ ሰዎች የዕለት እንጀራ ለማግኘት ጀርባቸው ሲጎብጥ ይውላል፡ እነዚህ
ማፊያዎች ግን ለፍቶ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየደገኑ፣ ለፍተው ያገኙትን
ተሽከርካሪዎች ያሽከረክራሉ፡፡ እነዚህን ወንጀለኞች በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ጠፍሮ በኮረንቲ እያንጨረጨሩ መግደል ነው የሚያዋጣው፡፡

ቶም ሉተርን ማሞኘት ቀላል አይደለም፡፡ ሚስቱን ካሮል አንን አግቷታል። ሉተር ያቀደውን ትልም ኤዲ ለማደናቀፍ ሞከረ ማለት በሚስቱ አንገት ላይ የታሰረውን ገመድ ሸምቀቆ አጠበቀ ማለት ነው፡፡ ሊያታልላቸው
ወይም ሊታገላቸው አይችልም፤ ያሉትን ከመፈጸም ውጭ፡

ሆዱን እንደጨነቀው ከወደቡ ወጥቶ በመንደሩ ያለችውን ብቸኛ መንገድ አቋርጦ ወደ አንድ ሆቴል ሄደ፡ ሆቴሉ እንዳለ የተያዘው በፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች ነው ማለት ይቻላል፡፡ እዚያም ካፒቴን ቤከርና ረዳቱ ጆኒ ዶት ከፓን አሜሪካ የፎየንስ ጣቢያ ኃላፊ ጋር የራዲዮ
መልእክቶችን እየገመገሙ የአትላንቲክ አቋራጭን በረራ ስለማድረግና አለማድረግ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ጉባኤ በተቀመጡበት ክፍል ኤዲ ገብቶ ተሰየመ፡

በአይሮፕላን በረራ ሳይንስ ቁልፍ ጉዳይ የነፋሱ ጥንካሬ ነው፡፡ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ ከጠንካራው ነፋስ ጋር እየታገሉ ነው በረራው የሚካሄደው፡ ከፊት ለፊት የሚመጣውን የንፋስ ግፊት ለመሸሽ ሲሉ ፓይለቶች
በተደጋጋሚ ከፍታቸውን ለመለዋወጥ ይገደዳሉ፡ ይህም ቴክኒክ በበረራው
ሳይንስ ‹ነፋሱን ማሳደድ›› ይባላል፡ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ያለ ነፋስ ግፊቱ ያነሰ
ቢሆንም አይሮፕላኑ ዝቅ እያለ በበረረ ቁጥር ከመርከብ ወይም ባህር ላይ ከሚዋልል የበረዶ ቋጥኝ ጋር ሊላተም ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚመጣን ንፋስ ግፊት ለመቋቋም በርካታ ነዳጅ ማቃጠል ይጠይቃል፡ ኃይለኛ የንፋስ ግፊት ካለ ከአይርላንድ እስከ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ከሁለት ሺህ ማይል
በላይ ለመብረር የሚበቃ ነዳጅ አይሮፕላኑ መያዝ ስለማይችል የነዳጅ
እጥረት ሊያጋጥም ይችላል፡ በዚህም ምክንያት በረራው ለሌላ ቀን ሊተላለፍ
ስለሚችል የአየሩ ጠባይ እስከሚሻሻል ተጓዦች በሆቴል ሊቆዩ የሚችሉበት
አጋጣሚ ይፈጠራል፡

የዚህ ዓይነት የአየር መዛባት ቢከሰት ካሮል አንን ምን ይውጣት ይሆን?

የአየር ጠባይ ሪፖርቱ ነፋሱ ከባድ መሆኑን፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ደግሞ ከባድ ማዕበል እንዳለ ያመለክታል፡፡ አይሮፕላኑ ሙሉ ሰው ጭኗል፡
ስለዚህ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ሁሉ ነገር በጥንቃቄ መሰላት አለበት፡፡ የአየሩ
ጠባይ መጥፎ መሆን የኤዲን ጭንቀት አባባሰው፡፡ ሚስቱ ካሮል አን በወዲያኛው የውቅያኖስ ጥግ በጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ወድቃ እሱ እዚህ አየርላንድ ውስጥ ተጣብቆ መቅረቱን
ሊቋቋመው የሚችለው ነገር
አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምግብ ይሰጧት ይሆን? የምትተኛበት ቦታስ አላት
ይሆን? ብርድስ ይመታት ይሆን?› እያለ ያስባል።

የአትላንቲክ ውቅያኖስን አካባቢ የሚያሳየው ማፕ ጋ ሄደና ቶም ሉተር የሰጠውን አይሮፕላኑ እንዲያርፍበት የሚፈለግበትን ቦታ ተመለከተ፡፡ ቦታው
ተጠንቶ የተመረጠ ነው ከካናዳ ጠረፍ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቆ ቤይ አፍ
ፈንዲ› የሚባል በጠረፉና በአንድ ትንሽ ደሴት መካከል የሚገኝ ቦታ ነው:
ምንም እንኳን ባህር ላይ ለሚያርፉ አይሮፕላኖች ማረፊያነቱ ብዙም
ተመራጭ ባይሆንም ከገላጣው የባህር ክፍል የተሻለ ነው፡፡ ይህን ሲያውቅ ኤዲ ተስፋው ለመለመ፡ ቢያንስ የማረፉ ነገር ብዙ ችግር የለውም፡፡ ሉተር ሚስቱን በእጁ እንዲያስገባለትና እቅዱ እንዲሳካ አቅሙን በሙሉ አሟጧዐየተጣለበትን ግዴታ መወጣት አለበት፡

አሁንም ግን አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ እንዴት ሊያሳርፍ እንደሚችልዐመጨነቁ አልቀረም፡ በዚህ ቦታ እንዲያርፍ ያደረኩት አንዱ የአይሮፕላኑ ሞተር ስለተበላሽ ነው ቢል በሶስት ሞተር ሊሄድ እንደሚችል ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ስለሚያውቅ ይህ ምክንያት ብዙም አያስኬድም የአዕምሮውን ጓዳ ቢያስስም ተጨባጭ መፍትሄ አልመጣለት አለ፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሶስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡

ማርክ እጇን ለቀም አድርጎ ሲይዝ እንዳይለቃት ፈራች፡፡ ‹አንድ ጊዜ ሃሳብሽን ለውጠሻል። አሁንም ደግመሽ መለወጥ ትችያለሽ›› አለ ለማሳመን፡፡
ከኔ ጋር አሜሪካ እንሂድና ላግባሽ፡፡ ልጆቻችንን ይዘን ባህር ዳር እንጫወታለን የምንወልዳቸው ልጆች ቴኒስ እየተጫወቱ፣ እየዋኙ ብስክሌት እየነዱ ያድጋሉ፡ ስንት ልጅ ነው መውለድ የምትፈልጊው?››

አሁን መወላወሉን አቁማለች፡፡ ‹‹ማርክ እያደረኩት ያለሁት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ተመልሼ ወዳገሬ እሄዳለሁ›› አለች፡፡
ያለችውን የተቀበለ መሆኑን ተረዳች፡፡ ሁለቱም ሀዘን ገብቷቸውና የሚሰሩትን አጥተው ዓይን ላይን ይተያያሉ፡፡ የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም
ዝም ብለዋል፡

ከዚያም መርቪን ቡና ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡

ዳያና ባሏ ፊቷ መጥቶ ድቅን ሲልባት ዓይኗን ማመን አቃታት፡ ልክ
አንድ የሆነ መንፈስ ፊት የቆመ ይመስል አፈጠጠችበት፡ እንዴት እዚህ ሊመጣ ቻለ? ሊሆን አይችልም

‹‹እዚህ ተገኘሽ አይደል!›› አለ መርቪን በተለመደው አስገምጋሚ ድምጹ
ዳያና ግራ ተጋባች፡፡ መርቪን እዚህ መገኘቱ አስደንቋታል፣ አስፈርቷታል፣ እፎይታ ሆኗታል፣ ቅሌት ውስጥም ከቷታል፡፡ ከሌላ ወንድ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ባሏ ሲደርስባት በደመነፍስ እጇን ከማርክ እጅ መንጭቃ አላቀቀች

ማርክም ‹‹ምንድነው እሱ?›› ሲል ጠየቃት ነገሩ ስላልገባው፡

መርቪን ሁለት እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ፊታቸው ተገትሯል፡

‹‹ማነው ይሄ ፊታችን የተገተረው?›› ሲል ጠየቀ ማርክ፡፡

‹‹ባሌ መርቪን ነው›› አለች በደከመ ድምጽ፡

‹‹ወይ አምላኬ!›› አለ ማርክ፡

‹‹እንዴት እዚህ ልትመጣ ቻልክ መርቪን?›› ስትል ጠየቀች ዳያና የምንተ እፍረቷን፡፡

‹‹ብራሴ አይሮፕላን በርሬ መጣሁ›› አለ ቁርጥ ባለ የአነጋገር ባህሪው:
ቆዳ ጃኬት የለበሰ ሲሆን በእጁ የሞተር ሳይክል ነጂ ቆብ አንጠልጥሏል፡፡
‹‹ኧረ ለመሆኑ እዚህ መሆናችንን እንዴት አወቅህ?›› ስትል ጥያቄዋን
ደገመች፡፡

‹በጻፍሽልኝ ደብዳቤ አሜሪካ እንደምትሄጂ ገልጸሻል፡ ወደ አሜሪካ
የሚኬደው ደግሞ በሰማይ በራሪ ጀልባ ብቻ መሆኑ ይታወቃል›› አለ በድል
አድራጊነት፡፡

የሷን ዱካ ተከታትሎ የምትሄድበትን መንገድ ገምቶ እሷ ጋ በመድረሱ ደስ እንዳለው ከገጽታው ይነበባል፡ በራሱ አይሮፕላን በርሮ ሊደርስባቸው
እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረችም፡፡ በዚህ መንገድ ተከታትሎ ስለደረሰባት ደካማ ነኝ ስትል አሰበች፡፡

ከእነሱ ትይዩ ባለው
ወንበር ላይ ተቀመጠና
‹‹እስቲ ዊስኪ አምጪልኝ›› ሲል አዘዘ አስተናጋጇን፡፡

ማርክ ብርጭቆውን አንስቶ ባንዴ ሲጨልጥ ዳያና ታየዋለች::በመጀመሪያ መርቪንን ሲያየው ተርበትብቶ ነበር፡፡ በኋላ ግን መርቪን አምባጓሮ እንደማያነሳ ሲገነዘብ ተረጋጋ ሆኖም ወምበሩን ገፋ አደረገና ከዳያና ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ፡፡ የሰው ሚስት እጅ እንደያዝ ባሏ ከተፍ ሲልበት ሳያፍር አልቀረም፡

ዳያና ድፍረት እንዲሰጣት ብላ ከአልኮሉ ተጎነጨች፡ መርቪን በጭንቀት ያያታል። ግራ መጋባቱንና መጎዳቱን ከፊቱ ስታይ ደረቱ ውስጥ
ተወሸቂ! ተወሸቂ! አላት፡፡ ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው ሳያውቅ እሷን ፍለጋ
አገር አቋርጦ መጥቷል፡፡ እጇን ሰዳ በማጽናናት ሁኔታ ክንዱን ያዝ አደረገችው፡፡

ሚስቱ በውሽማዋ ፊት ያዝ ስታደርገው መርቪን ማርክን በእፍረት አየት አደረገው፡፡ ዊስኪው ሲመጣለት አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው::
ማርክ በበኩሉ ዳያናን የሚያጣ መስሎት ወምበሩን ወደ እሷ አስጠጋ
ዳያና በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት
ገጥሟት አያውቅም:: ሁለቱም ሰዎች ይወዱዋታል ከሁለቱም ጋር ተኝታለች፡ ሁለቱም ይህን ያውቃሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ፡፡ ሁለቱንም ማጽናናት ፈለገች፧ ሆኖም ፈራች፡፡ አሁን ወደ መከላከሉ አዘምብላለች። ከሁለቱም ራቅ ብላ ተቀመጠችና ‹‹መርቪን አንተን ልጎዳ ብዬ አይደለም እዚህ መዘዝ ውስጥ የገባሁት›› አለች

መርቪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹አምንሻለሁ›› አለ
‹‹ታምነኛለህ? የሆነውን ሁሉ ትቀበለዋለህ?›› አለች ዳያና፡፡

መርቪን ማርክ ላይ አፍጥጦ ነገር ለመፈለግ በሚመስል ሁኔታ
ተጠጋውና ውሽማሽ አሜሪካዊ ይመስላል፤ከአፍ የወደቀ ጥሬ!
የተመኘሺውን አግኘተሻል›› አለ፡፡

ማርክ አፈገፈገ፤ ምንም ቃል ሳይተነፍስ መርቪንን አፍጥጦ ያየዋል ማርክ ጠብ ፈላጊ አይነት ሰው አይደለም፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶታል፡ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም መርቪን ዋና ባላንጣው ነው፡፡ ማታ ማታ ዳያና አቅፋው የምትተኛው ሰው ማን ይሆን?› ሲል ራሱን ሲጠይቅ ከርሟል፡፡ አሁን ማን እንደሆነ አውቆታል። ከማርክ ጋር ሲተያይ መርቪን ስለማርክ ምንም የተጨነቀ አይመስልም፡፡
ዳያና ሁለቱን ባላንጣዎች ተመለከተቻቸው፡ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም መርቪን ዘንካታ፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል፣ ኮስታራና ነርቨስ ነው ማርክ
ደግሞ አጭር፣ ሽክ ያለ፣ ነቃ ያለና ስው ሲናገር ጆሮ የሚሰጥ ሰው ነው ማርክ
አንድ ቀን ይህን ታሪክ በኮመዲ ስራው ውስጥ አካቶ ሳያቀርበው አይቀርም ስትል ዳያና አሰበች፡

አይኖቿ እምባ አንቆርዝዘዋል፡ መሃረብ አውጥታ ንፍጧን ተናፈጠች
«ልክስክስ መሆኔን አውቄዋለሁ›› አለች፡

‹‹ልክስክስ!›› ሲል አሾፈ መርቪን ቃሉ አንሶበት፡፡ ‹‹በጣም የጅል ስራ
ዳያና ባሏ በተናገረው ተሸማቀቀች፡ ብዙ ጊዜ ስድቡ አፏን እንዳዘጋት
ነው፡፡ ዛሬ ግን ከስድብም በላይ ይገባታል፡፡

አስተናጋጇና ጥግ ተቀምጠው መጠጣቸውን የሚኮመኩሙት ሁለት
ሰዎች ሁሉን ነገር ጣጥለው ትእይንቱን በጉጉት ይመለከታሉ፤ ‹‹ምን ይከተል ይሆን?› እያሉ።

መርቪን አስተናጋጇን ጠራና ‹የኔ ቆንጆ ሳንድዊች ብታመጪልኝ›› ሲል አዘዛት እሷም ‹‹እሺ የኔ ጌታ›› አለችው በፍጹም ትህትና፡፡
አስተናጋጆች መርቪንን ይወዱታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ እያስጠላኝ መጥቷል ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው አሜሪካ ለመሄድ የወሰንኩት›› አለች ዳያና፡፡

"ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው ያልሽው! አሜሪካ ጓደኛ የለሽ፣ ዘመድ የለሽ፣ ቤት የለሽ. . .አዕምሮሽ ማሰብ አቆመ እንዴ!›› አለ መርቪን፡፡

ዳያና መርቪን ስለደረሰላት አምላኳን ብታመሰግንም እንዳይጨክንባት
ፈርታለች ማርክ በእጁ ትከሻዋን ነካ አደረገና ‹‹ለምንድነው አሜሪካ ደስታ
የማታገኚው፧ እዚያ ለመሄድ ማሰብሽ ስህተት አይደለም›› አላት ድምጹን
ዝቅ አድርጎ፡፡

መርቪንን ከዚህ በላይ ማናደዱ አስፈርቷታል፡፡ ምናልባትም ትቷት
ተመልሶ ይሄድ ይሆናል፡ በማርክና በሉሉ ቤል ፊት ‹‹አልፈልግሽም›› ብሎ
ቢላት እንዴት እንደሚያበሳጫት መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አያደርግም
አይባልም፡፡ መርቪን ተከትሏት ባይመጣ ጥሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ
እዚሁ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ብርጭቆዋን አነሳችና ከንፈሯን አስነክታ ‹‹ይህን መጠጥ አልፈልግም›› ብላ መልሳ አስቀመጠችው

በዚህ ጊዜ ማርክ ‹‹ሻይ ላምጣልሽ?›› አላት፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_አራት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት.

መርቪንም ‹‹ከእዚያ ማጥ ውስጥ ወጥተው በዓይኔ በብረቱ ማየቴ ደስ
ብሎኛል፡ አዩ ጠፉ ሲባል እኛ ክፉ ነገር ደርሶባቸዋል ብለን ነበር የገመትነው በነገራችን ላይ እኔ መርቪን
ላቭሴይ እባላለሁ›› አላቸው:

‹‹ይሄ ጓደኛዬ ባሮን ጋቦን ይባላል፡ በህይወት እንዳመልጥ የረዳኝ እሱ
ነው አሉ ሃርትማንም።

መርቪንም ሁለቱንም ለስንብት ጨበጠና ‹‹ከዚህ በላይ አልረብሻችሁም
ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የተከሰተው ነገር ገርሟት የሚስቱን እግር በእግር መከታተል ተግባር ለደቂቃዎችም ቢሆን ያዘናጉት ሃርትማን
የተባሉት ሰው ታዋቂ ሰው ሳይሆኑ አይቀርም ስትል አስበችና ‹‹ማናቸው እኒህ ሰው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ካርል ሃርትማን በዓለም ታዋቂው የፊዚክስ ሳይንቲስት›› አላት፡ ‹‹አቶምን ለሁለት ለመሰንጠቅ በሚደረገው ምርምር ላይ የሚሰሩ
ሰው ነበሩ፡፡ ከናዚዎች ጋር የፖለቲካ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ስለነበር
ዓለም በሙሉ ከአፈር ተደባልቀዋል ብሎ ነው የገመተው አላት
‹‹ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ፊዚክስ ነበር የማጠናው፡፡ በዚያ ጊዜ ሳይንቲስት ለመሆን ነበር ምኞቴ፡፡ ግን ለዚህ ዓይነት ስራ ትዕግስት አልነበረኝም: ይሁን እንጂ በዚህ መስክ አልተውኩም፡፡ ታዲያ በዚህ የሳይንስ ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት አስደናቂ የሚደረጉትን ግስጋሴዎች መከታተል
ግኝቶች ተገኝተዋል፡፡››

‹‹ለምሳሌ?›› ስትል ጠየቀች ናንሲ፡

‹‹ሊዝ ሜይትነር የምትባል ኦስትሪያዊት ሳይንቲስት ከናዚዎች አምልጣ
በኮፐንሄገን በስደት የምትኖር ተጠቃሽ ናት፡፡ እሷም በምርምር ስራዋ
የዩራኒየምን አተም ባሪየምና ክሪፕተን ወደተባሉ ትንንሽ አተሞች መከፋፈል
ችላለች፡፡››

‹‹አተሞች የማይከፋፈሉ ነበር የሚመስለኝ›› አለች ናንሲ፡

‹‹እስከቅርብ ጊዜ እኛም እንዲህ ነበር የሚመስለን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ራበሳይንስ ትልቅ ግስጋሴ ተደረገ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው የወታደራዊው መስክ ይህን የሳይንስ ውጤት በእጅጉ የሚፈለገው፡፡ ስለዚህ የዚህን ሂደት መቆጣጠር ከቻሉ በዓለም ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል ያለውን ቦምብ መስራት ቻሉ ማለት ነው፡››

ናንሲ እንደ ቆቅ የሚደነብሩትንና ሰውን ሁሉ በፍርሃት የሚመለከቱትን እኒህን ሰው አንገቷን አዙራ አየት አደረገቻቸው፡፡ ‹‹እንዲህ ያሉ ሰው ያለ ጠባቂ ብቻቸውን እንዲሄዱ እንዴት እንደፈቀዱ የሚገርም ነው!›› አለች።

‹‹ብቻቸውን ናቸው ብዬ አልገምትም›› አለ መርቪን እዚያ ፈንጠር ብሎ የቆመውን ሰው ተመልከቺ፡፡,

የመርቪንን የግምባር ጥቅሻ ተከትላ ከመንገዱ ባሻገር አይኗን አማተረች፡ ሌላ ረጅም ቆብ የደፋና
ሙሉ ልብስ ከነሰደርያው የለበሰ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ተመለከተች፡:

‹‹ይህ ሰው የሳይንቲስቱ ጠባቂ ነው ብለህ ትገምታለህ?››

መርቪን ትከሻውን ነቀነቀና
‹‹ነጭ ለባሽ ይመስላል፡፡ ሃርትማን የሚጠበቁ መሆናቸውን አያውቁም ይሆናል፡፡ ሆኖም ጠባቂ ሳይኖራቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ›› አላት፡

hዚህ ቀደም መርቪን ያን ያክል ነገሮችን ይከታተላል ብላ አትገምትም ነበር፡፡

‹‹ቡና ቤቱ ይሄ ሳይሆን አይቀርም›› አለ መርቪን የውይይታቸውን ርዕስ ለውጦ፡፡ በኋላም በሩጋ ደርሶ ቆመ።

‹‹መልካም ዕድል›› አለችው ናንሲ ከልቧ፡ አናዳጅ ባህሪ ቢኖረውም ሰውየውን እየወደደችው እንደመጣች አሰበች፡፡

ፈገግ አለና ‹‹አመሰግናለሁ ላንቺም መልካም ዕድል እመኝልሻለሁ›› አላትና እሱ ወደ ቡና ቤቱ ሲገባ እሷ መንገዱን ይዛ ነጎደች።

ህንጻው ውስጥ አንድ ወጣት የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኛ ወዳለበት እንደነገሩ የተሰራ ቢሮ አየችና ወደ እሱ ሄደች፡
‹‹ወደ ኒውዮርክ ነው የምሄደው ቲኬት ብትሰጠኝ›› አለች፡
‹‹ቲኬት ፈልገው ነው? አልቋል›› አላት

ናንሲ ለወጣቱ ፈገግ አለችለት፡፡ ፈገግ ማለት የቢሮክራሲውን ማነቆ
ሊያለዝብ የሚችልበት ጊዜ አለ፡፡

‹‹አየህ የኔ ወንድም፤ ቲኬት ማለት ብጣሽ ወረቀት ነው›› አለችው
‹የቲኬቱን ዋጋ ልስጥህና አይሮፕላኑ ላይ ጫነኝ አይመስልህም?››

እሱም በፈገግታ ጥርሱን ብልጭ አደረገ፡ የሚችል ከሆነ እንደሚረዳት
ገመተች፡፡

‹‹አይሮፕላኑ ሙሉ ባይሆን እጭንዎት ነበር›› አላት፡፡

“ምን አይነት ነገር ነው! ስትል አጉተመተመች፡ ሰማይ የተደፋባት መሰላት፡፡ እስካሁን የደከመችው እንዲያው ነው እንዴ! ሆኖም ገና እጇን አልሰጠችም፡፡ በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለባትም፡፡

‹‹አንድ የሆነ ነገር መኖር አለበት›› አለች፡፡ ለመኝታ የሚሆን ቦታ ባይኖርም ግዴለም መቀመጫ ላይ እተኛለሁ፡፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች
ወንበር ቢሆንም ግድ የለኝም››
‹‹የሰራተኛ ወንበር ላይ ተሳፋሪ እንዲቀመጥ አይፈቀድም አንድ ያልተያዘ ቦታ ያለው የሙሽሮች ክፍል ብቻ ነው።
‹‹እሱን ቦታ ትሰጡኛላችሁ?›› ስትል ጠየቀች ተስፋዋ ለምልሞ
‹‹ምን ችግር አለ፤ ዋጋው ስንት እንደሆነ አላውቅም እንጂ››
‹‹እባክህ ጠይቅልኝ›› አለችው አስተዛዝና፡

‹‹ምናልባትም የሁለት መቀመጫ ዋጋ ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ማለትም
ሰባት መቶ ሃምሳ ዶላር የመሄጃ ብቻ፡፡ ምናልባትም ይበልጥ ይሆናል› አላት፡፡

ናንሲ ዋጋው ሰባት ሺ አምስት መቶ ዶላር ቢሆን ግድ የላትም፡፡ ‹‹ባዶ ቼክ እሰጥሃለሁ የፈለከውን ዋጋ መሙላት እንድትችል›› አለች በጉጉት ‹‹ነገ ኒውዮርክ መድረስ የምፈልግበት ብርቱ ጉዳይ አለብኝ›› አለች
የምትሄድበትን ጉዳይ ለመግለጽ ከዚህ የተሻለ አባባል አጥታ፡

‹‹እስቲ ካፒቴኑን ልጠይቅ›› አለ ወጣቱ ‹‹ከኔ ጋር ይምጡ፣ የኔ እመቤት››

ናንሲ የመወሰን ስልጣን የሌለው ሰው ጥረቴን ሁሉ መና ያስቀርብኝ
ይሆን ብላ እየሰጋች ሰውየውን ተከተለችው ምን ምርጫ አላት፡

አንድ ፎቅ ላይ የሚገኝ ቢሮ ውስጥ ገቡ፡፡ ቢሮው ውስጥ ሲጋራ እያጨሱና ቡና እየጠጡ የአየር ጠባይ ሁኔታ ቻርት ይዘው የሚወያዩ ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ የአዘቦት ልብሳቸውን የለበሱ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አሉ፡፡ ወጣቱ ሰራተኛም ናንሲን የአይሮፕላኑ ካፒቴን መርቪን ቤከር ጋ ወስዶ አቀረባት፡

ወጣቱ ሰው ‹‹ካፒቴን ወይዘሮ ሌኔሃን ወደ ኒውዮርክ የሚያስኬደኝ
ብርቱ ጉዳይ ስላለኝ የሙሽሮችን ክፍል ዋጋ ከፍዬም ቢሆን እሄዳለሁ እያሉ ነው፡፡ እንውሰዳቸው?›› ሲል ጠየቀ፡

ናንሲ የካፒቴኑን መልስ በጉጉት ጠበቀች፡፡ ካፒቴኑም ‹‹ወይዘሮ ሌኔሃን
ባለቤትሽ አብሮሽ አለ?›› ሲል ጠየቃት፡

‹‹ባለቤቴ ሞቷል ካፒቴን››
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።ስታልፍ እንድትቆም የእጅ ምልክት ሰጣት በመስታወት አሻግራ
ስታይ ተሳፋሪዎች ወደ አይሮፕላኑ የሚወስዳቸው ጀልባ ላይ ሲወጡ አየች፡፡
ሆኖም መርቪን ቁሚ ስላላት ቆመች፡ መርቪን በስልክ አሁን በዚህ ነገር
አታስቸግረኝ፡፡ ሰራተኞቹ የጠየቁህን ክፈልና ስራው እንዲቀጥል አድርግ›› ሲል አዘዘ፡፡

በመርቪን ፋብሪካ ውስጥ ሰሞኑን የአሰሪና ሰራተኛ ውዝግብ እንደነበር
ነግሯታል፡ ከእሱ ባህሪ በተቃራኒ ሲታይ አሁን ለሰራተኞቹ ጥያቄ እጁን
የሰጠ ይመስላል፡

ስልኩን የደወለው ሰው በመርቪን አነጋገር ሳይደነቅ አይቀርም፡፡
‹‹አዎ እንዳልኩህ አድርግ፤ የምሬን ነው፡፡ ከማንም ቀጥቃጭ ጋር
ለመጨቃጨቅ ጊዜ የለኝም፡ ደህና ሁን›› አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ ከዚያም
‹‹ስፈልግሽ ነበር?›› አላት ናንሲን፡፡

‹‹ተሳካልህ? ባለቤትህ አብሬህ እመጣለሁ አለች?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ገና በቀጥታ እንሂድ አላልኳትም››
‹‹አሁን የት ነው ያለችው?››
በመስኮት አየና ‹‹ያቻትልሽ ቀይ ኮት የለበሰችው››
ናንሲ በእድሜ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ቃጫ የመሰለ ጸጉር
ያላት ሴት አየች፡ ‹‹መርቪን ባለቤትህ በጣም ቆንጆ ናት!›› አለች፡ ናንሲ
በመርቪን ሚስት ቁንጅና ተደንቃለች፡፡ እሷ የገመተቻት እንዲህ አልነበረም፡
‹‹ይህቺ ሴት ከእጅህ እንዳትወጣ ለምን እንደፈለግህ አሁን ገባኝ›› አለች፡ዳያና አንድ ሰማያዊ ሱሪ የለበሰ ሰው ሶቶ ይዛለች፡፡ ማርክ እንደ መርቪን አያምርም፡ ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ፀጉሩ ከግንባሩ እየሸሸ ነው፡፡ ነገር ግን ፎልፎላ እና ተጫዋች ይመስላል ሲያዩት፡፡ ናንሲ የመርቪን ሚስት የባሏን
ተቃራኒ የሆነ ሰው መያዟን አስተዋለች፡፡ ለመርቪን አዘነችለት።
‹‹እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጥህ›› አለችው፡፡

‹‹ገና እጅ አልሰጠሁም›› አለ፡፡ ‹‹ኒውዮርክ ድረስ ተከትያት እሄዳለሁ››
ናንሲ የመርቪን አባባል አሳቃት፡ ‹‹ደግ አደረግክ! ባለቤትህ ማንም ወንድ ልጅ አትላንቲክን አቋርጦ የሚከተላት አይነት ሴት ናት፡››

‹‹የችግሩ መፍትሄ አንቺ እጅ ውስጥ ነው ያለው›› አላት ‹‹አይሮፕላኑ ሞልቷል ቦታ የለም››

‹‹እውነት ነው ታዲያ ኒውዮርክ ድረስ በምን ትሄዳለህ? ደግሞ
ምንድን ነው በእኔ እጅ ውስጥ ያለው መፍትሄ?››
‹‹አንቺ ነሽ ቀሪውን ትርፍ ወንበር የያዝሽው፡፡ የሙሽሮችን ክፍል
መያዝሽን ሰምቻለሁ፡ ትርፏን ወንበር ለኔ ሽጭልኝ››

ናንሲ ከት ብላ ሳቀችና ‹‹የሙሽሮችን ክፍል ከወንድ ጋር መጋራት
አልችልም፡፡ እኔ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንጂ የሆነች ዳንሰኛ አይደለሁም››
‹‹እኔ ግን ማንም ያላደረገልሽን ውለታ አድርጌልሻለሁ›› አላት ፍርጥም ብሎ።
‹‹ውለታህ ሊኖርብኝ ይችላል ክብሬን መሸጥ ግን አልችልም ናንሲ ያለችውን እንዳልተቀበለ ይመሰክራል ‹‹በአይሪሽ ባህር ላይ ከኔ ጋ
ስትበሪ ስለክብርሽ አልተጨነቅሽም››

‹‹እዚያ ላይ እኮ አብረን አላደርንም›› አለች፡፡ ብትረዳው በወደደች
ውቧን ሚስቱን ለማስመለስ ቁርጠኛ መሆኑ ልቧን ነክቷታል፡

‹‹ይቅርታ አድርግልኝ በዚህ እድሜዬ ካንተ ጋር አንድ ክፍል አድሬ የሰው መሳቅያ
መሆን አልፈልግም

‹‹ስለሙሽሮች ክፍል ጠይቄያለሁ። ከሌሎች ክፍሎች የሚለየው ነገር
የለም፡ ባለሁለት አልጋ ነው፡፡ ማታ ማታ በሩን ብንከፍተው ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች ፊት ለፊት የያዟቸው ትይዩ ወንበሮች መሆናቸው ይታያል፡››

‹‹ሰው ምን እንደሚል አስብ መርቪን››

‹‹ለማን ነው የምትጨነቂው? ባል የለሽ? ቤተሰቦችሽ ሞተዋል እዚህ
ለምታደርጊው ነገር ማን ግድ አለው?››

መርቪን አንድ ነገር ከፈለገ ፊት ለፊት ነው የሚናገረው፡
ይቀየመኛል ብሎ አያስብም፡፡

‹‹ሁለት ትልልቅ ወንድ ልጆች አሉኝ›› ስትል አነጋገሩን ተቃወመች።
‹‹ልጆችሽ ይህን ሲሰሙ ቀልድ ነው የሚመስላቸው››
ሊመስላቸው ይችላል አለች በሆዷ ሃዘን እየተሰማት፡ ‹‹እኔን የጨነቀኝ የድፍን ቦስተን ከተማ ሰው ምን እንደሚል ነው፡፡ እኔ ታዋቂ ሴት በመሆኔ ወሬው እንደ ቋያ እሳት በአንዴ ነው የሚዳረሰው››

‹‹ተመልከች! እንግሊዝ አገር እዚያ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ሆነሽ ምን ያህል ተቸግረሽ እንደነበር እንድወስድሽ ምን ያህል ፈልገሽ እንደነበር
አስታውሺ፡፡ ያኔ ከጉድ ነው ያወጣሁሽ፡፡ አሁን በተራዬ እኔ የማልወጣው ችግር ላይ ወድቄያለሁ፡ የኔ ጭንቀት አልገባሽም ማለት ነው?›› አላት

‹‹ይገባኛል››

‹‹ስለዚህ ችግር ላይ ስላለሁ ከጉድ አውጪኝ፡፡ ትዳሬን ለማዳን ያለኝ
የመጨረሻ እድል ይሄ ብቻ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ትችያለሽ፡፡ እኔ በችግርሽ ጊዜ ደርሼልሻለሁ፡ አሁን ብድር የምትመልሽበት ጊዜ መጥቷል።ሰው እንደሆነ አምቶ አምቶ ሲደክመው ይተዋል፡፡ የአንድ ሰሞን ሀሜት ደግሞ ሰውን አይገድልም፡፡››

የአንድ ሰሞን ሀሜቱን አሰበች፡፡ አንዲት የአርባ አመት እድሜ ላይ የምትገኝ ባሏ የሞተባት ሴት በግድ የለሽነት እንዲህ አይነት ነገር ብታደርግ ምን ችግር አለው፡፡ ይህን በማድረጓ አትሞት! መርቪን እንዳለው ክብሯንም አይቀንሰውም፡፡ አሮጊቶች ምነው ቀበጠች› እንደሚሏት ጥርጥር የለውም:፡
የእድሜ እኩዮቼ ግን ድፍረቴን ያደንቃሉ አለች በሃሳቧ የመርቪን የተጎዳና አቋመ ፅኑ ፊት ስታይ ልቧ ከእሱ ጋርሄደ የቦስተን ህዝብ ገደል ይግባ፡፡ ይህ ሰው ችግር ላይ ወድቋል፡ እኔ ተቸግሬ በነበረበት ሰዓት ለችግሬ ደርሷል፡ እኔ ባላመጣሽ ኖሮ ዛሬ እዚህ አትገኝም ነበር› ያለው እውነት ነው።

‹‹ናንሲ የያዝሽው ክፍል ውስጥ ታስገቢኛለሽ? የመጨረሻ ተስፋዬ አንቺ ነሽ"

‹‹አዎ አስገባሀለሁ›› አለች፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሄሪ ማርክስ የመጨረሻ አውሮፓ ትውስታ ለመርከበኞች ምልክት የሚሰጠውን የፓውዛ ማማ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ሞገድ እየመጣ
ሲለትመው ያየው ብቻ ነው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሚታይ መሬት
አልነበረም፧ ዳርቻ ከሌለው ባህር በስተቀር፡፡

አሜሪካ ስገባ ሀብታም እሆናለሁ› ሲል አሰበ፡፡

በሌዲ ኦክሰንፎርድ ሻንጣ ውስጥ የተሸጎጠው ጌጥ የወሲብ ያህል የሚያጓጓ ነው፡፡ ይህ እንቁ በዚህ አይሮፕላን ውስጥ አንድ ቦታ ይገኛል ዕንቁውን በእጁ ለማስገባት ቋምጧል፡

ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ እንቁ ከሌባ እጅ በመቶ ሺህ ብር ይገኛል።በዚህ ገንዘብ ጥሩ መኪና ምናልባትም የቴኒስ መጫወቻ ያለው ቤት እገዛለሁ ወይም ገንዘቡን ኢንቨስት አደርግና በወለዱ ብቻ እኖራለሁ፡ ስራ
ባልሰራ ደልቀቅ ብዬ እኖራለሁ› ሲል ተመኘ፡፡
በመጀመሪያ ግን እንቁውን በእጁ ማድረግ ይኖርበታል፡ ጌጡ በሌዲ ኦክሰንፎርድ አንገት ላይ አይታይም፡ ስለዚህ ሊኖር የሚችለው በእጅ ቦርሳቸው ውስጥ ወይም እዚህ አጠገባቸው ባለው ማስቀመጫ ወይም ደግሞ ሻንጣ የሚቀመጥበት ቦታ እኔ ብሆን ካጠገቤ አለየውም ነበር ከአይኔ ከራቀ እንቅልፍም አይዘኝም› ሲል አሰበ ሄሪ፡

መጀመሪያ የእጅ ቦርሳቸውን ይበረብራል፡ እንዴት እንደሚበረብር ግን
አልመጣለትም፡፡ ምናልባትም የሚሻለው ማታ ሰው ሁሉ ከተኛ በኋላ ነው።
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሰባት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡

‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ››

‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን ሊዋጋ ሄዶ አፈር በልቶ የቀረ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ የእሱን አርማ አንስቼ አላማውን ዳር ለማድረስ እታገላለሁ››ደ አለች በወኔና በሀዘን፡

‹‹ትወጂው ነበር?»

በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡

አይኗ እንባ እንዳቀረረ ተመለከተና በሀዘኔታ ክንዷን ያዝ አደረጋት
‹‹አሁንም ትወጂዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምን ጊዜም ከልቤ አይጠፋም›› አለች የሹክሹክታ ያህል ‹‹ስሙ ኢያን ይባላል፡››

ሄሪ አሳዘነችው፡፡ ማርጋሬትን ደረቱ ውስጥ ወሽቆ ሊያፅናናት
ቢፈልግም በየት በኩል። ውስኪያቸውን እየጨለጡ ጋዜጣ የሚያነቡ በርበሬ
ፊት አባቷ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል፡ እንደ ምንም እጁን ሰደደና አጇን ጨመቅ አደረገው፡፡ እሷም ለማፅናናት መሆኑ ገብቷት
ፈገግ አለች።

‹‹እራት ደርሷል ሚስተር ቫንዴርፖስት›› አለ አስተናጋጁ፡ ሄሪ አስራ
ሁለት ሰዓት ከምኔው እንደደረሰ ገርሞታል፡ ከማርጋሬት ጋር የጀመረውን
ጭውውት ማቋረጡ አሳዝኖታል፡፡ እሷም የእሱ ጭንቀት ገባትና ‹ብዙ
የምንጫወተው ነገር አለ›› አለች ‹‹ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት አብረን
እንሆናለን››

‹‹ልክ ነሽ›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እንደገና እጇን ዳበስ አደረገና ‹‹በኋላ
እንገናኝ›› አላት፡፡

ምስጢሩን በሙሉ የነገራት አጋሩ ሊያደርጋት ነው፡፡

ወደሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ክፍሉ ከሳሎን ቤት ወደ መብል ቤትነት ተለውጦ ሲያይ ተገረመ እያንዳንዳቸው አራት ሰዎች የሚቀመጡባቸው
ሶስት ጠረጴዛዎች የተዘረጉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ትንንሽ ጠረጴዛዎችም ይታያሉ፡፡ የእቃው አደራደር እንደ ምግብ ቤት ሲሆን ጠረጴዛዎቹ ጨርቅ
ለብሰዋል፡፡ በላያቸው ላይ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ስምና ምልክት ያለባቸው ብርጭቆዎች፣ ሰሃኖችና ናፕኪኖች ተቀምጠዋል። የመብል ክፍሉ ግርግዳ የአለም ካርታ ተለጥፎበታል አስተናጋጁ ሄሪን አንድ ሱፍ የለበሰ አጠርና ደልደል ካለ ሰው አጠገብ ወስዶ አስቀመጠው: ሄሪ የሰውዬው አለባበስ አስቀናው፡ ሰውዬው ክራቫት ያደረገ ሲሆን ውድ በሆነ ማያያዣ ጌጥ ከሸሚዙ ጋር አያይዞታል፡ ሄሪ እራሱን አስተዋወቀ፡ ሰውዬውም እጁን ለሰላምታ ዘረጋና ‹ቶም ሉተር እባላለሁ›› አለ፡፡ እጁ ላይ ያለው የወርቅ አምባር ከክራቫት ማያያዣው ጋር ይሄዳል፡፡ ለውድ ጌጣጌጥ ገንዘቡን
መበተን የሚወድ ሰው ማለት ይሄ ነው፡፡

ሄሪ የታጠፈውን ናፕኪን ዘረጋ፡፡ ሉተር አነጋገሩ የአሜሪካዊ ነው።
‹‹ከየት ሀገር ነው የመጣኸው?›› ሲል ሄሪ ጠየቀው ሰውዬውን
‹‹ፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ፧ አንተስ?››
‹‹ፊላደልፊያ›› አለ ሄሪ፡ ፊላደልፊያ የት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያልኖርኩበት ቦታ የለም፡፡ አባቴ የኢንሹራንስ ሰራተኛ
ነበር፡››

ሉተር አንገቱን ነቀነቀ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገም የሰውዬው ዝምተኛነት ለሄሪ ተስማምቶታል፡ ስለአኗኗሩ ሰው እንዲጠይቀው
አይፈልግም: በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው፡
ሁለት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በመጡና ራሳቸውን አስተዋወቁ፡ የበረራዐመሀንዲሱ ኤዲ ዲኪን ትከሻው የሰፋ፣ የደስ ደስ ያለው ፀጉረ ነጭ ሰው
ነው፡ ሁለተኛው ጃክ አሽፎርድ የሚባል ናቪጌተር ነው ፀጉረ ጥቁር ሲሆን
የለበሰው ዩኒፎርም ሄዶበታል።

ሰዎቹ እንደተቀመጡ በሉተርና በመሃንዲሱ መካከል የሆነ ጠብ እንዳለ
ሄሪ አስተዋለ።እራት ቀረበ፤ ሁለቱ የአይሮፕላን ሰራተኞች ኮካ ኮላ ሲመጣላቸው ሄሪ
ነጭ ቪኖ ቀረበለት፡ ቶምሉተር ማርቲኒ አዘዘ
ሄሪ እራት እየበላ ሳ
በአይሮፕላኑ መስኮት እያየ ስለማርጋሬትና ስፔን
ሄዶ ስለቀረው ቦይ ፍሬንዷ ያስባል፡፡ ስለእሱ አሁን ምን ያህል እንደምታስብ ማወቅ ፈለገ፡፡ ከእሷ እድሜ አንጻር አንድ አመት ትንሽ ጊዜ አይደለም፡፡

ጃክ አሽፎርድ ሄሪ በመስኮት እያየ መሆኑን ተገነዘበና ‹‹እስካሁን አየሩ
ጥሩ ስለሆነ እድለኞች ነን›› አለ፡

‹‹ሁልጊዜ እንዴት ነው አየሩ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ

‹‹አንዳንድ ጊዜ ከአየርላንድ እስከ ካናዳ በዝናብ የምንሄድበት ጊዜ አለ፡፡
‹‹አንዳንዴ ደግሞ በረዶና መብረቅ ያጋጥማል፡››

ሄሪ አንድ ጊዜ ያነበበውን አስታወሰና ‹‹በረዶ ከዘነበ ለአይሮፕላኑ አደገኛ አይደለም?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹በተቻለን መጠን ቀዝቃዛው የአየር ንብረት እንዳያገኘን እንጥራለን፡፡ለማንኛውም ተብሎ ግን አይሮፕላኑ ክንፎች ላይ የበረዶ ማቅለጫ ሸራ
ተደርጎለታል፡››

የመጪው የአየር ትንበያ ምን ያመለክታል?››

ጃክ ይህን መልስ ለመስጠት ሲጠራጠር አየና ስለአየሩ ባልጠየቅ ይሻል
ነበር›› ሲል አሰበ፡፡ ‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል››
አለ፡፡

‹‹ይህን ያህል መጥፎ ነው?›› ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹ዶፍ ዝናቡ መሃል ከገባን መጥፎ ነው፡ ሆኖም እኛ ከዶፍ ዝናቡ ራቅ ብለን እንበራለን›› አለ በሰጠው መልስ ብዙም ባለመተማመን፡፡

ቶም ሉተርም ቀጠለና ‹በዶፍ ዝናብ ውስጥ መጓዝ ምን ችግር አለው ሲል ጠየቀ።

ጃክ በዝርዝር አልተናገረም፤ ነገር ግን የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ፣ ቶም ሉተርን ለማስፈራራት ሲል ወደ እሱ እያየ ‹‹ልክ ባልተገራ ፈረስ የሚጋልቡ ይመስል ያነጥራል›› አለ፡

ሉተር ኤዲ ያለውን ሲሰማ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ኤዲ በተሳፋሪው
ፊት አፉ እንዳመጣ በመናገሩ ጃክ ገላመጠው:

ተሳፋሪዎቹ ሁለተኛ ዙር የእንቁራሪት መረቅ መጣላቸው:🤮

አሁን የሚያስተናግዱት ሁለቱ አስተናጋጆች ኒኪና ዴቪ ናቸው፡ ኒኪ ድብልብል ሲሆን ዴቪ ደግሞ ከአፍ የወደቀች ጥሬ ነው የሚያክለው፡፡

ሄሪ ሁለቱም ወንዳገረዶች ሳይሆኑ አይቀሩም› ሲል ገመተ፡ ታዲያ ቅልጥፍናው አስደስቶታል፡፡

ሄሪ በድብቅ እንደተከታተለው የበረራ መሀንዲሱ አዕምሮው በአንድ ነገር የተጠመደ ይመስላል፡፡

‹ሄሪ መሀንዲሱ ባህሪው አኩራፊ አይመስልም፡፡ ሲያዩት ተጫዋችና
ግልፅ ይመስላል› ሲል አሰበና እንዲናገር ለማበረታት ‹‹አንተ ምግብ በምትበላበት ጊዜ የበረራ ምህንድስናውን ስራ ማን ይሰራል?›› ሲል ጠየቀው
‹‹ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ነው›› አለ፡ ‹‹በፈረቃ ነው የምንሰራው፡፡ ጃክና እኔ ከሳውዝ ሃምፕተን በረራ ከጀመርንበት ከቀኑ
ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስለዚህ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት
ላይ እረፍት እናደርጋለን፡፡››

‹‹ካፒቴኑስ?›› ሲል ጠየቀ ቶም ሉተር ሀሳብ ገብቶት።
‹‹እንቅልፍ እንዳይዘው መድሃኒት ይውጣል፡ ከቻለ በተቀመጠበት ትንሽ ያንቀላፋል›› አለ ኤዲ፡ ‹‹ወደኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ስንደርስ
ፓይለቱ ምን አልባት ረጅም እረፍት ያደርጋል፡››

‹‹ስለዚህ በሰማይ በምንበርበት ጊዜ ፓይለቱ ይተኛል ማለት ነው?››
ሲል ጠየቀ ሉተር ሳያስበው ጮክ ብሎ፡

‹‹አዎ›› አለ ኤዲ በፈገግታ:፡ ሉተር ፍርሃት ፍርሃት እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ሄሪ ጨዋታው ሰላማዊ እንደሆነ በማሰብ ‹‹ወደኋላ
የማንመለስበት ሁኔታ ማለት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።

ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡

ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡

ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡

ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡

‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡

ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡

አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡

‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡

እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"

ባሮን ጋቦን ፊታቸው በድንጋጤ አመድ መስሏል ለሎርዱ መልስ ሊሰጡ አሰቡና ትተውት ፊታቸውን ወደ ሃርትማን መለሱ፡
ሆዳቸው እያረረ በፈገግታ አለፉት፡ ነገር ግን እሳቸው ከናዚ ጀርመን አምልጠው የመጡ በመሆናቸው ከዚህ በላይ ብዙ ክፉ ነገር የደረሰባቸው ስለሆነ ይህ ስድብ ለእሳቸው እንደ ምርቃት የሚቆጠር ነው።

ማርጋሬት ባሮን ጋቦንን ተመለከተች፡ ሎርዱ ያሉትን ከምንም ባለመቁጠር ማንኪያቸውን አንስተው ሾርባቸውን መጠጣታቸውን ቢቀጥሉም እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ስላስቸገራቸው ሰደርያቸው ላይ ሾርባው ተንጠባጠበ፡፡ውስጣቸው
የሚንተከተከው ንዴት ግን
መጠጣት ስላላስቻላቸው ማንኪያቸውን አስቀመጡት።

ማርጋሬት የባሮኑ ብስጭት ልቧን ነካው። በአባቷም ስድብ በጣም ተናደደችና ‹‹ድፍን አውሮፓ የሚያከብራቸውን ሁለት ትላልቅ ሰዎች እንደዚህ መሳደብ የለብህም›› አለቻቸው በድፍረት።

‹‹ሁለት የታወቁ ይሁዲዎች በይ›› አሉ አባቷ።

‹‹ይሁዳዊያን አያቴን ረሳሃቸው አባባ?›› አለ ፔርሲ ሁሉን ነገር ቀልድ አድርጎ።

አባት ወደ ልጃቸው ዞሩና ጣታቸውን ፔርሲ ላይ እያወዛወዙ ‹‹እንዲህ
ያለውን የማይረባ ቀልድህን ተወኝ ሰማኸኝ!›› ሲሉ አፈጠጡበት

ፔርሲ ነገሩ ስላላማረው ‹‹መጸዳጃ ቤት ልሂድ አሞኛል›› አለና ትቷቸው ሄደ፡ ማርጋሬት እሷና ፔርሲ አባታቸውን መቃወም እንደሚችሉና ምንም እንደማያመጡ አውቃለች፡ ይህም አንድ እድገት ነው ስትል አሰበች፡

‹‹ከቤታችን አባረው እንድንሰደድ ያደረጉን እነዚህ ሰዎች መሆናቸውን
እንዳትረሺ›› አሏት አባት ማርጋሬትን፡፡ ‹‹ከኛ ጋር የሚሄዱ ከሆነ ስርዓት
መማር አለባቸው›› አሉ፡

‹‹ቃ!›› ሲል ተደመጠ አንድ ድምጽ

ማርጋሬት ድምጹ ወደመጣበት አቅጣጫ ዞረች፡ ይህን ያለው ፎየንስ
ላይ የተሳፈረው መርቪን ላቭሴይ ነው፡፡ መርቪን እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ
የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ ጠረጴዛ ተደግፎ ቆሟል። አስተናጋጆቹ በድንጋጤ
ደርቀው ቆመዋል፡ ጠብ ይነሳል ብለው ፈርተዋል፡ ላቭሴይ የሰማይ ስባሪ
የሚያክል፣ ዕድሜው በአርባዎቹ ውስጥ የሚገመትና ጸጉሩ ገብስማ መልከ መልካም ሰው ነው፡፡ ሲያዩት የሚፈራው ነገር ያለ አይመስልም፡ የለበስው
ልብስ ውድ መሆኑ ያስታውቃል፡

‹‹ይህን አመለካከትህን ለራስህ ያዘው›› አላቸው በሚያስፈራ ድምጽ“

‹‹አንተን አያገባህም!›› አሉ ኦክሰንፎርድ።
‹‹ያገባኛል!››
ማርጋሬት አስተናጋጁ ውልቅ ብሎ ሲሄድ አየችው፡ የአይሮፕላኑን አስተናጋጆች ሊጠራ እንደሄደ ተገንዝባለች፡፡

‹ስለ እኚህ ሰውዬ ምንም አታውቅም፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማን ባንተ አፍ የሚጠሩ ሰው አይደሉም፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ሳይንቲስት ናቸው››
አለ ከመቆርቆር በመነጨ ብርቱ ስሜት፡

‹‹የፈለገውን ቢሆን ግድ የለኝም›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡
‹‹አንተ ግድ ባይኖርህ እኔ ግድ ይኖረኛል፡ ስለዚህ ይህን የከረፋ አስተሳሰብህን አስተካክል›› አለ ላቭሴይ፡

እኔ የፈለኩትን ማለት እችላለሁ›› አሉና ኦክሰንፎርድ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡
ላቭሴይ በጠንካራ እጁ የኦክሰንፎርድን ትከሻ ተጫነና አስቀመጣቸው፡፡
እንዳንተ ካሉ ሰዎች ጋር ነው ጦርነት የገጠምነው›› አለ፡፡

ኦክስንፎርድም በደከመ ድምጽ ‹‹ልቀቀኝ! ልቀቀኝ!›› ሲሉ ተወራጩ።

‹‹አፍህን የምትዘጋ ከሆነ ነው የምለቅህ››

‹ካፒቴኑን እጠራለሁ›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡

‹‹አያስፈልግም!›› አለ ሌላ ድምጽ፡ ካፒቴን ቤከር ሙሉ ዩኒፎርሙን ለብሶ ቆሟል የአዛዥነት መንፈስ ይታይበታል፡ ‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ ብትመለስ?›› አለ፡

‹‹እኔ ወደ ቦታዬ እመለሳለሁ›› አለ ላቭሴይ ‹‹ነገር ግን በመላው
አውሮፓ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው ሳይንቲስት በዚህ ሰካራም ሲሰደቡ
በዝምታ ማለፍ አልችልም፡››

‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ›› አለ ቤከር፡

ላቭሴይ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ወደ ኦክሰንፎርድ ዞር አለና ‹‹ሎርድ ኦክሰንፎርድ የተናገሩት
ነገር አስነዋሪ ነው፡ አንድ ተሳፋሪ ሌላውን ተሳፋሪ መስደብ አይችልም፡››

ማርጋሬት አባቷ የቤከርን ምክር እንዲቀበሉ ብትፈልግም እሳቸው ግን
ጠብ ጠብ እንዳላቸው ነው፡፡

‹‹አንተ ይሁዲ ብዬ ነው የጠራሁት፡፡ ይሁዲነቱን ሊክድ ነው!›› ሲሉ
አምባረቁ፡፡

‹‹አባባ ምነው ዝም ብትል›› ስትል ተቆጣች ማርጋሬት፡

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ማንንም እንዲሳደቡ አልፈቅድም›› አለ ቤከር፡

አባት ስድባቸውን ቀጠሉ ‹‹በይሁዲነቱ ያፍራል እንዴ?›› አሉ፡

ቤከር በቁጣ ገነፈለ፡፡ ‹‹ይሄ የአሜሪካ አይሮፕላን ነው ጌታዬ እኛ ደግሞ ጥብቅ የስነ ምግባር ደንብ እንከተላለን፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎችን መሳደብ
ካላቆሙ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው በሚያርፍበት ቦታ ላይ ለፖሊስ አስረክቦታለሁ፡፡ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም እንዲህ
አይነት ነገር ሲገጥም አየር መንገዱ ህግ የጣሱ ሰዎችን ይከሳል›››

ሎርዱ የክስ ነገር ሲነሳ ፍርሃት ፍርሃት አላቸው፡ የሚመጣውን በመፍራትም አፋቸውን ዘጉ፡፡ ማርጋሬት በእጅጉ በሃፍረት ተሽማቀቀች አባቷን ዝም ለማሰኘት ብዙ ብትጥርም የአባቷ አድራጎት አንገት
አስደፍቷታል ቅሌት ውስጥ የገቡት አባቷ ስለሆኑ::

‹‹ወደ መቀመጫችን እንመለስ›› አሉና አባት ተነሱ ወደ ሚስታቸውም ዞር ብለው ‹‹አንሄድም የኔ ውድ?›› አሏቸው።

ሁሉም ሰው ማርጋሬት ላይ አፈጠጠባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ከየተ መጣ ሳይባል ከመቀመጫዋ ኋላ መጥቶ ወምበሯን ያዝ አደረገላት” ሌዳ ማርጋሬት›› አለ በአክብሮት በመጠኑ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ማርጋሬት በሄሪ አድራጎት ልቧ ተነካ፡፡

እናት ጅንን ብለው ፊታቸው ላይ ምንም የእፍረት ምልክት ሳይታይባቸው ባላቸውን አስከትለው ወጡ፡፡

ሄሪ ለማርጋሬት በጨዋ ደምብ ክንዱን ሲሰጣት ክንዷን ከክንጿ ጋ ቆላለፈች፡፡ ይሄ ትልቅ ነገር ባይሆንም ለእሷ ግን አንድ የሆነ መተማመን ፈጥሮላታል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በእፍረት ቁንጫ አክላ የነበረችው ማርጋሬት በመጨረሻ በሄሪ እርዳታ በክብር ወደ ቦታዋ ተሸኘች፡፡ ከሄሪ ጋ ወደ መቀመጫዋ ስትመለስ ድምጹን አጥፍቶ አምባጓሮውን እንደ ትርኢት
ሲመለከት የነበረው ተሳፋሪ ከኋላ ሲንሾካሽክ ሰማች፡

‹‹አንተ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም›› አለችው
ሄሪን፡፡

‹‹የተፈጠረውን አታካሮ ስመለከት ነበር፡፡ በአባትሽ አድራጎት አንገትሽን
ስትደፊ ሳይ አሳዘንሽኝ፡፡››

‹‹እንደዚህ ቀን በሃፍረት ተሸማቅቄ አላውቅም›› አለች እየተንገፈገፈች

አባቷ ግን አሁንም አደብ አልገዙም፡፡ ‹‹አንድ ቀን ይቅርታ ይጠይቁ ይሆናል እነዚህ ጅሎች!›› አሉ፡ ሚስታቸው አንድ ቃል ሳይተነፍሱ እጥግ
ተቀምጠው ባላቸውን በአግራሞት ያይዋቸዋል፡፡

‹‹ይህ ጦርነት ያበቃና! ምናለ በሉኝ›› አሉ
አባት፡፡
📕ታአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ሁሉም ወደኋላ ግልምጥ እያሉ ከፊት ለፊታቸው ሊመጣ ያለውም እንዳያመልጣቸው እየፈሩ..ይመልሱለት ጀመር‹‹አይ የሆነ የተለየ ፍጡር አይተን ነው››
‹‹ኑ ባካችሁ ነገ ይደርሳል…አንተ ደግሞ አዲሷ ጓደኛህ እኮ ዱንኳንህ አጠገብ ተቀምጣ እየጠበቀችህ ነው››አለው ወደአንድሪው እየተመለከተ፡፡

‹‹የማ የእኔ…ኬድሮን ነች?››

‹‹ስሟን መች ለኔ  ነገረችኝ...ባለንስሯ አፍሪካዊት ልጅ››ሲለው እስከአሁን ከተገረመባት በላይ ይበልጥ እየተገረመና እንደጅል ካሜራውን ደቅኖ በዚህ ሲጠብቃት ቤት ዞር ከጀርባው እንደተገኝች በመደነቅ ካሜራውን እንዳንጠለጠለ ሁሉንም ባሉበት ጥሎ እየሮጠ ወደካንፑ ተመለሰ …ጓደኞቹም በሁኔታው ግራ ተጋብተው እየተሳሳቁና እየተገረሙ በዝግታ እርምጃ ተከተሉት፡፡
߷߷
እንደደረሰ ከጎኗ ዝርፍጥ ብሎ ተቀመጠና ካሜራውን እግሩ ስር አስቀምጦ ዝም ብሎ አቀርቅሮ ማለክለክ ጀመረ
‹‹ከሜራ ደቅነህ የምትጠብቀኝ ቀረጸህ ለአለም ልታሰራጭ ነበር አይደል?››

‹‹እና ገብቶሽ ነው የሸወድሺኝ?››

‹‹አይመስልህም?››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን እንድታውቂው የምፈለገው ፈርቼሻለሁም ወድጄሻለሁም››

‹‹አውቃለሁ›› አለችው፡፡

ሁሉም ተሰበሰበ፣ አካባቢው እየጨለመ መጣ.. ያላቸውን ፋኖስ ለኮሱና የተሰራውን እራት እየበሉ ሁሉም የጋራ የሆነ ጫወታ ሲጫወቱ ቆዩና አራት ሰዓት አካባቢ ሁሉም በእንቅልፍ እየተሸነፈ ተራ በተራ ወደ ድንኳኑ ገባ… 
አንድሪውና ኬድሮን እና ንስሯ ብቻ ቀሩ፡፡ሰማይ ላይ በቅርብ ባለ ኮርኒስ ላይ የተንጠለጠለች የምትመስለው ጨረቃ ብቻ ሳትሆን በዙሪያዋ በተን በተን የተደረጉ የሚመስሉ ልብ ሰንጣቂ ውበት ያላቸው ከዋክብትን  አንጋጠው እየተመለከቱ በራሳቸው ሀሳብ ቁዘማ ውስጥ ገቡ…፡፡

‹‹አሁን ድንኳን ውስጥ ገብተሸ ተኚ.››

‹‹አንተስ…?›

‹‹ችግር የለውም ካንድ ጓደኛዬ ጋር እዳበላለሁ››

‹‹አይ ችግር የለም…እኔ ካልፈለኩ ማንም ወንድ ሊደፍረኝ አይችልም…አብረን ገብተን እንተኛ፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነሽ?››

‹‹በንስሬ  ሙሉ እምነት አለኝ….ጀግናዬ አብረኸን ወደ  ድንኳን ትገባለህ ወይስ የተሻለ ማደሪያ ትፈልጋለህ?››ስትል ወደንስሯ ዞራ ጠየቀችው፡፡

በተተተት ብሎ ካለበት ተነሳና በጨለማ ውስጥ ሰንጥቆ በረረ..

‹‹ሄደብሽ እኮ››› አላት አንድሪው 
‹‹ይሂድ.. ሊያጣብበን ስላልፈለገ ነው…ና ተነስ እንግባ›› ብላ አንድ እጁን ይዛ እየጎተተች ልክ እንደራሷ ድንኳን ይዛው ገባች…..እጁን  በያዘችበት እጇ ከእሱ የሚነሳ የኤሌክትሪክ ሞገድ ወደውስጧ ሲፈስ በደንብ እየታወቃት ነው…የተነጠፈችው ፍራሽ ከአንድ ሜትር የማትበልጥ በመሆኗ ተጣብቆ ከመተኛት ውጭ ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም…..እሷ ደግሞ  ሲፈርድባት ከእናቷ እና ከንስሯ ውጭ ከሌላ ሰው ጋር የመተኛት ምንም አይነት አጋጣሚ ኖሯት አያውቅም፡፡በተለይ ከወንድ ጋር ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኞ ነው፡፡

ስለዚህ ወዲያው ነበር መፍራት ብቻ ሳይሆን መንቀጥቀጥ የጀመረችው፡፡

‹‹ታውቃለህ አይደለህ እሺ ብዬህ ድንኳን ውስጥ መግባት አልነበረብኝም›› አለችው በሚርበተበት ድምፅ..፡፡

‹‹ለምን ?ምን አጠፋሁ?›አላት ግራ በመጋት፡፡

‹‹አይ አንተ ምንም አላጠፋህ እኔ ግን…?››

‹‹አንቺ ምን?››

‹‹ድንግል ነኝ…እርግጥ በእናንተ ባህል ለድንግልና የምትሰጡት ግምትና በእኛ የተለየ ነው፡፡››

‹‹አውቃለሁ…ኢትዬጵያን በአካል ሄጄ ጎብኝቻታለሁ ስልሽ እኮ ልክ እንደአንድ ጎብኚ መልከ ምድሯንና የመስህብ ቦታዎቾን ብቻ ጎብኝቼ ነው የተመለስኩት እያልኩሽ አይደለም…እዛ ለሶስት ወር ነው የቆየሁት ፤በሞያዬ አንትሮፖሎጂስት ነኝ …ለሶስተኛ ዲግሪዬን ማሞያ ጥናቴን ለመስራት ነበር የሄድኩት …በዛም ምክንያት የሀገራችሁን ባህሏንና ታሪኮን በተቻለኝ መጠን ለማጥናትና ለማወቅ እድሉን አግኝቼለሁ.. በዛም የተነሳ የባህል ልዩነቱንም በደንብ እረዳለሁ፡፡››

የድንኳኑ ጣሪያ ላይ ሰክታ የነበረውን አይኖቾን አነሳችና  ከአንገቷ ወደእሱ ዞረች… በተመሰሳይ ሰዓት እሱም ወደእሷ ሲያዞር አፍንጫቸው ቀድሞ ተሳሳመ፡፡ ከእሱ አንደበት የሚወጣው ትንፋሽ ወደእሷ ሲስርግና ከእሷም ወደእሱ ሲመለስ ትንፋሽ ብቻ ሳይሆን ሉጋሙን የሳተ የወሲብ እሳት ነበር ከአንደኛው ወደሌላው እየተላለፈ የነበረው.. ፡፡በጠቅላላ አካለቸው በመሰራጨት ያነዳቸው ጀመረ….አንድሪው በዚህ ጉዳይ ለአመታት የበሰለና የጠነከረ ልምድ አለው….የብዙ ሀገር ዜግነት ያላቸውን ጥቁርም ፈረንጅ፤አረብም ከየአይነቱ በተለያየ ጊዜ በተለያ ሁኔታና መጠን ፍቅርን ተጋርቷል…በፍቅር ወድቋል በፍቅርም ጥሎ ያውቃል…በዚህ የተነሳ እራሱን ልክ እንደኤክስፐርት ነበር የሚቆጥረው…ማረጋገጫ ዲፕሎማ እጁ ላይ ባይኖረውም እንደሁለተኛ ሞያው ነው የሚቆጥረው…….ዛሬ ግን ከጎኑ ያለችው እንግዳና ተአምራዊ ልጅ ‹‹እኔ ልምድ የለኝም ድንግል ነኝ;›› ብላ እየነገረችው..ውስጡ የሚያምነው ግን ተቃራኒውን ነው፡፡
እሱ ራሱ ልምድ አልባ እንደሆነ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ጥልቀት ያለው የፍርሀት  ስሜት እየተሰማው እንደሆነ.... አሁን በሚሰማው ልክ የሚያቃትት የወሲብ ረሀብ ፍፅም ተሰምቶት እንደማያውቅ እርግጠኛ ነው ፡፡እስከመቼ ታግሶ መቆየት እንደሚችል እርግጠኛ አይደለም…ፍቃደኛ ካልሆነችለት ደግሞ በግድ ጉልበት ተጠቅሞ ሊሞክር አይችልም….እንደህ አይነት ድርጊት በህይወቱ በጣም የሚጠየፈው ከመሆኑም በተጨማሪ  ልጅቷም ለዛ አይነት ጥቃት ሽብርክ  የምትል እንዳልሆነች አፍ አውጥታ ነግራዋለች እና አምኗትል….ግን ደግሞ ረሀቡ ልክ የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ሰው  አሁን እሱ ባለበት ከፍታ ላይ ሲገኝ ኦክስጅን አንሶት መሬት ወድቆ እንደሚንፈራፈርና ምን አልባትም እስከ ወዲያኛው ሊዘጋና ሊሞት እንደሚችል እሱም እንደዛ አይነት አደጋ በራሱ ላይ  እንደሚደርስበት አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…ስለአፍሪካ ጠንቋዬች የተወሰነ ታሪክ አንብቧል….‹‹ዋናዋን ጠንቋይ ይሆን እንዴ በአካል ያገኘኋት …?.ቀልቧን አሳርፋብኝ እያደነዘቺኝ  ይሆን እንዴ?››ይሄን ሁሉ ጥያቄ በውስጡ የሚያጉላላው አይኖቹን አይኖቾ ላይ አፍጥጦ..አፍንጫውን ከአፍንጫዋ አጣብቆ ..ከንፈሮቹ እየተንቀጠቀጡ ነው፡፡
እጆቹን በጀርባዋ አሻግሮ ሊያቅፋትና ከንፈሩን ከንፈሮቾ ላይ ሊያጣብቅ በጣም ፈልጓል፤ ቀሚሷን ወደላይ ገልቦ ወይም ከስር ወደላይ ተርትሮ ቀዶ በመጣል መላ ሰውነቷን በግልፅ ማየት ፈልጎል  ፡፡እሱም የለበሰውን ልብስ ብቻ ሳይሆን ከተቻለ ቆዳውንም አውልቆ በመጣል ነፍሱን ከነፍሷ ማዋሀድና ማዋሰብ ነው የፈለገው….. ‹‹ነፍስ ከነፍስ ይዋሰባል እንዴ ?…በራሱ ምኞት ተገረመ ፡፡
የሚገርመው በእሷም በኩል ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነበር….የሚለየው ግን እሷ እታች ብልቷ አካባቢ ባለው ጭኖቾ መካከል የሆነ የሚርመሰመስ ነገር እንደገባባት እየተሰማት ነው፡፡የሚረብሽ የጉንዳን አይነት..ቆንጠጥ ..አከክ .ቦጨቅ የሚያደርግ….እግሮቾን በዘዴ እርስ በርስ ለማፋተግና ከሚበላት ነገር ለመገላገል ሙከራ ብታደርግም ከመባሳጨት ውጭ ምንም የተቀየረ ነገር የለም…..በዚህ ሰዓት ማድረግ የምትፈልገው ብቸኛ ነገር ቢኖር ቀጥታ እጇን ወደታች ሰዳ ቀሚሷን ገልባ  ፓንቷን ወደታች መንቅራ ጥላ አካባቢው እስኪቆስል ማከክ..አዎ ከዛም አልፎ እጣቷን ብልቷ ስንጥቅ ውስጥ ከታ የሚበላት ነገር አደብ እስኪገዛና እዛ ስፍራ የሚነተከተከው ነገር እስኪበርድላት ድረስ ማማሰል አዋ ያን ማድረግ ነው
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_አንድ

#ተከታታይ ልቦለድ

#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ዙሪያቸውን ሲያዩ ነግቷል …ቢያንስ 12 ሰዓት ሆኗል….ሁለቱም ከተጣበቁበት ተላቀው ልብሳቸውን ከየወዳደቀበት በመለቃቀም መልበስ ጀመሩ ..ኬድሮን መጀመሪያ ቀሚሷን አንስታ አጠለቀች….ቀጥሎ ፓንቷን ስታነሳ ቦታው ላይ የተወሰነ የተበታተነ ድንጋዬች በደም ነጠብጣብ ቀልመዋል…አንዱን ድንጋይ አነሳችና  ሱሪውን ለብሶ ጨርሶ ቲሸርቱን በመልበስ ላይ ወደአለው  አንድሪው ተጠጋችና በእጆቹ አስጨበጣችው..  በአካባቢው የተሰበሰቡትን ሰዎችን ከቁብ ሳትቆጥር ጉንጩን ሳመችና አጀቡን ሰንጥቃ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ ወደድንኳኑ  ተመለሰች….ስትደርስ ንስሯ ሻንጣው ላይ ቁጭ ብሎ የትዝብት በመሰለ አስተያየት እየተመከለታት ነበር ..ቶሎ ብላ አገልግሏን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች፡፡  ንስሩን ገፈትራ አስነስታ ሻንጣውንም አነሳች‹‹ጀግናዬ በል ቶሎ እንሂድ ››አለችው ንስሯን፡፡
ጊዜ አላጠፋም….ክንፉን ዘረጋና ወደላይ ከፍ ብሎ አንጠለጠላት..እይታዋን አንድሪውን ጥላ ወደመጣችበት አቅጣጫ ስታማትር እሱ ከፊት እየመራ ሌሎች ከኃላ እየተከተሉት  እሷ ወዳለችበት አቅጣጫ እየሮጠ ነው፡፡በመቶ ሜትር ከፍታ ላይ ሆና እጇን ለስንብት አውለበለበችለት…. ጥላው እንዳትሄድ በእጁም እየተወራጨ በእግሮቹ መሬቱን እየተመተመ፤ በአንደበቱም ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ ተማፀናት…ልቧ ራርቶ ልትመለስ አልቻለችም….ሶስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ስትደርስ ተስፋ ቆርጦ መሬት ላይ ዝርፍጥ አለ…..ከዛ ከእይታው ተሰወረች .፡፡

አምስት ሰዓት አካባቢ ከበረሩ በኃላ ነው ኬንያ ድንበር ሞምባሳ ወደብ  ተጠግቶ ከሚገኝ ኢንዲያና ውቅያኖስ ውስጥ የጣላት፡፡እሱ አገልግሏንና ሻንጣውን ይዞ ወደ ዳር  በረረና ዋኝታ ጨርሳ ሰእስክትመጣ ዛፍ ላይ በመቀመጥ እረፍት በመውሰድ ይጠብቃት ጀመር፡፡

የተለየ ምሽተና የተለየ ለሊት ነበር ያሳለፈችው….እና በወሲብ ወቅት የወራዛውን ላቧን  መሬት ላይ ስትንከባለል በአቧራ የቆሸሸና ሰውነቷን ድንግልናዋን ስታስረክብ  በጭኗ መካከል ተንሻሮ የተንጣበጠበ ደሟን በኢንድያና  ውቅያኖስ ጨዋማ ውሀ እያጠበችውና እያፀዳአቸው ነው……አሁን ትናንት የነበረችውን ኬድሮንን አይደለችም….ሴት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ሌላ የሆነ የተከፈተላት የኃይል በር እንዳለ እየተሰማት ነው…..አንድሪውን ወዳዋለች…..ከእሱ ጋር በፈፀመችው ነገር ምንም አይነት ፀፀት እየተሰማት አይደለም…እንደውም በተቃራኒው የተለየ አይነት እርካታን  የመሞላትና የመባረክ ስሜት ነው እየተሰማት ያለው…..ለምን ተጨማሪ ጊዜ ከእሱ ጋር እዳላሳለፈች አታውቅም…..የማትቆጣጣረው ኃይል በአስቸካይ አካባቢውን ለቃ እንድትወጣ አስገድዷታል…እንጂማ ቢያንስ አንድ ተጨማሪ ቀንና አንድ ተጨማሪ ወሲብ ከአንድሪው ጋር ቢኖራት ፍፅም ደስተኛ ትሆን ነበር፡፡
የሰውነቷንም ሆነ  የሀሳቧንም ቆሻሻ እዛው ኢንዲያና ውቅያኖስ  ላይ ካራገፈች በኃላ ወደወደቡ ዳር ወጥታ  ንስሯ ወዳለበት ቦታ ሄደችና እሱ ባለበት ዛፍ ስር ቁጭ አለች…..ከላይ ካለበት የዛፉ ጫፍ  ሻንጣውን እና አገልግሉን ይዞ በሮ በመውረድ  ከጎኗ አረፈ…..ሻንጣዋን ከፈተችና ሌላ ቀሚሰ በማውጣት የለበሰችውንና የረጠበውን ቀሚስ በማውለቅ ደህናውን ለበሰችና እርጥቡን ጨምቃ የግንዱ ቅርንጫፍ ላይ አሰጣችው፡፡
ከዛ አገልግሉን ወደራሷ አስጠጋችና እናቷ ከቆጠረችላት ገና ግማሹን እንኳን ያልተበላለት ጩኮ ከፈተችና ለመብላት ተዘጋጀች…ንስሯ አፍጥጦ ሲያያት ነበር ‹‹..ወይ ይቅርታ አንተም ለካ እርቦሀል….››ብላ ሄደህ የሚታደን ነገር ፈልገህ  ተመገብ …ታዲያ ከ30 ደቂቃ በላይ እንዳትቆይ….››አለችው

ልክ እንደ ሰው ያለችውን በፅሞና ሰምቶ በአየር ላይ ተንሳፈፈና ሰማዩን ሰንጥቆ ከእይታዋ ተሰወረ…..እሷም ጩኮዋን እየቆረሰች  በኮዳዋ በያዘችው ውሀ እየማገች መመገብ ጀመረች…እስክትጠግብ ከበላች በኃላ .. ግንዱን ተደግፋ  ጋደም ብላ ስለአንድሪው እያሰበች የንስሯን መምጣት እየተጠባበቀች ነው….20 ደቂቃ በኃላ ንስሯ በመንቁሩ የሆነ ቦርሳ ነገር አንጠልጥሎ መጣ ፤ግራ ገባት… ስሯ አረፈ….
‹‹የሚበላ ይዘህ ና አልኩህ እንጂ ቦርሳ አልኩህ?››
እጇ ላይ አስቀመጠላት…..የሚያምር አነስተኛ የእጅ ቦርሳ ነው፡፡ተቀበለችውና ከፈተችው…የሚያብረቀርቁና አይን ላይ ብዙ አይንት ቀላማትን ሚረጩ ሁለት የእጅ መዳፍ ያህል መጠን የሚሆኑ ጌጦች ናቸው››
‹‹ምንድናቸው…?››ንስሯን ጠየቀችው…፡፡
አእምሮውን ከፈተላት…አልማዝ እንደሆነ አወቀች፡፡
‹ከየት አመጣኸው?››
ባህሩ መሀከል …የመርከብ ዘራፊዎች እርስ በርስ እየተገዳደሉ አንድ ሌላውን ሲዘርፍ ከመሀከላቸው ነጥቆ እንዳመጣ ምስሉን በአእምሮዋ ልኮ እንድታውቀው አደረጋት፡፡
‹‹ስንት ያወጣል……?››
‹‹የአንድ ሻንጣ ብር  ምስሉን በእምሮዋ አሳያት……እስከዚህን ዕድሜዋ ድረስ ስለገንዘብ እስባም ሆነ ተጨንቃ አታውቅም…አሁን ግን እልማዙን ስታይ ሆነ ስለሚያወጣው ገንዘብ ንስሯ ሲነግራት የተለየ ስሜት ነው የተሰማት…ምን አልባት ይሄ ሴት ከመሆኟ ገራ በውስጧ በቅሎ ያደገ አዲስ ስሜት ሳይሆን እንደማይቀር ገመተች፡፡ብር  የሚያስገኛቸውን ነገሮች አንድ በአንድ ማጣጣም ቀጣይ ተግባሮ እንደሚሆን አለመች፡፡
‹‹በል አሁን ወደሀገራችን እንሂድ….የእማዬ ቡና ናፍቆኛል››አለችው፡፡
አንጠልጥሎት በአየር ላይ አዋላትና ዞሮ ከጀርባዋ ተጣበቀ..  ከኬንያ ወደ ኢትዬጵያ አቅጣጫውን አስተካክሎ መብረር ጀመረ፡፡

፦፦፦፦ይቀጥላል፦፦፦፦

#ክፍል 22,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሁለት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ይሄ ክስት ከተከሰተ ከ5 ዓመት በኃላ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ለመፈተን ዝግጅት ላይ እያለች  ድንገት እናትዬው በህይወቷ ለሁለተኛ ጊዜ  ክፉኛ ታመመች፡፡ አፋፍሰው ደሎ ሆስፒታል አስገቧት….ወደጎባ ወይም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ትባላለች ብለው ሲጠብቁ ከሶስት ቀን በኃላ ወደቤት መልሳችሁ ውሰዷት የሚል ትዕዛዝ ተሰጣቸው፡፡

ቀጥታ እየተውረገረገች ዶክተሩ ጋ ገባች፡፡

‹‹አቤት ምን ነበር?›

‹‹ስለእናቴ ጉዳይ ነበር››

‹‹ስለእናትሽ ምን?››

ዝልፍልፍ ብላ ደከማለች እኮ ….በህይወትና በሞት መካከል ሆና እየተመለከታችሁ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው...?

ካልቻላቸሁ አልቻልንም ብላችሁ ሪፈር ማለት ነው እንጂ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው….?ግልፅ አልሆነልኝም፡፡››

‹እስኪ ተረጋጋግተሸ ተቀመጪና ላስረደዳሽ..እንደው ስታስቢው ይሄንን ቀደም ተከተል ማናውቅ አድርገሽ ነው ምታስቢን ?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ አጋባችሁኛ››

‹‹ሁኔታውን እኮ ለአያትሽ አስረድቼቸዋለሁ...እሳቸው ቀስ ብለው ያስረዱሻል፡፡››

‹‹እና እናቴ …የእኔ ውዷ እናት …የሌላ አለም ፈጡርን  በፍቅር ጠብ ያደረገችው ተአምረኛዋ እናት እንደቀልድ በአንድ ወር ውስጥ ትሞታለች እያላችሁኝ  ነው?››

‹‹አይ እኛ አይደለም እንደዛ ያልነው.. እናትሽ ያለባቸው በሽታ ያለበት ደረጃ እና አሁን ባለው የሳይንስ ግኝት በሽታውን ለማከም ያለንን አቅም ከግምት በማስገባት ነው፡፡››

‹‹እና በቃ ውሳኔያችሁ እንደዛ ነው?››

‹‹አዝናለሁ…ለእሳቸውም የመጨረሻዎቹን ቀናቶች ወዲህ ወዲያ እያሉ ውጤት ለማይኖረው ነገር ከሚንገላቱ  በቤተሰባቸው እንክብካቤ ውስጥ ሆነው ቢያሳልፉ ይሻላቸዋል፡፡

‹‹እኔ እናቴን ካዳንኳት…ምን ትላለህ?››

‹‹ስለአንቺ የሰማሁትን ለማመን እገደዳለሁ››

‹‹ስለእኔ ምን ሰማህ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹የመላዕክት ዝርያ እንዳለብሽ››

‹‹አይ ያሉህ እንኳን እንደዛ አይደለም…የደቢሎስ ዝርያ አለባት ነው ሊሉህ የሚችሉት፡፡››

‹‹ያው ነው…ዳቢሎስም ሌላ ምንም ሳይሆን መላዐክ ነው…ለዛውም ከዋናዎቹ አንድና ዋነኛው የነበረ.በተወሰነ ያለመግባባት ከእግዚያብር የመኖሪያ ግዛት የተሰደደ…››

‹‹የተናገርከው ከልብህ ስለሆነ አስደስተሀኛል…ለማንኛውም ስለጮህኩብህ ይቅርታ.. እናቴን ወደቤት ወስዳታለሁ...እናም አድናታለሁ።››

‹‹እንግዲህ እንዳልኩሽ ነው….ለማንኛውም እቤት ብቅ እያልኩ አያቸዋለሁ..ድንገተኛ ነገር ተፈጥሮ ከፈለግሺኝም ደውይልኝ› ብሎ ቁጥሩን ሰጣት  ተቀበለችውና አመስግናለሁ ብላ ወጣች፡፡

ወዲያው ነበር እናቷን ይዛ ወደቤት የገባችው፡፡ግርግሩ ጋብ ሲል ወደ እናቷ መኝታ ቀረበችና…በቀናቶቸ በሽታ የሰለሉና የደከሙ እጆቾን በእጆቾ ውስጥ አስገብታ እየዳበሰች፡፡

‹‹ሀርሜ አይዞሽ እኔ ምንም እንድትሆኚ አልፈቅድም››

‹‹ልጄ በዚህ ጉዳይ እንድትጨነቂ አልፈልግም…እንደውም መሄድ እፈልጋለሁ።››ስትል መለሰችላት፡፡
እማ ምን ማለት ነው …እኔን ጥለሽ ወደየት ነው የምትሄጂው…አንቺ ከሌለሽ እኮ እኔም መኖር በጣም ነው የሚከብደኝ …ማን ነው የሚረዳኝ?›

‹‹ልጄ አንቺ የአባትሽ ልጅ ነሽ. .በጣም ጠንካራና የማትሰበሪ ነሽ…እኔ ብሄድ ምን አልባት አባትሽን አገኘው ይሆናል፡፡ምን አልባት መልሰን አንድ ላይ የመሆን እድል እናገኝ ይሆናል፡፡

‹አይ እንደዛ አይሆንም…የእሱ አለምና አንቺ ስትሞቺ የምትሄጂበት ቦታ አንድ መሆኑን በምን እርግጠኛ ሆንሽ? እንዲህ አይነት ቁማርማ እንድትጫወቺ  አልፈቅድም..በይ አሁን ደክሞሻል.. እረፊ .የሆነ ቦታ ደርሼ መጣሁ…››

‹‹ደግሞ ወዴት ልትሄጂ ነው?››

‹‹እማ ደግሞ የሆነ ቦታ አልኩሽ እኮ›ብላ ግንባሯን በመሳም ወጥታ ሄደች.. ግቢውን እንደለቀቀች ከጀርባዋ ንሰሯ እየተምዘገዘገ መጥቶ ተከሻዋ ላይ አረፈ.እርምጃዋን እልገታችም….በሀሳብ እየተብሰለሰለች ቀጥታ ከተማውን ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ነው የሄደችው…እናትና አባቷ ተገናኝተውበት ወደነበረ ልክ እንደቤተመቅደስ እያየች ወደ አደገችበት ቦታ ነው የሄደችው፡፡እንደደረሰች ንስሯ ከትከሻዋ ለቆ ተነሳና በአካበባቢው ካሉት ብዛት ያላቸው ግዙፉ ዛፎች መካከል አንዱ ላይ አረፈ.እሷም ልብሷን አወላልቃ ዛፉ ላይ እስከግማሽ እየተንጠላጠለችና እየተሳበች ወጣችና አስር ሜትር ከፍታ ላይ ከደረሰች በኃላ ዘላ እየተምዘገዘገች ወንዙ ውስጥ ቦጭረቅ ብላ ገባች…ከዛ ወደውስጥ ሰመጠችና  የሆነ ሚስጥራዊ ምርምር እንደሚያካሂድ የባህር ውስጥ አሳሽ ውስጥ ለውስጥ ትንፋሿን ተቆጣጥራ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሰች.፡፡
ግማሽ ለሚሆን ሰዓት ከዋኘች በኃላ የድካም ስሜት ሲሰማት ወጥታ ልብሷን ለበሰች፡፡የመጨናነቅ ስሜቷ አሁን ቀለል ብሏታል…ወደዚህ  ቦታ የምትመጠጣው ለመታደስ ነው.ከአባቷ መንፈስ ጋር ለመገናኘት..እሱ የረገጣቸውን የወንዙን ወለል ለመርገጥ ፤እሱ የተነፈሰባቸውን ቦታዎች እሷም ልትተነፍስባቸውና ከእሱ ጋር ያላትን የመንፈስ መስተጋብር  ለማጎልበት ነው....እናም ደግሞ ምን አልባት አንድ ቀን ቡልቅ ብሎ ከዚህ ከውሀው መሀል በመውጣት ተጠምጥሞ ይስመኛል…በሚል ድብቅ ምኞትም በመጓጓት ነው እንደዛ የምታደረግው;፡
ለባብሳ እንደጨረሰች ‹‹..ጀግናዬ የት ነህ?››ስትል ንስሯን ጠራችው.. እየተምዘገዘገ መጣና ከፊት ለፊቷ ካለ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አረፈ..
‹‹እሺ ና ተከተለኝ።›› ብላው ወደጥቅጥቁ ጫካ ተራመደች…ወደ ውስጥ ጠልቃ ገባችና የምትፈልገው ቦታ ስትደርስ ከዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ቅጠሎችን እየለመለመች መሬት አነጠፈችና እላዩ ላይ ተደላድላ ተቀመጠች…መጥቶ ከጎኗ ተቀመጠ

‹‹እንድናወራ ነው እዚህ የመጣሁት..››

‹‹እየሰማሀኝ ነው አይደል?›

እየሰማት መሆኑን እንድታውቅ አእምሮን ከፈተላት.

‹‹አዎ እንደዛ ነው…እናቴ እንድትድን አፈልጋለሁ።››

‹‹አይቻልም››የሚል መልስ ሰጣት

‹አይ ይቻላል…አንተ የሆነ ተአምር መስራት አያቅትህም ..ከፈለክ ከአባቴ ጋር ተገናኝና እናቴን ማጣት እንደማልፈልግ ንገረው››

‹‹አይቻልም››ፍርጥም ብሎ መለሰላት፡፡

‹‹ኡፍ..እንግዲያው እሷ ከሞተች እኔም መኖር አልፈልግም…. ይሄንን እወቀው››

‹አንቺ ከሞትሽ እኔም አጠፋለሁ››ብሎ ልክ በሞተችበት ቅፅበት እሱ እንዴት ድርቅርቅ ብሎ እንደሚሞትና ከደቂቃዎች በኃላ መላ አካሉ እንደድቄት ተበታትኖ እንደሚበን አሳያት፡፡ እዝን አላች፡፡

እንዲህ የእሱ ህይወት ከእሷ መኖር ጋር እንደተያያዘና ስትሞት ሟች እንደሆነ ፈፅሞ አታውቅም ነበር..እና እንደዛ በመሆኑ በጣም አዘነች…ቢሆንም ግን ሀሳቧን ለመቀየር ምንም እቅድ የላትም.. መልፈስፈስን አልፈለገችም፡፡
"በጣም እወድሀለሁ.. ታውቃለህ አይደል?.ግን ደግሞ እናቴን ከምንም በላይ ፤ከማንም በላይ ነው ምወዳት እና እንዳልኩህ እናቴ ከሞተች እኛም አብረናት እንሞታለን ማለት ነው።››

የመጨረሻ ውሳኔዋን ከምትናገረው ንግግር ሆነ ከውስጧ ልቧን በማንበብ ከተረዳ በኃላ ከጎኗ ብተት ብሎ ተነሳና ሰማይ ጠቀስ ዛፎችን አልፎ በረረ....ቀጥታ ጭጋጋማውን ደመና አልፎ ተሰወረ.. እዛው በተቀመጠችበት ወደላይ አንጋጣ በአይኖቾ ሸኘችውና ወደትካዜዋ ተመለሰች፡፡
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሶስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እዚህ አብሬያቸው ከምኖረው የሰው ልጆች የበለጠ እውቀትና የረቀቀ ጥበብ የሰጣችሁ እሱ መሆኑን ታማናለችሁ ወይ? .በመካከላችሁ ያለው ግንኙነትስ እንዴት ነው ?ማለቴ በእናንተ እና በእግዚያብሄር መካከል…አንድ ጊዜ ስለአንተ ከእማዬ የሰማሁትን ለአንድ ቄስ ብነግራቸው….እነሱ ከእግዚያብሄር ተጣልተው ወደምድር ተወርውረው የነበሩ የመላእክት ዘሮች ናቸው ብለው አስረዱኝ...ወደምድር መጥተው ከሰው ልጆች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም.እነሱ ግን መላውን የሰው ልጅ በከሉት ..ሰላማዊውን ፍጡር ጦር መሳሪያ አሰራርና ጎራዴ አሞረረድ ከዛም አልፎ የጦርነት ጥበብ እና የዘረፋና ግድያ ስልቶችን በማስተማር እርስ  በርስ አጫረሱት ..በስርዓትና ይኖር የነበረውን ግብረሰዶምና ሊዚቢያ አደረጉት..እግዚያብሄር በጥበብና በፍቅር በመፍጠር በምድር የበተናቸውን እንስሳትን አንዱን ከሌላው እያዳቀሉ አስፈሪና አጥፊ ፍጥረታትና መፍጠር ጀመሩ..የጥንቆላና የሞርት ጥበብን ለሰው ልጅ በማስተማር አእምሮውን በከሉት ከዛ አምላክ ተቆጣና የጥፋት ውሀ ላከ ..ምድርንም በውስጦ ያሉትን ከእነሱ ጋር የተባበሩትን ትምህርታቸውንና በጥባቸው የተደሙትን ሁሉ አጠፋ…የሰው  ለጅና እንስሳቱ ለዘር እንዲሆን ጥንድ እየሆነ በኖህ መርከብ ተጠልሎ እንደተረፈ ሁሉ.አነሱም የተወሰኑት የረቀቀ ጥበባቸው በመጠቀም ምድርን ለቀው በመሰደድ በጥፋት ውሀው ሙሉ በሙሉ ከመጥፋት እራሳቸውን ያተረፉ ይመስለኛል ….

እንደምገምተው ከሆነ አሁን አባቴ የምትይውና በሌላ አለም እንደሚኖር ለእናትሽ የነገራት ፍጥረት ከእነሱ አንዱ ነው አሉኝ…..፡፡ከእግዚያብሄር ጋረ የሚያቀያይምሽና ሀይማኖትሽ የሚያስክድሽ ከይሲ ፍጥረት ስለሆነ ቢመጣ እንኳን እንዳትቀርቢው.በስመአብ፤ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት ደጋግመሽ በማማተብ ከስርሽ አባሪው ብለው መከሩኝ ..አልተከራከርኮቸውም ምን አልባት ያሉት እውነት ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡እንኳን ሙለ በመሉ የእናንተ ዘር መሆነን ተችሎ ይቅርና እኔ እራሱ ያንተ ደም በውስጤ ስላለ በውስጤ የሚንቀለቀለው የክፋት ኃይልና የወሲብ ጥማት እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ከቄሱ ጋር ያልተስማማሁበት አንድ ነገር ቢኖር ቢመጣ እንዳትቀርቢው ብለው ያሉኝን ነው..ወይ ብትመጣ እንዴት እንደምጠመጠምብህ ሳስበው እራሱ ውስጤ በደስታ ይነዝራል፡፡

ይቀልዳሉ እንዴ? ሴይጣንም ሆንክ እግዚያሄር አባቴ ነህ…መርጬ አይደለም ካንተ የተፈጠርኩት..
እና ለማለት የፈለኩት እውነትም ቄሱ ያሉኝ ነገር የእውነት ከሆነ በመጀመሪያ በእናንተና በእግዚያሄር መካከል  የነበረውንም አለመጋባባት ምክንያትም የሚያስረዳኝ አካል አላገኘሁም…ስለዚህ ማን ጥፋተኛ ማን ትክክል  እንደሆነ መወሰን አልችልም…ደግሞ እግዚያብሄር ይሳሳታል እንዴ?አቦ እኔ እንጃ …ለማኛውም እስከአሁን የዘበዘብኩትን ሁሉ እርሳውና ለእናቴ እባክህ ምትችለውን አድርግ…›ሀሳቧን ሳትቋጭ ዝናቡ ዣ ብሎ መርገፈ ጀመረ….በትላልቅ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና በርካታ ቁጥቆጦችና ሰርጎ  የሚረግፍ በመሆኑ ዝናቡ ከላይ በሚረግፈው ልክ ሳይሆን በየቅርንጫፎቹ እየተሹለኮለከ በቅጠሎች ላይ  የተንኳለለ ነበር እሷ  ጋር ሚደርሰው፡፡ እሷ  ግን ግድም አልነበራትም…..ቦታም ቀይራ ለመጠለል አልሞከረችም…. ልክ እዛ ደን ውስጥ ዛፎቹ  ስር ተተክላ እንደበቀለች ታዳጊ ችግኝ.. በደስታ ቅርንጫፎቾንና መላ አካሏን ወዲህ ወዲያ እያዋወዘች የሚዘንበውን ዝናብ በፍቅር እንደምትመጥ አይነት እሷም ተመሳሳዩን ነበር ያደረገችው..

ከ20 ደቂቃ በኃላ ዝናቡ  ቢያባራም እየተንኳለለ ከቅርንጫፎቹ ቅጠሎች  የሚንጠባጠበው ውሀ ግን አልተቋረጠም ነበር….ንስሯ እንደአካሄዷ አካባቢውን እየደረማመሰ መጥቶ ከፊት ለፊቷ   አረፈ፤በቅርንጫፎቹ  ውስጥ እየሾለከ ሲመጣ አካሉ ላይ ካረፉበት የውሀ እንክበብሎች በስተቀር ሲሄድ እንደነበረው ፍፅም ደረቅ አካል ነው ያለው፡፡ያው ይሄ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ንስሮች ፀጋ ነው፡ዝናብ ሲዘንብ ደመናውን ሰንጥቀው አልፈው ከበላዩ ይሆኑን ወደታች አዘቅዝቀው በትዝብት ያዩታል..ምድርና በውስጧ ያሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ ግን በሰማይ የሚበሩትን ሌሎች እዋፍቶችም ሳይቀሩ ወደዱም አልወዱም ወይ መሸሸጊያ ዋሻ  ይፈልጋሉ ወይ ደግሞ በዝናቡ ይቀጠቀጣሉ፡፡

‹‹እሺ የት ሄደህ መጣህ?››

እምሮውን ከፈተላት.የሄደበትን ቦታ ሳይሆን እናቷ የምትድንበትን ዘዴ ነው የነገራት፡፡መጀመሪያው መድሀኒት ጨካኝ ነፍስ ያላቸው…ከ7 ሰዎች በላይ የገደሉ የሶስት ሰዎችን አንገት ቆርጦ እናትትሽ ቤት ውስጥ መቅበር ነው›የሚል መልዕክት በእምሮዋ ፃፈላት፡

‹‹ምን  እያልከኝ ነው….እኔ ሰው ልገድል ነው…?ለዛውም አስፈሪና ጭራቅ የሆኑ ሰዎችን?››
‹‹ለዚህ እኮ ነው….የእናትሽን ሞት በፀጋ ተቀበይ የምልሽ››ሲል በእምሮ መለሰላት፡፡

‹‹አንተ ከእናቴ ነጥለህ ብቻዬን ምን ልታደርገኝ  አስበሀል….?ሀዘኔ ያስደስትሀል ማለት ነው..?››

እዕምሮውን በነጭ  ቀለም ሞላው …እንዲህ የሚያደርገው ሲያዝንና በንግግሯ ወይም በድርጊቷ ሲበሳጭ እንደሆነ ታውቃለች፡››

‹‹ይቅርታ ላስከፋህ ፈልጌ አይደለም….በቃ አደርገዋለሁ…ሶስት ሰው ጭንቅላት አይደል፡፡ለዛውም የሶስት ጨካኝና ገዳይ የሆኑ ሰዎች ጭንቅላት… .አረ አደርገዋለሁ ደግሞ ለእናቴ››ስትል ፎከረች፡፡

‹‹እንደዛ ከሆነ በ15 ቀን ውስጥ ጭንቅላቱ ተገኝቶ መቀበር አለበት….ይሄ ጉዳይ በትክክል ከተፈፀመ እናትሽን ለአንድ አመት  በህይወት ያቆያታል፡፡

‹‹ፈክቶና በተስፋ  ተሞልቶ የነበረው ፊቷ በአንዴ ጨለመ››

‹‹ምን ማለት ነው…?እኔ ለእናቴ እኮ መቶ አመት ነው የምመኝላት….ከተቻለም ዘላለም እንድትኖር፡››

‹‹መጀመሪያ ይሄንን ማድረግ ነው የምትችይው ..ከዛ ደግሞ ሌላውን ዕድሜ እናትሽ እንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እናወራለን›››

‹‹ለምን ያኔ ?አሁን አትነግረኝም…ምን ያሰደብቅሀል ?››

‹‹የመጀመሪያው ካልተሳካ ሁለተኛውን ማወቅሽ ምንም እርባን የለውም …..››ብሎ ፍቃዷን ሳይጠብቅ ከአካባቢው ለቆ በረረ…ሆዱ ባዶ ስለሆነ የሚበላ ነገር ለማደን ነው ወደ ደኑ በጥልቀት የገባው….እሷም እንዴት አድርጋ  ጨካኝና ወንጀለኛ   ሰዎችን ጭንቅላት በ3 ቀን ውስጥ ማግኘት እደምተችል እያሰላሰለች ወደቤቷ  ጉዞዋን ቀጠለች፡፡  

ንስሯ ግን ተከትሏት አልሄደም..በተቃራኒው ሰማዩን ሰንጥቆ በረረ…

ይቀጥላል

#ክፍል 24,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_አራት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ለሊት ተኝታ በአልጋዋ በላይ ያለው መስኮት ይቆረቆራል…ባነነችና ማዳመጥ ጀመረች..ደጋግሞ ሲቆረቆር ግራ ገባት..ያለምንም ፍርሀት መስኮቱን በርግዳ ከፈተች… ንስሯ ነው፡፡

‹‹እንዴ ምን እየሰራ…?››ዓረፍተ ነገሩን መጨረስ አልቻለችም…የአንድ ሰው ጭንቅላት በመንቀቁሩ አንጠልጥሎ አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ከአልጋው ፊት ለፊት ያለው  ወለል ላይ ጥሎላት ተመልሶ በሮ ወጣ….ትኩር ብላ አየችው..የተንጨበረረ ፀጉር ..ተጉረጥርጦ ወደ ውጭ የወጣ አይን… በደም የተበከለ የተጎመደ አንገት….አጥወለወላትና አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች…ምን አይነት ተአምር ነው..?ስትል አሰበች፡፡ ይህንን ነገር እራሷ ልታደርገው ትናንትና ወስና ነበር...አሁን ግን እንዳሰበችው ቀላል ስራ እንዳልነበረ ገባት…እርግጥ አሁንም ገና ሁለት የሚቆረጥ ጭንቅላት ይቀራታል….ግን እንዴት አድርጋ ነው የሰውን አንገት እንዲህ ምትከትፈው? ለነገሩ ከባድ ሆኖ የታየኝ ሰው የመሆን ዲኤን.ኤ በውስጤ ስላለ ሳይሆን አይቀርም…?ግን ነው እንዴ? በዚህ ጉዳይ ሰው ከሌላው ከማንኛውም ፍጡር በላይ ገዳይ አራጅ አይደለምን?የሚል ጥያቄ መጣባት.. 
ከሀሳቧ ሳትወጣ እግሯ ስር …ዷ ብሎ የወደቀ ነገር ተሰማተና ነቃ ብላ ትኩረቷን ሰበሰበች… ቀኝ እግሯ ስር አንድ ከአንገቱ የተቆረጠ ሰው በግራ እግሯ  ደግሞ ሌላ ጭንቅላት ቀደም ብሎ ደግሞ የመጣው ትንሽ ከእሷ ራቅ ብሎ በአጠቃላይ በዛች ትንሸ መኝታ ቤት  አንገታቸው የተቆረጠና ጭንቅላቻው ብቻ የቀረ ሶስት ሰዎች ተረፍርፈዋል፡፡ የንስሯ መንቁሩ በደም ተጨማልቆ በኩራትና በልበ ሙሉነት አፍጥጦ እያያት ነው፡፡

‹‹ምንድነው የሰራሀው?››

‹‹ልፋትሽን አቃለልኩልሽ››

‹‹እነዚህን ሁሉ በአንድ ቀን ከየት አገኘሀቸው?››

‹‹ምን ደግሞ ወንጀልና ገዳይ በበዛበት ሀገር ሶስት ሰዎች ማግኘት ይከብዳል?››

‹‹አሁን እነዚህ.. በተለይ እኚ ሁለቱ እንኳን ሰው ዶሮ ለሚስታቸው አርደው ያውቃሉ….እንዴ ይህቺኛዋ ደግሞ  ሴት ነች እንዴ?››

‹‹አዎ ሁለት ወንድሞቾን ጨምሮ  10 ሰዎችን በመርዝ ገድላለች፡፡››

‹‹ምን ለማግኘት?››

‹ብር ነዋ ሀብታም ለመሆን…ለውርስ ብላ››

‹‹ይገርማል..››

‹‹አሁን መገረምሽን አቁሚና እነዚህን ሶስት ጭንቅላቶች እናትሽ አልጋ ስር ቅበሪያቸው››

‹እንዴት አድርጌ ?››

‹‹ይህቺማ ቀላል ስራ ነች..ለማንኛውም ይንጋ…አሁን ተመልሰሽ ተኚ.. እኔም እነዚህን ጨካኞች ሳድን ድክም ብሎኛል አላት…

‹‹ውይ እውነትህን ነው የእኔ ጀግና ..ና አለችና በደም  የጨቀየውን መንቁሩን ታጥቦና ተጣጥፎ በተቀመጠው ነጭ ፎጣዋ  ጠራርጋ አፀዳችለትና ወደአልጋው እንዲሄድ አድርገ መስኮቱን በመዝጋት እሷም ወደአልጋዋ በማምራት ወደ ላይ ወጣች. ብርድልብሱን ለበሰችና ንስሯንም አለበሰችው፡፡ከዛ ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳት፡
ጥዋት ሳሎን ቤተሰቦቾ ሲንጫጩ ነው ከእንቅልፏ የባነነችው..ከጎኗ ንስሯ እንደተኛ ነው…በርግጋ ተነሳችና ከአልጋ ላይ ወርዳ ቆመች.. ወለሉ ቅንጣት የደም ጠብታ የሌለው ንፅህ ከመሆኑም በላይ  ባዶ ነው….ምንም ጭንቅላት የለም፡፡
ንስሯ ተነስቶ እያያት ነበር..

‹‹ምን ተፈጠረ ጭንቅላቶቹስ ?››
ምንም መልስ ላለመስጠት አእምሮውን ዘጋባት

‹‹መልስልኝ እንጂ››ልክ በባሏ ተግባር እንደተበሳጨች ጮሂ ሚስት አንቧረቀችበት፡፡

ንስሩ ግን ዝም

‹‹ቀበርካቸው እንዴ…?››

አሁንም እምሮውን እደቆለፈ ነው፡
በራ ክፍሏን ለቃ ወጣችና እናቷ ወደተኛችበት ክፍል አመራች፡፡
ባልተረጋጋ ስሜትና በተንቀዠቀዠ አነጋገር‹‹ሀርሜ እንዴት አደርሽ?;››አለች

‹ሰላም ነኝ ልጄ.አንቺ ደህና ነሽ ?ምነው የደነገጥሽ ትመስያለሽ?››

‹‹አይ ደህና ነኝ…ንስሬ እዚህ አንቺ ጋር መጥቶ ነበረ..?››

‹‹የት እዚህ.. አረ አልመጣም››

‹‹ከክፍልሽ ወጥተሸ ነበረ…››

‹‹እንዴ ምን ነክቶሻል? እንዴት ብዬ ወጣለሁ…?››

‹‹አይ ማለቴ እንቅልፍ ወስዶሽ መጥቶ ሄዶ ከሆነ ብዬ ነው…››

‹‹አረ ተረጋጊ ለሊት አንቺ ከዚህ ከሄደሸ ጀምሮ እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም እና ንስርሽም እልመጣም…ምን አልባት አደን ሄዶ እንዳይሆን?››

‹‹አይ አልሄደም… እሱማ እኔ ክፍል ነው ያለው››

የልጅቷ ቅብዥርዥር ያለ ወሬ ግራ ስላጋባት ‹‹ልጄ ግን ደህና ነሽ?ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ደህና ነኝ ሀርሜ… ››አለችና በርክ ብላ አንገቷን በመድፋት አልጋ ስር ገባችና ወሉን ማየት ጀመረች …ምንም የተቆፈረ …ምንም የተነካካ ነገር የለም…?››

‹‹መጣው እናቴ…ሰላም ነኝ አታስቢ›› ብላ ወደክፍሏ ተመለሰች..ንስሯ አሁንም አልጋው ላይ ተኮፍሶ እንደተቀመጠ ነው፡፡
እንደገባች ‹‹ለምን ታበሳጨኛለህ ?አለችው የእውነትም ተበሳጭታ፡፡

አእምሮውን ከፈተላትና እንድትረጋጋ ወደእምሮዋ መልዕክት አስተላለፈላት

‹‹ዝም ብዬ እንዴት እረጋጋለሁ…?ምንድነው የሆነው…?ለሊት የሶስት ሰዎች አንገት ቆርጠህ አምጥተህልኝ ነበር..እንደውም መንቁርህ በደም ተነክሮ በምወደው ነጭ ፎጣ ነው የጠራረኩልህ .››አለችና በደም የተበከለውን ፎጣ ስታስታውስ  ፎጣው ወደተቀመጠበት ጠረጴዛ ስትሄድ እንደተጣጠፈና  ግራ እንደመጋባት ብላ አነሳችና ፈታችው… ምንም የደም ጠብታ የለበትም… ከትናንት ወዲያ አጥባ አጣጥፋ እንዳስቀመጠችው ነው…‹‹.እንዴ ህልም ነበር እንዴ?››ብላ ግራ በመጋባት አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ይሄ የአንተ እና የአባቴ ስራ ነው አይደል….?በል አሁን ተዘጋጅ የሚገደል ሰው ፍለጋ እንሄዳለን… ምን ያህል ቀን እንደሚፈጅብን አላውቅም››አለችው፡
በንስሩ የአእምሮ ሰሌዳ ላይ አያስፈልግም የሚል መልእክት አነበበች፡፡

‹‹እንዴት የእናቴ ህይወት እኮ ነው…?››

‹‹እኮ በሌለ መንገድ አንድ አመት እንድትታገኝ ማድረግ ተችሏል ..በሶስት ቀን ውስጥ ድና ትነሳለች፡፡››

‹‹እውነትህን ነው?››

‹‹እውነቴን እንደሆነ ታውቂያለሽ›› አላት፡፡

በደስታ አቀፈችውና እየሳመች ወደእናቷ ክፍል ይዛው ሄደች፤እናትዬው ከቅድሙ ሁኔታዋ በተቃራኒ እየሳቀችና እየፈነደቀች ንስሯን አቅፋ ሰታገኛት ተደሰተች‹‹ልጄ ከመቼው ወደ ፈንጠዝያ ገባሽ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹እማ በጣም ደስ ብሎኛል…ለምን መሰለሽ? አንቺ ስለምትድኚልኝ.››
‹‹አይ ልጄ ..ብዙም ተስፋ አታድርጊ››

    ይቀጥላል

#ክፍል 25,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ታአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_አምስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ነገርኩሽ እኮ… ዛሬ እሮብ ነው አይደል እስከቅዳሜ አልጋሽን ለቀሽ ያልደረሻቸውን ለቅሶዋችና የታመሙ ወዳጆችሽን እየዞርሽ ትጠይቂያለሽ…››

‹‹እንደአፍሽ ያድርገው››

‹‹እማ እኔ እንዲህ በቁም ነገር ተናግሬ ያልሆነ ነገር አለ…ደግሞ ጀግናዬ ነው መልዕክቱን የነገረኝ…ምን አልባት መድሀኒቱን አባቴ ማለቴ  የድሮ ፍቅረኛሽ ይሆናል በሚስጥራዊ መንገድ  በእሱ በኩል የላከልሽ››

እናትዬዋ በንግግሯ ባለመደሰት ኮስተር ብላ‹‹አባትሽ የድሮ ፍቅረኛዬ ሳይሆን ….የዘላለም ፍቅረኛዬ ነው።››አለቻት፡፡

"እሺ ይሁንልሽ…አሁን ቻው ያዶት ልንሄድ  ነው…ደስ ስላለኝ በዚህ በጥዋት ሂጄ መዋኘት እፈልጋለሁ።››

‹‹እንዴ ቁርስ አፍሽ ላይ ጣል ሳታደርጊ?››

‹‹አይ ስመለስ››ብላ ንስሯን እንዳቀፈች ከቤት ወጣችና ግቢውንም ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ጀግናዬ ስላደረጋችሁት ነገር በጣም አመስግናለሁ...ማለት አንተና አባቴ….ቃል በገባሁት መሰረት የዘላለም ውለታችሁ አለብኝ...ግን እናቴ ከአመት በኃላ ቀጣይ ዕድሜ እንዲኖራትስ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ…? መቼስ ከባድ ነገር ነው የሚጠበቅብኝ?››

‹‹አይ ቀላል ነው››

‹‹ቀላል ነው ስትል? 

‹ከእናትሽ ጋር መኖር ማቆምሽ ለእሷ ተጨማሪ ዕድሜ ይሰጣታል፡፡

አንቺ ከተፈጥሮሽ የተነሳ ፍቅርሽ እሷን ለመኖር ያላትን ኃይል ይመጣል….አንቺ ስትወጂም ሆነ ስትጠይ እኩል ነው ሰውን ምትጎጂው….በፍቅርም ሆነ በጥላቻ የተለየ ትኩረት ያሳረፍሽበት ማንኛውንም የሰው ልጅ ኃይሉን ነው ምትመጪበት… ያ ኃይል ደግሞ ከዕድሜው ላይ ይጎመዳል..ምን አልባት እናትሽ አንድ ቀን ከአንቺ ጋር ለማሳለፍ ከእድሜዋ ላይ ሀያ ሰላሳ ቀን መገበር ይጠበቅባት ይሆናል…"
የምትሰማውን ዜና ተቋቁማ ወደፊት መቀጠል አልቻለችም …ከመንገድ ጎራ ብላ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባችና የተደላደለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠች… ንስሯን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠችው…. ከንፈር የማይንቀሳቀስበት ፤አፍ ማይከፈትበት ድምፅ አልባ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹.እና አሁን ከእናቴ አልለይም የሆነው ይሁን የምትይ ከሆነ አንድ አመቱን ከእሷ ጋር አሪፍ የምትይውን የደስታ ጊዜ አሳልፊ…አይ እናቴ አርባ ሀምሳ አመት መኖር አለባት የምትይ ከሆነ ግን ዛሬ ነገ ሳትይ ይሄን ሀገር ለቀን መሄድ አለብን፡፡››

‹‹ግን እናቴን ምን እላታለሁ?››
‹‹እውነቱን ንገሪያት..እርግጥ አትስማማም…ግን ቢሆንም ንገሪያትና አንቺ ውሳኔውን ወስኚ።››

‹‹ቆይ ብዋሻትስ?››

‹‹ምን ብለሽ?››

‹‹ለምሳሌ እኔ አብሬአት መኖር ምቀጥል ከሆነ በሽታው ወደእኔ ተላልፎ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደምሞት እንዳወቅኩ ብነግራት የእኔን መሞት ማሰብም ስለማትፈልግ በፍጥነት የምትስማማ ይመስለኛል›"
ላቀረበችው ሀሳብ ከአእምሮው የድጋፍ ወይም የተቃውሞ መልስ ለማንበብ ስትጠብቅ….እሱ በተለየ ብርሀን የደመቁ አይነት ቀለማትን ረጨ.እንዲህ የሚያደረገው በነገሮች ሲደነቅ ወይም ሲደሰት እንደሆነ ታውቃለች፡፡

‹‹ምነው የማይረባ ሀሳብ ነው እንዴ?››

‹‹አረ አባትሽም እንዲህ  አይነት ሸር በዚህ ፍጥነት ማሰብ መቻሉን ስለተጠራጠርኩ አድንቄሽ ነው..››

‹ዲቃላ መሆን ጥቅሙ እኮ ይሄ ነው…ግን አሁን የት ነው የምንሄደው ..ማለቴ የት ሀገር ብንኖር ይሻላል?፡፡››

‹‹ደስ ያለሽ ቦታ..ደስ ያለሽ ሀገር››

‹‹ምን ሰርተን ነው የምንኖረው…ትምህርቴን ገና የ10 ክፍል ማትሪክ እንኳን አልተፈተንኩ..ከብት ከማርባት እና እትክልቶችን ከመንከባከብ ውጭ ምንም ሌላ ማውቀው ሞያ የለኝም››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ አንቺ እኮ ማንኛውንም ሞያ ለመልመድ ከሌላው የሰው ልጅ በመቶ እጥፍ በላይ አቅም ነው ያለሽ....በዛ ላይ ታንዛኒያ የሄድን ጊዜ ኬኒያ ድንበር ያገኘነውን ዳይመንድ አለን....በጣም ሀብታም ነሽ እኮ››

‹‹ማለት አባቴ የሌላ አለም ፍጡር ስለሆነ?››

‹‹አዎ ለሰው ልጆች ጥበብ እና እውቀትን ያስተማሩት እኮ አባትሽ እና ከእሱ ጋር ከገነት የወደቁት ጭምር ናቸው››

‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው ማለት ነው?››

"አዎ..በከፊል እውነት ነው››
‹‹በከፊል ስትል.ከፊሉስ እውነት?››

‹እሱን ሌላ ጊዜ..እንድነግርሽ ሲፈቀድልኝ?››

‹‹እንዳልክ …ግን የአባቴ ዘመዶች ለሰው ልጆች ያሰተማሯቸው ዕውቀትንና ጥበብን ብቻ ነው …?››

‹‹አይ እሱማ ክፋትና ተንኮልን…ግድያንና ዘረፋንም ጭምር አስተምረዋል፡፤››

‹‹እና የሰው ልጅ ባለውለታ ናቸው ነው የሚባለው ወይስ ጠላት?››

‹‹አይ እኔ ምለው ማንም ቢሆን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ለማግኘት መክፈል ሚገባው ክፍያ አለ…አባትሽና ወገኖቹ ለሰው ልጆች ያበረከቱት ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ከሰው ልጆችም የነጠቁት መልካምነቶች አሉ››

‹‹ሳስበው ሳስበው የሰው ልጅ ግን ውለታ ቢስ እኮ ነው፡፡

በየቤተክርስቲያኑም ሆነ መስጊዱ ምሰማው የክፋት ሁሉ ምንጭ ሰይጣን እንደሆነ ጥበብና እውቀትን ደግሞ እግዚያብሄር እንዳስተማራቸው  ነው የሚያወሩት››
መልስ ብትጠብቅም ምንም አልመለሰላትም. እዕምሮዋን ዘጋባት

‹‹ምነው? አንተም እግዚያብሄርን ትፈራዋለህ እንዴ?›

አሁንም የተቀየረ ነገር የለም..ለንግግሯ ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት እምሮውን እንደቆለፈ በዛው ገፋበት…ተደነቀች፡፡

‹‹የኃያላን  ኃያል ፤ የጌቶች ሁሉ ጌታ እሱ እግዚያብሄር ነው..የሚል ስብከት መስማቷን አስታወሰችና መልሳ በልቧ አኖረችው…
ሄዶ ሄዶ የሁሉ  ነገር ማሰሪያና የኃይሎች ሁሉ ጥቅል ኃይል እግዚያብሄር ከሆነ ታዲያ የእነ አባቴ ቀድሞ መንፈራገጥ ለምን ይሆን ?ብላ እራሷን ጠየቀችና  ..መልሳ ሌላውን ጥያቄ ተወችና 
‹‹ በል ተነስ እንሂድ.. ወደየት ሀገር እንደምንሄድ አስብበት.››ብላ መንገዷን ስትቀጥል እሱ ክንፍን አማቶና በአየር ላይ ተርገፍግፎ እሷን በመተው በተቃራኒው ወደ ደኑ ውስጥ ገባ..‹‹እርቧሀል ማለት ነው ?››ብላ እሷ ለመዋኘት ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

    ይቀጥላል

#ክፍል 26,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከሶስት አመት በኃላ..
እናትዬውን አሳምና ከደሎ ለቃ ስትወጣ  አንድ ሻንጣ ልብሷን ይዛ በትራንስፖርት ሳይሆን በንስሯ አማካይነት እየበረረች ነበር የተጓዘችው..በእጇ እናቷ ያስጨበጠቻትን 2000 ሺ ብር እና አጎቷ የሰጣትን 5 ሺ ብር .. በቃ ይሄንን ነው የያዘችው፡፡ግን ሻንጣዋ ውስጥ ከአመታት በፊት ኪኒማጀሮን ለመጓብኘት በሄደች ጊዜ ንስሯ ከባህር ወንበዴዎች ነጥቆ የሰጣት ዳይመንድ እንደቀልድ እንዳስቀመጠችው ስለነበረ ይዛው ነበር.። አዲስ አበባ እንደገቡ በደላላ 45 ሚሊዬን ብር ተሸጠ.
በ25 ሚሊዬን ብር  ለገጣፎ ከተማ አካባቢ ምታርፍበት የራሷ የሆነ  2ሺ ካ.ሬ ሜትር  ግቢ ላይ ጥጉን ይዞ የታነፀ ባለአምስት ክፍል   ቢላ ቤት  ገዝታ ከንስሯ ጋር የብቸኝነት ኑሮ መኖር ጀመረች፡፡
እንደመጣች ሰሞን ብቸኝነቱ በጣም ከብዷት ነበር.. የምታውቀው ሰው በዙያዋ ካለመኖሩም በተጨማሪ ከደንና ጫካ ውስጥ ወጥቶ በፎቅና በመኪና የታጠረ አካባቢ መኖር በጣም ሚረብሽ ሆኖባት ነበር…ቆይቶ ግን እየለመደችው መጣች፡የገዛችውንም ጊቢ እንደምትፈልገው አደረገችው….እነሆ አሁን ከሶስት አመት በኃላ ከቤቱ ይልቅ በግቢ ውስጥ ያሉ ዛፎች ዕጻዋቶች እና ፍራፍሬዎች ይበልጥ ያስደምማሉ፡፡ በግቢዋ ውስጥ ከ1140 በላይ የዕፅዋት አይነቶች ይገኛሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ 83ቱን ከተለያዩ አህጉራት በዞረችባቸው ወቅት ቀልቧን ስበውት ወይም አስደምመዋት አምጥታ የተከለቻቸው ናቸው፡፡እርግጥ  አምጥታ የተከለቻቸው ከዚህ አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነበር..ከአዲስ አበባ የአየር ፀባይ ጋር ተላምደው  መጽደቅ የቻሉት ግን እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡
ግቢዋ ውስጥ ያሉ ዕጽዋቶች ሁሉ አስደማሚነታቸው ለአይን መስብ ከመሆናቸው እና ንጽህ አየር ሚያመርቱ መንፈሳዊ ማሽኖች ስለሆኑ ብቻ አይደለም እዚህ ግቢ የመትከል ተተክሎም የመብቀል እድል ያገኙት…እያንዳንዱ የተለየ ሚስጥር እና ጥበብ የሚገለጽባቸው የእግዚያብሄርን  ሚስጥራዊ ሹክሹክታ በቅጠሎቻቸው እና በስሮቻቸው ነስለሚተነፍሱ ነው…::መድሀኒት ናቸው… ታአምራትን የሚሰራባቸው ናቸው..ብዙ ብዙ ነገር…በየዛፎች ቅርንጫፍች ላይ ቁጥራቸውን የማይታወቅ የወፍ ጎጆዎች ሞልተውባቸዋል፤ሶስት ጉሬዛ እና አራት ዝንጀሮዎችም አሏት ..ሁሉንም ያመጣቻው ከሀገሯ ጫካ ነው… ከደሎ መና፡፡እንደዛ ያደረገችው..ልጅነቷን ስለሚያስታውሷት ነው.እንደዛ ያደረገችው..አብራቸው እነሱን እያየች ከእነሱ እየተጫወተች ስላደገች ዘመዷቾ ስለሚመስሏት ነው… ስለምትወዳቸውና ከእነሱ ውጭ ህይወት ስለማይታያት ነው.. ስለምትወዳቸውና የሚወዷትም ስለሚመስላት ነው፡፡
አብረዋት የሚኖሩ አንድ የስልሳ ሁለት አመት አዛውንት ሰውዬ አሉ፡፡ጋሽ ተክለወልድ ይማም ይባላሉ፡፡ይሄንን ጊቢ እንዲህ ያሳመረችውም የምታስተዳድረውም ከእሳቸው ጋር ነው፡፡

እሷ ያው አብዝታ ከአንድ የምድር ጫፍ ወደሌላው መስፈንጠር የዘወትር ድርጊቷ ስለሆነ በሌለችበት ጊዜ እሳቸው ናቸው ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስዱላት፡፡ ዘበኛ  ወይም አትክልተኛ አይደሉም፡፡ከዕጽዋቶች ጋር በፍቅር የወደቁ ከሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ለ32 ዓመት ያስተማሩና በቅርቡ ጡረታ የወጡ የዕጽዋት ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

ሌላው  በዋናነት ለብቸኝነቷ መድሀኒት የሆናት  ንስሯ ነው ፡፡ የንስሯ እና የእሷ ግንኙነት ለሌላ ሰው ለማስረዳት ቀላል መንገድ የለም፡፡ እያንዳንዱ የሰው ልጅ እንዲጠብቀው እንዲንከባከበው እና ከክፉ ነገር እንዲከልለው ከፈጣሪው የተመደበለት ጠባቂ መልዐክ አለው ተብሎ በአብዛኛው ሰው ይታመናል፡፡ግን እነዚህ ጠባቂ መላዕክቶች አካል አልባ መንፈስ ናቸው ፡፡አይታዩም፤መታየት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰውም ጠባቂ መልአኩን በትከሻው ላይ ተሸክሞ እንደሚዞር አያውቅም… አያምንምም፡፡ስለዚህ አይገለገልባቸውም …አያዳምጣቸውም፡፡ሰው በጨለማ ውስጥ ሲጓዝ ማጅራት መቺ ከኃላው ካለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይሰማ ትከሻዬን ከበደኝ ይላል፤ያ ምን  ማለት ነው? ለሚያምንበት ሰው ጠባቂ መላዕክ የማስጠንቂያ ደውል ነው…. እሱ ያልተመለከተውን በጭለማ ውስጥ የተሸሸገውን  አጥቂውን ጠባቂ መልአኩ አይቶት ሹክ ብሎታል ማለት ነው፡፡እንግዲህ ያ ሰው ብልህ ከሆነ ማድረግ ያለበት መልዕክቱን አምኖ ተፈትልኮ በመሮጥ ማምለጥ ወይም ጥቃቱን ለመመከት እራሱን ማዘጋጀት ነው፡፡አይ ዝም ብሎ ተራ ፍራቻ ነው ብሎ የደረሰውን መልዕክት ችላ ብሎ በእንዝላልነቱ ከገፋበት ግን ማጃራቱን  ተመቶ  ይዘረራልም..ይዘረፋልም ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

እና ለእሷ ይሄ ንስር አሞራ ጠባቂ መላዕኳ በሉት፡፡በአካል አብሯት የሚንቀሳቀስ የሚያወራት የምታወራው ጠባቂ መልአክ ስላለት፡፡የፈለገችበት የአለም ጥግ አንጠልጥሎ የሚወስዳት...ከሚንቀለቀል እቶን እሳት ውስጥ ብትገባ እንኳን አንጠልጥሎ በማውጣት ሀይቅ ውስጥ ጨምሮ የሚያቀዘቅዘት፡፡ካለሀሪ በረሀ ላይ ወስዶ በጥም ጉሮሮዋ ከደረቀ  ከመንቁሩ ወይን አመንጭቶ የሚያጠጣት…..ከፈለገች የሲ.አይ .ኤን የስለላ መረብ በጣጥሶ የዋይት ሀውስ ራት ግብዝ ላይ አስገብቶ የሚጥላት፡፡ሱፐር ሂዩማን እንድትሆን ሱፐር ሆኖ ሱፐር የሚያደርጋት መልዐኳ ነው፡፡የማታውቀው አባቷ ስጦታ፡ከሀገሯ አብሮት የተሰደ የደስታዋም ሆነ የሀዘኗ ጊዜ ተጋሪዋ፡፡

በንስራ አካል ውስጥ ባለው የነቃና የበቃ  ነፍስ እገዛ እሱ  ያየውን አንደምታይ እና ያሰበውን እንዳምታስብ ታውቃለች፡፡ልክ በአንድ ዲኮደር እንደሚሰራ ሁለት ቴሌቪዝን በሉን….እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እሱ አየሩን ሰንጥቆ  በሚበርበት የምድር ጥግ ሁሉ እያየ ያለውን ነገር ጥርት ባለ ምስል በአዕምሮዋ ታያለች…የንስርን አይን ደግሞ የሚታውቅ ነው..እያንዳንዱ ንስር  ቅንጣት በቀላሉ በአይኑ ሌንስ ይቀልባታል፡፡ይሄ ገለጻ ለብዙዎችን ግራ ሊያጋባ ይችላል፡፡
ይሄ መልአክ ነው ሰይጣን የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡መልአክ ከሆነ ለምን በእርግብ አካል ውስጥ አላደረም ወይንም እንደተለመደው  ለምን የበግ ስጋና ቆዳ አለበሰም፡፡እሱን የሚያውቀው ይሄ እንዲሆን ያደረገው የማታውቀውና የሌላ አለም ፍጡር የሆነው አባቷ ነው፡፡ለእሷ ግን  ምንም ግድም አይሰጣትም፡፡ዋናው በእርግጠኝነት የምታውቀው ነገር የእሷ እኔነት እና የንስሩ ነፍስ የተሳሰረ መሆኑን ነው፡፡ የኖረውን ያህል ኖራ በሚሞትበት ቀን የምትሞት እንደሆነም ይሰማታል፡፡ወይንም የእሱ ነፍስ ከንስር አካሉ ውስጥ ተንጠፍጥበፎ በሚወጣበት ቅጽበት የእሷም ነፍስ ከዚህ የሰው ሰውነት ወይም አካል ውስጥ ተንጠፍጥፎ በመውጣት ከእሱ ነፍስ ጋር በመተቃቀፍ ወደሚሄድበት ሚስጥራዊ ቦታ አብሮት እንደሚነጉድ ታውቃለች… የመዳረሻቸው ፍጻሜም  የአምላክ እቅፍ ይሆን የሉሲፈር ጓዲያ  ምንም የምታውቀው ነገር የለም ፡፡
አሁን ባሉበት ቦታ ሁለቱምን  ደስተኞች ናቸው ፡፡በዚህች ምድር ሚስጥር እየተደመሙበት ነው፡፡

ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 27,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ኬድሮን ከዕንቅልፋ የነቃችው 11 ሰዓት አካበቢ ቢሆንም መኝታ ቤቷን ለቃ ወደ በረንዳው  የወጣችው 12 ሰዓት ተኩል ካለፈ በኋላ ነው፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ዘወትር እንደምታደርገው ዮጋ እየሰራች ነበር የቆየችው፡፡እቤቷን ለቃ ስትወጣ ንስሯ ተከትሏት ወጣ፡፡እሷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ማንበቧን ጀመረች ፡፡

ከ12 ሰዓት እስከሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ግቤዋ ውስጥ ባሉት ዛፎች ላይ የሰፈሩትን የተለያ አይነት የወፎች ህብረ ዝማሬ እየሰማች  ንፁህ በሆነ አዕምሮዋ ተረጋግታ በተመስጦ የምታነብበት ሰዓት ነው፡፡ከሀገሯ ወጥታ ለገጣፎ ከከተመች በኃላ ያዳበረችው አዲስ ልምድ ንባብ ነው፡፡ከመፅሀፍቶች ጋር ያላት ቁርኝት ለእሷም ለራሷ እስኪገርማት ድረስ በጣም የጠነከረ ሆኗል፡፡በአጠቃላይ ሱሰኛ ሆናለች ፡፡

አንድ ሰዓት አካባቢ  ከእሷ መኝታ ቤት ጎን ያለው የፕሮፌሰሩ በራፍ ተከፈተ ፡፡ያልጠበቀችው ክስተት ነበር፡፡ምክንያቱም  ደግሞ የፕሮፌሰሩ ባህሪ ከእሷ የተለየ ስለሆነ ነው፡፡እሳቸው እሰከ ለሊቱ አስር ሰዓት  ድረስ  ይቆዩና የተለየ ፕሮግራም  ከሌላቸው በስተቀር እስከ ጥዋቱ አራት ሰዓት ድረስ ይተኛሉ፡፡እና ስታነብ የነበረውን መጻሀፏን አጠፍ አድርጋ አይኗን ወደፕሮፌሰሩ በራፍ ላከች፡፡ከክፍሉ የወጡት ፕሮፌሰሩ ሳይሆኑ አንድ የ20 ዓመት አካባቢ ሚሆናት መልከ መልካም ሴት ነች፡፡ፈገግ አለች ፡፡
እኚ ሽማጊሌው ሙሁር ከአልማዝ የጠነከረ ጽናት እና የሚያስገርም ስብዕና ቢኖራቸውም ሴት ላይ ያላቸው አመል ግን የተለየ እና  የሚገርም ነው፡፡ካሉበት ዕድሜ ጋር የሚቃረን አይነት ነው፡፡እሳቸው ግን  ይሄንን ድክመታቸውን እንደድክመት ተመልክተውት አያውቁም፡፡ ለጤነኝነቴ እና በዚህ ዕድሜዬ ላይ ላለኝ ጥንካሬ ሚስጥሩ  ሁለት ነው ፤የመጀመሪያው ከእጽዋት ጋር ያለኝ ፍቅር እና ቁርኝት ሲሆን ሌላው ደግሞ  ለወሲብ ያለኝ ፍቅር ነው ብለው በድፍረት ለጠየቃቸው ሁሉ ይመልሳሉ፡፡ ጫን ብለው ለጠየቃቸውም ስለወሲብ ጥሩነት ዘርዘር አድርገው ለማስረዳት ይገደዳሉ‹‹…. የወሲብ ብቃት ቀጥታ ከጤነኝነት ጋር ትስስር አለው፣አንድ የወሲብ ብልቱ አልታዘዝ ያለው ሰው የሆነ የጓደለው ነገር አለው ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ ትልቅ ቢዝነስ ሚያንቀሳሰቅሱ ባለሀብቶች ወይም ትልቅ ድርጅት ሚያሰተዳድሩ የስራ መሪዎች የወሲብ ስሜታቸው ሚቀሰቀሰው ከእለታቶች በአንድ ቀን ፤ለዛውም በብዙ ድካምና የመድሀኒት እገዛ ነው ፡፡ይህ የሚሆነበት ዋናው ምክንያት በጭንቀት የተበረዘ አዕምሮ እና በስራ የዛለ አካል ስላላቸው ነው ለወሲብ ዝግጁ መሆን የማይችሉት:: አልያም ድባቴ ውስጥ ገብተው በጭንቀት በሽታ እየተሰቃዩ ነው፡፡

ጥናተቶች አንደሚያመለክቱት የአንድ ሰው ብልቱ ሲቆም ያለው ጥንካሬ እና የልብ ጥንካሬ ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው…ተገትሮ የሚሰነጥቅ ብልት ያለው ወንድ ልቡም እንደዛው የተደራረበ ጠንካራና ከብረት የደደረ ነው፡፡ በሳምንት 4 ቀን ወሲብ የሚፈጽም ሰው ከማይፈጽም ሰው በልብ ድካም የመያዝ  ዕድሉ 58 ፐርሰንት የበለጠ የተሻለ ነው ፡፡…..››እያሉ መሰል መረጃዎችን በመደርደር ያስረዳሉ፡፡

ስለእሳቸው ማሰቧን ገታ አድርጋ ፊት ለፊቷ ወዳለችው ልጅ ትኩረቷን መለሰች፡፡በዛ ተመሳሳይ ሰዓትም ንስሯ ፡፡ ከተቀመጠችበት ወንበር ትክክል ጣራው ላይ ሰፍሮ ዘና ብሎ ቁልቁል እሷንም ጊቢውንም እየቃኘ እና የጥዋቷን ፀሀይ አብሯት እየሞቀ እና የምትመለከታትን ልጅ እየተመለከተ ነው፡፡
ልጅቷ በራፉን መልሳ ዘጋችና ወደውጨኛው  በራፍ ለመሄድ እርምጃ ስትጀምር  አዕምሮዋን ሰረሰራት፡፡ቀና ብላ ወደ ንስሯ ስታይ እነዛ ሰርሰሪ አይኖቹን ልጅቷ ላይ ሰክቷል…‹‹ ነገር አለ›› አለችና እሷም ትኩረቷን በመሰብሰብ የሚያየየውን ለማየት ሞከረች…. የልጅቷ ልብ ጭልም ብሎ ነው እየታያት ያለው‹‹‹ ..በሀዘን ኩምትርትር ያለ….ደግሞ ግራ የተጋባ የተመሰቃቀለ  ነፍስ ነው ያላቻት ›ስትለ አጉረመረመች.. ..ወጣቷ ቆንጆ ለሚያያት ሁሉ በፈገግታ  የደመቀ ፊት ስለሚታየው በጨለማ የተሞላች  ነፍስ አላት ተብሎ ቢነገረው ማንም አያምንም ፡፡

‹‹የእኔ እህት ››ብላ ጠራቻት

‹‹አቤት››አለችና ባለችበት ቆማ ፊቷን ወደ እሷ አዞረች…

‹‹ደህና አደርሽ …?››

‹‹ደህና ››አለች ግራ በመጋባት

‹‹ምነው በለሊት…?››

በንግግሯ ግራ ተጋብታ በእጇ የያዘችውን ሞባይል አብርታ አየችና‹‹እንድ ሰዓት እኮ ሆኗል…?››አለቻት፡፡

‹‹ካልቸኮልሽ ቁርስ አብረን እንብላና ትሄጄያለሽ›› …..ይህን ስትላት ልጅቱ እንደማትቸኩል እርግጠኛ ነኝ ….በቃ እንደውም የምትሄድበትም ያላት አይነት እንዳልሆነች  ተረድታለች፡፡

እንደማቅማማት አለችና ፊቷን አዙራ ወደእሷ መጣች፤እንደዛ ያደረገችው ዝም ብላ አይደለም ….ውስጧ እንደዛ እንዳታደርግ ስለገፋፋት ነው…. ሁሌ ፕሮፌሰሩ የሚያመጧቸውን ሴቶች ወደ ክፍሏ በማስገባት ቁርስ እያበላች ትሸኛቸዋለች ማለት አይደለም፡፡በዛ ላይ እኮ ገና ቁርስም አልሰራችም፡፡ብቻ ይዛት ገባችና ቁጭ እንድትል ነገረቻት ..ያመለከተቻት ቦታ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ይቅርታ ቁርሱ አልተሰራም …ግን በፍጥነት ይደርሳል፡፡››ብላ እስቶቩን  ለኮሰች

‹‹አረ ችግር የለም…››

ወደ ፊሪጅ አመራችና ከፍታ አንድ  ብርጭቆ የማንጎ ጂውስ ሰጠቻት…… አመስግና ተቀበለቻትና መጠጣት ጀመረች ….እሷም  እያወራቻት ቁርሱን መስራት ጀመረች… 

‹‹እኔ ሶፊያ እባላለሁ…አንቺስ

…?››ሶፊያ የሚለውን ስም ለገጣፎ ከተመች ቡኃላ ደጋጋማ መጠቀም ጀምራለች፡፡ምንያቱም ከአዲስ ሰው ጋር ሁሉ ስትተዋወቅ ኬድሮን እባላለው ስትል‹‹ ኬድሮን ማለት ምን ማለት ነው?›› ብለው ሲጠየቋት እንዴት ብላ እንደምታስረዳ ግራ እየገባት ስለተቸገረች ነው፡ኬድሮን ማለት በማርስና በመሬት መካከል የሚገኝ ፕላኔት ነው ፤አባቴ የዛ ፕላኔት ኑዋሪ ነው…ትርጉሙ የዕውቀት ምድር ማለት ነው .እሱን ለማስታወስ ስትል እናቴ በፕላኔቷ ስም ስሜን ኬዴርን ብላ ሰየመችኝ ብላ ብታስረዳ‹‹እንዴ ኬድሮን የሚባል ፐላኔት መቼ ነው የተገኘው? ብለው ወደጎግል ይሮጣሉ… ምንም ሚጎለጎል መረጃ ሲያጡ እሷን እንደ እብድ ይመለከታቷል …ይሄ ነገር ሲደጋገምባት ሰለቻትና ለምን ሁለተኛ ስሜን አልጠቀምም አለችና ‹ሶፊያ› የሚል ስሞን አብዝታ መገልገል ጀመረች ፤እና ሁለቱንም ስሞቾን እንደአስፈላጊነቱ እየቀያየረች መጠቀም ጀመረች፡

‹‹አለም››

‹‹እሺ አለም….. አይዞሽ..ነገሮች ይስተካከላሉ››አለቻት፡፡

‹‹ ፍጥጥ ብላ አየቻት፡፡ምክንያቱም ስለታሪኳ ምንም አልነገረቻትም፡፡ እንዴት ልታውቅ ቻለች፤ ብላ ግራ ተጋብታ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም ››አለቻት፡፡

‹‹አይ አሁን ያለሽበት ችግር ይፈታል ማለቴ ነው››

በፍራቻም በጥርጣሬም እያየቻት ‹‹ነገርኩሽ እንዴ…? ››ጠየቀቻት …

‹‹አይ እንዲሁ ሳይሽ ውስጥሽ የተጨነቀ እንደሆነ ስለገባኝ ነው፡፡በጣም አዝነሻል፡፡››

እንባዋን መገደብ አቅቷት ዘረገፈችው፡፡

‹‹አዎ ከባድ ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡››
‹‹አይዞሽ..እስኪ ንገሪኝ››

‹‹እንደምታስቢው ሸርሙጣ አይደለሁም…ይሄንን ስራ ከጀመርኩ ሳምንትም አይሆነኝም…››

‹‹አይዞሽ ..ተረጋጊና አጫውቺኝ››
‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ስምንት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››

‹‹በባሏ ጠርጥራሽ ነው አይደል …?››ያው እኔ ሳላስበው ነው ቀደም ቀድም የምለው ….ምክንያቱም እሷ ታሪኳን በቃላት አቀናብራ ለሶፊ ከመናገሯ በፊት እሷ ቀድሞ ይታያታል…ንስሯ የበራፍ  በረንዳ ላይ ሶፊ ከለቀቀችበት ወንበር ላይ ተፈናጦ ክፍት በሆነው በራፍ ወደውስጥ አጨንቁሮል ….እርግጥ ልጅቷ ጀርባውና ስለሰጠችው እስከአሁን አላየችውም… እሷ ግን ፊት ለፊት ይታያታል ሁለቱም የልጅቷን ታሪክ ላይ አተኩረዋል …ለዛ ነው ቀደም ቀደም የምትለው….ያ ደግሞ ልጅቷን ግራ እያጋባት ስለሆነ መረጋጋት እንዳለባት ለራሷ እየነገረች ነው፡፡

‹‹አዎ ትክክል ነሽ…ብታይ ጭራቅ ሴት ነች፡፡ቅናቷ አያድረስ ነው፡፡በቃ ሰይጣናዊ የቅናት ዛር ነው የሰፈረባት፡፡ኑሮዬን ሁሉ ሲኦል ነው ያደረገችው፡፡››

‹‹ሙሉውን ሶስት አመት እዛው ነው የኖርሺው…?››

‹‹አዎ ሶስት አመት ሙሉ አንድ ቤት ነበርኩ…እርግጥ መጀመሪያውን  አንድ አመት አካባቢ ጥሩ ሴት ነበረች…ሁሉ ነገር መልካም ነበር… ደሞዜን በስርአቱ ትከፍለኛለች..እርግጥ እስከመጨረሻውም ደሞዜን ከልክላኝ ወይም አቋርጣብኝ አታውቅም…ለቤተሰቦቼ የምልከው ተጨማሪ ብር ሁሉ ትሰጠኝ ነበር፡፡ከዛ ድንገት ፀባይዋ ተቀያየረ….ለዓይኖቾ ተጠየፈችኝ….

‹‹ለምን ታዲያ አትለቂም ነበር..?ማለት ሌላ ማዳም ጋር ቀይረሽ መስራት ትቺይ ነበር…››

‹‹ያው እንደነገርኩሽ በህገወጥ መንገድ ነው የሄድኩት.. እንደልቤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሼ ስራ ማማረጥ አልችልም..ሌላው …››ብላ ዝም አለች ..ላውራ ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋ ሙግት የገጠመች መሆኑን አውቃባታለች…

‹‹ሌላው ምን…?››

‹‹ሰውዬው በጣም መልካም ሰው ነው…ልጆቹንም በጣም ነው የምወዳቸው….ለእነሱ ስል ነው ታግሼያት የኖርኩት››

ፈገግ አለች‹‹መጨረሻ ታዲያ እንዴት ሆነ?››

‹‹ቅናቷ ከቁጥጥር በላይ ሆነብኛ››
‹‹ያው  ምታደርጉትን እኮ ስለምታይ ነው››

‹‹ማለት…? እንዴት ታውቃለች……?›.
‹‹እርግጥ የእሷን አለመኖር  እየጠበቃችሁ ነው ፍቅራችሁን የምትወጡት… ግን እሷ በደንብ ታውቃለች ..እንደውም ጥሩ ሰው ነች››አለቻት
ልጅቷ ግራ ገባት ..ከድንጋጤዋ የተነሳም ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ሁሉ ለቃ  መውጣት ፈልጋለች..…

‹‹አይዞሽ አትደንግጪ …እሷን ለማስቀየም ወይም ለመበደል ብለሽ ሳይሆን ፍቅር ላይ ስለወደቅሽ ነው እንደዛ ያደረግሽው…ያ ደግሞ ከሰውዬው ቀረቤታ እና መልካምነት የተነሳ ነው..በዛ ላይ በጣም ቆንጆ እና ዘናጭ ነው…እንደምትወጂው አውቃለሁ  ፡፡እሱም በደንብ ነው የሚያፈቅርሽ፡፡በጣም የከፋው ነገር ግን ቅናተኛ ላልሻት ሴት ደግሞ ሰውዬው ሁለመናዋ ነው…እናንተ እርስ በርስ ከምትዋደዱት በላይ እሷ እሱን ትወደዋለች፡፡እና ሴትዬዋ በተፈጥሮዋ መጥፎ ሆና አንቺን በማሰቃየት የምትረካ ስለሆነች ሳይሆን ባሏን ላለማጣት የምታደረግው መፋለም እና ጥረት  ነበር፡፡እንደውም አንቺን ባሰቃየች ቁጥር እሱንም የምታስከፋው እና የምታጣው  መስሎ ስለሚሰማት በጣም ትጨናነቅ እና ትጠነቀቅ  ነበር…አንቺን ጎድታኛለች ብለሽ ከምታወሪው በላይ እሷ እራሷን አሰቃይታለች ….የጨጋራ በሽተኛ ሆናለች….››

‹‹ቆይ አንቺ ይሄን ሁሉ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…?››

እሱን ልታስረዳት አልቻለችም ‹‹..ትኩረት ከሰጠው  አንዳንድ ነገሮችን ማየት እችላለሁ፡፡

በውስጥሽ ይህቺ ልጅ ጠንቆይ ነች እንዴ…? እያልሽ እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ..እንደዛ በይው ችግር  የለውም››

‹‹አይ ማለቴ ….ልዋሽሽ አልችልም እንዳልሽው ነበር እያሰብኩ ያለሁት…ይገርማል ያልሻቸውን  ብዙውን ነገሮች ትክክል ነሽ››

‹‹ምንድነው ትክክል ያልሆንኩት…?››

‹‹እሷ ስለእኛ ግንኙነት በእርግጠኝነት ማወቋን እና..ከእኔ በላይ እሱን ማፍቀሯን››

‹‹ሁለታችሁ ፍቅር የምትሰሩት አንቺ ክፍል አይደል…?››

‹‹አዎ ግን እሷ ስራ በምትሆንበት እና ከቤት እርቃ በሄደችበት ጌዜ ጠብቀንና ተጠንቅቀን ነው››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ …በሁለታችሁ ያልተለመደ መቀራረብ ጥርጣሬ ካደረባት በኃላ ግን ክፍልሽ ውስጥ በስውር ካሜራ ስላስቀመጠች የተቀዳውን በፈለገችው ጌዜ ከፍታ ታየው ነበር፡፡››

‹‹ያማ አይሆንም..…?እንዴት ተደርጎ…?››

‹‹እንደዛ ነበር የሆነው…ከእኔ በላይ አታፈቅረውም ያልሺው ደግሞ ያው በራስሽ ሚዛን ስለምትመዝኚው ነው እንደዛ የምታስቢው እንጂ እንቺ በእሷ ቦታ ብትሆኚ እርግጠኛ ነኝ ወይ ጥለሺው ትሄጂያለሽ ..ወይ ሌላ እርምጃ ትወስጂያለሽ ….እሷ  ግን ካንቺ ጋር ብትጨቃጨቅም ….አንቺን ላይ ችግር ለመፍጠር ብትሞክርም አንድ ቀን እንኳን እሱ ላይ ተነጫንጫበት ወይንም  ጉዳዩን አንስታበትና ወቅሳው አታውቅም..ለእሷ እሱ ብቸኛው ፍቅሯ ነው..ለአንቺ ግን የመጀመሪያ ምርጫሽ አይደለም..ስለምታፈቅሪው ብቻ ሳይሆን ማዳሞ ከምታውቀው ሌላ ተጨማሪ ብር ስለሚሰጥሽ ነው  ..ፍቅርሽ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ምንጭሽም ስለሆነ ነው…ለእሷ ግን እንደዛ አልነበረም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው….የእውነት ካሜራው ኖሮ የምናደርገውን ሁሉ እያየች በትዕግስት አልፋን ከሆነ የሚገርም ነው…እኔ ብሆን ልገድለው ሁሉ እችላለሁ…አረ ሁለቱንም ነው በተቃቀፉበት የማጠፋቸው››

‹‹አየሽ..ሴትየዋ የምታስቢያትን ያህል ክፉ አልነበረችም….ከዚህም በላይ ልታሰቃይሽ ምክንያቱን ሰጥተሻት ነበር…ግን እሷ በተቻላት መጠን እራሷን ለመቆጣጠር ሞክራለች፡፡››

‹‹አዎ አንቺ ይገርማል… አሁን ሳስበው በህይወት ስላለውም እድለኛ ነኝ….››

‹‹እና እዚህ ስትመጪ ደግሞ ሌላ ታሪክ አጋጠመሽ››

‹‹አዎ በጣም የሚያንገበግበው እና ስብርብር ያደረገኝ ደግሞ ይሄኛው ነው›› አለች …..አሁን በፍራቻ እና በአድናቆት ነበር የምትመልስልኝ
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹መቼስ ታውቂዋለሽ…አንድ ቀን ወደ ሀገሬ ስመለስ ቤት ይኖረኛል….አገባዋለሁ..ልጅ ወልድለታለሁ ብዬ ደሞዜንም .ሰውዬው ይሰጠኝ የነበረውንም ብር እልክለት ነበር…ቤት እየሰራው ነው ይለኛል….የቤት ዕቃ እያሞለው ነው ይለኛል..ምን አለፋሽ ከሶስት መቶ ሺ ብር በላይ  ነው የላኩለት …..ግን ስደርስ ሌላ ሴት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዶ ጠበቀኝ…..ከዛ ምን ልንገርሽ ሁሉ ነገር አስጠላኝ …ክፍለሀገር ወደ ቤተሰቦቼም መሄድ አልፈለግኩም እንዴት ብዬ ምን ይዤ ሄዳለሁ…?……..  
‹‹አዎ ለእሱ ያልሽውን ሶስት መቶ ሺብር ስትልኪለት ለቤተሰቦችሽ የላክሺው ብር ሲደመር 50 ሺ ብርም አይሞላም..››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..የሚያንገበግበኝ እና ሞራሌን እንክትክት ያደረገው እና ዛሬ እዚህ ያስገኘኝ ይሄው  ነው….

አይዞሽ እናስተካክለዋለን ..በእኔ ተማመኚ..አልኳትና የደረሰውን ቁርስ አቅርቤ መብላት ጀመርን›…

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 29,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡

‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡››

‹‹ፎቶው አለሽ?›› 

‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ‹‹ተከተይኝ ››አለቻት እና  ወደበረንዳው ወጡ…ንስሯ ተረጋግቶ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ስታየው እንደመፍራትም ግራ እንደመጋባትም አለችና፡፡

‹‹ምን አይነት አሞራ ነው..አይፈራም እንዴ? ››

‹‹የእኔ ነው››

‹‹አሞራው?››

‹‹አዎ…ግን አሞራ ሳይሆን  ንስር ነው…የእኔ ንሰር ፡፡››

‹‹ምን ያደርግልሻል?፡፡››

‹‹እሱማ ለእኔ ብዙ ነገሬ ነው… የፈለኩትን ነገር ያደርግልኛል..እኔ እንደውም የሚገርመኝ እኔ ለእሱ ምን አደርግለታለሁ ሚለውን ነው››

‹‹ይቅርታ ግን ያስፈራል…. .በተለይ አይኖቹ እና መንቁሩ…››እሷን ችላ አለቻትና ሞባይሏ ላይ ያለውን የልጅቷን ፍቅረኛ ፎቶ ለንስሯ እያሳየች ‹‹….እንርዳት መሰለኝ…እወነቱን ማወቅ መብት አላት››ስትለው ክንፎቹን አርገፈገፈና   መቀመጫውን ለቆ በአየር ላይ ተንሳፈፈ…እሷ  በርግጋ ወደኃላዋ አፈገፈገች….ወደላይ ተምዘግዝጎ አየሩን እየሰነጠቀ ከፍታውን ለአይን መታየት እሰከማይችል ድረስ ርቆ ተሰወረ፡

‹‹ቁጭ በይ› አለቻትና በረንዳው ላይ ካለው ወንበር አንዱን እያሳየቻት እሷ ንስሯ በለቀቀላት ወንበር ላይ እየተቀመጠች፡፡

‹‹ሄደብሽ እኮ …እንዲህ እርቆ ሄዶ አሁን አውቆ ተመልሶ ይመጣል?፡፡››

‹‹አዎ የእኔ እወቀት ዘጠና ፐርሰንቱ ከእሱ የማገኘው ነው…ንስሮች በተፈጥሮቸው በጣም ልዩ የሆኑ የአእዋፋት ዝርያዎች ናቸው፡፡እይታቸውም ጥልቅ አስተሳሰባቸውም ስል እና የተሞረደ  ነው፡፡ከዛም በላይ ግን የእኔ ንስር የተለየ ነው፡፡እንዴት የሚለውን ነገር ላብራራልሽ አልችልም..ግን አሁን የሚያደርገውን ታያለሽ ..ከዛ እራስሽ ትፈርጂያለሽ››

‹‹እንዴት?››

‹‹አሁን ፍቅረኛሽን ፎቶ እያሳየሁት ሳወራው አላየሽም?››

‹‹አይቻለው.ግን እናቴም ሲጨንቃት እና በሆዷ ነገር ሲገባ ከምታልባት ላም  ጋር ታወራ ነበር…እንደውም ለእሱ ስታወሪ እናቴ ነች ትዝ ያለችኝ፡፡››

‹‹አይ ይሄ ይለያል..አሁን ያንችን ችግር ማለት ስለፍቅረኛሽ ትክክለኛ ነገር እንዲያጣራልኝ ነው የላኩት››

‹‹እንዲት አድርጎ››

‹‹በቃ የተለየ ችሎታ አለው… ማንኛውም ነገር ካተኮረበት የውስጡን ሀሳብ እና ጠቅላላ ታሪኩን ማንበብ ይችላል…እኔ ደግሞ ከሱ አዕምሮ ማንበብ እችላለሁ..ወይም እንዳውቀው አዕምሮውን ይከፍትልኛል..ቅድም ያንቺን ታሪክ ላውቅ የቻልኩት ከእሱ ነው፡፡››

‹‹እኔ አላምንም ..ንስር ይሄን ሁሉ…. እንዴት  ተደርጎ?››

‹‹አየሽ እንዳልኩሽ የእኔ ንስር ልዩ ነው..ከእኔ  ጋር ያለውም ትስስር ከተፈጥሮ ክስተቶች እንደ አንድ ነው..ያም ሆኖ ግን እንዲሁ ንስር እና የሰው ልጅ ከጥንትም ጀመሮ የመንፈስ ትስስር እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡፡ሌላውን ተይና  በሀገራችን ጥንታዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ንስር የትንሳኤ ምልክት ነበር… በምጥቀት ማሰብ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር መንፈስ ተምሳሌ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡በግብጽ ደግሞ መቃብራቸውን ጋንኤል እንዳይደፍረው የንስር ምስል ከመቃብሩ በራፍ ላይ ያስቀምጡ ነበር…ያ የንስር ምስል የጋንኤሉ መንፈስ አልፎት ወደውስጥ ሊጋባ ስለማይችል እሬሳቸው ከጥቃት የተጠበቀ ይሆናል ብለው ያምናሉ..፡፡
የጲላጦስ ሀገር የሆነችው ግሪክ ደግሞ ከአመልክቶቾ ውስጥ አንድ የሆነው የአማልዕክቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው ዜዎስ በንስር ይመሰል እንደነበረ ይነገራል፡፡በጥንት ጊዜ አሜሪካኖች  ደግሞ እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው ያለቸውን ጥልቅ ፍቅር ሚገልጽት የንስር ላባ በመስጠት ነው፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ሲራክም  ሶስት እራስ እና አስራ ሁለት ክንፎች ሳላለው ንስር በህልሙ ራዕይ አይቶ ነበር….የራዕይው ፍቺ በየተራ ስለሚነግሱ ነገስታት ሲገለጽለት ነበር…ንስር የኃይልን እና የስልጣን ምልክት ነው፡፡…››ስብከት የመሰለ ንግግሯዋን ተናግራ ሳትጨርስ….ዶክተሩ በራፋቸውን ከፍተው ወጡና ወደእነሱ መጡ

…‹‹.ሶፊ ደህና ነሽ?››

‹‹እንዴት አደሩ ዶክተር?››
‹‹አለሁ….ዛሬ እንግዳ ከየት አገኘሽ ?››አለት እንግዳዋ ላይ በማተኮር፡፡

‹‹አያውቋትም?››

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት ግን ያየኋት ይመስለኛል››

‹‹አዎ ከባሌ የመጣች የአክስቴ ልጅ ነች…ከዚህ በፊትም መጥታ ስለነበረ.. ተገናኝታችኋል››
‹‹ለዛ ነዋ ፊቷ አዲስ ያልሆነብኝ….በሉ ተጫወቱ አንዲት ቀጠሮ አላለችብኝ ..ከሰዓት እንገናኛለን ..›ብለው ተሰናብተዋቸው ወደመኪናቸው ማቆሚያ ጥለዋቸው ሄዱ
ሶፊያ ሳቋ  አፍኗት  ስለነበር እንደራቁላት ለቀቀችው

…‹‹ሳያውቁኝ ቀርተው ነው ወይስ አውቀው ነው?››

‹‹አይ ተምታቶባቸዋል…ያው ማታ መጠጥም ስለሚወሳስዱ ነው ቅር አይበልሽ››

‹‹አረ ምን ቅር ይለኛል ነገራቸው ገርሞኝ እንጂ››ብትልም ቅር እንዳላት ግን በግልፅ ከንግግሯ ቃና በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እዚህ ቤት ከጥዋት ጀምሮ የሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ይገርማል አይደል?››

‹‹ምን መገረም ብቻ ከአዕምሮም በላይ ነው….እኔ እንዲህ….››ንግግሯን ሳትጨርስ  ንስሩ እየተምዘገዘገ መጣና ከእነሱ ፊት ለፊት በአምስት ሜትር ርቀት ያህል በሚገኝ የጽድ ዛፍ ላይ ሲያርፍ ስለተመለከተች  አቆረጠችና …ምን እንደሚከሰት ለማወቅ መጎጎቷን በሚያስታውቅባት መንፈስ‹‹መጣ ››አለቻት፡፡

‹‹ትንሽ ታገሺኝ ››አለቻትና አዕምሮዋን ሰብሰባ  ትኩረቷን በሙሉ  ከንስሯ ጋር በማቋራኘት እምሮውን  ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መምጣትሽን ፍቅረኛሽ አያውቅም አይደል?፡፡››

‹‹አዎ..አንዴ በእሱ ክህደትና ዘረፋ የሞትኩት አንሶኝ ጭራሽ መምጣቴን ነግሬው ስሩ ቆሜ ሁለተኛ ሞት ልሙት እንዴ? አላደርገውም ….ፍቅሬን መልስልኝ ብዬ ልማፀነው..?ወይስ ብሬን መልስልኝ ልበለው?››

በንስሯ አእምሮ አሻግራ እያየች ያለችው ታሪክ አሰገርሟት፡፡‹‹ቆይ ቆይ…በዚህ ሰዓት ፍቅረኛሽ ምን እየሰራ እንደሆነ ታውቂያለሽ…?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን እየሰራ ነው..?.ከሚስቱ እየተዳራ ወይም ልጁን እያጫወተ ይሆናል››ብስጭት እና ቅናት በተቀላቀለበት ድምፀት መለሰችላት፡፡

‹‹አይደለም …ትናንትና ወደ  ጊኒጪ ሄዶ እናትሽን  አምጥቶ ግሩም ጠቅላላ  ሆስፒታል እያሳከማቸው ነው…››

‹‹የእኔን እናት .. ?ምን ሆና ነው…?››በድንጋጤና በመገረም .እናም ደግሞ ባለማመን ጠየቀች፡፡

‹‹አትደንግጪ ያው የተለመደው በሽታዋ ነው….ድሮም ከፍተኛ የጨጎራ ቁስለት እንዳለባት ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹ግን እኔን እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ያሰጠጉታል …እናቴ ምንም የሚያስታምማት እና ሚያሳክማት ሰው ብታጣ እንዴት ልጇን ከከዳ ሰው ጋር ትተባበረለች…?እኔ ይሄን ማመን አልችልም …፡፡ሌላው ይቅር እናቴ እንኳን ለስላሳ እና የዋህ ስለሆነች  ይቅር ልትለው ትችላለች… እህቴ ግን እርግጠኛ ነኝ ይቅር አትለውም ፤ እርግጥ ሁሉም ለእሱ የላኩለትን ብር አያውቁም …ግን በጣም እንደማፈቅረውና ላገባውም  እንደምፈልግ ከዛም አልፎ ቃል እንደተግባባን ግን በደንብ ያውቃሉ፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ…በጣም ነው የሚያፈቅርሽ፡፡››