ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
289 photos
1 video
16 files
240 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
💀የጠፋው ሬሳ💀
#ክፍል ሀያ-ሁለት


...ብልጭ ድርግም በሚለው የሆስፒታሉ መብራት የሆነ ሰው ይታየኛል አሁን ፊቴን አኮሳትሬ ግንባሬን ጨምድጄ እልሄን ሰብስቤ ወደፊት መጠጋቴን ጀመርኩ የጓደኞቼን ደም ለመበቀል ከመፈለጌ የተነሳ ወደኔ እንኳን እስኪመጣ አልጠበኩትም ራሴ ተጠጋሁት የያዝኩትን ቢላ ዘቅዝቄ እጀታውን በማርያም ጣቴ ጋር አድርጌ ስለቱን ወደ ክርኔ አስደግፌ በለዘበ አረማመድ መጠጋቴ ቀጠልኩ ነገር ከኔ ተቃራኒ ጥግ ላይ ያለው ሰው አይንቀሳቀስም ለምን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን በድፍረት እና በንዴት እየተጠጋሁት ነው...የሆስፒታሉ መብራት ብልጭ ድርግሙን ትቶ ቀጥ ብሎ በራ ጥግ የተመለከትኩት ነገር አይደለም ሊገለኝ ይልቁና በፍርሃት ተሸማቆ ራሱን አሳንሶ ተኮራምቶ ፊቱን ሸሽጎ ተቀምጧል..."እንደ ወንድ ተነስተህ ና እንደ ፈሪ አትሸፋፈን እንደ ገዳይ ፊት ለፊት ውጣ አትርመጥመጥ" አልኩት ንግግሬን በእርጋት ጀምሬ ንዴቴ ሲብስ እየጮውኩኝ ነገር ግን አሁንም ዝምታ ነበር መልሱ...ወደሗላ አድርጌ የነበረውን ስለት ወደ ፊት መልሼ ደረቱ ላይ ለመሰንቀር ወደ ተቀመጠበት ስፍራ ኮቴ ቢስ በሆነ እርምጃ ተጠጋሁት ነገር ግን ከሗላይ በሰከንድ ሽርፍራፊ እጅግ ፈጣን ሰው አለፈ...ከመቅፅበትም ፊቴን መልሼ የያዝኩን ስለታማ ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን አንዳች ያጠቃሁት ፍጡር የለም ከአጠገቤ ያለው የሆስፒታሉ ክፍል አሁን እንደተከፈተ ያስታውቃል እንቅስቃሴውን እንኳን አላቆመም...በጥሞና ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ግን ማንም አልነበረም ከቆምኩበት ሁለት ከፍል አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶስተኛው ክፍል ሲከፈት ተሰማኝ ሆስፒታሉ ፀጥ ብሎ ስለነበር ሲከፈት ያለው የበር ድምፅ ይሰማል "ሲጢጥ" ሲል....አሁን መሃል ላይ ገብቻለሁ ከፊትለፊት የሆነ ሰው አለ ከሗላ ደግሞ ተኮራምቶ የተቀመጠው ፡...ዞር ብዬ ጀርባዬን ቃኘው ማንም ያ ሰው አሁንም ኩርምት እንዳለ ነው የመግደልም አቅም ያለው አልመሰለኝም ልክ እንደኔና ጓደኞቼ ጥቃት የደረሰበት ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ ይሄን ሁላ ማሰላስለው ሲከፈት ድምፁ ወደተሰማኝ በር እያመራሁ በአይኖቼም መለስ ብዬ ጀርባዬን እየተመለከትኩ ነው አሁን ክፍሉጋ ልደርስ አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶኛል የቀረኝንም እርምጃ እግሬን አንስቼ ልራመድ ስል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ ከመቅፅበትም አጠገቤ ያለው ግድግዳ ላይ ተደግፌ ቁልቁል ወርጄ ድምፄን አጥፍቼ ፀጥ አልኩኝ በጨለማው መሀል የትልቅ ከስክስ ጫማ ድምፅ ተሰማኝ ሰፋ ያለ የእግር አጣጣል እንዳለው ከምሰማው የእግር ኮቴ ተረዳሁ ውስስጤ ፍርሃት የሚባል የለም በቀል እንጂ ነገር ግን ጨለማወው ነገሮችን በብዙ እያከበደብኝ ነው "ቢሆንም ግን ገድዬው ወይ ገሎኝ ከዚ አረመኔ ነፍሰ በላ ጋር እለያያለሁ" አልኩኝ ለራሴ እርምጃው እየቀረበኝ ነው የያዝኩትን ስለት በተጠንቀቅ አዘጋጅቼ እየጠበኩ ነው...በድንገት መብራቱ ፏ ብሎ በራ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነስቼ የእግር ዱካው ይሰማኝ ወደነበረው ስፍራ የያዝኩትን ስለታም ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያውኑ ጎላና ጎርነን ባለ ድምፅ ልብን የሚያርድ ሳቅ ተሰማ ባለሁበት ተንበረከኩ እንደሚዲህ ህፃን ቀዳዴ እየሄድኩ ግራና ቀኜን ተመለከትኩ ነገር ግን ምንም የለም ነበር ሳቁ ሳቅ ብቻ አይደለም አንዳች ሃይል አለው ቁጣዬን ነጠቀኝ እልሄን በፍርሃት ለወጠው በቀሌን የሽሽት አደረገው በጣም ተደነኩኝ አብዝቶም ገረመኝ ካልመጣ ስል የነበርኩት ቤት ልውጣ ብዬ ተጨነኩኝ ጣቶቼ ቢላውን መጨበጥ እስኪያቅታቸው ተብረከረኩ በዛ የውድቅት ምሽት ከየት መጡ የማይባሉ ቁራዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ተመሙ ራሳቸውን ከግድግዳ ጋር እያጋጩ ኮሪደሩን በደም አጨቀዩት አብዝተውም ይጮሁ ነበር መሃል ላይ ሆኜ በግንባሬ ከወለሉ ተዋድጄ ሞቴን መጠበቅ ጀመርኩኝ አቀርቅሬ ባለሁበት ጊዜ አንገቴ ላይ ያለው የብር ሃብል ወለሉ ላይ ተመለከትኩት ግንባሬንም ቀና አድርጌ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው አንድ አምላክ የተሰቀለበት መስቀል ነበር መስቀሉ ላይም የኔ እና የዓለሙ አዳኝ እንዳላቀረቅር አቀርቅሮ አየሁት ህመሜን ታሞልኝ ተቸንክሮ አየሁት....እሱን ባየው ጊዜ ንዴቴ እና እልሄ መታደስ ጀመረ ስልቱን ጨብጬ በሁለት እግሬ ቆምኩኝ ነገር ግን ሆስፒታሉ በደም ጨቅይቶ የነበረው በቁራ ድምፅ የታወከው ስነሳ ግን ሰላም ነበር...መጀመሪያ ጥግ ላይ ካየሁት ሰው በቀር በድጋሜ ማንም አልነበረም ወደዛም ሰው ቀጥ ብዬ ተጠጋሁ ስደርስም "እባክህ አትግደለኝ እባክህ" እያለች ሳግ እየተናነቃት የምትማፀን ሴት ነበረች "አይዞሽ አልጎዳሽም ተነሺ" ስላት "ሜርሲዬ" ብላ አቀፈችኝ የመየውን ማመን አልቻልኩም ሞቱ ካልኳቸው ጓደኞቼ መሃል ቄድስቴ ነች "ቅድስቴ አንቺ ነሽ እንዴ ተጎዳሽ የሆንሽው ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ሰውነቷን እየደባበስኩ "ምንም አልሆንኩም ባባን ወስዶታል ባርሳ ደሞ የት እንዳለች አላውቅም" አለችኝ "አታልቅሺ እናገኛቸዋለን" ብዬ አባበልኳትና እጇን ይዤ ወደ መውጫው ሳመራ "ሜርሲዬ ይሄ ለመገለን የሚፈልገው ሰው ትዝ ካለሽ ከወር በፊት ጠፋ የተባለ ሬሳ ነበር ሰዎችም እንደሚሉትም ሞቶ የተነሳ የመናፍስት እጅ ያለበት...እያለች እየነገረችኝ ሳለ ዞር ብዬ የምትለው ገርሞኝ እንግዳ ሆኖብኝም ልሰማ ስቆም ሰውዬው ከየት መጣ ሳይባል የእግሩ ዱካ ሳይሰማ አንዳችም ነገር ሳይታወቀን በንፋስ ፍጥነት ከቅድስታ ጀርባ ቆሟል..............

..........ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ ሶስት እንዲቀጥል👍
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን

📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሁለት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አይሮፕላኑን ባህሩ ላይ እንድጥለው ትፈልጋለህ?››
‹‹እንደዚያማ ማድረግ አትችልምº እኔ አይሮፕላኑ ውስጥ አለሁ
ፓይለቱ እዚያ ቦታ ላይ በድንገት እንዲያርፍ የሚያስገድደው አንድ ችግር ፍጠር›› አለው በሚገባ በተከረከመ ጥፍሩ ፖስት ካርዱ ላይ ያለውን ቦታ እያመለከተው፡፡
የበረራ መሃንዲሱ ፓይለቱ በድንገት አይሮፕላኑን ለማሳረፍ የሚያስገድደው ችግር መፍጠር አያቅተውም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍ ችግር መፍጠር ለጊዜው ኤዲ አልከሰትልህ አለው፡፡

‹‹ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን የማይሆን ነገር ግን አይደለም
እኔም ይህን ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጫለሁ››
‹‹ማነው ይህን የነገረህ? እናንተስ እነማን ናችሁ? አለ ኤዲ ንዴቱ ተቀስቅሶ፡

‹‹ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ መጠየቅ አትችልም›› አለው ሉተር::

ኤዲ መጀመሪያ ሉተርን ሊያስፈራራው ሞከረ፣ አሁን ግን አቅመ ቢስ ሆኗል፡ አሁን በፍርሃት መሸበብ የእሱ ተራ ሆኗል፡ ሉተር ይህን ጉዳይ በሚገባ ያቀደ የወሮበላ ቡድን አባል ነው፡፡ ኤዲን ለእኩይ ተግባራቸው
በመሳሪያነት ሊጠቀሙበት ነው የመረጡት፡ ውጥናቸውን ዳር ለማድረስ
ደግሞ ካሮል አንን እመዳፋቸው ስር አውለዋታል፡

ኤዲ ፖስት ካርዱን ኪሱ ከተተና ትተባበራለህ ወይስ አትተባበርም?›› ሲል ሉተር በጉጉት ጠየቀ፡፡

ኤዲ ዞር አለና አፈጠጠበት፡ ከዚያም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ፡

ኤዲ በጠላቶቹ ፊት ፈርጠም ያለ ባህሪ ለማሳየት ቢሞክርም እውነታው ግን እንዳንበረከኩት ነው የሚያሳየው እነዚህ ወሮበሎች ለምንድነው ይህን ማድረግ የፈለጉት? ባንድ ወቅት ጀርመኖች ቦይንግ 314 አይሮፕላንን
ሰርቀው ዲዛይኑን ኮፒ ለማድረግ ፈልገው እንደነበር ያውቃል፡ አሁን ይህን ማድረግ ቢፈልጉ አይሮፕላኑን ሜይን ስቴት ውስጥ ሳይሆን አውሮፓ
ውስጥም ሰርቀው መውሰድ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡

አይሮፕላኑን በሚፈልጉበት ቦታ ላይ እንዲወርድ ለማድረግ ማሰባቸው
ቦታው ላይ የሚጠብቅ ጀልባ እንዳላቸው ይጠቁማል፡ ‹ግን ለምን?› ሉተር ሻንጣ ሙሉ ሃሺሽ፣ ባዙቃ፣ ኮሚኒስት አብዮተኛ ወይስ የናዚ ሰላይ ነው
ወደ አሜሪካ ማስገባት የፈለገው? እነ ሉተር እዚህ ችግር ውስጥ ለመግባት
የወሰኑት መቼም ሊያስገቡት ያሰቡት ሰው ወይም ነገር በጣም ጠቃሚ
ስለሆነ ነው፡፡

ኤዲ ከሌሎቹ የስራ ባልደረቦቹ ይልቅ እሱን የመረጡበት ምክንያት
አሁን ገብቶታል፡አይሮፕላኑን አንድ ቦታ በድንገት እንዲያርፍ ከተፈለገ
ይህን ማድረግ የሚችለው የበረራ መሀንዲሱ ነው፡፡ ናቪጌተሩ ምንም ማድረግ አይችልም የሬዲዮ ኦፕሬተሩም እንዲሁ፤ ፓይለቱ ደግሞ የረዳት
ፓይለቱ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡ የበረራ መሀንዲሱ ግን ብቻውን
የአይሮፕላኑን ሞተር ቀጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ሉተር የፓን አሜሪካንን አየር መንገድ መሀንዲሶች ስም ዝርዝር ሳያገኝ አልቀረም፡ ስም ዝርዝሩንም ማግኘት ከባድ አይደለም:፡ የአየር መንገዱን መረጃ ለማየት አንድ ምሽት ላይ አንዱ የሉተር ጓደኛ የአየር መንገዱን ቢሮ ሰብሮም ቢሆን ሊያገኘው ይችላል ወይም አንዷን ጸሐፊ በጉቦ መደለል ነው፡፡ ለምን ግን ኤዲን መረጡ? ሉተር በዚህ ቀን የሚበረው የበረራ
መሃንዲስ ስም እጁ ገብቷል ከዚያም ኤዲ ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር
እንዲሆን ለማድረግ ሲያስብ አንድ መላ ያገኛል፤ ሚስቱን ማገት፡፡
እነዚህን ወንበዴዎች መርዳት ለኤዲ ልብ የሚሰብር ጉዳይ ሆኖበታል፡
ወንበዴዎች እጣ ክፍሎቹ አይደሉም፡ ሰርተው ከማግኘት ይልቅ ሌት ተቀን
ከሚለፉ ሰዎች አፍ እየነጠቁና እያጭበረበሩ ተንደላቀው ይኖራሉ፡ ህግ
አክባሪ ሰዎች የዕለት እንጀራ ለማግኘት ጀርባቸው ሲጎብጥ ይውላል፡ እነዚህ
ማፊያዎች ግን ለፍቶ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየደገኑ፣ ለፍተው ያገኙትን
ተሽከርካሪዎች ያሽከረክራሉ፡፡ እነዚህን ወንጀለኞች በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ጠፍሮ በኮረንቲ እያንጨረጨሩ መግደል ነው የሚያዋጣው፡፡

ቶም ሉተርን ማሞኘት ቀላል አይደለም፡፡ ሚስቱን ካሮል አንን አግቷታል። ሉተር ያቀደውን ትልም ኤዲ ለማደናቀፍ ሞከረ ማለት በሚስቱ አንገት ላይ የታሰረውን ገመድ ሸምቀቆ አጠበቀ ማለት ነው፡፡ ሊያታልላቸው
ወይም ሊታገላቸው አይችልም፤ ያሉትን ከመፈጸም ውጭ፡

ሆዱን እንደጨነቀው ከወደቡ ወጥቶ በመንደሩ ያለችውን ብቸኛ መንገድ አቋርጦ ወደ አንድ ሆቴል ሄደ፡ ሆቴሉ እንዳለ የተያዘው በፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች ነው ማለት ይቻላል፡፡ እዚያም ካፒቴን ቤከርና ረዳቱ ጆኒ ዶት ከፓን አሜሪካ የፎየንስ ጣቢያ ኃላፊ ጋር የራዲዮ
መልእክቶችን እየገመገሙ የአትላንቲክ አቋራጭን በረራ ስለማድረግና አለማድረግ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ጉባኤ በተቀመጡበት ክፍል ኤዲ ገብቶ ተሰየመ፡

በአይሮፕላን በረራ ሳይንስ ቁልፍ ጉዳይ የነፋሱ ጥንካሬ ነው፡፡ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ ከጠንካራው ነፋስ ጋር እየታገሉ ነው በረራው የሚካሄደው፡ ከፊት ለፊት የሚመጣውን የንፋስ ግፊት ለመሸሽ ሲሉ ፓይለቶች
በተደጋጋሚ ከፍታቸውን ለመለዋወጥ ይገደዳሉ፡ ይህም ቴክኒክ በበረራው
ሳይንስ ‹ነፋሱን ማሳደድ›› ይባላል፡ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ያለ ነፋስ ግፊቱ ያነሰ
ቢሆንም አይሮፕላኑ ዝቅ እያለ በበረረ ቁጥር ከመርከብ ወይም ባህር ላይ ከሚዋልል የበረዶ ቋጥኝ ጋር ሊላተም ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚመጣን ንፋስ ግፊት ለመቋቋም በርካታ ነዳጅ ማቃጠል ይጠይቃል፡ ኃይለኛ የንፋስ ግፊት ካለ ከአይርላንድ እስከ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ከሁለት ሺህ ማይል
በላይ ለመብረር የሚበቃ ነዳጅ አይሮፕላኑ መያዝ ስለማይችል የነዳጅ
እጥረት ሊያጋጥም ይችላል፡ በዚህም ምክንያት በረራው ለሌላ ቀን ሊተላለፍ
ስለሚችል የአየሩ ጠባይ እስከሚሻሻል ተጓዦች በሆቴል ሊቆዩ የሚችሉበት
አጋጣሚ ይፈጠራል፡

የዚህ ዓይነት የአየር መዛባት ቢከሰት ካሮል አንን ምን ይውጣት ይሆን?

የአየር ጠባይ ሪፖርቱ ነፋሱ ከባድ መሆኑን፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ደግሞ ከባድ ማዕበል እንዳለ ያመለክታል፡፡ አይሮፕላኑ ሙሉ ሰው ጭኗል፡
ስለዚህ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ሁሉ ነገር በጥንቃቄ መሰላት አለበት፡፡ የአየሩ
ጠባይ መጥፎ መሆን የኤዲን ጭንቀት አባባሰው፡፡ ሚስቱ ካሮል አን በወዲያኛው የውቅያኖስ ጥግ በጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ወድቃ እሱ እዚህ አየርላንድ ውስጥ ተጣብቆ መቅረቱን
ሊቋቋመው የሚችለው ነገር
አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምግብ ይሰጧት ይሆን? የምትተኛበት ቦታስ አላት
ይሆን? ብርድስ ይመታት ይሆን?› እያለ ያስባል።

የአትላንቲክ ውቅያኖስን አካባቢ የሚያሳየው ማፕ ጋ ሄደና ቶም ሉተር የሰጠውን አይሮፕላኑ እንዲያርፍበት የሚፈለግበትን ቦታ ተመለከተ፡፡ ቦታው
ተጠንቶ የተመረጠ ነው ከካናዳ ጠረፍ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቆ ቤይ አፍ
ፈንዲ› የሚባል በጠረፉና በአንድ ትንሽ ደሴት መካከል የሚገኝ ቦታ ነው:
ምንም እንኳን ባህር ላይ ለሚያርፉ አይሮፕላኖች ማረፊያነቱ ብዙም
ተመራጭ ባይሆንም ከገላጣው የባህር ክፍል የተሻለ ነው፡፡ ይህን ሲያውቅ ኤዲ ተስፋው ለመለመ፡ ቢያንስ የማረፉ ነገር ብዙ ችግር የለውም፡፡ ሉተር ሚስቱን በእጁ እንዲያስገባለትና እቅዱ እንዲሳካ አቅሙን በሙሉ አሟጧዐየተጣለበትን ግዴታ መወጣት አለበት፡

አሁንም ግን አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ እንዴት ሊያሳርፍ እንደሚችልዐመጨነቁ አልቀረም፡ በዚህ ቦታ እንዲያርፍ ያደረኩት አንዱ የአይሮፕላኑ ሞተር ስለተበላሽ ነው ቢል በሶስት ሞተር ሊሄድ እንደሚችል ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ስለሚያውቅ ይህ ምክንያት ብዙም አያስኬድም የአዕምሮውን ጓዳ ቢያስስም ተጨባጭ መፍትሄ አልመጣለት አለ፡፡
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሁለት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ይሄ ክስት ከተከሰተ ከ5 ዓመት በኃላ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ለመፈተን ዝግጅት ላይ እያለች  ድንገት እናትዬው በህይወቷ ለሁለተኛ ጊዜ  ክፉኛ ታመመች፡፡ አፋፍሰው ደሎ ሆስፒታል አስገቧት….ወደጎባ ወይም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ትባላለች ብለው ሲጠብቁ ከሶስት ቀን በኃላ ወደቤት መልሳችሁ ውሰዷት የሚል ትዕዛዝ ተሰጣቸው፡፡

ቀጥታ እየተውረገረገች ዶክተሩ ጋ ገባች፡፡

‹‹አቤት ምን ነበር?›

‹‹ስለእናቴ ጉዳይ ነበር››

‹‹ስለእናትሽ ምን?››

ዝልፍልፍ ብላ ደከማለች እኮ ….በህይወትና በሞት መካከል ሆና እየተመለከታችሁ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው...?

ካልቻላቸሁ አልቻልንም ብላችሁ ሪፈር ማለት ነው እንጂ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው….?ግልፅ አልሆነልኝም፡፡››

‹እስኪ ተረጋጋግተሸ ተቀመጪና ላስረደዳሽ..እንደው ስታስቢው ይሄንን ቀደም ተከተል ማናውቅ አድርገሽ ነው ምታስቢን ?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ አጋባችሁኛ››

‹‹ሁኔታውን እኮ ለአያትሽ አስረድቼቸዋለሁ...እሳቸው ቀስ ብለው ያስረዱሻል፡፡››

‹‹እና እናቴ …የእኔ ውዷ እናት …የሌላ አለም ፈጡርን  በፍቅር ጠብ ያደረገችው ተአምረኛዋ እናት እንደቀልድ በአንድ ወር ውስጥ ትሞታለች እያላችሁኝ  ነው?››

‹‹አይ እኛ አይደለም እንደዛ ያልነው.. እናትሽ ያለባቸው በሽታ ያለበት ደረጃ እና አሁን ባለው የሳይንስ ግኝት በሽታውን ለማከም ያለንን አቅም ከግምት በማስገባት ነው፡፡››

‹‹እና በቃ ውሳኔያችሁ እንደዛ ነው?››

‹‹አዝናለሁ…ለእሳቸውም የመጨረሻዎቹን ቀናቶች ወዲህ ወዲያ እያሉ ውጤት ለማይኖረው ነገር ከሚንገላቱ  በቤተሰባቸው እንክብካቤ ውስጥ ሆነው ቢያሳልፉ ይሻላቸዋል፡፡

‹‹እኔ እናቴን ካዳንኳት…ምን ትላለህ?››

‹‹ስለአንቺ የሰማሁትን ለማመን እገደዳለሁ››

‹‹ስለእኔ ምን ሰማህ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹የመላዕክት ዝርያ እንዳለብሽ››

‹‹አይ ያሉህ እንኳን እንደዛ አይደለም…የደቢሎስ ዝርያ አለባት ነው ሊሉህ የሚችሉት፡፡››

‹‹ያው ነው…ዳቢሎስም ሌላ ምንም ሳይሆን መላዐክ ነው…ለዛውም ከዋናዎቹ አንድና ዋነኛው የነበረ.በተወሰነ ያለመግባባት ከእግዚያብር የመኖሪያ ግዛት የተሰደደ…››

‹‹የተናገርከው ከልብህ ስለሆነ አስደስተሀኛል…ለማንኛውም ስለጮህኩብህ ይቅርታ.. እናቴን ወደቤት ወስዳታለሁ...እናም አድናታለሁ።››

‹‹እንግዲህ እንዳልኩሽ ነው….ለማንኛውም እቤት ብቅ እያልኩ አያቸዋለሁ..ድንገተኛ ነገር ተፈጥሮ ከፈለግሺኝም ደውይልኝ› ብሎ ቁጥሩን ሰጣት  ተቀበለችውና አመስግናለሁ ብላ ወጣች፡፡

ወዲያው ነበር እናቷን ይዛ ወደቤት የገባችው፡፡ግርግሩ ጋብ ሲል ወደ እናቷ መኝታ ቀረበችና…በቀናቶቸ በሽታ የሰለሉና የደከሙ እጆቾን በእጆቾ ውስጥ አስገብታ እየዳበሰች፡፡

‹‹ሀርሜ አይዞሽ እኔ ምንም እንድትሆኚ አልፈቅድም››

‹‹ልጄ በዚህ ጉዳይ እንድትጨነቂ አልፈልግም…እንደውም መሄድ እፈልጋለሁ።››ስትል መለሰችላት፡፡
እማ ምን ማለት ነው …እኔን ጥለሽ ወደየት ነው የምትሄጂው…አንቺ ከሌለሽ እኮ እኔም መኖር በጣም ነው የሚከብደኝ …ማን ነው የሚረዳኝ?›

‹‹ልጄ አንቺ የአባትሽ ልጅ ነሽ. .በጣም ጠንካራና የማትሰበሪ ነሽ…እኔ ብሄድ ምን አልባት አባትሽን አገኘው ይሆናል፡፡ምን አልባት መልሰን አንድ ላይ የመሆን እድል እናገኝ ይሆናል፡፡

‹አይ እንደዛ አይሆንም…የእሱ አለምና አንቺ ስትሞቺ የምትሄጂበት ቦታ አንድ መሆኑን በምን እርግጠኛ ሆንሽ? እንዲህ አይነት ቁማርማ እንድትጫወቺ  አልፈቅድም..በይ አሁን ደክሞሻል.. እረፊ .የሆነ ቦታ ደርሼ መጣሁ…››

‹‹ደግሞ ወዴት ልትሄጂ ነው?››

‹‹እማ ደግሞ የሆነ ቦታ አልኩሽ እኮ›ብላ ግንባሯን በመሳም ወጥታ ሄደች.. ግቢውን እንደለቀቀች ከጀርባዋ ንሰሯ እየተምዘገዘገ መጥቶ ተከሻዋ ላይ አረፈ.እርምጃዋን እልገታችም….በሀሳብ እየተብሰለሰለች ቀጥታ ከተማውን ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ነው የሄደችው…እናትና አባቷ ተገናኝተውበት ወደነበረ ልክ እንደቤተመቅደስ እያየች ወደ አደገችበት ቦታ ነው የሄደችው፡፡እንደደረሰች ንስሯ ከትከሻዋ ለቆ ተነሳና በአካበባቢው ካሉት ብዛት ያላቸው ግዙፉ ዛፎች መካከል አንዱ ላይ አረፈ.እሷም ልብሷን አወላልቃ ዛፉ ላይ እስከግማሽ እየተንጠላጠለችና እየተሳበች ወጣችና አስር ሜትር ከፍታ ላይ ከደረሰች በኃላ ዘላ እየተምዘገዘገች ወንዙ ውስጥ ቦጭረቅ ብላ ገባች…ከዛ ወደውስጥ ሰመጠችና  የሆነ ሚስጥራዊ ምርምር እንደሚያካሂድ የባህር ውስጥ አሳሽ ውስጥ ለውስጥ ትንፋሿን ተቆጣጥራ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሰች.፡፡
ግማሽ ለሚሆን ሰዓት ከዋኘች በኃላ የድካም ስሜት ሲሰማት ወጥታ ልብሷን ለበሰች፡፡የመጨናነቅ ስሜቷ አሁን ቀለል ብሏታል…ወደዚህ  ቦታ የምትመጠጣው ለመታደስ ነው.ከአባቷ መንፈስ ጋር ለመገናኘት..እሱ የረገጣቸውን የወንዙን ወለል ለመርገጥ ፤እሱ የተነፈሰባቸውን ቦታዎች እሷም ልትተነፍስባቸውና ከእሱ ጋር ያላትን የመንፈስ መስተጋብር  ለማጎልበት ነው....እናም ደግሞ ምን አልባት አንድ ቀን ቡልቅ ብሎ ከዚህ ከውሀው መሀል በመውጣት ተጠምጥሞ ይስመኛል…በሚል ድብቅ ምኞትም በመጓጓት ነው እንደዛ የምታደረግው;፡
ለባብሳ እንደጨረሰች ‹‹..ጀግናዬ የት ነህ?››ስትል ንስሯን ጠራችው.. እየተምዘገዘገ መጣና ከፊት ለፊቷ ካለ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አረፈ..
‹‹እሺ ና ተከተለኝ።›› ብላው ወደጥቅጥቁ ጫካ ተራመደች…ወደ ውስጥ ጠልቃ ገባችና የምትፈልገው ቦታ ስትደርስ ከዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ቅጠሎችን እየለመለመች መሬት አነጠፈችና እላዩ ላይ ተደላድላ ተቀመጠች…መጥቶ ከጎኗ ተቀመጠ

‹‹እንድናወራ ነው እዚህ የመጣሁት..››

‹‹እየሰማሀኝ ነው አይደል?›

እየሰማት መሆኑን እንድታውቅ አእምሮን ከፈተላት.

‹‹አዎ እንደዛ ነው…እናቴ እንድትድን አፈልጋለሁ።››

‹‹አይቻልም››የሚል መልስ ሰጣት

‹አይ ይቻላል…አንተ የሆነ ተአምር መስራት አያቅትህም ..ከፈለክ ከአባቴ ጋር ተገናኝና እናቴን ማጣት እንደማልፈልግ ንገረው››

‹‹አይቻልም››ፍርጥም ብሎ መለሰላት፡፡

‹‹ኡፍ..እንግዲያው እሷ ከሞተች እኔም መኖር አልፈልግም…. ይሄንን እወቀው››

‹አንቺ ከሞትሽ እኔም አጠፋለሁ››ብሎ ልክ በሞተችበት ቅፅበት እሱ እንዴት ድርቅርቅ ብሎ እንደሚሞትና ከደቂቃዎች በኃላ መላ አካሉ እንደድቄት ተበታትኖ እንደሚበን አሳያት፡፡ እዝን አላች፡፡

እንዲህ የእሱ ህይወት ከእሷ መኖር ጋር እንደተያያዘና ስትሞት ሟች እንደሆነ ፈፅሞ አታውቅም ነበር..እና እንደዛ በመሆኑ በጣም አዘነች…ቢሆንም ግን ሀሳቧን ለመቀየር ምንም እቅድ የላትም.. መልፈስፈስን አልፈለገችም፡፡
"በጣም እወድሀለሁ.. ታውቃለህ አይደል?.ግን ደግሞ እናቴን ከምንም በላይ ፤ከማንም በላይ ነው ምወዳት እና እንዳልኩህ እናቴ ከሞተች እኛም አብረናት እንሞታለን ማለት ነው።››

የመጨረሻ ውሳኔዋን ከምትናገረው ንግግር ሆነ ከውስጧ ልቧን በማንበብ ከተረዳ በኃላ ከጎኗ ብተት ብሎ ተነሳና ሰማይ ጠቀስ ዛፎችን አልፎ በረረ....ቀጥታ ጭጋጋማውን ደመና አልፎ ተሰወረ.. እዛው በተቀመጠችበት ወደላይ አንጋጣ በአይኖቾ ሸኘችውና ወደትካዜዋ ተመለሰች፡፡