ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
183K subscribers
280 photos
1 video
16 files
200 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
📕ታአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_አምስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ነገርኩሽ እኮ… ዛሬ እሮብ ነው አይደል እስከቅዳሜ አልጋሽን ለቀሽ ያልደረሻቸውን ለቅሶዋችና የታመሙ ወዳጆችሽን እየዞርሽ ትጠይቂያለሽ…››

‹‹እንደአፍሽ ያድርገው››

‹‹እማ እኔ እንዲህ በቁም ነገር ተናግሬ ያልሆነ ነገር አለ…ደግሞ ጀግናዬ ነው መልዕክቱን የነገረኝ…ምን አልባት መድሀኒቱን አባቴ ማለቴ  የድሮ ፍቅረኛሽ ይሆናል በሚስጥራዊ መንገድ  በእሱ በኩል የላከልሽ››

እናትዬዋ በንግግሯ ባለመደሰት ኮስተር ብላ‹‹አባትሽ የድሮ ፍቅረኛዬ ሳይሆን ….የዘላለም ፍቅረኛዬ ነው።››አለቻት፡፡

"እሺ ይሁንልሽ…አሁን ቻው ያዶት ልንሄድ  ነው…ደስ ስላለኝ በዚህ በጥዋት ሂጄ መዋኘት እፈልጋለሁ።››

‹‹እንዴ ቁርስ አፍሽ ላይ ጣል ሳታደርጊ?››

‹‹አይ ስመለስ››ብላ ንስሯን እንዳቀፈች ከቤት ወጣችና ግቢውንም ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ጀግናዬ ስላደረጋችሁት ነገር በጣም አመስግናለሁ...ማለት አንተና አባቴ….ቃል በገባሁት መሰረት የዘላለም ውለታችሁ አለብኝ...ግን እናቴ ከአመት በኃላ ቀጣይ ዕድሜ እንዲኖራትስ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ…? መቼስ ከባድ ነገር ነው የሚጠበቅብኝ?››

‹‹አይ ቀላል ነው››

‹‹ቀላል ነው ስትል? 

‹ከእናትሽ ጋር መኖር ማቆምሽ ለእሷ ተጨማሪ ዕድሜ ይሰጣታል፡፡

አንቺ ከተፈጥሮሽ የተነሳ ፍቅርሽ እሷን ለመኖር ያላትን ኃይል ይመጣል….አንቺ ስትወጂም ሆነ ስትጠይ እኩል ነው ሰውን ምትጎጂው….በፍቅርም ሆነ በጥላቻ የተለየ ትኩረት ያሳረፍሽበት ማንኛውንም የሰው ልጅ ኃይሉን ነው ምትመጪበት… ያ ኃይል ደግሞ ከዕድሜው ላይ ይጎመዳል..ምን አልባት እናትሽ አንድ ቀን ከአንቺ ጋር ለማሳለፍ ከእድሜዋ ላይ ሀያ ሰላሳ ቀን መገበር ይጠበቅባት ይሆናል…"
የምትሰማውን ዜና ተቋቁማ ወደፊት መቀጠል አልቻለችም …ከመንገድ ጎራ ብላ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባችና የተደላደለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠች… ንስሯን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠችው…. ከንፈር የማይንቀሳቀስበት ፤አፍ ማይከፈትበት ድምፅ አልባ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹.እና አሁን ከእናቴ አልለይም የሆነው ይሁን የምትይ ከሆነ አንድ አመቱን ከእሷ ጋር አሪፍ የምትይውን የደስታ ጊዜ አሳልፊ…አይ እናቴ አርባ ሀምሳ አመት መኖር አለባት የምትይ ከሆነ ግን ዛሬ ነገ ሳትይ ይሄን ሀገር ለቀን መሄድ አለብን፡፡››

‹‹ግን እናቴን ምን እላታለሁ?››
‹‹እውነቱን ንገሪያት..እርግጥ አትስማማም…ግን ቢሆንም ንገሪያትና አንቺ ውሳኔውን ወስኚ።››

‹‹ቆይ ብዋሻትስ?››

‹‹ምን ብለሽ?››

‹‹ለምሳሌ እኔ አብሬአት መኖር ምቀጥል ከሆነ በሽታው ወደእኔ ተላልፎ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደምሞት እንዳወቅኩ ብነግራት የእኔን መሞት ማሰብም ስለማትፈልግ በፍጥነት የምትስማማ ይመስለኛል›"
ላቀረበችው ሀሳብ ከአእምሮው የድጋፍ ወይም የተቃውሞ መልስ ለማንበብ ስትጠብቅ….እሱ በተለየ ብርሀን የደመቁ አይነት ቀለማትን ረጨ.እንዲህ የሚያደረገው በነገሮች ሲደነቅ ወይም ሲደሰት እንደሆነ ታውቃለች፡፡

‹‹ምነው የማይረባ ሀሳብ ነው እንዴ?››

‹‹አረ አባትሽም እንዲህ  አይነት ሸር በዚህ ፍጥነት ማሰብ መቻሉን ስለተጠራጠርኩ አድንቄሽ ነው..››

‹ዲቃላ መሆን ጥቅሙ እኮ ይሄ ነው…ግን አሁን የት ነው የምንሄደው ..ማለቴ የት ሀገር ብንኖር ይሻላል?፡፡››

‹‹ደስ ያለሽ ቦታ..ደስ ያለሽ ሀገር››

‹‹ምን ሰርተን ነው የምንኖረው…ትምህርቴን ገና የ10 ክፍል ማትሪክ እንኳን አልተፈተንኩ..ከብት ከማርባት እና እትክልቶችን ከመንከባከብ ውጭ ምንም ሌላ ማውቀው ሞያ የለኝም››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ አንቺ እኮ ማንኛውንም ሞያ ለመልመድ ከሌላው የሰው ልጅ በመቶ እጥፍ በላይ አቅም ነው ያለሽ....በዛ ላይ ታንዛኒያ የሄድን ጊዜ ኬኒያ ድንበር ያገኘነውን ዳይመንድ አለን....በጣም ሀብታም ነሽ እኮ››

‹‹ማለት አባቴ የሌላ አለም ፍጡር ስለሆነ?››

‹‹አዎ ለሰው ልጆች ጥበብ እና እውቀትን ያስተማሩት እኮ አባትሽ እና ከእሱ ጋር ከገነት የወደቁት ጭምር ናቸው››

‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው ማለት ነው?››

"አዎ..በከፊል እውነት ነው››
‹‹በከፊል ስትል.ከፊሉስ እውነት?››

‹እሱን ሌላ ጊዜ..እንድነግርሽ ሲፈቀድልኝ?››

‹‹እንዳልክ …ግን የአባቴ ዘመዶች ለሰው ልጆች ያሰተማሯቸው ዕውቀትንና ጥበብን ብቻ ነው …?››

‹‹አይ እሱማ ክፋትና ተንኮልን…ግድያንና ዘረፋንም ጭምር አስተምረዋል፡፤››

‹‹እና የሰው ልጅ ባለውለታ ናቸው ነው የሚባለው ወይስ ጠላት?››

‹‹አይ እኔ ምለው ማንም ቢሆን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ለማግኘት መክፈል ሚገባው ክፍያ አለ…አባትሽና ወገኖቹ ለሰው ልጆች ያበረከቱት ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ከሰው ልጆችም የነጠቁት መልካምነቶች አሉ››

‹‹ሳስበው ሳስበው የሰው ልጅ ግን ውለታ ቢስ እኮ ነው፡፡

በየቤተክርስቲያኑም ሆነ መስጊዱ ምሰማው የክፋት ሁሉ ምንጭ ሰይጣን እንደሆነ ጥበብና እውቀትን ደግሞ እግዚያብሄር እንዳስተማራቸው  ነው የሚያወሩት››
መልስ ብትጠብቅም ምንም አልመለሰላትም. እዕምሮዋን ዘጋባት

‹‹ምነው? አንተም እግዚያብሄርን ትፈራዋለህ እንዴ?›

አሁንም የተቀየረ ነገር የለም..ለንግግሯ ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት እምሮውን እንደቆለፈ በዛው ገፋበት…ተደነቀች፡፡

‹‹የኃያላን  ኃያል ፤ የጌቶች ሁሉ ጌታ እሱ እግዚያብሄር ነው..የሚል ስብከት መስማቷን አስታወሰችና መልሳ በልቧ አኖረችው…
ሄዶ ሄዶ የሁሉ  ነገር ማሰሪያና የኃይሎች ሁሉ ጥቅል ኃይል እግዚያብሄር ከሆነ ታዲያ የእነ አባቴ ቀድሞ መንፈራገጥ ለምን ይሆን ?ብላ እራሷን ጠየቀችና  ..መልሳ ሌላውን ጥያቄ ተወችና 
‹‹ በል ተነስ እንሂድ.. ወደየት ሀገር እንደምንሄድ አስብበት.››ብላ መንገዷን ስትቀጥል እሱ ክንፍን አማቶና በአየር ላይ ተርገፍግፎ እሷን በመተው በተቃራኒው ወደ ደኑ ውስጥ ገባ..‹‹እርቧሀል ማለት ነው ?››ብላ እሷ ለመዋኘት ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

    ይቀጥላል

#ክፍል 26,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄