ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
196K subscribers
280 photos
1 video
16 files
208 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"

ባሮን ጋቦን ፊታቸው በድንጋጤ አመድ መስሏል ለሎርዱ መልስ ሊሰጡ አሰቡና ትተውት ፊታቸውን ወደ ሃርትማን መለሱ፡
ሆዳቸው እያረረ በፈገግታ አለፉት፡ ነገር ግን እሳቸው ከናዚ ጀርመን አምልጠው የመጡ በመሆናቸው ከዚህ በላይ ብዙ ክፉ ነገር የደረሰባቸው ስለሆነ ይህ ስድብ ለእሳቸው እንደ ምርቃት የሚቆጠር ነው።

ማርጋሬት ባሮን ጋቦንን ተመለከተች፡ ሎርዱ ያሉትን ከምንም ባለመቁጠር ማንኪያቸውን አንስተው ሾርባቸውን መጠጣታቸውን ቢቀጥሉም እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ስላስቸገራቸው ሰደርያቸው ላይ ሾርባው ተንጠባጠበ፡፡ውስጣቸው
የሚንተከተከው ንዴት ግን
መጠጣት ስላላስቻላቸው ማንኪያቸውን አስቀመጡት።

ማርጋሬት የባሮኑ ብስጭት ልቧን ነካው። በአባቷም ስድብ በጣም ተናደደችና ‹‹ድፍን አውሮፓ የሚያከብራቸውን ሁለት ትላልቅ ሰዎች እንደዚህ መሳደብ የለብህም›› አለቻቸው በድፍረት።

‹‹ሁለት የታወቁ ይሁዲዎች በይ›› አሉ አባቷ።

‹‹ይሁዳዊያን አያቴን ረሳሃቸው አባባ?›› አለ ፔርሲ ሁሉን ነገር ቀልድ አድርጎ።

አባት ወደ ልጃቸው ዞሩና ጣታቸውን ፔርሲ ላይ እያወዛወዙ ‹‹እንዲህ
ያለውን የማይረባ ቀልድህን ተወኝ ሰማኸኝ!›› ሲሉ አፈጠጡበት

ፔርሲ ነገሩ ስላላማረው ‹‹መጸዳጃ ቤት ልሂድ አሞኛል›› አለና ትቷቸው ሄደ፡ ማርጋሬት እሷና ፔርሲ አባታቸውን መቃወም እንደሚችሉና ምንም እንደማያመጡ አውቃለች፡ ይህም አንድ እድገት ነው ስትል አሰበች፡

‹‹ከቤታችን አባረው እንድንሰደድ ያደረጉን እነዚህ ሰዎች መሆናቸውን
እንዳትረሺ›› አሏት አባት ማርጋሬትን፡፡ ‹‹ከኛ ጋር የሚሄዱ ከሆነ ስርዓት
መማር አለባቸው›› አሉ፡

‹‹ቃ!›› ሲል ተደመጠ አንድ ድምጽ

ማርጋሬት ድምጹ ወደመጣበት አቅጣጫ ዞረች፡ ይህን ያለው ፎየንስ
ላይ የተሳፈረው መርቪን ላቭሴይ ነው፡፡ መርቪን እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ
የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ ጠረጴዛ ተደግፎ ቆሟል። አስተናጋጆቹ በድንጋጤ
ደርቀው ቆመዋል፡ ጠብ ይነሳል ብለው ፈርተዋል፡ ላቭሴይ የሰማይ ስባሪ
የሚያክል፣ ዕድሜው በአርባዎቹ ውስጥ የሚገመትና ጸጉሩ ገብስማ መልከ መልካም ሰው ነው፡፡ ሲያዩት የሚፈራው ነገር ያለ አይመስልም፡ የለበስው
ልብስ ውድ መሆኑ ያስታውቃል፡

‹‹ይህን አመለካከትህን ለራስህ ያዘው›› አላቸው በሚያስፈራ ድምጽ“

‹‹አንተን አያገባህም!›› አሉ ኦክሰንፎርድ።
‹‹ያገባኛል!››
ማርጋሬት አስተናጋጁ ውልቅ ብሎ ሲሄድ አየችው፡ የአይሮፕላኑን አስተናጋጆች ሊጠራ እንደሄደ ተገንዝባለች፡፡

‹ስለ እኚህ ሰውዬ ምንም አታውቅም፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማን ባንተ አፍ የሚጠሩ ሰው አይደሉም፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ሳይንቲስት ናቸው››
አለ ከመቆርቆር በመነጨ ብርቱ ስሜት፡

‹‹የፈለገውን ቢሆን ግድ የለኝም›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡
‹‹አንተ ግድ ባይኖርህ እኔ ግድ ይኖረኛል፡ ስለዚህ ይህን የከረፋ አስተሳሰብህን አስተካክል›› አለ ላቭሴይ፡

እኔ የፈለኩትን ማለት እችላለሁ›› አሉና ኦክሰንፎርድ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡
ላቭሴይ በጠንካራ እጁ የኦክሰንፎርድን ትከሻ ተጫነና አስቀመጣቸው፡፡
እንዳንተ ካሉ ሰዎች ጋር ነው ጦርነት የገጠምነው›› አለ፡፡

ኦክስንፎርድም በደከመ ድምጽ ‹‹ልቀቀኝ! ልቀቀኝ!›› ሲሉ ተወራጩ።

‹‹አፍህን የምትዘጋ ከሆነ ነው የምለቅህ››

‹ካፒቴኑን እጠራለሁ›› አሉ ኦክሰንፎርድ፡

‹‹አያስፈልግም!›› አለ ሌላ ድምጽ፡ ካፒቴን ቤከር ሙሉ ዩኒፎርሙን ለብሶ ቆሟል የአዛዥነት መንፈስ ይታይበታል፡ ‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ ብትመለስ?›› አለ፡

‹‹እኔ ወደ ቦታዬ እመለሳለሁ›› አለ ላቭሴይ ‹‹ነገር ግን በመላው
አውሮፓ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው ሳይንቲስት በዚህ ሰካራም ሲሰደቡ
በዝምታ ማለፍ አልችልም፡››

‹‹ሚስተር ላቭሴይ ወደ ቦታህ›› አለ ቤከር፡

ላቭሴይ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ወደ ኦክሰንፎርድ ዞር አለና ‹‹ሎርድ ኦክሰንፎርድ የተናገሩት
ነገር አስነዋሪ ነው፡ አንድ ተሳፋሪ ሌላውን ተሳፋሪ መስደብ አይችልም፡››

ማርጋሬት አባቷ የቤከርን ምክር እንዲቀበሉ ብትፈልግም እሳቸው ግን
ጠብ ጠብ እንዳላቸው ነው፡፡

‹‹አንተ ይሁዲ ብዬ ነው የጠራሁት፡፡ ይሁዲነቱን ሊክድ ነው!›› ሲሉ
አምባረቁ፡፡

‹‹አባባ ምነው ዝም ብትል›› ስትል ተቆጣች ማርጋሬት፡

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ማንንም እንዲሳደቡ አልፈቅድም›› አለ ቤከር፡

አባት ስድባቸውን ቀጠሉ ‹‹በይሁዲነቱ ያፍራል እንዴ?›› አሉ፡

ቤከር በቁጣ ገነፈለ፡፡ ‹‹ይሄ የአሜሪካ አይሮፕላን ነው ጌታዬ እኛ ደግሞ ጥብቅ የስነ ምግባር ደንብ እንከተላለን፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎችን መሳደብ
ካላቆሙ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው በሚያርፍበት ቦታ ላይ ለፖሊስ አስረክቦታለሁ፡፡ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ የሚከሰት ቢሆንም እንዲህ
አይነት ነገር ሲገጥም አየር መንገዱ ህግ የጣሱ ሰዎችን ይከሳል›››

ሎርዱ የክስ ነገር ሲነሳ ፍርሃት ፍርሃት አላቸው፡ የሚመጣውን በመፍራትም አፋቸውን ዘጉ፡፡ ማርጋሬት በእጅጉ በሃፍረት ተሽማቀቀች አባቷን ዝም ለማሰኘት ብዙ ብትጥርም የአባቷ አድራጎት አንገት
አስደፍቷታል ቅሌት ውስጥ የገቡት አባቷ ስለሆኑ::

‹‹ወደ መቀመጫችን እንመለስ›› አሉና አባት ተነሱ ወደ ሚስታቸውም ዞር ብለው ‹‹አንሄድም የኔ ውድ?›› አሏቸው።

ሁሉም ሰው ማርጋሬት ላይ አፈጠጠባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ከየተ መጣ ሳይባል ከመቀመጫዋ ኋላ መጥቶ ወምበሯን ያዝ አደረገላት” ሌዳ ማርጋሬት›› አለ በአክብሮት በመጠኑ አንገቱን ዝቅ አድርጎ ማርጋሬት በሄሪ አድራጎት ልቧ ተነካ፡፡

እናት ጅንን ብለው ፊታቸው ላይ ምንም የእፍረት ምልክት ሳይታይባቸው ባላቸውን አስከትለው ወጡ፡፡

ሄሪ ለማርጋሬት በጨዋ ደምብ ክንዱን ሲሰጣት ክንዷን ከክንጿ ጋ ቆላለፈች፡፡ ይሄ ትልቅ ነገር ባይሆንም ለእሷ ግን አንድ የሆነ መተማመን ፈጥሮላታል፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በእፍረት ቁንጫ አክላ የነበረችው ማርጋሬት በመጨረሻ በሄሪ እርዳታ በክብር ወደ ቦታዋ ተሸኘች፡፡ ከሄሪ ጋ ወደ መቀመጫዋ ስትመለስ ድምጹን አጥፍቶ አምባጓሮውን እንደ ትርኢት
ሲመለከት የነበረው ተሳፋሪ ከኋላ ሲንሾካሽክ ሰማች፡

‹‹አንተ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ እንዴት እንደማመሰግንህ አላውቅም›› አለችው
ሄሪን፡፡

‹‹የተፈጠረውን አታካሮ ስመለከት ነበር፡፡ በአባትሽ አድራጎት አንገትሽን
ስትደፊ ሳይ አሳዘንሽኝ፡፡››

‹‹እንደዚህ ቀን በሃፍረት ተሸማቅቄ አላውቅም›› አለች እየተንገፈገፈች

አባቷ ግን አሁንም አደብ አልገዙም፡፡ ‹‹አንድ ቀን ይቅርታ ይጠይቁ ይሆናል እነዚህ ጅሎች!›› አሉ፡ ሚስታቸው አንድ ቃል ሳይተነፍሱ እጥግ
ተቀምጠው ባላቸውን በአግራሞት ያይዋቸዋል፡፡

‹‹ይህ ጦርነት ያበቃና! ምናለ በሉኝ›› አሉ
አባት፡፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡

‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡››

‹‹ፎቶው አለሽ?›› 

‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ‹‹ተከተይኝ ››አለቻት እና  ወደበረንዳው ወጡ…ንስሯ ተረጋግቶ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ስታየው እንደመፍራትም ግራ እንደመጋባትም አለችና፡፡

‹‹ምን አይነት አሞራ ነው..አይፈራም እንዴ? ››

‹‹የእኔ ነው››

‹‹አሞራው?››

‹‹አዎ…ግን አሞራ ሳይሆን  ንስር ነው…የእኔ ንሰር ፡፡››

‹‹ምን ያደርግልሻል?፡፡››

‹‹እሱማ ለእኔ ብዙ ነገሬ ነው… የፈለኩትን ነገር ያደርግልኛል..እኔ እንደውም የሚገርመኝ እኔ ለእሱ ምን አደርግለታለሁ ሚለውን ነው››

‹‹ይቅርታ ግን ያስፈራል…. .በተለይ አይኖቹ እና መንቁሩ…››እሷን ችላ አለቻትና ሞባይሏ ላይ ያለውን የልጅቷን ፍቅረኛ ፎቶ ለንስሯ እያሳየች ‹‹….እንርዳት መሰለኝ…እወነቱን ማወቅ መብት አላት››ስትለው ክንፎቹን አርገፈገፈና   መቀመጫውን ለቆ በአየር ላይ ተንሳፈፈ…እሷ  በርግጋ ወደኃላዋ አፈገፈገች….ወደላይ ተምዘግዝጎ አየሩን እየሰነጠቀ ከፍታውን ለአይን መታየት እሰከማይችል ድረስ ርቆ ተሰወረ፡

‹‹ቁጭ በይ› አለቻትና በረንዳው ላይ ካለው ወንበር አንዱን እያሳየቻት እሷ ንስሯ በለቀቀላት ወንበር ላይ እየተቀመጠች፡፡

‹‹ሄደብሽ እኮ …እንዲህ እርቆ ሄዶ አሁን አውቆ ተመልሶ ይመጣል?፡፡››

‹‹አዎ የእኔ እወቀት ዘጠና ፐርሰንቱ ከእሱ የማገኘው ነው…ንስሮች በተፈጥሮቸው በጣም ልዩ የሆኑ የአእዋፋት ዝርያዎች ናቸው፡፡እይታቸውም ጥልቅ አስተሳሰባቸውም ስል እና የተሞረደ  ነው፡፡ከዛም በላይ ግን የእኔ ንስር የተለየ ነው፡፡እንዴት የሚለውን ነገር ላብራራልሽ አልችልም..ግን አሁን የሚያደርገውን ታያለሽ ..ከዛ እራስሽ ትፈርጂያለሽ››

‹‹እንዴት?››

‹‹አሁን ፍቅረኛሽን ፎቶ እያሳየሁት ሳወራው አላየሽም?››

‹‹አይቻለው.ግን እናቴም ሲጨንቃት እና በሆዷ ነገር ሲገባ ከምታልባት ላም  ጋር ታወራ ነበር…እንደውም ለእሱ ስታወሪ እናቴ ነች ትዝ ያለችኝ፡፡››

‹‹አይ ይሄ ይለያል..አሁን ያንችን ችግር ማለት ስለፍቅረኛሽ ትክክለኛ ነገር እንዲያጣራልኝ ነው የላኩት››

‹‹እንዲት አድርጎ››

‹‹በቃ የተለየ ችሎታ አለው… ማንኛውም ነገር ካተኮረበት የውስጡን ሀሳብ እና ጠቅላላ ታሪኩን ማንበብ ይችላል…እኔ ደግሞ ከሱ አዕምሮ ማንበብ እችላለሁ..ወይም እንዳውቀው አዕምሮውን ይከፍትልኛል..ቅድም ያንቺን ታሪክ ላውቅ የቻልኩት ከእሱ ነው፡፡››

‹‹እኔ አላምንም ..ንስር ይሄን ሁሉ…. እንዴት  ተደርጎ?››

‹‹አየሽ እንዳልኩሽ የእኔ ንስር ልዩ ነው..ከእኔ  ጋር ያለውም ትስስር ከተፈጥሮ ክስተቶች እንደ አንድ ነው..ያም ሆኖ ግን እንዲሁ ንስር እና የሰው ልጅ ከጥንትም ጀመሮ የመንፈስ ትስስር እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡፡ሌላውን ተይና  በሀገራችን ጥንታዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ንስር የትንሳኤ ምልክት ነበር… በምጥቀት ማሰብ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር መንፈስ ተምሳሌ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡በግብጽ ደግሞ መቃብራቸውን ጋንኤል እንዳይደፍረው የንስር ምስል ከመቃብሩ በራፍ ላይ ያስቀምጡ ነበር…ያ የንስር ምስል የጋንኤሉ መንፈስ አልፎት ወደውስጥ ሊጋባ ስለማይችል እሬሳቸው ከጥቃት የተጠበቀ ይሆናል ብለው ያምናሉ..፡፡
የጲላጦስ ሀገር የሆነችው ግሪክ ደግሞ ከአመልክቶቾ ውስጥ አንድ የሆነው የአማልዕክቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው ዜዎስ በንስር ይመሰል እንደነበረ ይነገራል፡፡በጥንት ጊዜ አሜሪካኖች  ደግሞ እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው ያለቸውን ጥልቅ ፍቅር ሚገልጽት የንስር ላባ በመስጠት ነው፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ሲራክም  ሶስት እራስ እና አስራ ሁለት ክንፎች ሳላለው ንስር በህልሙ ራዕይ አይቶ ነበር….የራዕይው ፍቺ በየተራ ስለሚነግሱ ነገስታት ሲገለጽለት ነበር…ንስር የኃይልን እና የስልጣን ምልክት ነው፡፡…››ስብከት የመሰለ ንግግሯዋን ተናግራ ሳትጨርስ….ዶክተሩ በራፋቸውን ከፍተው ወጡና ወደእነሱ መጡ

…‹‹.ሶፊ ደህና ነሽ?››

‹‹እንዴት አደሩ ዶክተር?››
‹‹አለሁ….ዛሬ እንግዳ ከየት አገኘሽ ?››አለት እንግዳዋ ላይ በማተኮር፡፡

‹‹አያውቋትም?››

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት ግን ያየኋት ይመስለኛል››

‹‹አዎ ከባሌ የመጣች የአክስቴ ልጅ ነች…ከዚህ በፊትም መጥታ ስለነበረ.. ተገናኝታችኋል››
‹‹ለዛ ነዋ ፊቷ አዲስ ያልሆነብኝ….በሉ ተጫወቱ አንዲት ቀጠሮ አላለችብኝ ..ከሰዓት እንገናኛለን ..›ብለው ተሰናብተዋቸው ወደመኪናቸው ማቆሚያ ጥለዋቸው ሄዱ
ሶፊያ ሳቋ  አፍኗት  ስለነበር እንደራቁላት ለቀቀችው

…‹‹ሳያውቁኝ ቀርተው ነው ወይስ አውቀው ነው?››

‹‹አይ ተምታቶባቸዋል…ያው ማታ መጠጥም ስለሚወሳስዱ ነው ቅር አይበልሽ››

‹‹አረ ምን ቅር ይለኛል ነገራቸው ገርሞኝ እንጂ››ብትልም ቅር እንዳላት ግን በግልፅ ከንግግሯ ቃና በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እዚህ ቤት ከጥዋት ጀምሮ የሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ይገርማል አይደል?››

‹‹ምን መገረም ብቻ ከአዕምሮም በላይ ነው….እኔ እንዲህ….››ንግግሯን ሳትጨርስ  ንስሩ እየተምዘገዘገ መጣና ከእነሱ ፊት ለፊት በአምስት ሜትር ርቀት ያህል በሚገኝ የጽድ ዛፍ ላይ ሲያርፍ ስለተመለከተች  አቆረጠችና …ምን እንደሚከሰት ለማወቅ መጎጎቷን በሚያስታውቅባት መንፈስ‹‹መጣ ››አለቻት፡፡

‹‹ትንሽ ታገሺኝ ››አለቻትና አዕምሮዋን ሰብሰባ  ትኩረቷን በሙሉ  ከንስሯ ጋር በማቋራኘት እምሮውን  ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መምጣትሽን ፍቅረኛሽ አያውቅም አይደል?፡፡››

‹‹አዎ..አንዴ በእሱ ክህደትና ዘረፋ የሞትኩት አንሶኝ ጭራሽ መምጣቴን ነግሬው ስሩ ቆሜ ሁለተኛ ሞት ልሙት እንዴ? አላደርገውም ….ፍቅሬን መልስልኝ ብዬ ልማፀነው..?ወይስ ብሬን መልስልኝ ልበለው?››

በንስሯ አእምሮ አሻግራ እያየች ያለችው ታሪክ አሰገርሟት፡፡‹‹ቆይ ቆይ…በዚህ ሰዓት ፍቅረኛሽ ምን እየሰራ እንደሆነ ታውቂያለሽ…?››ስትል ጠየቀቻት፡፡

‹‹ምን እየሰራ ነው..?.ከሚስቱ እየተዳራ ወይም ልጁን እያጫወተ ይሆናል››ብስጭት እና ቅናት በተቀላቀለበት ድምፀት መለሰችላት፡፡

‹‹አይደለም …ትናንትና ወደ  ጊኒጪ ሄዶ እናትሽን  አምጥቶ ግሩም ጠቅላላ  ሆስፒታል እያሳከማቸው ነው…››

‹‹የእኔን እናት .. ?ምን ሆና ነው…?››በድንጋጤና በመገረም .እናም ደግሞ ባለማመን ጠየቀች፡፡

‹‹አትደንግጪ ያው የተለመደው በሽታዋ ነው….ድሮም ከፍተኛ የጨጎራ ቁስለት እንዳለባት ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹ግን እኔን እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ያሰጠጉታል …እናቴ ምንም የሚያስታምማት እና ሚያሳክማት ሰው ብታጣ እንዴት ልጇን ከከዳ ሰው ጋር ትተባበረለች…?እኔ ይሄን ማመን አልችልም …፡፡ሌላው ይቅር እናቴ እንኳን ለስላሳ እና የዋህ ስለሆነች  ይቅር ልትለው ትችላለች… እህቴ ግን እርግጠኛ ነኝ ይቅር አትለውም ፤ እርግጥ ሁሉም ለእሱ የላኩለትን ብር አያውቁም …ግን በጣም እንደማፈቅረውና ላገባውም  እንደምፈልግ ከዛም አልፎ ቃል እንደተግባባን ግን በደንብ ያውቃሉ፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ…በጣም ነው የሚያፈቅርሽ፡፡››