ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
289 photos
1 video
16 files
240 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ሰባት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡

‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ››

‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን ሊዋጋ ሄዶ አፈር በልቶ የቀረ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ የእሱን አርማ አንስቼ አላማውን ዳር ለማድረስ እታገላለሁ››ደ አለች በወኔና በሀዘን፡

‹‹ትወጂው ነበር?»

በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡

አይኗ እንባ እንዳቀረረ ተመለከተና በሀዘኔታ ክንዷን ያዝ አደረጋት
‹‹አሁንም ትወጂዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምን ጊዜም ከልቤ አይጠፋም›› አለች የሹክሹክታ ያህል ‹‹ስሙ ኢያን ይባላል፡››

ሄሪ አሳዘነችው፡፡ ማርጋሬትን ደረቱ ውስጥ ወሽቆ ሊያፅናናት
ቢፈልግም በየት በኩል። ውስኪያቸውን እየጨለጡ ጋዜጣ የሚያነቡ በርበሬ
ፊት አባቷ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል፡ እንደ ምንም እጁን ሰደደና አጇን ጨመቅ አደረገው፡፡ እሷም ለማፅናናት መሆኑ ገብቷት
ፈገግ አለች።

‹‹እራት ደርሷል ሚስተር ቫንዴርፖስት›› አለ አስተናጋጁ፡ ሄሪ አስራ
ሁለት ሰዓት ከምኔው እንደደረሰ ገርሞታል፡ ከማርጋሬት ጋር የጀመረውን
ጭውውት ማቋረጡ አሳዝኖታል፡፡ እሷም የእሱ ጭንቀት ገባትና ‹ብዙ
የምንጫወተው ነገር አለ›› አለች ‹‹ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት አብረን
እንሆናለን››

‹‹ልክ ነሽ›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እንደገና እጇን ዳበስ አደረገና ‹‹በኋላ
እንገናኝ›› አላት፡፡

ምስጢሩን በሙሉ የነገራት አጋሩ ሊያደርጋት ነው፡፡

ወደሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ክፍሉ ከሳሎን ቤት ወደ መብል ቤትነት ተለውጦ ሲያይ ተገረመ እያንዳንዳቸው አራት ሰዎች የሚቀመጡባቸው
ሶስት ጠረጴዛዎች የተዘረጉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ትንንሽ ጠረጴዛዎችም ይታያሉ፡፡ የእቃው አደራደር እንደ ምግብ ቤት ሲሆን ጠረጴዛዎቹ ጨርቅ
ለብሰዋል፡፡ በላያቸው ላይ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ስምና ምልክት ያለባቸው ብርጭቆዎች፣ ሰሃኖችና ናፕኪኖች ተቀምጠዋል። የመብል ክፍሉ ግርግዳ የአለም ካርታ ተለጥፎበታል አስተናጋጁ ሄሪን አንድ ሱፍ የለበሰ አጠርና ደልደል ካለ ሰው አጠገብ ወስዶ አስቀመጠው: ሄሪ የሰውዬው አለባበስ አስቀናው፡ ሰውዬው ክራቫት ያደረገ ሲሆን ውድ በሆነ ማያያዣ ጌጥ ከሸሚዙ ጋር አያይዞታል፡ ሄሪ እራሱን አስተዋወቀ፡ ሰውዬውም እጁን ለሰላምታ ዘረጋና ‹ቶም ሉተር እባላለሁ›› አለ፡፡ እጁ ላይ ያለው የወርቅ አምባር ከክራቫት ማያያዣው ጋር ይሄዳል፡፡ ለውድ ጌጣጌጥ ገንዘቡን
መበተን የሚወድ ሰው ማለት ይሄ ነው፡፡

ሄሪ የታጠፈውን ናፕኪን ዘረጋ፡፡ ሉተር አነጋገሩ የአሜሪካዊ ነው።
‹‹ከየት ሀገር ነው የመጣኸው?›› ሲል ሄሪ ጠየቀው ሰውዬውን
‹‹ፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ፧ አንተስ?››
‹‹ፊላደልፊያ›› አለ ሄሪ፡ ፊላደልፊያ የት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያልኖርኩበት ቦታ የለም፡፡ አባቴ የኢንሹራንስ ሰራተኛ
ነበር፡››

ሉተር አንገቱን ነቀነቀ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገም የሰውዬው ዝምተኛነት ለሄሪ ተስማምቶታል፡ ስለአኗኗሩ ሰው እንዲጠይቀው
አይፈልግም: በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው፡
ሁለት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በመጡና ራሳቸውን አስተዋወቁ፡ የበረራዐመሀንዲሱ ኤዲ ዲኪን ትከሻው የሰፋ፣ የደስ ደስ ያለው ፀጉረ ነጭ ሰው
ነው፡ ሁለተኛው ጃክ አሽፎርድ የሚባል ናቪጌተር ነው ፀጉረ ጥቁር ሲሆን
የለበሰው ዩኒፎርም ሄዶበታል።

ሰዎቹ እንደተቀመጡ በሉተርና በመሃንዲሱ መካከል የሆነ ጠብ እንዳለ
ሄሪ አስተዋለ።እራት ቀረበ፤ ሁለቱ የአይሮፕላን ሰራተኞች ኮካ ኮላ ሲመጣላቸው ሄሪ
ነጭ ቪኖ ቀረበለት፡ ቶምሉተር ማርቲኒ አዘዘ
ሄሪ እራት እየበላ ሳ
በአይሮፕላኑ መስኮት እያየ ስለማርጋሬትና ስፔን
ሄዶ ስለቀረው ቦይ ፍሬንዷ ያስባል፡፡ ስለእሱ አሁን ምን ያህል እንደምታስብ ማወቅ ፈለገ፡፡ ከእሷ እድሜ አንጻር አንድ አመት ትንሽ ጊዜ አይደለም፡፡

ጃክ አሽፎርድ ሄሪ በመስኮት እያየ መሆኑን ተገነዘበና ‹‹እስካሁን አየሩ
ጥሩ ስለሆነ እድለኞች ነን›› አለ፡

‹‹ሁልጊዜ እንዴት ነው አየሩ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ

‹‹አንዳንድ ጊዜ ከአየርላንድ እስከ ካናዳ በዝናብ የምንሄድበት ጊዜ አለ፡፡
‹‹አንዳንዴ ደግሞ በረዶና መብረቅ ያጋጥማል፡››

ሄሪ አንድ ጊዜ ያነበበውን አስታወሰና ‹‹በረዶ ከዘነበ ለአይሮፕላኑ አደገኛ አይደለም?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹በተቻለን መጠን ቀዝቃዛው የአየር ንብረት እንዳያገኘን እንጥራለን፡፡ለማንኛውም ተብሎ ግን አይሮፕላኑ ክንፎች ላይ የበረዶ ማቅለጫ ሸራ
ተደርጎለታል፡››

የመጪው የአየር ትንበያ ምን ያመለክታል?››

ጃክ ይህን መልስ ለመስጠት ሲጠራጠር አየና ስለአየሩ ባልጠየቅ ይሻል
ነበር›› ሲል አሰበ፡፡ ‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል››
አለ፡፡

‹‹ይህን ያህል መጥፎ ነው?›› ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹ዶፍ ዝናቡ መሃል ከገባን መጥፎ ነው፡ ሆኖም እኛ ከዶፍ ዝናቡ ራቅ ብለን እንበራለን›› አለ በሰጠው መልስ ብዙም ባለመተማመን፡፡

ቶም ሉተርም ቀጠለና ‹በዶፍ ዝናብ ውስጥ መጓዝ ምን ችግር አለው ሲል ጠየቀ።

ጃክ በዝርዝር አልተናገረም፤ ነገር ግን የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ፣ ቶም ሉተርን ለማስፈራራት ሲል ወደ እሱ እያየ ‹‹ልክ ባልተገራ ፈረስ የሚጋልቡ ይመስል ያነጥራል›› አለ፡

ሉተር ኤዲ ያለውን ሲሰማ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ኤዲ በተሳፋሪው
ፊት አፉ እንዳመጣ በመናገሩ ጃክ ገላመጠው:

ተሳፋሪዎቹ ሁለተኛ ዙር የእንቁራሪት መረቅ መጣላቸው:🤮

አሁን የሚያስተናግዱት ሁለቱ አስተናጋጆች ኒኪና ዴቪ ናቸው፡ ኒኪ ድብልብል ሲሆን ዴቪ ደግሞ ከአፍ የወደቀች ጥሬ ነው የሚያክለው፡፡

ሄሪ ሁለቱም ወንዳገረዶች ሳይሆኑ አይቀሩም› ሲል ገመተ፡ ታዲያ ቅልጥፍናው አስደስቶታል፡፡

ሄሪ በድብቅ እንደተከታተለው የበረራ መሀንዲሱ አዕምሮው በአንድ ነገር የተጠመደ ይመስላል፡፡

‹ሄሪ መሀንዲሱ ባህሪው አኩራፊ አይመስልም፡፡ ሲያዩት ተጫዋችና
ግልፅ ይመስላል› ሲል አሰበና እንዲናገር ለማበረታት ‹‹አንተ ምግብ በምትበላበት ጊዜ የበረራ ምህንድስናውን ስራ ማን ይሰራል?›› ሲል ጠየቀው
‹‹ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ነው›› አለ፡ ‹‹በፈረቃ ነው የምንሰራው፡፡ ጃክና እኔ ከሳውዝ ሃምፕተን በረራ ከጀመርንበት ከቀኑ
ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስለዚህ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት
ላይ እረፍት እናደርጋለን፡፡››

‹‹ካፒቴኑስ?›› ሲል ጠየቀ ቶም ሉተር ሀሳብ ገብቶት።
‹‹እንቅልፍ እንዳይዘው መድሃኒት ይውጣል፡ ከቻለ በተቀመጠበት ትንሽ ያንቀላፋል›› አለ ኤዲ፡ ‹‹ወደኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ስንደርስ
ፓይለቱ ምን አልባት ረጅም እረፍት ያደርጋል፡››

‹‹ስለዚህ በሰማይ በምንበርበት ጊዜ ፓይለቱ ይተኛል ማለት ነው?››
ሲል ጠየቀ ሉተር ሳያስበው ጮክ ብሎ፡

‹‹አዎ›› አለ ኤዲ በፈገግታ:፡ ሉተር ፍርሃት ፍርሃት እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ሄሪ ጨዋታው ሰላማዊ እንደሆነ በማሰብ ‹‹ወደኋላ
የማንመለስበት ሁኔታ ማለት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ኬድሮን ከዕንቅልፋ የነቃችው 11 ሰዓት አካበቢ ቢሆንም መኝታ ቤቷን ለቃ ወደ በረንዳው  የወጣችው 12 ሰዓት ተኩል ካለፈ በኋላ ነው፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ዘወትር እንደምታደርገው ዮጋ እየሰራች ነበር የቆየችው፡፡እቤቷን ለቃ ስትወጣ ንስሯ ተከትሏት ወጣ፡፡እሷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ማንበቧን ጀመረች ፡፡

ከ12 ሰዓት እስከሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ግቤዋ ውስጥ ባሉት ዛፎች ላይ የሰፈሩትን የተለያ አይነት የወፎች ህብረ ዝማሬ እየሰማች  ንፁህ በሆነ አዕምሮዋ ተረጋግታ በተመስጦ የምታነብበት ሰዓት ነው፡፡ከሀገሯ ወጥታ ለገጣፎ ከከተመች በኃላ ያዳበረችው አዲስ ልምድ ንባብ ነው፡፡ከመፅሀፍቶች ጋር ያላት ቁርኝት ለእሷም ለራሷ እስኪገርማት ድረስ በጣም የጠነከረ ሆኗል፡፡በአጠቃላይ ሱሰኛ ሆናለች ፡፡

አንድ ሰዓት አካባቢ  ከእሷ መኝታ ቤት ጎን ያለው የፕሮፌሰሩ በራፍ ተከፈተ ፡፡ያልጠበቀችው ክስተት ነበር፡፡ምክንያቱም  ደግሞ የፕሮፌሰሩ ባህሪ ከእሷ የተለየ ስለሆነ ነው፡፡እሳቸው እሰከ ለሊቱ አስር ሰዓት  ድረስ  ይቆዩና የተለየ ፕሮግራም  ከሌላቸው በስተቀር እስከ ጥዋቱ አራት ሰዓት ድረስ ይተኛሉ፡፡እና ስታነብ የነበረውን መጻሀፏን አጠፍ አድርጋ አይኗን ወደፕሮፌሰሩ በራፍ ላከች፡፡ከክፍሉ የወጡት ፕሮፌሰሩ ሳይሆኑ አንድ የ20 ዓመት አካባቢ ሚሆናት መልከ መልካም ሴት ነች፡፡ፈገግ አለች ፡፡
እኚ ሽማጊሌው ሙሁር ከአልማዝ የጠነከረ ጽናት እና የሚያስገርም ስብዕና ቢኖራቸውም ሴት ላይ ያላቸው አመል ግን የተለየ እና  የሚገርም ነው፡፡ካሉበት ዕድሜ ጋር የሚቃረን አይነት ነው፡፡እሳቸው ግን  ይሄንን ድክመታቸውን እንደድክመት ተመልክተውት አያውቁም፡፡ ለጤነኝነቴ እና በዚህ ዕድሜዬ ላይ ላለኝ ጥንካሬ ሚስጥሩ  ሁለት ነው ፤የመጀመሪያው ከእጽዋት ጋር ያለኝ ፍቅር እና ቁርኝት ሲሆን ሌላው ደግሞ  ለወሲብ ያለኝ ፍቅር ነው ብለው በድፍረት ለጠየቃቸው ሁሉ ይመልሳሉ፡፡ ጫን ብለው ለጠየቃቸውም ስለወሲብ ጥሩነት ዘርዘር አድርገው ለማስረዳት ይገደዳሉ‹‹…. የወሲብ ብቃት ቀጥታ ከጤነኝነት ጋር ትስስር አለው፣አንድ የወሲብ ብልቱ አልታዘዝ ያለው ሰው የሆነ የጓደለው ነገር አለው ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ ትልቅ ቢዝነስ ሚያንቀሳሰቅሱ ባለሀብቶች ወይም ትልቅ ድርጅት ሚያሰተዳድሩ የስራ መሪዎች የወሲብ ስሜታቸው ሚቀሰቀሰው ከእለታቶች በአንድ ቀን ፤ለዛውም በብዙ ድካምና የመድሀኒት እገዛ ነው ፡፡ይህ የሚሆነበት ዋናው ምክንያት በጭንቀት የተበረዘ አዕምሮ እና በስራ የዛለ አካል ስላላቸው ነው ለወሲብ ዝግጁ መሆን የማይችሉት:: አልያም ድባቴ ውስጥ ገብተው በጭንቀት በሽታ እየተሰቃዩ ነው፡፡

ጥናተቶች አንደሚያመለክቱት የአንድ ሰው ብልቱ ሲቆም ያለው ጥንካሬ እና የልብ ጥንካሬ ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው…ተገትሮ የሚሰነጥቅ ብልት ያለው ወንድ ልቡም እንደዛው የተደራረበ ጠንካራና ከብረት የደደረ ነው፡፡ በሳምንት 4 ቀን ወሲብ የሚፈጽም ሰው ከማይፈጽም ሰው በልብ ድካም የመያዝ  ዕድሉ 58 ፐርሰንት የበለጠ የተሻለ ነው ፡፡…..››እያሉ መሰል መረጃዎችን በመደርደር ያስረዳሉ፡፡

ስለእሳቸው ማሰቧን ገታ አድርጋ ፊት ለፊቷ ወዳለችው ልጅ ትኩረቷን መለሰች፡፡በዛ ተመሳሳይ ሰዓትም ንስሯ ፡፡ ከተቀመጠችበት ወንበር ትክክል ጣራው ላይ ሰፍሮ ዘና ብሎ ቁልቁል እሷንም ጊቢውንም እየቃኘ እና የጥዋቷን ፀሀይ አብሯት እየሞቀ እና የምትመለከታትን ልጅ እየተመለከተ ነው፡፡
ልጅቷ በራፉን መልሳ ዘጋችና ወደውጨኛው  በራፍ ለመሄድ እርምጃ ስትጀምር  አዕምሮዋን ሰረሰራት፡፡ቀና ብላ ወደ ንስሯ ስታይ እነዛ ሰርሰሪ አይኖቹን ልጅቷ ላይ ሰክቷል…‹‹ ነገር አለ›› አለችና እሷም ትኩረቷን በመሰብሰብ የሚያየየውን ለማየት ሞከረች…. የልጅቷ ልብ ጭልም ብሎ ነው እየታያት ያለው‹‹‹ ..በሀዘን ኩምትርትር ያለ….ደግሞ ግራ የተጋባ የተመሰቃቀለ  ነፍስ ነው ያላቻት ›ስትለ አጉረመረመች.. ..ወጣቷ ቆንጆ ለሚያያት ሁሉ በፈገግታ  የደመቀ ፊት ስለሚታየው በጨለማ የተሞላች  ነፍስ አላት ተብሎ ቢነገረው ማንም አያምንም ፡፡

‹‹የእኔ እህት ››ብላ ጠራቻት

‹‹አቤት››አለችና ባለችበት ቆማ ፊቷን ወደ እሷ አዞረች…

‹‹ደህና አደርሽ …?››

‹‹ደህና ››አለች ግራ በመጋባት

‹‹ምነው በለሊት…?››

በንግግሯ ግራ ተጋብታ በእጇ የያዘችውን ሞባይል አብርታ አየችና‹‹እንድ ሰዓት እኮ ሆኗል…?››አለቻት፡፡

‹‹ካልቸኮልሽ ቁርስ አብረን እንብላና ትሄጄያለሽ›› …..ይህን ስትላት ልጅቱ እንደማትቸኩል እርግጠኛ ነኝ ….በቃ እንደውም የምትሄድበትም ያላት አይነት እንዳልሆነች  ተረድታለች፡፡

እንደማቅማማት አለችና ፊቷን አዙራ ወደእሷ መጣች፤እንደዛ ያደረገችው ዝም ብላ አይደለም ….ውስጧ እንደዛ እንዳታደርግ ስለገፋፋት ነው…. ሁሌ ፕሮፌሰሩ የሚያመጧቸውን ሴቶች ወደ ክፍሏ በማስገባት ቁርስ እያበላች ትሸኛቸዋለች ማለት አይደለም፡፡በዛ ላይ እኮ ገና ቁርስም አልሰራችም፡፡ብቻ ይዛት ገባችና ቁጭ እንድትል ነገረቻት ..ያመለከተቻት ቦታ ቁጭ አለች፡፡

‹‹ይቅርታ ቁርሱ አልተሰራም …ግን በፍጥነት ይደርሳል፡፡››ብላ እስቶቩን  ለኮሰች

‹‹አረ ችግር የለም…››

ወደ ፊሪጅ አመራችና ከፍታ አንድ  ብርጭቆ የማንጎ ጂውስ ሰጠቻት…… አመስግና ተቀበለቻትና መጠጣት ጀመረች ….እሷም  እያወራቻት ቁርሱን መስራት ጀመረች… 

‹‹እኔ ሶፊያ እባላለሁ…አንቺስ

…?››ሶፊያ የሚለውን ስም ለገጣፎ ከተመች ቡኃላ ደጋጋማ መጠቀም ጀምራለች፡፡ምንያቱም ከአዲስ ሰው ጋር ሁሉ ስትተዋወቅ ኬድሮን እባላለው ስትል‹‹ ኬድሮን ማለት ምን ማለት ነው?›› ብለው ሲጠየቋት እንዴት ብላ እንደምታስረዳ ግራ እየገባት ስለተቸገረች ነው፡ኬድሮን ማለት በማርስና በመሬት መካከል የሚገኝ ፕላኔት ነው ፤አባቴ የዛ ፕላኔት ኑዋሪ ነው…ትርጉሙ የዕውቀት ምድር ማለት ነው .እሱን ለማስታወስ ስትል እናቴ በፕላኔቷ ስም ስሜን ኬዴርን ብላ ሰየመችኝ ብላ ብታስረዳ‹‹እንዴ ኬድሮን የሚባል ፐላኔት መቼ ነው የተገኘው? ብለው ወደጎግል ይሮጣሉ… ምንም ሚጎለጎል መረጃ ሲያጡ እሷን እንደ እብድ ይመለከታቷል …ይሄ ነገር ሲደጋገምባት ሰለቻትና ለምን ሁለተኛ ስሜን አልጠቀምም አለችና ‹ሶፊያ› የሚል ስሞን አብዝታ መገልገል ጀመረች ፤እና ሁለቱንም ስሞቾን እንደአስፈላጊነቱ እየቀያየረች መጠቀም ጀመረች፡

‹‹አለም››

‹‹እሺ አለም….. አይዞሽ..ነገሮች ይስተካከላሉ››አለቻት፡፡

‹‹ ፍጥጥ ብላ አየቻት፡፡ምክንያቱም ስለታሪኳ ምንም አልነገረቻትም፡፡ እንዴት ልታውቅ ቻለች፤ ብላ ግራ ተጋብታ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም ››አለቻት፡፡

‹‹አይ አሁን ያለሽበት ችግር ይፈታል ማለቴ ነው››

በፍራቻም በጥርጣሬም እያየቻት ‹‹ነገርኩሽ እንዴ…? ››ጠየቀቻት …

‹‹አይ እንዲሁ ሳይሽ ውስጥሽ የተጨነቀ እንደሆነ ስለገባኝ ነው፡፡በጣም አዝነሻል፡፡››

እንባዋን መገደብ አቅቷት ዘረገፈችው፡፡

‹‹አዎ ከባድ ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡››
‹‹አይዞሽ..እስኪ ንገሪኝ››

‹‹እንደምታስቢው ሸርሙጣ አይደለሁም…ይሄንን ስራ ከጀመርኩ ሳምንትም አይሆነኝም…››

‹‹አይዞሽ ..ተረጋጊና አጫውቺኝ››
‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››