ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
197K subscribers
281 photos
1 video
16 files
209 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

...አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።ስታልፍ እንድትቆም የእጅ ምልክት ሰጣት በመስታወት አሻግራ
ስታይ ተሳፋሪዎች ወደ አይሮፕላኑ የሚወስዳቸው ጀልባ ላይ ሲወጡ አየች፡፡
ሆኖም መርቪን ቁሚ ስላላት ቆመች፡ መርቪን በስልክ አሁን በዚህ ነገር
አታስቸግረኝ፡፡ ሰራተኞቹ የጠየቁህን ክፈልና ስራው እንዲቀጥል አድርግ›› ሲል አዘዘ፡፡

በመርቪን ፋብሪካ ውስጥ ሰሞኑን የአሰሪና ሰራተኛ ውዝግብ እንደነበር
ነግሯታል፡ ከእሱ ባህሪ በተቃራኒ ሲታይ አሁን ለሰራተኞቹ ጥያቄ እጁን
የሰጠ ይመስላል፡

ስልኩን የደወለው ሰው በመርቪን አነጋገር ሳይደነቅ አይቀርም፡፡
‹‹አዎ እንዳልኩህ አድርግ፤ የምሬን ነው፡፡ ከማንም ቀጥቃጭ ጋር
ለመጨቃጨቅ ጊዜ የለኝም፡ ደህና ሁን›› አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ ከዚያም
‹‹ስፈልግሽ ነበር?›› አላት ናንሲን፡፡

‹‹ተሳካልህ? ባለቤትህ አብሬህ እመጣለሁ አለች?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ገና በቀጥታ እንሂድ አላልኳትም››
‹‹አሁን የት ነው ያለችው?››
በመስኮት አየና ‹‹ያቻትልሽ ቀይ ኮት የለበሰችው››
ናንሲ በእድሜ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ቃጫ የመሰለ ጸጉር
ያላት ሴት አየች፡ ‹‹መርቪን ባለቤትህ በጣም ቆንጆ ናት!›› አለች፡ ናንሲ
በመርቪን ሚስት ቁንጅና ተደንቃለች፡፡ እሷ የገመተቻት እንዲህ አልነበረም፡
‹‹ይህቺ ሴት ከእጅህ እንዳትወጣ ለምን እንደፈለግህ አሁን ገባኝ›› አለች፡ዳያና አንድ ሰማያዊ ሱሪ የለበሰ ሰው ሶቶ ይዛለች፡፡ ማርክ እንደ መርቪን አያምርም፡ ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ፀጉሩ ከግንባሩ እየሸሸ ነው፡፡ ነገር ግን ፎልፎላ እና ተጫዋች ይመስላል ሲያዩት፡፡ ናንሲ የመርቪን ሚስት የባሏን
ተቃራኒ የሆነ ሰው መያዟን አስተዋለች፡፡ ለመርቪን አዘነችለት።
‹‹እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጥህ›› አለችው፡፡

‹‹ገና እጅ አልሰጠሁም›› አለ፡፡ ‹‹ኒውዮርክ ድረስ ተከትያት እሄዳለሁ››
ናንሲ የመርቪን አባባል አሳቃት፡ ‹‹ደግ አደረግክ! ባለቤትህ ማንም ወንድ ልጅ አትላንቲክን አቋርጦ የሚከተላት አይነት ሴት ናት፡››

‹‹የችግሩ መፍትሄ አንቺ እጅ ውስጥ ነው ያለው›› አላት ‹‹አይሮፕላኑ ሞልቷል ቦታ የለም››

‹‹እውነት ነው ታዲያ ኒውዮርክ ድረስ በምን ትሄዳለህ? ደግሞ
ምንድን ነው በእኔ እጅ ውስጥ ያለው መፍትሄ?››
‹‹አንቺ ነሽ ቀሪውን ትርፍ ወንበር የያዝሽው፡፡ የሙሽሮችን ክፍል
መያዝሽን ሰምቻለሁ፡ ትርፏን ወንበር ለኔ ሽጭልኝ››

ናንሲ ከት ብላ ሳቀችና ‹‹የሙሽሮችን ክፍል ከወንድ ጋር መጋራት
አልችልም፡፡ እኔ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንጂ የሆነች ዳንሰኛ አይደለሁም››
‹‹እኔ ግን ማንም ያላደረገልሽን ውለታ አድርጌልሻለሁ›› አላት ፍርጥም ብሎ።
‹‹ውለታህ ሊኖርብኝ ይችላል ክብሬን መሸጥ ግን አልችልም ናንሲ ያለችውን እንዳልተቀበለ ይመሰክራል ‹‹በአይሪሽ ባህር ላይ ከኔ ጋ
ስትበሪ ስለክብርሽ አልተጨነቅሽም››

‹‹እዚያ ላይ እኮ አብረን አላደርንም›› አለች፡፡ ብትረዳው በወደደች
ውቧን ሚስቱን ለማስመለስ ቁርጠኛ መሆኑ ልቧን ነክቷታል፡

‹‹ይቅርታ አድርግልኝ በዚህ እድሜዬ ካንተ ጋር አንድ ክፍል አድሬ የሰው መሳቅያ
መሆን አልፈልግም

‹‹ስለሙሽሮች ክፍል ጠይቄያለሁ። ከሌሎች ክፍሎች የሚለየው ነገር
የለም፡ ባለሁለት አልጋ ነው፡፡ ማታ ማታ በሩን ብንከፍተው ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች ፊት ለፊት የያዟቸው ትይዩ ወንበሮች መሆናቸው ይታያል፡››

‹‹ሰው ምን እንደሚል አስብ መርቪን››

‹‹ለማን ነው የምትጨነቂው? ባል የለሽ? ቤተሰቦችሽ ሞተዋል እዚህ
ለምታደርጊው ነገር ማን ግድ አለው?››

መርቪን አንድ ነገር ከፈለገ ፊት ለፊት ነው የሚናገረው፡
ይቀየመኛል ብሎ አያስብም፡፡

‹‹ሁለት ትልልቅ ወንድ ልጆች አሉኝ›› ስትል አነጋገሩን ተቃወመች።
‹‹ልጆችሽ ይህን ሲሰሙ ቀልድ ነው የሚመስላቸው››
ሊመስላቸው ይችላል አለች በሆዷ ሃዘን እየተሰማት፡ ‹‹እኔን የጨነቀኝ የድፍን ቦስተን ከተማ ሰው ምን እንደሚል ነው፡፡ እኔ ታዋቂ ሴት በመሆኔ ወሬው እንደ ቋያ እሳት በአንዴ ነው የሚዳረሰው››

‹‹ተመልከች! እንግሊዝ አገር እዚያ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ሆነሽ ምን ያህል ተቸግረሽ እንደነበር እንድወስድሽ ምን ያህል ፈልገሽ እንደነበር
አስታውሺ፡፡ ያኔ ከጉድ ነው ያወጣሁሽ፡፡ አሁን በተራዬ እኔ የማልወጣው ችግር ላይ ወድቄያለሁ፡ የኔ ጭንቀት አልገባሽም ማለት ነው?›› አላት

‹‹ይገባኛል››

‹‹ስለዚህ ችግር ላይ ስላለሁ ከጉድ አውጪኝ፡፡ ትዳሬን ለማዳን ያለኝ
የመጨረሻ እድል ይሄ ብቻ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ትችያለሽ፡፡ እኔ በችግርሽ ጊዜ ደርሼልሻለሁ፡ አሁን ብድር የምትመልሽበት ጊዜ መጥቷል።ሰው እንደሆነ አምቶ አምቶ ሲደክመው ይተዋል፡፡ የአንድ ሰሞን ሀሜት ደግሞ ሰውን አይገድልም፡፡››

የአንድ ሰሞን ሀሜቱን አሰበች፡፡ አንዲት የአርባ አመት እድሜ ላይ የምትገኝ ባሏ የሞተባት ሴት በግድ የለሽነት እንዲህ አይነት ነገር ብታደርግ ምን ችግር አለው፡፡ ይህን በማድረጓ አትሞት! መርቪን እንዳለው ክብሯንም አይቀንሰውም፡፡ አሮጊቶች ምነው ቀበጠች› እንደሚሏት ጥርጥር የለውም:፡
የእድሜ እኩዮቼ ግን ድፍረቴን ያደንቃሉ አለች በሃሳቧ የመርቪን የተጎዳና አቋመ ፅኑ ፊት ስታይ ልቧ ከእሱ ጋርሄደ የቦስተን ህዝብ ገደል ይግባ፡፡ ይህ ሰው ችግር ላይ ወድቋል፡ እኔ ተቸግሬ በነበረበት ሰዓት ለችግሬ ደርሷል፡ እኔ ባላመጣሽ ኖሮ ዛሬ እዚህ አትገኝም ነበር› ያለው እውነት ነው።

‹‹ናንሲ የያዝሽው ክፍል ውስጥ ታስገቢኛለሽ? የመጨረሻ ተስፋዬ አንቺ ነሽ"

‹‹አዎ አስገባሀለሁ›› አለች፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሄሪ ማርክስ የመጨረሻ አውሮፓ ትውስታ ለመርከበኞች ምልክት የሚሰጠውን የፓውዛ ማማ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ሞገድ እየመጣ
ሲለትመው ያየው ብቻ ነው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሚታይ መሬት
አልነበረም፧ ዳርቻ ከሌለው ባህር በስተቀር፡፡

አሜሪካ ስገባ ሀብታም እሆናለሁ› ሲል አሰበ፡፡

በሌዲ ኦክሰንፎርድ ሻንጣ ውስጥ የተሸጎጠው ጌጥ የወሲብ ያህል የሚያጓጓ ነው፡፡ ይህ እንቁ በዚህ አይሮፕላን ውስጥ አንድ ቦታ ይገኛል ዕንቁውን በእጁ ለማስገባት ቋምጧል፡

ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ እንቁ ከሌባ እጅ በመቶ ሺህ ብር ይገኛል።በዚህ ገንዘብ ጥሩ መኪና ምናልባትም የቴኒስ መጫወቻ ያለው ቤት እገዛለሁ ወይም ገንዘቡን ኢንቨስት አደርግና በወለዱ ብቻ እኖራለሁ፡ ስራ
ባልሰራ ደልቀቅ ብዬ እኖራለሁ› ሲል ተመኘ፡፡
በመጀመሪያ ግን እንቁውን በእጁ ማድረግ ይኖርበታል፡ ጌጡ በሌዲ ኦክሰንፎርድ አንገት ላይ አይታይም፡ ስለዚህ ሊኖር የሚችለው በእጅ ቦርሳቸው ውስጥ ወይም እዚህ አጠገባቸው ባለው ማስቀመጫ ወይም ደግሞ ሻንጣ የሚቀመጥበት ቦታ እኔ ብሆን ካጠገቤ አለየውም ነበር ከአይኔ ከራቀ እንቅልፍም አይዘኝም› ሲል አሰበ ሄሪ፡

መጀመሪያ የእጅ ቦርሳቸውን ይበረብራል፡ እንዴት እንደሚበረብር ግን
አልመጣለትም፡፡ ምናልባትም የሚሻለው ማታ ሰው ሁሉ ከተኛ በኋላ ነው።
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከሶስት አመት በኃላ..
እናትዬውን አሳምና ከደሎ ለቃ ስትወጣ  አንድ ሻንጣ ልብሷን ይዛ በትራንስፖርት ሳይሆን በንስሯ አማካይነት እየበረረች ነበር የተጓዘችው..በእጇ እናቷ ያስጨበጠቻትን 2000 ሺ ብር እና አጎቷ የሰጣትን 5 ሺ ብር .. በቃ ይሄንን ነው የያዘችው፡፡ግን ሻንጣዋ ውስጥ ከአመታት በፊት ኪኒማጀሮን ለመጓብኘት በሄደች ጊዜ ንስሯ ከባህር ወንበዴዎች ነጥቆ የሰጣት ዳይመንድ እንደቀልድ እንዳስቀመጠችው ስለነበረ ይዛው ነበር.። አዲስ አበባ እንደገቡ በደላላ 45 ሚሊዬን ብር ተሸጠ.
በ25 ሚሊዬን ብር  ለገጣፎ ከተማ አካባቢ ምታርፍበት የራሷ የሆነ  2ሺ ካ.ሬ ሜትር  ግቢ ላይ ጥጉን ይዞ የታነፀ ባለአምስት ክፍል   ቢላ ቤት  ገዝታ ከንስሯ ጋር የብቸኝነት ኑሮ መኖር ጀመረች፡፡
እንደመጣች ሰሞን ብቸኝነቱ በጣም ከብዷት ነበር.. የምታውቀው ሰው በዙያዋ ካለመኖሩም በተጨማሪ ከደንና ጫካ ውስጥ ወጥቶ በፎቅና በመኪና የታጠረ አካባቢ መኖር በጣም ሚረብሽ ሆኖባት ነበር…ቆይቶ ግን እየለመደችው መጣች፡የገዛችውንም ጊቢ እንደምትፈልገው አደረገችው….እነሆ አሁን ከሶስት አመት በኃላ ከቤቱ ይልቅ በግቢ ውስጥ ያሉ ዛፎች ዕጻዋቶች እና ፍራፍሬዎች ይበልጥ ያስደምማሉ፡፡ በግቢዋ ውስጥ ከ1140 በላይ የዕፅዋት አይነቶች ይገኛሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ 83ቱን ከተለያዩ አህጉራት በዞረችባቸው ወቅት ቀልቧን ስበውት ወይም አስደምመዋት አምጥታ የተከለቻቸው ናቸው፡፡እርግጥ  አምጥታ የተከለቻቸው ከዚህ አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነበር..ከአዲስ አበባ የአየር ፀባይ ጋር ተላምደው  መጽደቅ የቻሉት ግን እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡
ግቢዋ ውስጥ ያሉ ዕጽዋቶች ሁሉ አስደማሚነታቸው ለአይን መስብ ከመሆናቸው እና ንጽህ አየር ሚያመርቱ መንፈሳዊ ማሽኖች ስለሆኑ ብቻ አይደለም እዚህ ግቢ የመትከል ተተክሎም የመብቀል እድል ያገኙት…እያንዳንዱ የተለየ ሚስጥር እና ጥበብ የሚገለጽባቸው የእግዚያብሄርን  ሚስጥራዊ ሹክሹክታ በቅጠሎቻቸው እና በስሮቻቸው ነስለሚተነፍሱ ነው…::መድሀኒት ናቸው… ታአምራትን የሚሰራባቸው ናቸው..ብዙ ብዙ ነገር…በየዛፎች ቅርንጫፍች ላይ ቁጥራቸውን የማይታወቅ የወፍ ጎጆዎች ሞልተውባቸዋል፤ሶስት ጉሬዛ እና አራት ዝንጀሮዎችም አሏት ..ሁሉንም ያመጣቻው ከሀገሯ ጫካ ነው… ከደሎ መና፡፡እንደዛ ያደረገችው..ልጅነቷን ስለሚያስታውሷት ነው.እንደዛ ያደረገችው..አብራቸው እነሱን እያየች ከእነሱ እየተጫወተች ስላደገች ዘመዷቾ ስለሚመስሏት ነው… ስለምትወዳቸውና ከእነሱ ውጭ ህይወት ስለማይታያት ነው.. ስለምትወዳቸውና የሚወዷትም ስለሚመስላት ነው፡፡
አብረዋት የሚኖሩ አንድ የስልሳ ሁለት አመት አዛውንት ሰውዬ አሉ፡፡ጋሽ ተክለወልድ ይማም ይባላሉ፡፡ይሄንን ጊቢ እንዲህ ያሳመረችውም የምታስተዳድረውም ከእሳቸው ጋር ነው፡፡

እሷ ያው አብዝታ ከአንድ የምድር ጫፍ ወደሌላው መስፈንጠር የዘወትር ድርጊቷ ስለሆነ በሌለችበት ጊዜ እሳቸው ናቸው ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስዱላት፡፡ ዘበኛ  ወይም አትክልተኛ አይደሉም፡፡ከዕጽዋቶች ጋር በፍቅር የወደቁ ከሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ለ32 ዓመት ያስተማሩና በቅርቡ ጡረታ የወጡ የዕጽዋት ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

ሌላው  በዋናነት ለብቸኝነቷ መድሀኒት የሆናት  ንስሯ ነው ፡፡ የንስሯ እና የእሷ ግንኙነት ለሌላ ሰው ለማስረዳት ቀላል መንገድ የለም፡፡ እያንዳንዱ የሰው ልጅ እንዲጠብቀው እንዲንከባከበው እና ከክፉ ነገር እንዲከልለው ከፈጣሪው የተመደበለት ጠባቂ መልዐክ አለው ተብሎ በአብዛኛው ሰው ይታመናል፡፡ግን እነዚህ ጠባቂ መላዕክቶች አካል አልባ መንፈስ ናቸው ፡፡አይታዩም፤መታየት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰውም ጠባቂ መልአኩን በትከሻው ላይ ተሸክሞ እንደሚዞር አያውቅም… አያምንምም፡፡ስለዚህ አይገለገልባቸውም …አያዳምጣቸውም፡፡ሰው በጨለማ ውስጥ ሲጓዝ ማጅራት መቺ ከኃላው ካለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይሰማ ትከሻዬን ከበደኝ ይላል፤ያ ምን  ማለት ነው? ለሚያምንበት ሰው ጠባቂ መላዕክ የማስጠንቂያ ደውል ነው…. እሱ ያልተመለከተውን በጭለማ ውስጥ የተሸሸገውን  አጥቂውን ጠባቂ መልአኩ አይቶት ሹክ ብሎታል ማለት ነው፡፡እንግዲህ ያ ሰው ብልህ ከሆነ ማድረግ ያለበት መልዕክቱን አምኖ ተፈትልኮ በመሮጥ ማምለጥ ወይም ጥቃቱን ለመመከት እራሱን ማዘጋጀት ነው፡፡አይ ዝም ብሎ ተራ ፍራቻ ነው ብሎ የደረሰውን መልዕክት ችላ ብሎ በእንዝላልነቱ ከገፋበት ግን ማጃራቱን  ተመቶ  ይዘረራልም..ይዘረፋልም ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

እና ለእሷ ይሄ ንስር አሞራ ጠባቂ መላዕኳ በሉት፡፡በአካል አብሯት የሚንቀሳቀስ የሚያወራት የምታወራው ጠባቂ መልአክ ስላለት፡፡የፈለገችበት የአለም ጥግ አንጠልጥሎ የሚወስዳት...ከሚንቀለቀል እቶን እሳት ውስጥ ብትገባ እንኳን አንጠልጥሎ በማውጣት ሀይቅ ውስጥ ጨምሮ የሚያቀዘቅዘት፡፡ካለሀሪ በረሀ ላይ ወስዶ በጥም ጉሮሮዋ ከደረቀ  ከመንቁሩ ወይን አመንጭቶ የሚያጠጣት…..ከፈለገች የሲ.አይ .ኤን የስለላ መረብ በጣጥሶ የዋይት ሀውስ ራት ግብዝ ላይ አስገብቶ የሚጥላት፡፡ሱፐር ሂዩማን እንድትሆን ሱፐር ሆኖ ሱፐር የሚያደርጋት መልዐኳ ነው፡፡የማታውቀው አባቷ ስጦታ፡ከሀገሯ አብሮት የተሰደ የደስታዋም ሆነ የሀዘኗ ጊዜ ተጋሪዋ፡፡

በንስራ አካል ውስጥ ባለው የነቃና የበቃ  ነፍስ እገዛ እሱ  ያየውን አንደምታይ እና ያሰበውን እንዳምታስብ ታውቃለች፡፡ልክ በአንድ ዲኮደር እንደሚሰራ ሁለት ቴሌቪዝን በሉን….እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እሱ አየሩን ሰንጥቆ  በሚበርበት የምድር ጥግ ሁሉ እያየ ያለውን ነገር ጥርት ባለ ምስል በአዕምሮዋ ታያለች…የንስርን አይን ደግሞ የሚታውቅ ነው..እያንዳንዱ ንስር  ቅንጣት በቀላሉ በአይኑ ሌንስ ይቀልባታል፡፡ይሄ ገለጻ ለብዙዎችን ግራ ሊያጋባ ይችላል፡፡
ይሄ መልአክ ነው ሰይጣን የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡መልአክ ከሆነ ለምን በእርግብ አካል ውስጥ አላደረም ወይንም እንደተለመደው  ለምን የበግ ስጋና ቆዳ አለበሰም፡፡እሱን የሚያውቀው ይሄ እንዲሆን ያደረገው የማታውቀውና የሌላ አለም ፍጡር የሆነው አባቷ ነው፡፡ለእሷ ግን  ምንም ግድም አይሰጣትም፡፡ዋናው በእርግጠኝነት የምታውቀው ነገር የእሷ እኔነት እና የንስሩ ነፍስ የተሳሰረ መሆኑን ነው፡፡ የኖረውን ያህል ኖራ በሚሞትበት ቀን የምትሞት እንደሆነም ይሰማታል፡፡ወይንም የእሱ ነፍስ ከንስር አካሉ ውስጥ ተንጠፍጥበፎ በሚወጣበት ቅጽበት የእሷም ነፍስ ከዚህ የሰው ሰውነት ወይም አካል ውስጥ ተንጠፍጥፎ በመውጣት ከእሱ ነፍስ ጋር በመተቃቀፍ ወደሚሄድበት ሚስጥራዊ ቦታ አብሮት እንደሚነጉድ ታውቃለች… የመዳረሻቸው ፍጻሜም  የአምላክ እቅፍ ይሆን የሉሲፈር ጓዲያ  ምንም የምታውቀው ነገር የለም ፡፡
አሁን ባሉበት ቦታ ሁለቱምን  ደስተኞች ናቸው ፡፡በዚህች ምድር ሚስጥር እየተደመሙበት ነው፡፡

ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 27,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏